Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

በየዓመቱ የሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ዘንድሮም በታላቅ ድምቀት ተከበረ፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከሚከበሩት ታላላቅ ሃይማኖታዊ ብሔራውያን በዓላት ውስጥ ትልቅ መንፈሳዊና ሃገራዊ ፋይዳ ገንዘብ ያደረገውን የመስቀል ደመራ በዓላችን ዘንድሮም በታላቅ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት በመስቀል አደባባይ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳሳት ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፤ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የወላይታ ኮንታና ዳውሮ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ጥንግ ድርብ የለበሱ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ካህናትና ምዕመናን እንዲሁም የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች፣ የመንግስት ባለስልጣናት፣ አምባሳደሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ተከብሮል፡፡ በዕለቱ የተቀረጸውን ቪድዮ ከዚህ በመቀጠል ይመልከቱ፡፡

ክፍል 1

ክፍል 2

ክፍል 3

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ ተጀመረ

ጥቅምት 12 ቀን 2006 ዓ.ም ከጧቱ 2፡30 ላይ በመንበረ ፓትርያርክ የቅዱስ ሲኖዶስ አዳራሽ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳሳት ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ርዕሰ መንበርነትና ንግግር ተከፍቷል፡፡

ቅዱስነታቸውም "ወይእዜኒ አዕብይዋ ወአብድርዋ ለትምህርተ ተስፋክሙ" አሁንም ተስፋ መንግስት ሰማያት ያላት ትምህርተ ወንጌልን ውደዷት፡፡ ከፍ ከፍም አድርጓት ዕብ. 12፡5 በማለት ጉባኤውን በንግግር ከፍቷል፡፡
ሙሉ ቃሉን ከዚህ በታች ያንብቡ፤

Picture 187 Picture 192 Picture 195 Picture 201 Picture 202 Picture 207 Picture 208 Picture 209 Picture 210 Picture 212 Picture 213 Picture 214 Picture 215 Picture 217 Picture 226 Picture 227

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ቸርነት ገንዘቡ የሆነ እግዚአብሔር አምላካችን፣ ሁላችንንም ከምናገለግልበት ሀገረ ስብከት አሰባስቦ፣ ከዚህ ቅዱስ ጉባኤ በአንድነት ስላገናኘን ከሁሉ በፊት እርሱን እናመሰግናለን ፡፡

‹‹ወይእዜኒ አዕብይዋ ወአብድርዋ ለትምህርተ ተስፋክሙ፤
አሁንም ተስፋ መንግሥተ ሰማያት ያላት ትምህርተ ወንጌልን ውደዷት፣ ከፍ ከፍም አድርጓት›› (ዕብ. 12፡5)

ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፤

የዛሬው ጉባኤያችን፣ በፍትሕ መንፈሳዊ በተደነገገው መሠረት፣ ወቅታዊ የሆኑ የቤተ ክርስቲያናችን ጉዳዮችን በማንሣት ለመወያየትና፣ መንፈስ ቅዱስ በሚገልጽልን መንፈሳዊ ጥበብ እየተመራን፣ መፍትሔ ማግኘት ያለባቸው ጉዳዮች፣ መፍትሔ እንዲያገኙ ለማድረግ እንደሆነ ሁላችሁም ታውቃላችሁ ፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

የቅዱስ ሲኖዶስ ዓመታዊ ጉባአ በጸሎት ተከፈተ

ጥቅምት 11 ቀን 2006 ዓ.ም በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱመ ወእጨጌ ዘመነበረ ተክለሃይማኖት ፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያው ኃላፊዎች ከመላ ሀገሪቱ የተሰበሰቡ የቤተ ክርስቲያኒቱ ተወካዮች ምእመናንና ምእመናት በተገኙበት ከቀኑ 10-11.40 ተካሂዷል፡፡

የሠርክ ጸሎት ዳዊት፣ ውዳሴ ማርያም፣ አድኅነነ እግዚኦ፣ መልከአ ማርያም፣ መልከአ ኢየሱስ ተደግሞ "ኢትግድፈነ ወኢትመንነነ አምላከ ሰላም ተራድአነ" በማለት በዜማ ደርሷል፡፡

በመቀጠልም መስተብቁዕና ሊጦን በቅዱስነታቸው መሪነት በሊቃነ ጳጳሳት በግእዝ ዜማ ደርሷል፡፡ "አምላክነ ዘዲበኪሩቤል ትነብር" የሚለውን በአራራይ ዜማ ተዚሟል፡፡

ብፁዕ አቡነ ገሪማ /ዶ/ር የብፁዕ ወቅዱስ ልዩ ጽ/ቤትና የውጭ ጉዳይ የበላይ ኃላፊ "ሃሌ ሉያ ዘበእንቲአሃ ለቤተ ክርስቲያን ተጸፋዕከ በውስተ አውድ" የሚለው ዋዜማን ተመርቷል፡፡ ከዚያም በማያያዝ "መሐረነአብ" ተብሎ እግዚኦታ በዜማ የደረሰ ሲሆን በሊቀ ዲያቆኑ "ባርክ ቤተ አሮን" ወባርክ እለይፈርሕዎ ለእግዚአብሔር ለንኡሶሙ ወለአቢዮሙ" የሚለው የዳዊት መዝሙር በዜማ ከሰበከ በኋላ ብፁዕ አቡነ ገሪማ የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 28 ቁ. 19-20 "ሑሩ ወመሐሩ ውስተ ኲሉ አጽናፈ ዓለም ወእንዘታጠምቅዎሙ በሉ በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ" የሚለው ኃይለ ቃል በንባብ አሰምቷል፡፡ ከዚያም በቅዱስነታቸው መሪነት የሰርክ ጸሎተ ኪዳን ደርሷል፡፡ በመቀጠልም በቅዱስነታቸው ፈቃድ ብፁዕ ዶ/ር አቡነ ገሪማ /ዶ/ር/ ጥናታዊ ትምህርት "ሑሩ ወመሐሩ" ሒዱና አስተምሩ ይላል እግዚአብሔር አምላካችን በሚል ርዕስ አስተምሯል፡፡

ሙሉ ቃሉን ከዚህ በታች ይመልከቱ፤

 በተጨማሪ ያንብቡ…

መደበኛ የጥቅምት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተጀመረ

ጥቅምት 11 ቀን 2006 ዓ.ም በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱመ ወእጨጌ ዘመነበረ ተክለሃይማኖት ፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያው ኃላፊዎች ከመላ ሀገሪቱ የተሰበሰቡ የቤተ ክርስቲያኒቱ ተወካዮች ምእመናንና ምእመናት በተገኙበት ከቀኑ 10-11.40 ተካሂዷል፡፡

የሠርክ ጸሎት ዳዊት፣ ውዳሴ ማርያም፣ አድኅነነ እግዚኦ፣ መልከአ ማርያም፣ መልከአ ኢየሱስ ተደግሞ "ኢትግድፈነ ወኢትመንነነ አምላከ ሰላም ተራድአነ" በማለት በዜማ ደርሷል፡፡

በመቀጠልም መስተብቁዕና ሊጦን በቅዱስነታቸው መሪነት በሊቃነ ጳጳሳት በግእዝ ዜማ ደርሷል፡፡ "አምላክነ ዘዲበኪሩቤል ትነብር" የሚለውን በአራራይ ዜማ ተዚሟል፡፡

ብፁዕ አቡነ ገሪማ /ዶ/ር የብፁዕ ወቅዱስ ልዩ ጽ/ቤትና የውጭ ጉዳይ የበላይ ኃላፊ "ሃሌ ሉያ ዘበእንቲአሃ ለቤተ ክርስቲያን ተጸፋዕከ በውስተ አውድ" የሚለው ዋዜማን ተመርቷል፡፡ ከዚያም በማያያዝ "መሐረነአብ" ተብሎ እግዚኦታ በዜማ የደረሰ ሲሆን በሊቀ ዲያቆኑ "ባርክ ቤተ አሮን" ወባርክ እለይፈርሕዎ ለእግዚአብሔር ለንኡሶሙ ወለአቢዮሙ" የሚለው የዳዊት መዝሙር በዜማ ከሰበከ በኋላ ብፁዕ አቡነ ገሪማ የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 28 ቁ. 19-20 "ሑሩ ወመሐሩ ውስተ ኲሉ አጽናፈ ዓለም ወእንዘታጠምቅዎሙ በሉ በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ" የሚለው ኃይለ ቃል በንባብ አሰምቷል፡፡ ከዚያም በቅዱስነታቸው መሪነት የሰርክ ጸሎተ ኪዳን ደርሷል፡፡ በመቀጠልም በቅዱስነታቸው ፈቃድ ብፁዕ ዶ/ር አቡነ ገሪማ /ዶ/ር/ ጥናታዊ ትምህርት "ሑሩ ወመሐሩ" ሒዱና አስተምሩ ይላል እግዚአብሔር አምላካችን በሚል ርዕስ አስተምሯል፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከጥቅምት 4-11 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም. ድረስ የተካሔደው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ 32ኛ መደበኛ ስብሰባ፣ ቃለ ጉባኤ፡-

የጉባኤው መደበኛ አባላትና ተሳታፊዎች፡-

 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም፣ወዕጨጌ ዘመንበረ ተ/ሃይማኖት የጉባኤው ርእሰ መንበር፣

 • ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የጠ/ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የወላይታ ኮንታና ዳውሮ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የጉባኤው መርሐ-ግብር መሪ፣

 • ብፁዕ አቡነ ሉቃስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የሰቲት ሁመራ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የጉባኤው አባል፣

 • ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የጉባኤው አባላት፣

 • ክቡር ዶ/ር አባ ኅ/ማርያም መለሰ የጠ/ቤተ ክህነት፣ ምክትል ሥራ አስኪያጅ የጉባኤው አባል፣

 • ክቡር ንቡረ እድ ኤልያስ አብርሃ የጠ/ቤተ ክህነት የመን/ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ የጉባኤው አባል፣

 • ክቡራን የጠ/ቤተ ክህነት የየመምሪያውና ድርጅት ሓላፊዎች፣ የጉባኤው አባላት፣

 • የየሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች የጉባኤው አባላት ፣

 • የአህጉረ ስብከት የካህናት፣ የምእመናን፣ የሰንበት ት/ቤቶች ተወካዮች የጉባኤው አባላት፣

 • የአህጉረ ስብከት ሰበካ ጉባኤ ማደራጃና የስብከተ ወንጌል ክፍል ሓላፊዎች የጉባኤው አባላት፣

 • ክቡራን በውጭ ሀገር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አህጉረ ስብከት ተወካዮች የጉባኤው አባላት ሆነው በየመንበራቸው ተገኝተዋል፡፡

 • እንዲሁም የጠ/ቤተ ክህነት የየመምሪያው ምክትል ሓላፊዎችና የዋና ክፍል ሓላፊዎች፣

 • በዐዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የየክፍለ ከተማው ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጆችና ጸሐፊዎች፣

 • የዐዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፣ የሰበካ ጉባኤያት ምክት/ሊቃነ መናብርት፣

 • የማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል የአመራር አባላት፣

 • የደብረ ሊባኖስ ገዳም ጸባቴና የቁሉቢ ደብረ ኅ/ቅ/ገብርኤል ገዳም አስተዳዳሪ ሁለት ራሳቸው በክብር ተሳታፊነት ተገኝተዋል፡፡

የጉባኤው መንፈሳዊ ሒደት፡-


- ለጉባኤው በወጣው መርሐ ግብር መሠረት ጥቅምት 4 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም. ከጧቱ 2-2፡3ዐ የጉባኤው አባላትና ተሳታፊዎች እየተመዘገቡ በአዳራሹ ከቀድሞው ለየት ባለ አኳኋን የተዘጋጀ ቦታ ቦታቸውን ይዘዋል፡፡
የጉባኤው አባላት ቦታ ቦታቸውን እንደያዙም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ሊቀ ጳጳስ ዘአኲሱም፣ ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በአዳራሹ በአባታዊ ክብር ተገኝተዋል፡፡ ጉባኤውም በብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጅ መሪነት በታላቅ አክብሮት ተቀብሏቸዋል፡፡ ቅዱስነታቸው ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳጳሳት ጋር በአዳራሹ እንደተገኙ ጉባኤው በቅዱስነታቸው ጸሎተ ቡራኬ በይፋ ተከፍቶ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ልኡካን ጸሎተ ወንጌል ደርሷል፡፡ በጸሎተ ወንጌሉም ከመዝ.64፦5

"ስምዐነ አምላክ ወመድኅኒነ፣
ተስፋሆሙ ለኩሎሙ አጽናፈ ምድር፣
ወለእለሂ ውስተ ባሕር ርሑቅ" የሚለው ምስባክ እንደ ሥርዐቱ ተሰብኮ እንደአበቃ ከማቴዎስ ወንጌል ምዕ.18፡8-21 ያለው በቅዱስነታቸው ተነቧል፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የወላይታ ኮንታና ዳውሮ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በ2ዐዐ6 ዓ.ም. የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ 32ኛ አጠቃላይ መደበኛ ስብሰባ፣ በመንበረ ፓትርያርክ ያስተላለፉት መልእክት

 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣

 • ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት

 • ክቡራን የጉባዔው ተሳታፊዎች

‹‹ኮልኬ ዘበዕራይስጢ
እለቅቡዓን በደመ ሐርጌ ዘገለአድ
በህየ ሐመት ብከ እምከ
ወበህየ ሐመት ብከ እምከ ወላዲትከ››

ከእንኮይ በታች አስነሳሁህ፤
በዚያ እናትህ ወለደችህ፣
በዚያም ወላጅ እናትህ አማጠችህ፡፡
መሐልየ ሰሎሞን 8፡5

ወላዷ እናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እያማጠች ወልዳ፣ እየተራበች አጥብታ፣ እየተቸገረች አብልታ፣ እየሞተች አድና፣ እየደከመች አጽናንታ፣ ልጆቿን ከዲቁና ወደቅስና፣ ከቅስና ወደ ምንኩስና፣ ከምንኩስና ወደ ጵጵስና ከዛም መርጣ ለፕትርክና እያዘጋጀች መልካም ውበቷ ሳይደበዝዝ መካሪ ወንጌሏ ሳይታጠፍ፣ በረከት ማዕዷ ሳይጐል እስከአሁን ከአበው ነቢያት እስከ ሐዋርያት ከዛም እስከ ሰማዕታት ጻድቃን ሊቃውንት አበው ካህናት ድረስ ፊት ለፊት በመተያየት እስከ አሁን ድረስ የተራራ ላይ መብራቷ እንደበራና እንደደመቀ ይታያል፣ ሲታይም ይኖራል፡፡ ይህንንም የብርሃን መብራት በዓይናችን እያየነው በአንደበታችን እያደነቅነው እየመሰከርነው እንገኛለን፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

በኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን
መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
የትምህርትና ማሰልጠኛ መምሪያ የ5 ዓመት መሪ ዕቅድ ማዘጋጀቱን ይፋ አደረገ

አንጋፋው እና የቤተ ክርስቱያናችን እና የሀገራችን ባለውለታ የሆነው የትምህርትና ማሠልጠኛ መምሪያ ለአያሌ ዘመናት ተዘንግቶ የቆየ ሲሆን አሁን ወደ ጥንተ ክብሩ ለመመለስ ዘርፈ ብዙ ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለሀገር ለወገን የሚጠቅም እጅግ ብዙ ታላላቅ ሥራዎችን አበርክታለች እንደሀገር ስለኢትዮጵያ ታሪክ ሲነሣም ይህቺ ቤተ ክርስቲያን መነሳቷ የማይቀር ነው ምክንያቱም የሀገሪቱ ታሪክ አብዛኛው የተሠራው በዚች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከተገኙት ልጆቿ በመሆኑ ነው፡፡

ዛሬ የምናወሳው የራሷ ሥነ ጽሑፍ ፣ ፊደል ፣ ቋንቋ እያልን የምንናገረው በዘመናችን ያለው የዘመናዊ ት/ቤት ከመጀመሩ በፊት ቤተ ክርስቲያን የአብነት ትምህርት ቤቶችን በመክፈት ፊደሉን ፣ ቋንቋውን ፍልስፍናውን ጥበቡን ቅኔውን ዜማውን ትርጓሜውን ፣ የዕለታት የአውራህ የዓመታትና የዘመናት ቀመር በመቀመር ለሀገራችን ኢትዮጵያ ያበረከተችው ምትክ የማይገኝላቸው ውለታዎች አሁን ላለው የዘመናዊ ት/ቤትም በር ከፋች እንደሆነች የታሪክ ድርሳናት ይመሰክራሉ ፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

የ32ኛ የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ተጀመረ፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በ32ዓ የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ የሰበካ ጉባኤ ከመላው ሀገሪቱ ለተሰበሰበው ጉባኤተኛ የመክፈቻ ንግግር አድርጓል፡፡
በመቀጠልም ብፁዕ አቡመ ማቴዎስ የመንበረ ፓትርያርክ ዋና ሥራ አስኪያጅ የወላይታ ኮንታና ዳውሮ አኅጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የ2005 ዓ.ም አጠቃላይ ሪፖርት ለጉባኤው አርጓል ዝርዝር ይዞታውን ወደፊት እናቀርባለን፡፡

ክፍል 1

ክፍል 2

ክፍል 3

ክፍል 4

የ2006 ዓ.ም የተቀፀል ጽጌ በዓል በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተከበረ፡፡

በየዓመቱ መስከረም 10 ቀን በድምቀት የሚከበረው የተቀፀል ጽጌ በዓል በዘንድሮውም ዓመት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፣ብፁዓን ሊቃ ጳጳሳት፣የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያው ኃላፊዎች፣ የአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና፣የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች እንዲሁም ምእመናን በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል ፡፡
በበዓሉ ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ እንደገለፁት ይህ በዓል ዘመን በተቀየረ በ10ኛው ቀን ላይ የሚከበር ሲሆን የበዓሉ ታሪካዊ አመጣጥና የአከባበር ሥርዓቱም አስደሳችና ማራኪ ነው እኛም ከበዓሉ ሥርዓት በማስከተል የዓመቱ መጀመሪያ እንደ መሆኑ መጠን ለአገልግሎታችንና ለሥራችን እቅድ አውጥተን ሥራችንን የምንጀምርበት በመሆኑ ሁላችንም ተባብረንና ተጋግዘን ተግባራችንን እንድንፈጽም እንዲሆን እየገለጽኩ አዲሱ ዓመት የሥራና የብልጽግና እንዲሆን እመኛለሁ በማለት ገልጸዋል ፡፡
በበዓሉ ላይ የምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት፣የቆሜ አጫብር መዘምራንና የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች በዓሉን አስመልክተው ጣእመ ዝማሬ አቅርበዋል ፡፡

Picture 1342 Picture 1344 Picture 1348 Picture 1352 Picture 1371 Picture 1376 Picture 1378 Picture 1379 Picture 1380 Picture 1381 Picture 1382 Picture 1383 Picture 1384

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት እና ብፁዓን ሊቃ ጳጳሳት በሰበታ ጌቴሴማኒ ቤተ ደናግል ጠባባት ገዳም ሐዋርያዊ ጉብኝት አደረጉ

 ክፍል 1

 ክፍል 2

የማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች ምረቃ ሥነ ሥርዓት፡፡

 ክፍል 1

 ክፍል 2

 

የ2005 ነሐሴ ዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣን ለማንበብ ምስሉን ይጫኑ

More Articles...

የፎንት ልክ መቀየሪያ