Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም.

በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣ በዓመት ሁለት ጊዜያት እንዲሆን በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 በተደነገገው መሠረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የመክፈቻው ሥርዓተ ጸሎት ከተፈጸመበት ከጥቅምት 11 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. ድረስ የተለመደውን ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባን በማካሔድ፣

 • ለቤተ ክርስቲያናችንና ለኅብረሰተባችን የሚጠቅመውን፣
 • ለሀገርና ለዓለም ሰላም የሚበጀውን አጀንዳ በማመቻቸት በስፋትና በጥልቀት ተወያይቶ የሚከተለውን ውሳኔ አሳልፏል፡፡

ወቅታዊውን የሀገራችንን የሰላም ሁኔታ አስመልክቶ
"ኢትዮጵያ ታበጽሕ እደዊሃ ኀበ እግዚአብሔር"
"ኢትዮጵያ ኢትዮጵያውያን ኢትዮጵያውያት እጆቻቸቸውን ወደ እግዚአብሐር ይዘረጋሉ" ይላል ነቢየ እግዚብሔር ዳዊት (መዝ. 67፣31)
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ክፍለ ዓለም፣ በአፍሪካ ቀንድ በሰሜን ምሥራቅ አፍሪካ በዓባይ ሸለቆ ዙሪያ በቀይ-ባሕር አካባቢ የምትገኝ ሀገር ናት፡፡
ሀገራችን ኢትዮጵያ የነጻነት፣ የአንድነት ዕድሜ የተቈጠረላት በዚህም ረዥም የነጻነትና የአንድነት ዕድሜዋ ብዙ አገልግሎት ያበረከተች ሰፊ ታሪክ ያስመዘገበች ሉዓላዊት ሀገር ናት፡፡
አገራችን ኢትዮጵያ ባሳለፈችው ረዥም ዘመኗ በርካታ ደጋግ መልካም ሥራና ስም የነበራቸው ታላላቅ ሰዎች አልፈውባታል፡፡ ለታሪኳ፣ ለቅርሷ፣ ለባህሏ፣ ለዕድገቷ፣ ለድንበሯ ለአንድነቷ፣ ለነጻነቷ፣ ለክብሯ በሚገርም ወኔና ጀግንነት ደማቸውን ያፈሰሱላት፣ አጥንቶቻቸውን የከሰከሱላት ጀግኖች እንደነበሩአት አሁንም እንዳሏት በታሪክ ተመዝግቧል፡፡
ይህም በመሆኑ ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን በዘመናቸው እርስ በርሳቸው በመከባበር የተራበውን በማብላት፣ የተጠማውን በማጠጣት፣ የታረዘውን በማልበስ፣ ያለማውን በማልማት፣ ቤት የእግዚአብሔር ነው በሚል አገራዊ ትውፊት እንግዳ እየተቀበሉ እግር እያጠቡ ቤት ያፈራውን ተካፍለው በመብላት ተከባብረው በመኖር የታወቁ ደጋግ አባቶች ልጆች መሆናችን ይታወቃል፡፡
ሀገራችን ኢትዮጵያ የተለያየ ቋንቋ ተናጋሪ የኅብረተሰብ ክፍሎች ለአያሌ ዘመናት የኖሩባትና አሁንም የሚኖሩባት በአርአያነት ልትጠቀስ የሚገባት ብቸኛ ሀገር መሆኗ ከማንም ግንዛቤ የተሰወረ አይደለም፡፡
ይሁንና በአሁኑ ጊዜ በሀገራችን፡-

 • የሰዎች ሕይወት እየጠፋ መሆኑ፣
 • የአገር ሀብትና ንብረት እየወደመ መታየቱ፣
 • ከነበሩበት እና ከኖሩበት ቦታ የሕዝቦችን ፍልሰት ማስከተሉ፣
 • በእነዚህም እየታዩ ባሉ ችግሮች ምክንያት በሰላማዊው ኅብረተሰብ ዘንድ ከፍተኛ ስጋት እየሰፈነ መምጣቱና ልማታዊ ሥራዎችም ሊስተጓጐሉ እንደሚችሉ መገንዘብ ተችሏል፡፡

ስለዚህ የዚሁ የጥቅምቱ 2009 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በአገሪቱ እየታየ ባለው የሰላም ችግር ላይ በሰፊው በመወያየትና በመነጋገር የሚከተለውን መግለጫ አውጥቷል፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ

ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በየዓመቱ ከምታካሂዳቸው ታላላቅ ጉባኤያት መካከል አንደኛው ጉባኤ በጥቅምት የሚካሄደው ዓለም አቀፍ አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ነው፡፡
ይህ ጉባኤ የሚካሄደው አጠቃላይ ዓለም አቀፋዊና ሀገራዊው የቤተ ክርስቲያንም ያለችበት ደረጃ የሚያሳዩ የተለያዩ ከአራቱ ማዕዘነ ዓለም ዓለም አቀፋዊ ሪፖርቶች ይቀርቡበታል፣ ይደመጥበታል፣ ውሳኔም ይሰጥበታል፡፡ይህ ጉባኤ ከተጀመረ እነሆ 35 ዓመታት አስቆጥሯል፡፡
በዚህ ጉባኤ ቤተ ክርስቲያንም የራስዋ የአቅም ግንባታ ከግምት አስገብታ በከፍተኛ ፍጥነት እየገሰገሰች መሆንዋን ማየት ይቻላል፡፡
በዘንድሮ ዓመትም ይህ ታላቅ ጉባኤ ከጥቅምት 7 – 10 ቀን 2009 ዓ.ም ተካሂዶል፡፡

 • አጠቃላይ ጉባኤው የሦስት ቀናት ውሎ መልእክቶች
 • የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ የመክፈቻ ንግግርና
 • የብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዓመታዊ ሪፖርት፣
 • የመምሪያው ዋና ኃላፊ መልዕክት
 • የመምሪያዎችና የየድርጅቶች ሪፖርት፣
 • የየአህጉረ ስብከቶ ሪፖርት፣
 • የ49 አህጉረ ስብከት አኃዛዊ መረጃ የሚያሳይ
 • የአቋም መግለጫ
 • እነዲሁም የ2009 ዓ.ም የቤተ ክርስቲያኗ ዓለማቃፋዊ የሥራ አቅጣጫ የሚጠቁም ውሳኔ ከዚህ በታች ቀርቧል እንዲከታተሉ፡፡
 •  የ2009 ዓ.ም የቤተ ክርስቲያኗ ዓለማቃፋዊ የሥራ አቅጣጫ

በመምህር ሙሴ ኃይሉ

በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ቅዱስ ዮሐንስም መስከረም 2 ቀን 2009 ዓ.ም በጠቅላይ ቤተ ክህነት ስብከተ ወንጌል አዳራሽ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያ ኃላፊዎች እና አጠቃላይ ሠራተኞች፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ኃላፊዎችና ሠራተኞች፣ የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ የሰ/ት/ቤት ወጣቶች መዘምራንና ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች በተገኙበት በደማቅ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ተከብሮአል፡፡

የዕለቱ ተረኛ የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢ ታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ሊቃውንት ያሬዳዊ መዝሙር በማቅረብ የተጀመረ ሲሆን የሊቃውንት ቅኔ እና በመካነ ሕያዋን ሰ/ት/ቤት መዘምራን የአጫብር ቆሜ ወረብ በዓሉ እጅግ ደማቅ እንዲሆን አስችለውታል፡፡
በመቀጠልም ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና በክልል ትግራይ የደበባዊ ዞን፣ ደቡብ ምሥራቅ እና ምሥራቃዊ ዞን አኅጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አጠቃላይ የጠቅላ ቤተ ክህነት ሠራተኞችን በመወከል የእንኳን አደረስዎ መልካም ምኞት አስተላልፈዋል፡፡ ከብፁዕነታቸው ተከትሎም የአዲስ አበባ ገዳማት እና አድባራት አስተዳዳሪዎች እንደተለመደው የእንኳን አደረስዎ መልካም ምኞታቸውን በማኅበረ ካህናት እና ምዕመናን ስም አስተላልፈዋል፡፡

በዕለቱ መርሐ ግብር መሃል ላይ ቤተ ክርስቲን ለዘመናት በልዩ ክብር እና ጥንቃቄ ጠብቃ ያቆየችውን እና ቤተ ክርስቲያንዋን ከሚያስከብሩት ጥንታውያን የቅዱስ ያሬድ ድርሰቶች መካከል የሆነውን እና በከፍተኛ ጥናት እና ጥንቃቄ በቤተ ክርስቲያንዋ ታትሞ ለስርጭት የተዘጋጀውን መጽሐፈ ድጓ በቅዱስ ፓትርያርኩ ተመርቆ መታተሙን ይፋ የተደረገ ሲሆን በሁሉም አኅጉረ ስብከት እንዲሰራጭ ተደርጎ በተለይም ለዜማ መምህራንና ለአድራሽ የአብነት ተማሪዎች የዋጋ ጭማሪ እንዳይደረግበት ሆኖ ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን በዕለቱ ማሳሰቢያ ተሰጥቶአል፡፡

በመጨረሻም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ በመርሐ ግብሩ ለተገኙት ልጆቻቸው ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ አስተላልፈዋል፡፡ ቅዱስነታቸው በቃለ ምዕዳናቸው በዋናነት የሰላምን አስፈላጊነት በስፋት አትተው ሁሉም የሰላም ሐዋርያ ሆኖ በክርስቶስ መሾሙን አስረድተዋል፡፡ "ሰላም የምናመጣውም ሆነ የምናሳጣው እኛ ነን፤ ሰላም በእጃችን ሳለ እንደ ቀላል እንቆጥረዋለን ስናጣው ግን ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ እንረዳለን፤ የሰላም ባለቤት ኢየሱስ ክርስቶስ ሰላሙ ሰጥቶና፤ ይህ የክርስቶስ ሰላም በመላ ሀገራችን እንዲሁም በመላ ዓለማችን ጸንቶ እንዲኖር ሁላችንም የሰላም ሐዋርያት፣ የሰላም መምህራን፣ የሰላም መልእክተኞች በመሆን የሚጠበቅብንን መንፈሳዊ ኃላፊነት መወጣት አለብን" በማለት የሰላምን አስፈላጊነት በስፋት አትተው በየደረጃው የሚገኙ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች የሰላም ሐዋርያት ሆነው ሕዝቡን እንዲያገለግሉ አባታዊ መመሪያ አስተላልፈዋል፡፡ በመቀጠልም ያለፈውን ዓመት የነበረውን የሀገራችን የድርቅ ችግር አስታውሰው እግዚአብሔር የልጆቹ ጸሎት የሚሰማና ለልጆቹ የሚራራ ርህሩህ አምላክ ስለሆነ ያንን ድርቅ አሳልፎ ሀገራችን በሐመልማል በረከት ጎብኝቷል በማለት ያለውን ወቅታዊ የሀገራችን የአየር ጸባይ ካስረዱ በኋላ ይህ አሁን የምናየው ልምላሜ ከፍሬ እንዲያደርስልን እና እኛ ከማናውቀው መቅሰፍት ሁሉ ሰውሮ የተባረከ ዘመን እንዲያደርግል አሁንም ጸሎት ያስፈልጋል በማለት ሰፊ ትምህርተ ወንጌል ሰጥተዋል፡፡

በመጨረሻም ስለ ሰላም፣ ስለ አትክልቱ እና አዝርእቱ፣ ስለ ሕዝባች ፍቅር እና አንድነት፣ ስለ ዓለም ሰላም ሁሉ በማሰብ ዓውደ ዓመቱን በጸሎተ ምኅላ እንዲጀመር በማለት ለሁለተኛ ጊዜ የጸሎተ ምኅላ ሱባኤ እንዲያዝ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡ ቀደም ብሎ ለመጀመሪያ ጊዜ በጾመ ፍልሰታ ጊዜ ጸሎተ ምኅላ መታዘዙን ያስታወሱት ቅዱስ ፓትርያርኩ አሁንም ለሁለተኛ ጊዜ በሁሉም አድባራትና ገዳማት እንዲካሄድ መመሪያ ካስተላለፉ በኋላ ዘመኑ ዘመነ ሰላም፣ ዘመነ በረከት፣ ዘመነ ዕድገት እንዲሆንልን በመመኘት መርሐ ግብሩ በጸሎት ዘግተውታል፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡

 • በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣
 • ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤
 • የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፤
 • በሕመም ምክንያት በየሆስፒታሉ ያላችሁ፤
 • እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፤

ዘመናትና ዓመታት የማይቆጠሩለት እግዚአብሔር አምላካችን እንኳን ከ2008 ዓ.ም. ዘመነ ዮሐንስ ወደ 2009 ዓ.ም. ዘመነ ማቴዎስ በሰላምና በጤና አደረሳችሁ ፡፡

‹‹ወእስምያ ለዓመተ እግዚአብሔር ኅሪተ፤ የተመረጠችውንና የተወደደችውን የእግዚአብሔር ዓመት እሰብክ ዘንድ ልኮኛል›› (ኢሳ.61፡2፤ ሉቃ.4፡19)፡፡

ሁላችንም እንደምናውቀው እንደ ሌላው ሁሉ ዓመትም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው፤ ዓመት የጊዜ መለኪያ ነው፤ ጊዜም የሥራ መሣሪያ ነው ፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

 • በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡

በመምህር ሙሴ ኃይሉ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የደብረ ሊባኖስ ገዳም ባደረገላቸው ገዳማዊ ጥሪ ምክንያት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያ ኃላፊዎች ሊቃውንትን አስከትለው በመሄድ ነሐሴ 28 ቀን 2008 ዓ.ም. የፍቼ ዞን አስተዳደር፣ የወረዳው አስተዳደር እና የዞኑ የፀጥታ ዘርፍ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የገዳሙ አበው መነኮሳት፣ የአካባቢው ምዕመናን እና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በተገኙበት በገዳሙ ሐዋርያዊ ጉብኝት በማድረግ የተሠሩ ልማቶችንም መርቀዋል፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

በመምህር ሙሴ ኃይሉ

ቅድስት ልደታ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በ2008 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን በኮምፕሬሄንሲቭ ነርሲንግ በሚድዋይፍ፣ በሕክምና ላብራቶሪ ቴክኖሎጂና በፋርማሲ ቴክኖሎጂ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያ ኃላፊዎች፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሥራ ኃላፊዎች፣ የአድባራትና የገዳማት አስተዳዳሪዎች እንዲሁም የተመራቂ ቤተሰቦች በተገኙበት በቤተ ክህነት ስብከተ ወንጌል አዳራሽ ነሐሴ 21 ቀን 2008 ዓ.ም. በከፍተኛ መንፈሳዊ ድምቀት አስመረቀ ፡፡

የዕለቱ መርሐ ግብር የደብሩ የሰ/ት/ቤት መዘምራን ያሬዳዊ መዝሙር በማቅረብ የተጀመረ ሲሆን ከዚህ በመቀጠልም የኮሌጁ ዲን የሆኑት ወ/ሮ ሕሊና ሞገሴ የእንኳን ደህና መጣችሁና አጠቃላይ የኮሌጁ የትምህርት መርሐ ግብርን አስመልክተው ሰፋ ያለ ገለጻ አድርገዋል ፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የትምህርትና ማሰልጠኛ መምሪያ ኃላፊ በመሆን በትጋትና በቅንነት እንዲሁም በታማኝነት ሲያገለግሉ የቆዩት መምህር ቆሞስ አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል በአሁን ጊዜ አሉን ከምንላቸው የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት መካከል አንዱ ሲሆኑ፣ የሥራ ትጋታቸው፣ የቤተ ክርስቲያን ሁለገብ ትምህርታቸው እነዲሁም የቋንቋ ችሎታቸው፣ ሙያቸውንና ሕይወታቸውን ግምት ውስጥ በማስገባት የተሻለ አገልግሎት ሊያበረክቱ ወደሚችሉበት ቦታ ማለትም የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ፀሐፊ ሆነው ተሾሙ፡፡

መምህር ቆሞስ አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል የትምህርትና ማሰልጠኛ መምሪያ ኃላፊ በነበሩበት ወቅት በ38 አህጉረ ስብከት እስከ የገጠሪቱ ሀገራችን ክፍል በየገዳማቱና በየአድባራቱ ያሉትንና የተረሱትን የአብነት ትምህርት ቤቶች፣ መምህራንና ደቀ መዛሙርት በብፁዕ ወቅዱስ አባታችን አቡነ ማትያስ መሪነት እንዲጎበኙ በወቅቱ በነበሩት ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ በብፁዕ አቡነ ማቴዎስ አመራር ሰጪነት እስከ ገጠሪቱ የደረሰ የዳሰሳ ጥናት እነዲደረግ ከፍተኛ አሰተዋጽኦ አድርገዋል፡፡

በአቋምም፣ በዓላማም፣ ወደር የሌላቸው ስለ ቤተ ክርስቲያኗ ጉዳይ ማንንም ሳይፈሩ የሚጋፈጡ እና የሚናገሩ የቤተ ክርስቲያኗን ክብር የሚያስጠብቁ አንደበተ ርቱእ ምሁር የቤተ ክርስቲያን ልጅ ናቸው፡፡ መምህር ቆሞስ አባ ሠረቀ ብርሃን ወ/ሳሙኤል እስከ አሁን በሠሩባቸው መምሪያዎች ለውጥ ፈጣሪ በመሆን አቅማቸው የፈቀደውን አገልግለዋል፡፡

በአሁኑ ሰዓት የፐብሊክ ዲፕሎማሲ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት አባል ሆነው በቤተ ክርስቲያናቸውና በሀገራቸው የተጣለባቸውን ኃላፊነት በመወጣት ላይ ይገኛሉ፡፡

አሁንም ይህንን አገልግሎታቸውን ማዕከል በማድረግ የበለጠ ሊያገለግሉ ወደሚችሉበት የሥራ ዘርፍ እንዲዛወሩ ከሐምሌ 12 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት መልካም ፈቃድ ይሠሩበት ከነበረው መምርያ ተዛውረው አዲስ በተመደቡበት የሥራ ዘርፍ እንዲያገለግሉ የተደረገ መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል፡፡

መምህር ሙሴ ኃይሉ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያ ኃላፊዎች፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሥራ ኃላፊዎችና የአጥቢያው ምእመናንና የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች በተገኙበት ሐምሌ 10 ቀን 2008 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የፈለገ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ሰበካ ጉባኤ ለሚያሠራው አዲስ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን የመሠረት ድንጋይ ባርከው አስቀመጡ፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

 • በቦታው ላይ የተሠሩ ልዩ ልዩ ልማቶች መርቀዋል፡፡

በመምህር ሙሴ ኃይሉ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ሰኔ 21 ቀን 2008 ዓ.ም. በጥንታዊቷ የአምባ ሰነይቲ ውቅሮ ማርያም በዓለ ንግሥ አከበሩ ፡፡ ቅዱስ ፓትርያርኩ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትና ቅዱስ አባታችንን አጅበው የሔዱት የየመምሪያው ኃላፊዎች እምባሰነይቲ ሲደርሱ በአከባቢው ምእመናን ታላቅ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን ገዳሙ ሲደርሱም እንዲሁ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችና ምእመናን በከፍተኛ መንፈሳዊ አቀባበል ተቀብሏቸዋል፡፡

ቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በወቅቱ ለተገኙ ምእመናን ዙሪያውን ከባረኩ በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ በመግባት ጸሎተ ኪዳን ካደረሱ በኋላ የዓውደ ምሕረት መርሐ ግብር ተከናውኗል፡፡

ቅዱስ ፓትርያርኩ፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትና ከአዲስ አበባ የመጡ እንግዶች ቦታ ቦታቸውን እንደያዙ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና የአካባቢው የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች ለዕለቱ የሚስማማ ያሬዳዊ መዝሙርና ቅኔ በማቅረብ መርሐ ግብሩን ጀምረዋል፡፡

በተጨማሪ ያንብቡ…

 • ቅዱስነታቸው ለቤተ ክርስቲያኑ ማሠሪያ የ50 ሺህ ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡

በመምህር ሙሴ ኃይሉ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በመቀሌ ከተማ በአክሱም ጽዮን ዲዛይን በልዩ ቴክኖሎጂ በመገንባት ላይ የሚገኘው የዓዲሐውሲ ጌቴ ሴማኒ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትና ከአዲስ አበባ ከሔዱ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያ ኃላፈዎች፣ ከአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች፣ ከአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች በመሆን ሰኔ 20 ቀን 2008 ዓ.ም. ተዘዋውረው ጎበኙ፡፡

በተጨማሪ ያንብቡ…

 • ለሕንፃው ግንባታ 40 ሺ ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡

በመምህር ሙሴ ኃይሉ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን አስከትለው በመቀሌ ከሳቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርትን ለመመረቅ በተገኙበት ወቅት የመንግሥት አደረጃጀትን ተከትሎ አዲስ የተቋቋመው የደቡብ ምሥራቅ ትግራይ ሀገረ ስብከት መንበረ ጵጵስና ጽ/ቤት ለመገንባት መንግሥት በመቀሌ ከተማ በሰጠው 2072 ሜትር ካሬ ቦታ ትልቅ ሕንፃ ለመሥራት ሰኔ 20 ቀን 2008 ዓ.ም. ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የደቡብ ምሥራቅ ትግራይ ሀገረ ስብከት የየወረዳው ቤተ ክህነት ኃላፊዎችና የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና ብዛት ያላቸው ምእመናን በተገኙበት የመሠረት ድንጋይ አስቀምጠዋል ፡፡

በተጨማሪ ያንብቡ…

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፤

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ መደበኛ ስብሰባ በዓመት ሁለት ጊዜያት እንዲሆን በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀፅ 5 ቁጥር 164 በተደነገገው መሠረት ምልዓተ ጉኤው የዘንድሮውን መደበኛ የርክበ ካህናት ስብሰባ የጉባኤው መክፈቻ ሥርዓተ ጸሎት ከተፈጸመበት ከበዐሉ ዋዜማ ከግንቦት 16 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ሰኔ 1 ቀን 2008 ዓ.ም. ድረስ ለ16 ቀናት ያህል ባደረገው ጉባኤ ጠቀሜታ ባላቸው የአጀንዳ ነጥቦች ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፎአል ፡፡

በተጨማሪ ያንብቡ…

More Articles...

የፎንት ልክ መቀየሪያ