Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

የአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት ሰንበት ትምህርት ቤቶች ለጠቅላይ ሚንስቲሩ ያላቸውን ጥልቅ ሐዘን ገለጹ፡፡

የአዲስ አበባ አድባራት ገዳማትና አድባራት ሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ከቅዱስ ፓትርያርኩ ሥርዓተ ቀብር በኋላ የደንብ ልብሳቸውን ለብሰው በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምርያ አስተባባሪነት በቤተ መንግስት ተገኝተው በክቡር ጠቅላይ ሚንስትር በአቶ መለስ ዜናዊ ድንገተኛ ሕልፈት ሕይወት የተሰማቸው ጥልቅ ሐዘን ነሐሴ 17 ቀን 2004 ዓ.ም ገለጹ፡፡

የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶቹ በሥነ ሥርዓት በቤተ መንግስት ቦታ ተዘጋጅቶላቸው ከገቡ በኋላ "ኢትዮጵያ ታበጽሕ እደዊሃ ኀበ እግዚአብሔር፡- ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች፤ ማርያም ድንግል ሐዘነ ልቡና ታቀልል" የሚሉትን መዝሙሮች አቅርበዋል፡፡ በመቀጠልም በቦታው የተገኙ የጠቅላይ ሚንስትሩ የሥራ ባልደረቦችና ቤተሰቦች እንዲሁም ለአጠቃላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ በቤተ ክርስቲያናችን፣ በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምርያና በሁሉም የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት ስም መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ሥርዓተ ቀብር ዛሬ ነሐሴ 17 ቀን 2004 ዓ.ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጸመ፡፡

at holly trinity final hour government officials at ht marching band open view pm giving speach prayer the crowd

የብፁዕ ወቅዱስ ዶ/ር አቡነ ጳውሎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንትና የዓለም የሰላም አምባሳደር ሥርዓተ ቀብር ዛሬ ነሐሴ 17 ቀን 2004 ዓ.ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ዋና ጸሐፊና ልዑካን፣ የኦሬንታል አብያተ ክርስቲያናት የቅዱሳን ፓትርያርኮች ተወካዮችና ልዑካን፣ የተለያዩ የሃይማኖት መሪዎች፣ ክቡር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትርና የውጭ ጉዳይ ሚንስትር፣ አቶ አባዱላ ገመዳ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ፣ አቶ ኩማ ደመቅሳ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ እና በአጠቃላይ ሁሉም ሚንስትሮችና ዲፕሎማቶች፣ የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አገልጋዮችን ምዕመናን በተገኙበት ከቀኑ በሰባት ሰዓት ላይ ተፈጽሞአል፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አስከሬን ደማቅ አሸኛኘት ተደረገለት፡፡

on the way to saint triniry police m.band sunday school 1 sunday school 2

በሐያት ሆስፒታል የቆየው የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አስከሬን ነሐሴ 16 ቀን 2004 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ወደ መንበረ ፓትርያርክ የስብከተ ወንጌል አዳራሽ መጥቶ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት ካህናትና ምዕመናን እንዲሁም የቅዱስ ፓትርያርኩ ቤተሰቦች በተገኙበት ለተወሰነ ጊዜ አርፎ ጸሎት ወንጌል በብፁዕ አቡነ ናትናኤል የመንበረ ፓትርያርክ ዓቃቤ መንበርና የአርሲ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ መሪነት ተካሂዶአል፡፡

በመቀጠልም የቅዱስ ፓትርያርኩ አስከሬን በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ በካህናትና በምዕመናን በከፍተኛ ክብር ታጅቦ በሕይወት እያሉ በዋናነት ያገለግሉበትና በዚህ በሱባኤ ጾመ ፍልሰታም ሱባኤ ይዘው ሲያገለግሉበት የነበሩት ገዳማቸው ወደ መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ከቀኑ በስድስት ሰዓት ገብቶ አርፎአል፡፡ ከጸሎተ ፍትሐቱ በተጨማሪ ጸሎተ ቅዳሴውም እዚሁ ገዳማቸው ተቀድሶበታል፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

"ለፈራሔ እግዚአብሔር ይሤኒ ደኅሪቱ፣ ወይትባረክ ዕለተ ሞቱ"

"እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ፍፃሜው ያምራል፡፡ በሚሞትበትም ቀን ይከበራል" ሲራ. 1፡13፡፡

የብፁዕ ወቅዱስ ዶ/ር አቡነ ጳውሎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንት የዓለም የሰላም አምባሳደር የቀብር ሥነ ሥርዓት የወጣ መርሐ ግብር

 በተጨማሪ ያንብቡ…

animated_candleAbune_paulos_and_prime_minster_melesanimated_candle

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ መለስ ዜናዊ አረፉ

meles_zenawi

ኢትዮጵያን በመምራት ለሃያ አንድ ዓመታት ሀገራቸውንንና ህዝባቸውን ሲያገለግሉ የቆዩ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን የኢፌድሪ መንግስት ዛሬ በይፋ ገልጾአል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ያደረባቸው ሕመም ያለዕረፍት ለብዙ ጊዜ በሥራ ላይ በመቆየታቸው ምክንያት የመጣ መሆኑንና በውጭ ሃገር የሕክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደነበር ቀደም ብሎ መንግስት መግለጹ ይታወሳል፡፡ በመሆኑም ጠቅላይ ሚኒስቴሩ በሕክምና ሲረዱ ከቆዩ በኋላ ዛሬ መንግስት ዜና ዕረፍታቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያም በክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ሞት በቤተ ክርስቲያኒትዋ ስምና በመላ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ወጣቶች እንዲሁም በመምሪያው ስም የተሰማውን መሪር ሐዘን ይገልጻል፡፡ እግዚአብሔር ነፍሳቸውን በገነት መንግስተ ሰማያት ያሳርፍልን፡፡ አሜን፡፡

ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ዓቃቤ መንበረ ፓትርያርክ ሆነው መመረጣቸውን ቅዱስ ሲኖዶስ አስታወቀ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ዛሬ ባደረገው ስብስባ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ዓቃቤ መንበር ሆነው መመረጣቸውን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል አስታወቁ፡፡

ብፁዕነታቸው ዛሬ ከቀኑ 9፡30 ሰዓት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት ምልዓተ ጉባኤው ዛሬ ባደረገው ስብሰባ ለቅዱስ ፓትርያርኩ ሥርዓተ ቀብር የሚመጡ የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ሀገር እንግዶች በአግባቡ ማስተናገድ እንዲቻልና መንበርም ያለ ኃላፊ አንድም ቀን ማደር ስለማይገባ በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 17 መሠረት በማድረግ ቀደምትነት ካላቸው ብፁዓን አባቶች መካከል ብፁዕ አቡነ ናትናኤል መመረጣቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡

ከዚህ በተያያዘ መልኩም ከዓቃቤ መንበር ብፁዕ አቡነ ናትናኤልና ከቋሚ ሲኖዶስ ጋር በመሆን ሥራውን የሚያከናውኑ ሥራ አስፈጻሚዎች ምልአተ ጉባኤው መሰየሙን ስማቸውን ጠቅሶ አስረድተዋል፡፡ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የተሰየሙ ብፁዓን አባቶች ስም ዝርዝር እንደሚከተለው ነው፡፡

1. ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ

2. ብፁዕ አቡነ ገብርኤል

3. ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ

4. ብፁዕ አቡነ ሉቃስ

5. ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል

6. ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ

7. ብፁዕ አቡነ አብርሃም ናቸው፡፡

የቅዱስ ፓትርያርኩ ሥርዓተ ቀብር ነሐሴ 17 ቀን 2004 ዓ.ም እንደሚፈጸም ቅዱስ ሲኖዶስ አስታወቀ፡፡

animated_candleabune_paulos_funeral_1animated_candle

የብፁዕ ወቅዱስ ዶክተር አቡነ ጳውሎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የዓለም ሃይማኖቶች የሰላም የክብር ፕሬዝዳንት ሥርዓተ ቀብር ነሐሴ 17 ቀን 2004 ዓ.ም በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በታላቅ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት እንደሚፈጸም ዛሬ ጥዋት ቅዱስ ሲኖዶስ ተሰብስቦ ውሳኔ ካስተላለፈ በኋላ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ከቀኑ በዘጠኝ ሰዓት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቶበታል፡፡

በማያያዝም የቅዱስ ፓትርያርኩ ሥርዓተ ቀብር ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን አባት ብቻ ሳይሆኑ የዓለም አብያተ ክርስቲያናትም አባት እንደመሆናቸው መጠን በሀገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ሁሉም ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፤ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምርያ ኃላፊዎችና መላ ሠራተኞች፣ የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች በአጠቃላይ ሁሉም አገልጋዮች፣ የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን፣ መላ የኢትዮጵያ ሕዝብ፤ ከውጭ የሚመጡ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት የሥራ ኃላፊዎች፣ የአምስቱ አኃት አብያተ ክርስቲያናት ፓትርያርኮችና ልዑካኖች፣ የመንግስት ኃላፊዎችና አምባሳደሮች በተገኙበት እጅግ በታላቅ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት እንደሚፈም አስረድቶአል፡፡

የሥርዓተ ቀብሩ መርሐ ግብርና አፈጻጸምም እንደሚከተለው ነው፡፡

 • ረቡዕ ነሐሴ 16 ቀን 2004 ዓ.ም ከቀትር በኋላ የቅዱስ ፓትርያርኩ አስከሬን በሠረገላ ሆኖ በሚታይ መስተዋት ምዕመናን እያዩና ኃዘናቸውን እየገለጹ አዕይንተ እግዚአብሔር ካህናትም ስብሐተ እግዚአብሔር እያደረሱ ታጅቦ ወደ መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይወሰዳል፡፡

 • እዛም እንደ ደረሰ ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ጀምሮ ሥርዓተ ፍትሐት ይጀመራል፡፡

 • ሐሙስ ጠዋት ከሥርዓተ ቅዳሴ በኋላ የዓውደ ምሕረቱ መርሐ ግብር የሚፈጸም ሆኖ የቅዱስነታቸው የሕይወት ታሪክ በተፈቀደላቸው አባት ይነበባል፡፡

 • በመቀጠልም ቅዱሳን ፓትርያርኮች ኃዘናቸውን ይገልጻሉ፡፡

 • የመንግስት ባለሥልጣናትና አምባሳደሮችም በተመደበላቸው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት የኃዘን መግለጫቸውን ካነበቡ በኋላ የቀብሩ ሥርዓት ይፈጸማል፡፡

የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት ለቅዱስ ፓትርያርኩ ሥርዓተ ቀብር የተለያዩ ዝግጅቶች እያደረጉ መሆናቸውን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምርያ አስታወቀ

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የአድባራትና የገዳማት የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች በቅዱስ አባታቸው ድንገተኛ ሞት ጥልቅ ሐዘን እንደተሰማቸውና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ሳይሆን የዓለም አብያተ ክርስቲያናትም አባት እንደመሆናቸው በሚካሄደው ዓለም አቀፍ ሥርዓተ ቀብር ወጣቶች የሰንበት ትምህርት ቤት የደንብ ልብሳቸውን ለብሰው አስፈላጊ የሆኑ መዝሙራትን አጥንተው ጥቁር ሪቫንን አጥልቀው ሥርዓተ ቀብሩን የሠመረ እንዲሆን የበኩላቸውን አገልግሎት ለማበርከት በዝግጅት ላይ መሆናቸውን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምርያ አስታወቀ፡፡ ማደራጃ መምሪው አያይዞም ይህንን መርሐ ግብር ማለትም የአሰላለፉንም ሆነ የመዝሙሩ ሁኔታ በአግባቡ የሚመሩ ኮሚቴዎች እስከታች ድረስ ተቋቊሞ ሥራ መጀመሩም ገልጾአል፡፡

ዝርዝር መርሐ ግብሩ በቅዱስ ሲኖዶስ በበተሰየመው ዓቢይ ኮሚቴ ካወጣ በኋም የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራኑ አሰላለፍ እንደሚወሰንና ለወደፊትም እንደሚገለጽ አስታውቋል፡፡

የቅዱስ አባታችን ማረፍን ተከትሎ ፕሮፌሰር ይስሐቅና የሀገር ሽማግሌዎች ያስተላለፉት የኃዘን መግለጫ

Coalition & Council of Ethiopian & Horn of Africa Elders

Addis Ababa, Ethiopia

+251-911-546340

704 Rosedale Rd, Princeton, NJ

609-577-2233

FOUNDERS:

Read more...

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት የተሰጠ

"የኀዘን መግለጫ"

"መኑ ሰብእ ዘየሐዩ ወኢይሬእያ ለሞት"

"ሰው ሆኖ ተፈጥሮ ከሞት የሚቀር ማን ነው"

animated_candle abune_paulos_patriaric_ethiopiaanimated_candle

 

በማለት ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት በትንቢትም በትምህርትም እንደተናገረው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንት ዛሬ ነሐሴ 10 ቀን 2004 ዓ.ም ከንጋቱ በ11፡00 ሰዓት ላይ ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ ተለይተዋል፡፡

ስለሆነም የቀብሩ ሥነ ሥርዓት አፈጻጸም፣ ጊዜና ቦታ በተከታታይ የሚገለጽ መሆኑን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት ያሳስባል፡፡

በክርስቶስ ሰላም

አባ ገሪማ (ዶር)

የብፁዕ ወቅዱስ ልዩ ጽ/ቤት የውጭ ግንኙነት የበላይ ኃላፊ

የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝዳንትና

የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንት ቢሮ ዋና ጸሐፊና

የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ዋና ሊቀ ጳጳስ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ፣ የግብፅን ፕሬዚዳንት ዶ/ር መሐመድ ሙርሲን ተቀብለው አነጋገሩ ፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ፣ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ፕሬዚዳንትና የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዚዳንት ፕሬዚዳንቱ በምርጫ በማሸነፋቸው እንኳን ደስ ያለዎት ካሉ በኋላ በተለያዩ የጋራ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ መክረዋል ፡፡

በዚህ ረገድ ቤተ ክርስቲያኗ የበኩሏን አስተዋፅኦ በማበርከት ላይ መሆኗንም ጭምር ገልፀዋል ፡፡

የሁለቱ ሀገራት ህዝቦች ከሁሉም በበለጠ የሚያገናኙዋቸው የጋራ ጉዳዮች በርካታ መሆናቸውን የተናገሩት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ፣ ሁለቱም መንግሥታት በሁሉም ዘርፍ ተባብረው በመሥራት የሁለቱንም ህዝቦች ፍላጐት ማሟላት እንደሚጠበቅባቸውም አስገንዝበዋል ፡፡

እንደ የግብፅ ፕሬዚዳንትነታቸውም የሀገሪቱ ብዙኃኑም ሆነ አናሳው በርካታ በጐ ተግባራትን እንደሚጠብቁም ቅዱስ ፓትርያርኩ አባታዊ ምክር ሰጥተዋቸዋል ፡፡

የግብፁ ፕሬዚዳንት ዶ/ር መሐመድ ሙርሲ በበኩላቸው በኢትዮጵያ ቆይታቸው እንደተደሰቱ በመግለፅ ከኢትዮጵያ ህዝብና መንግሥት ጋር በርካታ ሥራዎችን ለመሥራት እቅድ እንዳላቸው ተናግረዋል ፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

More Articles...

የፎንት ልክ መቀየሪያ