Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምለክ አሜን !

በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 ላይ ከበዓለ ትንሣኤ በኋላ በሃያ አምስትኛው ቀን የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ እንዲካሔድ በተደነገገው ቀኖና ቤተክርስቲያን መሠረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ከግንቦት 21 – 30 ቀን 2005 ዓ.ም ተካሒዷል፡፡


ይህ ጉባኤ የርክበ ካህናት ጉባኤ ተብሎ የሚታወቅ ሲሆን ከላይ በተጠቀሰው ቀኖና ቤተክርስቲያን እንደተገለፀው ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በቤተክርስቲያን ያለውን አጠቃላይ መንፈሳዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኀበራዊ ጉዳዮችን በማየት በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ታላላቅ ውሳኔዎችን የሚወስንበት ዓበይት ጉባኤ ነው፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ በቤተክርስቲያናችን ውስጥ ያሉትን ወቅታዊና ማህበራዊ ጉዳዮችን ለመመርመርና ለመገምገም ባለው ሐዋርያዊ ኃላፊነት ለቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ተልእኮ አፈጻጸም እንቅፋት ናቸው ብሎ ያመነባቸውን ጉዳዮች በአጀንዳ ቀርጾ፣ በስፋትና በጥልቀት ተወያይቶ ውሳኔ ሰጥቶባቸዋል፡፡

ቅድስት ቤተክርስቲያናችን በምድር ላይ ያለች የእግዚአብሔር መንግሥት ማዕከል ፣በባሕርይዋም ንጽሕትና ቅድስት ብትሆንም ኃጢአትና ስሕተት በነገሠበት ዓለም ያለች በመሆንዋ ከእርስዋ መሠረታዊ ባሕርይ ጋር የማይስማማ ተግባራት እንዳይጋቡባት የመጀመሪያው ጥበቃ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ላይ ያረፈ ነው፡፡ በተለይም የአሁኑ ዓላማችን ጥበብ ሕዝበ ክርስቲያኑን መምራት፣ ማስተማርና ማገልግል ይጠበቅበታል፡፡ በቤተክርስቲያናችን እነዚህን የተቀደሱ ተግባራት በሥራ ለመተርጐም ወቅታዊ እንቅፋት ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮች ምን ምን ናቸው በማለት ቅዱስ ሲኖዶስ በጥልቅ ተመልክቶአል፡፡

በዚህም መሠረት ጉባኤው ብዙ ውይይት ካደረገ በኋላ የሚከተሉትን ዓበይት ውሳኔዎች አሳልፎአል፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በሥነ ተዋልዶና በእናቶች ጤና ላይ ያላትን አቋም በሚመለከት ባለ 10 ነጥብ መግለጫ ሰጠች

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዓመታዊ መደበኛ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ እየተካሄደ በሚገኝበት መካከል የእናቶችን ጤናን አስመልክቶ ግንቦት 28 ቀን 2005 ዓ.ም ከቀኑ 9-10፡00 ሰዓት ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ሚኒስትሮች፣ የተለያዩ የዓለም አቀፍ ድርጅት ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ምልዓተ ጉባኤው በሚካሄድበት አዳራሽ በእናቶች ጤናና በሥነ ተዋልዶ ላይ ያላትን የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮና አቋም በአሥር ነጥቦችን በመዘርዘር በቅዱስ ፓትርያርኩ አማካይነት ይፋ አደረገች፡፡

ይህንን መርሐ ግብር ያቀናጀው በልማት ኮሚሽን የኤች. አይ. ቪ መምሪያ አስቀድሞ ስለ ጉዳዩ ሰፊ ማብራሪያ በመምሪያ ኃላፊው በቀሲስ ሶምሳን የተሰጠ ሲሆን ይህንን የቤተ ክርስቲያን አቋምና ትምህርት ወቅታዊና ታሪካዊ መሆኑም በዕለቱ የተገኙ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ገልጾዋል፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

በቤተ ክርስቲያኒቱ የሚታየውን ብልሹ አሠራር በማስወገድ ተልዕኮን ለማስፈጸም ተጠያቂነትን የሚፈጥር አሠራር ሊኖራት እንደሚገባ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ገለፁ፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ይህንን የገለፁት ዛሬ በተጀመረው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ላይ ነው፡፡

በዓመት ሁለት ጊዜ በቤተ ክርስቲያኗ፣ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ሰፊ ውይይት በሚደረግበት በዚህ ጉባኤ ላይ ፓትርያርኩ እንደገለፁት የቤተ ክርስቲያኗ አስተዳደር ሂደት ሲመረመር እጅግ የተንዛዛ ቢሮክራሲ የሰፈነበትና የሰው ኃይል አመዳደቡም ከመሠረታዊው የቤተ ክርሰቲያኗ ተልዕኮ ዕቅድ ጋር ያልተቀናጀ ከመሆኑም በላይ በወገንተኝነትና በሙስና የተከናወኑ የሥራ ሒደቶች በመሆናቸው ለእድገቷ ማነቆ ሆነው ተገቢውን ሥራ ለማከናወን ባለመቻሏ ሁኔታውን ለማረም ቅዱስ ሲኖዶስ በአስቸኳይ የእርምት እርምጃ ሊወስድ ይገባል በማለት ገልፀዋል፡፡

የሀገሪቱ መንግሥት ሙስናን ለማጥፋት በሚታገልበት በዚህ ወቅት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ፍጹም ይህ መታየት የለበትም ያሉት ቅዱስ ፓትርያርኩ የቤተ ክርስቲያኗን ስም ለማጥራት እንዲቻል ሥር ነቀል ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል እርምጃዎች በቆራጥነት ተግባራዊ እንዲሆን ላሳስብ እወዳለሁ ብለዋል፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በዓለ ሲመት

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስድስተኛው ፓትርያርክ ምርጫ ብፁዕ አቡነ ማቲያስን በምምረጥ ተጠናቋል።

ዛሬ የካቲት 21 ቀን 2005 ዓ.ም ከጠዋቱ በ 12 ሰዓት ጅምሮ ብፀዓን ሊቃነ ጳጳሳት፤ የመምሪያ ሓላፊዎች፤ የሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጆችና ሌሎችም በቅደም ተከተል በተገኙበት የመራጭነት ቃለ መሓላ ከፈጸሙ በኃላ በሊቃነ ጳጳሳቱ መሪነት ምርጫው በጠቅላይ ቤተክህነት የስብከተ ወንጌል አዳራሽ ውስጥ በሰላማዊ እና ሐዋርያዊ ትውፊቱን በጠበቀ መንገድ ከ806 ድምጽ 500 ድምጽ በማግኝት ብፁዕ አቡነ ማቲያስ ስድስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ሆነው መመረጣችወን በይፋ ተገልጾል።

 • ብፁዕ አቡነ ማቲያስ 500 ድምጽ

 • ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ 98 ድምጽ

 • ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ 98 ድምጽ

 • ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል 70 ድምጽ

 • ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ 39 ድምጽ

ዝርዝር ዜናውን ተከታትልን እንድምናቀርብ ከወዲሁ እንግልጻልን።

የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ልዑካን በጠቅላይ ቤተክህነት የስብከተ ወንጌል አዳራሽ ተገኝትው ድምጽ ሰጡ።

የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ ጋራ ባላት ስምምነት መሠረት አምስት ድምጽ ሰጪዎች በዛሬው ዕለት የ6ኛ ፓትርያርክ ምርጫ ላይ በጠቅላይ ቤተክህነት የስብከተ ወንጌል አዳራሽ ተገኝትው ህጉ በሚፈቅድላችው መሠረት አምስቱ ልዑካን የምርጫ ካርዳችውን በመውሰድ ድምጻቸውን ሰጥትዋል።

ከድምጽ ሰጪዎቹ መካከል ሦስቱ ሊቃነ ጳጳሳት ሲሆኑ ሁለቱ ደግሞ የቤተክርስቲያኒቱ ከፍተኛ ሃላፊዎች ናቸው። ከምርጫው አስቀድሞ ከግብፅ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ልዑካን ድምጽ ሰጪዎች መካከል አንድ አባት ሰፊ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራችው "እኛ ከግብፅ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ የመጣነው ድምጽ ለምስጠት ብቻ ሳይሆን ከኢትዮጵያውያን ወንድሞቻችን ጋር ጎን በመሆን ለዚህች ለተቀደሰች ቤ/ክ እግዚአብሔር መልካም እረኛ እንዲሰጣት ለመጸለይም ጭምር ነው፤እኛ ከግብፅ የቅዱስ ማርቆስን በረከትን ይዘንላችሁ መጥተናል፤ ከዚህም ደግሞ የቅዱስ አባታችን አቡነ ተ/ሃይማኖትን በረከት ይዘን እንሄዳለን፤ መንፈሳዊ ምርጫ ለመንፈሳዊ አገልግሎት ነው በመሆኑም ይሄንን ሃላፊነት የሚሸከም አባት እግዚአብሔር ለዚህች እህት ቤ/ክ እንዲሰጣት ተነሱና አብረን እንጸልይ" በማለት ጸሎት አድርገዋል። በመቀጠልም አምስቱ ልዑካን የመረጡ ሲሆን ታዛቢዎችም በተዘጋጀላቸው ቦታ ላይ ሆንው በመታዘብ ላይ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ የ6ኛ ፓትርያርክ ምርጫ እየተካሄደ ነው።

ዛሬ የካቲት 21 ቀን 2005 ዓ.ም ከጠዋቱ በ 12 ሰዓት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ከየአሃጉረ ስብከቱ የመጡ ተወካዮች በተገኙበት የመራጭነት ቃለ መሓላ ከፈጸሙ በኃላ በሊቃነ ጳጳሳቱ መሪነት ምርጫው በጠቅላይ ቤተክህነት የስብከተ ወንጌል አዳራሽ ውስጥ ሐዋርያዊ ትውፊቱን በጠበቀ መለኩ በሰላማዊ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል።
ምርጫው እንደተጠናቀቀ አሸናፊው ፓትሪያርክ በዛሬው ዕለት ይፋ የሚድረግ ሲሆን፡ ውጤቱን እየተከታተልን የምናቀርብ መሆኑን ከወዲሁ እንገልጻለን።

 

የስድስተኛው ፓትርያርክ አስመራጭ ኮሚቴ ዛሬ የካቲት 18 ቀን 2005 ዓ.ም ዕጩ ፓትርያርኮችን አስመልክቶ መግለጫ ሰጠ፡፡

ስድስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ አስመራጭ ኮሚቴ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በተገኙበት ዛሬ የካቲት 18 ቀን 2005 ዓ.ም የአምስቱ ዕጩ ፓትርያርኮች ስም ዝርዝርና የምርጫ ሁኔታውን አስመልክቶ መግለጫ ሰጠ፡፡

አሰመራጭ ኮሚቴው በመግለጫው እንደገለጸው አስቀድሞ ለምዕመኑ በተላለፈው ጥሪ መሠረት ጥቆማ ማካሄዱን ገልጾ ይህንን ጥቆማ እንደግብአት በመጠቀም የምርጫ ሕጉ መሠረት በማድረግ ሰፊ ምክክርና ጥልቅ ውይይት ከተደገረ በኋላ አምስት አባቶችን መርጦ ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አቅርቦ ምልዓተ ጉባኤው በአስመራጭ ኮሚቴው የቀረቡ አባቶች በሙሉ ተቀብሎ በማሳለፉ ምክንያት ዛሬ ስማቸው ለሕዝብ በይፋ ለሕዝብ ለመግለጽ በቅተናል ብሎአል፡፡

የዕጩ ፓትርያርኮቹ ስም ዝርዝር፡-


1. ብፁዕ አቡነ ማቲያስ

2. ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ

3. ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል

4. ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ

5. ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ መሆናቸውን ይፋ አድርጎአል፡፡ አስመራጭ ኮሚቴው ያስተላለፈውን ሙሉ መግለጫ ከዚህ እንደሚከተለው ቀርቦአል፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

የስድስተኛው ፓትርያርክ አስመራጭ ኮሚቴ ዛሬ የካቲት 18 ቀን 2005 ዓ.ም ዕጩ ፓትርያርኮችን አስመልክቶ መግለጫ ሰጠ፡፡

ስድስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ አስመራጭ ኮሚቴ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በተገኙበት ዛሬ የካቲት 18 ቀን 2005 ዓ.ም የአምስቱ ዕጩ ፓትርያርኮች ስም ዝርዝርና የምርጫ ሁኔታውን አስመልክቶ መግለጫ ሰጠ፡፡

አሰመራጭ ኮሚቴው በመግለጫው እንደገለጸው አስቀድሞ ለምዕመኑ በተላለፈው ጥሪ መሠረት ጥቆማ ማካሄዱን ገልጾ ይህንን ጥቆማ እንደግብአት በመጠቀም የምርጫ ሕጉ መሠረት በማድረግ ሰፊ ምክክርና ጥልቅ ውይይት ከተደገረ በኋላ አምስት አባቶችን መርጦ ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አቅርቦ ምልዓተ ጉባኤው በአስመራጭ ኮሚቴው የቀረቡ አባቶች በሙሉ ተቀብሎ በማሳለፉ ምክንያት ዛሬ ስማቸው ለሕዝብ በይፋ ለሕዝብ ለመግለጽ በቅተናል ብሎአል፡፡

የዕጩ ፓትርያርኮቹ ስም ዝርዝር፡-


1. ብፁዕ አቡነ ማቲያስ

2. ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ

3. ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል

4. ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ

5. ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ መሆናቸውን ይፋ አድርጎአል፡፡ አስመራጭ ኮሚቴው ያስተላለፈውን ሙሉ መግለጫ ከዚህ እንደሚከተለው ቀርቦአል፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

ራሱን "ቅዱስ ሲኖዶስ" ብሎ የጠራው አካል ያወጣውን የሐሰት መግለጫ በተመለከተ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

"ኢያስሕቱክሙ አኃዊነ ፍቅራን፤
የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ እንዳያስቷችሁ ተጠንቀቁ" ያዕ. 1፡16

ስሕተት በባህርዩ ጎጂና በማናቸውም ጊዜ የማይደገፍ ቢሆንም ከሰው ጋር አብሮ የሚኖር በመሆኑ ሰው ከስሕተት ጸድቶ አያውቅም፣ ስሕተትም ከሰው ጠፍቶ አያውቅም፡፡

ቅዱስ መጽሐፍ ለሰው የሚያስተላልፈው ቋሚ ምክር ሰው ስሕተትን እንዳይፈጽም ነው፤ አውቆም ሆነ ሳያውቅ ስሕተት ከፈጸመ ደግሞ በንሥሐ እንዲመለስ ነው፣ ቅዱስ መጽሐፍ ስሕተት እንዳይፈጸም አጥብቆ ከማስተማሩም በተጨማሪ ስሕተትን በንስሐ ማሰረዝ የሚያስችል ጸጋ አለው፣ ሰዎች በዚህ ጸጋ እየተጠቀሙ ራሳቸውን ያስተካክላሉ እግዚአብሔርንም ያስደስታሉ፡፡

ሰው በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ፍጹም ተወቃሽ የሚሆነው ስሕተትን በመፈጸሙ ብቻ ሳይሆን ስሕተቱን አምኖ በመቀበል በንስሐ ለመታረም ዝግጁ ባለመሆኑ ነው፡፡

በክርስቶስ ደም የተመሠረተችና በመንፈስ ቅዱስ ጥበቃ የምትጠበቅ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በሃይማኖቷ፣ በትምህርቷና በሥርዓቷ እንከን የለሽ ቤተ ክርስቲያን ለመሆኗ ዓለም የሚመሰክረው ሐቅ ነው፡፡ ይሁንና በውስጧ የሚገኙ አገልጋዮች ሰው እንደመሆናቸው መጠን አልፎ አልፎ ስሕተት አይፈጽሙም ማለት አይቻልም፡፡

በተጨማሪ ያንብቡ…

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የ6ኛው ፓትርያርክ አስመራጭ ኮሚቴ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

downloadበቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የተቋቋመው የስድስተኛው ፓትርያርክ አስመራጭ ኮሚቴ የምርጫውን ሂደት በተመለከተ ጥር ሰላሳ ቀን 2005 ዓ.ም አጠቃላይ መግለጫ መሰጠቱ ይታወሳል፡፡ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫም የሚዲያ ተቋማት መልእክቱን ለሕዝብ እንዲደርስ ስላደረጋችሁ በቤተ ክርስቲያናችን ስም እናመሰግናለን፡፡

ባለፈው ሳምንት የተፈጸሙ የሥራ ክንውኖች፡-

1. አስመራጭ ኮሚቴው ባጸደቀውና በቋሚ ሲኖዶስ በተወሰነው መሪ ዕቅድና የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ከየካቲት አንድ ቀን 2005 ዓ.ም እስከ የካቲት ስምንት ቀን 2005 ዓ.ም ድረስ ማኅበረ ካህናቱና ምዕመናኑ በአግባቡ መምራተት የሚችል አባት እግዚአብሔር አምላካችን ለቤተ ክርስቲያን እንዲሰጥ በጸሎት እንድንጠይቅ መልዕክት መተላለፉ ይታወሳል፡፡ መላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናትና ምዕመናን የቤተ ክርስቲያን ድምጽ ሰምተን ጸሎታችንን ለፈጣሪያችን በማቅረብ ላይ ነን፡፡ በቀጣይም የምርጫው ሂደት እስከሚጠናቀቅ ድረስ ካህናትና ምዕመናን ጸሎታችንን አጠናክረን መቀጠል ይኖርብናል፡፡

በተጨማሪ ያንብቡ…

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ካህናት ምዕመናንና የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ጥቆማ መስጠታቸውን ቀጥለዋል፤

 • የጥቆማ አሠጣጥ ክዋኔ በመርሐ ግብሩ መሠረት ዛሬ ይጠናቀቃል፡፡

 • አስመራጭ ኮሚቴው ዛሬ በአሥር ሰዓት አጠቃላይ መግለጫ ይሠጣል

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በወሰነው መሠረት የስድስተኛው ፓትርያርክ አስመራጭ ኮሚቴ ተቋቁሞ የሥራ መርሐ ግብርን በመገናኛ ብዙኃን ይፋ አድርጎ መንቀሳቀስ ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡ በመሆኑም አስመራጭ ኮሚቴው የመርሐ ግብሩ መጀመሪያ ያደረገው የቤተክርስቲያኒቷ ልጆች በአገር ውስጥ ያሉ በአካል እየቀረቡ በተዘጋጀላቸው ቦታ ፎርም በሞሙላት፤ በውጭ ሀገር ያሉ በፋክስ ተጠቅመው ስድስተኛ ፓትርያርክ እንዲሆን የሚፈሉጉትን አባት ጥቆማ እንዲያካሂዱ የማድረግ ሥርዓት ነው፡፡

በመሆኑም በውጭ ሀገር የሚገኙ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ምዕመናንና አገልጋዮች ፋክስ እያደረጉ ሲሆን በሀገር ውስጥ የሚገኙትን ደግሞ በመንበረ ፓትርያርክ ለዚህ ተግባር ወደ ተዘጋጀ ቢሮ በአካል በመቅረብ ፎርሙን በመሙላት ወደ ታሸጉት ሳጥኖች በማስገባት የልጅነት ድርሻቸውን በመወጣት ላይ ይገኛሉ፡፡

በተለይ ደግሞ ከአዲስ አበባ ውጭ ከየክፍለ ሀገሩ የሚመጡ ምዕመናን የትራንስፖርታቸውን ሙሉ ወጪ እየተሸፈነላቸው እንደሆነም ከኮሚቴው መረዳት ተችሎአል፡፡ ይህ የጥቆማ መርሐ ግብር ዛሬ ዓርብ 08/05/2005 ዓ.ም ከምሽቱ በአስራ ሁለት ሰዓት የሚጠናቀቅ ሲሆን ይህንንና መሰል የምርጫ ጉዳዮችን በማስመልከት አስመራጭ ኮሚቴው ዛሬ በአስር ሰዓት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥ ለማወቅ ተችሎአል፡፡ የተከበራችሁ አንባቢዎች የመግለጫውን ሙሉ ይዘት ተከታትለን እናቀርባለን፡፡

More Articles...

የፎንት ልክ መቀየሪያ