Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

ዓሠርቱ ቀናት ለማኅበረ ቅዱሳን

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሥር ከሚገኙት በርካታ ማህበራት መካከል አንዱ ማኅበረ ቅዱሳን መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ ማህበረ ቅዱሳን ከተቋቋመለት ዓላማ ውጭ በመሆን መንገዱን ስቶ መሄዱን በርካታ የማህበሩ አባላት እየገለጹ ከመሆናቸውም በላይ የማህበሩ አካሄድ ለቤተ ክርስቲያን ከባድ አደጋ እንደሆነ በማስጠንቀቅ ላይ ናቸው፡፡ ለዚህ ደግሞ አንጋፋው የማህበረ ቅዱሳን መሥራች የነበረው መምህር በድረ ገጽ ላይ ሥውር አመራር እና ግልጽ አመራረ እያለ በመተንተን በሚገባ በማህበሩ ውስጥ የሚሠራውን ሴራ አስነብቦን እንደነበር ግልጽ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅትም የማህበሩ አካሄድ ከቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅር ሥር እያፈነገጠ ባለበት በዚህ ወቅት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሳይቀር የስህተት ምሳሌ ሆኖ መጠቀሱ ይታወሳል፡፡ እንግዲህ በዚህ የ20 ዓመት ጉዞው ውስጥ ማህበሩ በቤተ ክርስቲያን ስም እያመካኘ ነገር ግን ለራሱ የሚሠራ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ግን ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ እያመዘነ መምጣቱን አንዳንድ ለቤተ ክርስቲያኒቱ የሚቆሙ የማህበሩ አመራር አባላት ይናገራሉ፡፡ ትተው እንዳይወጡ ደሞዝ እንዳይሰሩም ጭንቅ የሆነባቸው ወንድሞች በማህበረ ቅዱሳን ውስጥ በርካታ ናቸውና፡፡ ይህን የምንለው የማህበሩን አካሄድ አታውቁም ብለን ሳይሆን እናስታውሳችሁ ብለን ነው፡፡ የረሳችሁትን እንድታስታውሱ ስንል ያልሰማችሁትን ደግሞ እንድትሰሙ ፈቃዳችን ነው፡፡ ባሳለፍነው ወር ማለትም በሚያዝያ ወር ውስጥ በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ኃላፊነት ተሰይመው የነበሩት መልዐከ ጽዮን አባ ኅሩይ ወንድይፍራው ተደርጎ የማይታወቅ ጉዳይ ይዘው ብቅ በማለታቸው ሳይሾሙ ተሻሩ፡፡

ጉዳዩ እንዲህ ነው፡፡ በማህበረ ቅዱሳን ጤናማ ያልሆነ አካሄድ ላይ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት እና የመንግሥት ሚኒስትሮች እንዲሁም የቤተ ክርስቲያኒቱ ታላላቅ አመራር ተገኝተው መስከረም 12 ቀን 2002ዓ.ም ባለ 6 ነጥብ ውሳኔ አስተላልፈዋል፡፡ ያንን ውሳኔ ለማስፈጸም ማደራጃ መምሪያው ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ሲታገል ቆይቷል፡፡ ማህበረ ቅዱሳን ግን ለመፈጸም ፈጽሞ ፈቃደኛ ሊሆን አልቻለም፡፡ በመሆኑም በአሁኑ ሰዓት ከ10 ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የተወሰነውን ውሳኔ እንዲፈጽም ካልሆነ ግን አስተዳደራዊ እርምጃ እንወስዳለን የሚል ደብዳቤ እንዲጻፍ ይወሰናል፡፡ በወቅቱ አባ ኅሩይ አምነውበት ተቀብለው ከፈረሙበት በኋላ ሁለት ቀናትን አሳልፈው በመምጣት ደብዳቤውን ስላላመንኩበት አይወጣም በማለት ከመዝገብ ቤት ክብ ማህተም ነጥቀው ተሰውረው ነበር፡፡ በእርግጥ ይህ ዓይነቱ አካሄድ ከአንድ አባት የሚጠበቅ ጉዳይ አልነበረም፡፡ ይሁን እንጂ የቢሮ አሠራር ስለማያውቁ እና በወቅቱ ከማህበረ ቅዱሳን ጸሐፊ ከዲ/ን ሙሉጌታ ኃይለማርያም ባገኙት ምክር መልካም ነገር መስሏቸው አደረጉ፡፡ የማደራጃ መምሪያው ሰራተኞች ግን በወቅቱ እጅግ ተገርመው ጉዳዩን ይከታተሉ ነበር፡፡ ማህተሙ በተነጠቀበት ጊዜ ዲ/ን ሙሉጌታ ኃ/ማርያም በማደራጃ መምሪያው መኪና ከአባ ህሩይ ጋር ቢሮ ገብቶ ሲያበረታታ ነበር፡፡ አባ ህሩይ በዚህ ጊዜ ነው የማህበሩ ቀኝ እጅ መሆናቸው በጥርጥር ውስጥ የገባው፡፡ አባቶች ለማህበራት ሳይሆን ለቤተ ክርስቲያን ሲቆሙ ቤተ ክርስቲያንን በደሙ የዋጃት አምላክ አብሯቸው ይቆማል ነገር ግን ከማህበራት ጋር ሲቆሙ ገንዘብ ብቻ አብሯቸው ይቆማል ገንዘብ ደግሞ ሕይወት አይሆንም፡፡ እንግዲህ ከላይ እንደተገለጸው አንድ ሃይማኖትን ይጠብቃል ያስጠብቃል ብለን የምናምነው አባት በጣም ቀላል የሆነውን ለማህበረ ቅዱሳን መስተካከያ እና መታረሚያ የሚሆን ደብዳቤ መጻፍ ከፈራና ዋጋ መክፈል ካቃተው በቤተ ክርስቲያን የአመራር ቦታ ላይ መቀመጡ ምንም ዓይነት ጥቅም የለውም ማለት ነው፡፡ ስለሆነም ቦታውን ለቆ መሄድ አማራጭ የሌለው ምርጫ ነው፡፡ ይህንንም ምክንያት አድርገን እውነታውን ትረዱ ዘንድ መልዐከ ጽዮን አባ ኅሩይ ወንድይፍራው ፈርመውበት የነበረውንና ኋላ ግን የፈረምኩት አስገድደውኝ ነው ያሉትን ደብዳቤ እንዲሁም አሁን በአዲሱ የማደራጃ መምሪያው ዋና ኃላፊ በመ/ር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ተፈርሞ የወጣውን ደብዳቤ ከዚህ በታች እንደሚከተለው አስቀምጠንላችኋል፡፡

መልካም ንባብ

1. መልዐከ ጽዮን አባ ኅሩይ ወንድይፍራው ፈርመውበት የነበረውንና ኋላ ግን የፈረምኩት አስገድደውኝ ነው ያሉትን ደብዳቤ PDF

2. በአዲሱ የማደራጃ መምሪያው ዋና ኃላፊ በመ/ር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ተፈርሞ የወጣውን ደብዳቤ PDF

የልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ በቅዱስ አባታችን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር ላይ በመገኘት የግብፁ አምባሳደር ሙሐመድ እድሪስ በመንበረ ፓትርያርክ ስብከተ ወንጌል አዳራሽ ተገኝተው ያደረጉት ንግግርና የቅዱስ ፓትርያርኩ ቃለ በረከት በድምጽ ወምስል እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡

 

የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ከአዲስ አበባ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጋር በጥምቀት በዓል አከባበር ዙርያ ምክክር አካሄደ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሚከበሩት ዓበይት ዓለም ዓቀፍ በዓላት አንዱ የጥምቀት በዓል አካባበርን በተመለከተ የነበሩት መልካም የአገልግሎት ሂደቶች ተጠናክረው ድክመቶች ካሉም ታርመውና ተስተካክለው የበለጠ በመንፈሳዊ ትሩፋት አሸብርቆ የሚከበርበት ሁኔታ ለማመቻቸት ከአዲስ አበባ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ተጠሪዎች ጋር ሰፊ ምክክር አካሄደ፡፡

የሰንበት ትምህርት ቤት ተጠሪዎች ሥርዓት ሊበጅላቸው ይገባል ያሏቸውን ሐሳብ ለማደራጃ መምሪያ የቀረቡ ሲሆን በቀረቡት ሐሳቦች ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ የመፍትሔ ሐሳቦች ሊሆኑ የሚችሉትንም አያይዘው ገልጸዋል፡፡ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ በበኩሉ የበዓሉ መልካም ገጽታ እንቅፋት የሚሆኑ ነገሮች እንዳይኖሩ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጋር በመመካከር ለመፍታት ሌት ተቀን እንደሚተጋና የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ግን በዓሉን የበለጠ ለማክበር ከወዲሁ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ አደራ በማለት የምክክር ጉባኤው ተጠናቋል፡፡

በስብከተ ወንጌልና ሐዋያዊ ተልዕኮ መምሪያ የተዘጋጀ የሦስት ቀን ሀገር አቀፍ የሠላም ጉባዔ ተጠናቀቀ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ ከአሜን ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ሀገር አቀፍ የሠላም ጉባኤ ታሥሳስ 7 ቀን 2004ዓ.ም ተጠናቀቀ፡፡

የሠላም ጉባኤው ባርከው የከፈቱት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንት ሲሆኑ ጉባኤውን በተመለከተ ሰፊ ገለጻና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ ......

የአክሱም ጽዮን የሙዝየም ሥራ በቅዱስ ፓትርያርኩና በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት እንዲሁም በከፍተኛ የመንግስት ባለሥልጣናት ተጐበኘ

የተከበራችሁ አንባቢዎቻችን ከዚህ በፊት ስለ አክሱም ጽዮን የሙዝየም ሥራ ሂደትና የቅዱስ ፓትርያርኩ የላሰለሰ አባታዊ ጥረት የቅዱስ ሲኖዶስ መልካም ፈቃድና ከፍተኛ ድጋፍ የቤተክርስቲያኒቷ አገልጋዮች ሰፊ ተሳትፎና አስተዋጽኦ ... በተመለከተ ከዚህ ቀደም ማቅረባችን ይታወቃል፡፡ በዘንድሮ የህዳር ጽዮን በዓል ምክንያት በማድረግ የሙዝየሙ የሥራ ሂደት ምን እንደሚመስልና የት ደረጃ እንደደረሰ ለማወቅ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንት መሪነት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የተከበሩ አቶ አባይ ወልዱ የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንትን ጨምሮ ከፍተኛ የክልሉ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የዞኑ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ከዓመታዊ በዓሉ በረከት ለመሳተፍ የመጣ በብዙ ሺህ የሚቆጠር ሕዝብና ልዩ ልዩ እንግዶች በተገኙበት በቦታው በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል፡፡ በጉብኝቱ ወቅትም ቅዱስ ፓትርያርኩ በታሪክ ያለሕዝብ ተሳትፎ ታሪክ ተሠርቶ እንደማያውቅና ለወደፊትም ሕዝብ ያላሳተፈ ታሪክ እንደማይኖር ገልጸው ይኸው የታሪክ ማኅደር ሆኖ ለትውልድ ታሪክንና የሀገር ሃብት የሆኑ ውድ ቅርሶችን በአግባቡ ጠብቆ ለትውልድ የሚያስተላልፍ ሙዝየም ከፍጻሜ ለማድረስ ሁሉም ሰው የታሪክ አሻራውን እንዲያሳርፍ አደራ ጭምር አባታዊ ጥሪአቸውን አስተላልፎአል፡፡

በመቀጠልም የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ አባይ ወልዱ በበኩላቸው ቤተክርስቲያኒቷ ምዕመናንዋን በማስተባበር ይህን የመሰለ ታሪካዊ ተግባር የሙዝየም ሥራ መጀመርዋ እጅግ እንደሚያስመሰግናት ገልጸው መንግስትም በዚህ ጉዳይ ላይ በስፋት ተወያይቶ የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማድረግ መዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡ ይህንኑ እውነት የበለጠ ለመረዳት ይቻል ዘንድ ድምጽ ወምስሉን ከዚህ /ቪድዮውን/ ቀጥለን አቅርበናል፡፡

 

በሃይማኖት ጉዳይ የተሳሳተና ሚዛናዊ ያልሆነ መረጃ መስጠት ይቁም፡፡

"ዕንቁ" መጽሔት ቅጽ 4 ቁጥር 55 ሕዳር 2004 ዓ/ም በፊት ለፊት ገጽ "አስደንጋጩ የክርስቶስ ፊልም ከጀርመን-ላሊበላ" በሚል ርእስ በተለይ ፊልሙ እንዲሠራ ከቤተ ክህነት ፈቃድ ተሰጥቷል የሚል ዘገባ ማውጣቱ ይታወቃል ፡፡

ፊልሙ ሃይማኖትን፣ትውፊትን፣ባሕልንና መልካም የሕዝብ አኗኗርን የሚቃረን ክርስትናንም የሚነቅፍ ይዘት ያለው በመሆኑ ጉዳዩን አስመልክቶ ለሕዝብ ተገቢ መረጃ መስጠቱ ባልከፋ ነበር፡፡ ነገር ግን የተሳሳተና ሚዛናዊነት የጎደለው መረጃ ከፍተኛ ጉዳት ስለሚያስከትል ጋዜጠኞች ጥንቃቄ ማድረግና ሙያዊ ሥነ ምግባርን መከተል ይኖርባቸዋል፡፡ ሊቃውንት ጉባኤ ፣ጠቅላይ ቤተ ክህነት፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በጉዳዩ ዙሪያ ተጠይቀው የተሟላ ዘገባ ማቅረብ ሲቻል ጠ/ቤተ ክህነት ባልተጠየቀበት ሁኔታ ጉዳዩን እንደ ፈቀደ ብሎም ቸል እንዳለው በማስመሰል ሕዝብን የሚያሳስት መረጃ ማውጣት ተገቢ ካለመሆኑም በላይ ሊቃውንት ጉባኤን በጣም አሳዝኗል፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሠራተኞች የወር ደሞዛቸውን ለመስጠት ወሰኑ

በመምህር ይቅርባይ እንዳለ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከምትታወቅባቸው ታላላቅ ሥራዎች አንዱና ዋነኛው ያለውጭ እርዳታ ባሏት ምዕመናን ልዩ ልዩ ታላላቅ አድባራትንና ገዳማትን ትምህርት ቤቶችንና ኮሌጆችን አልፎም የጤና ተቋማትን ወዘተ መስራትንና ማሳየት ነው፡፡

ይህ የቤተክርስቲያኒቷ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ በመቀጠል ይልቁንም በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ዘመን እጅግ አስገራሚ ሁኔታ ላይ እንደደረሰ ሁሉም የአገራችን ህዝብ እንዲሁም የአለም አብያተ ክርስቲያናት ፕሬዝደንት ሆነው መመረጣቸውን ተከትሎ የአለም ህዝብ ሁሉ የሚያውቀው ጉዳይ ነው:: በዚህም ምክንያት በፊት የአራት ኪሎን አስቤዛ የጠገቡት አይጦች ደረታቸውን ገልብጠው በማን አለብኝነት ሲርመሰመሱበት የነበረውንና እንኳን ለቢሮ ሥራ ለመጋዘንነት የማያስመኘውን የበፊቱን የጠቅላይ ቤተክህነት ቢሮ ድጋሚ በአእምሮአችን እንዳናስበው ግብአተ መሬቱን የፈፀሙት አቡነ ጳውሎስ ዛሬ የኢትዮጵያ ምዕመናን ግቢ ውስጥ ሲገቡ መንፈሳቸውን የሚያድስ ታሪካዊ የሆነ ህንፃ ማቆማቸው እጅግ የሚያስደንቅ ነው፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን በግርማ ሞገሱ ዓለምን የሚያስደምመው ለዓለም አብያተ ክርስቲያናት ተወካዮች ማረፊያና መሰብሰቢያ የሚያገለግለው ህንፃ እጅግ ከማርካቱም በላይ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን ህያው የሆነ ሥራ የሚመሰክር ነው፡፡ ሳንጠቅሰው ከማለፍ በማለት እንጂ በቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ዘመን ምን ተሰራ ብሎ ከመጠየቅ ምን ቀረ ቢባል ውበት ያለው ጥያቄ እንደሚሆን አያጠራጥርም፡፡

በተጨማሪ ለማንበብ …..

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትሪያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት የክብር ፕሬዝዳንት የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንት ሐዋርያዊ ጉዙ በግብፅ

ቅዱስ ፓትርያርኩ የግብፅ ኮፕቲክ ቤተ ክርስቲያን አቻቸው የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ 4ዐኛ በዓለ ሲመት በዓል ላይ ተገኝተዋል፡፡ የ88 ዓመቱ የግብፅ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ የግብፅ 117ኛ ፓትርያርክ ናቸው ፡፡

በዚሁ ወቅት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፖፕ ሽኖዳ ላለፉት ዓመታት ለሰላምና ለልማት ያደረጉትን አገልግሎት ካወሱ በኋላ ረጅም ዕድሜና ጤና ተመኝተውላቸዋል፡፡ በዕለቱ የተቀረጸውን የድምጽና የምስል ቀረጻ ከዚህ ቀጥለን አቅርበናል፡፡

 

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የተከበራችሁ አንባቢዎቻችን ቅዱስ ፓትርያርኩ በድምጽ ያስተላለፉትን የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ በጽሑፍ ማንበብ ለምትፈልጉ ከዚህ ቀጥሎ ቀርቧል፡፡ መልካም ንባብ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፤ በዓመት ሁለት ጊዜያት እንዲሆን በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 በተደነገገው መሠረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የመክፈቻው ሥርዓተ ጸሎት ከተፈጸመበት ከጥቅምት 11 ቀን 2004 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ጥቅምት 25 ቀን 2004 ዓ.ም. ድረስ የተለመደውን ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባን በማካሔድ፤

 • ለቤተ ክርስቲያናችንና ለኅብረተሰቡ የሚጠቅመውን፤
 • ለሀገርና ለዓለም ሰላም የሚበጀውን አጀንዳ በማመቻቸት በስፋትና በጥልቀት ተወያይቶ የሚከተለውን ውሳኔ አሳልፏል፤

በተጨማሪ ያንብቡ…

ማደራጃ መምርያው በውኑ "የተሐድሶ እንቅስቃሴ የለም" ብሎአልን?

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ግንቦት 23 ቀን 2003ዓ.ም አጠቃላይ የመምርያው የሥራ እንቅስቃሴን በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠቱ ይታወሳል፡፡

ይሁን እንጂ በጋዜጣዊ መግለጫው ዕለት ያልነበሩ አንዳንድ ድርጅቶችም ሆኑ ግለሰቦች የተሳሳተ መረጃ በማቅረብ የዋሃን ምዕመናንን በሐሰት ለማደናገር የማደራጃ መምሪያው ኃላፊ ቆሞስ አባ ሠረቀብርሃን ወ/ሳሙኤል "ተሐድሶ መናፍቃን የሚባል ነገር ፈጽሞ የለም" ብለዋል በሚል ለተሳሳተ ዓለማቸው ማስፈጸሚያ ግብአት እያደረጉት እንደሚገኙ ግልጽ ነው፡፡ ይኸውም ውስጥ ለውስጥ ባደረጉት የስም ማጥፋት ዘመቻ በደብዳቤ ጭምር በመፈራረም ለምን የለም አሉ? የሚል ጥያቄ ለመምርያው ቀርቦ ተመልክቶታል፡፡ አሁንም የሐሰት ምስክሮች የተሳሳተ ወሬአቸው በመቀጠል ላይ ከመሆናቸውም በላይ የዋሃኑን ምዕመናን እንዳያስስቱ በማሰብ መምርያው መወቅቱ የሰጠው መግለጫ በጽሑፍ ዕለቱኑ ያስነበበ ሲሆን ተሐድሶ የለም ብለዋል እያሉ የሚሉት ከጋዜጠኞች በቀረበላቸው ጥያቄ ላይ ስለሆነ ውሸት ቢደጋገም እውነት ስለማይሆን ሁሉም አንባቢ በራሱ ጊዜ በቆሞስ አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል የተሰጡትን መልሶች ሰምቶ እውነቱን ይረዳ ዘንድ ምስልና ድምጽ ሙሉውን ሳይቆራረጥ በሁለት ክፍል ከፍለን አቅርበናል፡፡

በመሆኑም መግለጫው ተነቦ እንዳለቀ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ የተሐድሶ መናፍቃንን እንቅስቃሴ ጉዳይ በሚመለከት ቆሞስ አባ ሠረቀብርሃን ወ/ሳሙኤል ምን ብለው መለሱ? ይህንን ጥያቄ በሚገባ መልኩ መልሱን እንድታገኙት በማለት በዕለቱ የተቀረጸውን የድምጽና የምስል ቀረጻ ከዚህ ቀጥለን ስናቀርብ እውነትን ትተው ሐሰትን ተከትለው ለሚናገሩም ሆነ ለሚጽፉ ድርጅቶችም ሆነ ግለሰቦች እግዚአብሔር ቀና መንገዱን እንዲገልጽላቸው እንጸልያለን፡፡


 

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን

የቅዱስ ሲኖዶስ ዓመታዊ ምልዓተ ጉባዔ ተጀመረ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሲወርድ ሲዋረድ በመጣው ሐዋርያዊ ትውፊት መሠረት የሰበካ መንፈሳዊ ጉባዔ ተከትሎ የሚካሄደው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ ተጀመረ፡፡ ቅዱስ ሲኖዶሱ በቅዳሜ ዕለት ጥቅምት 11 ቀን 2004ዓ.ም ከ9፡00 ሰዓት ጀምሮ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በመገኘት በጸሎት የተጀመረ ሲሆን እሁድ ጥቅምት 12 ቀን 2004ዓ.ም በመንበረ ጻባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የተለመደውን ዓመታዊ የአባቶች ጸሎተ ፍትሐት ተካሂዷል፡፡

ሰኞ ጥቅምት 13 ቀን 2004ዓ.ም መደበኛ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ የመወያያ አጀንዳዎችን ቀርጾ በማጽደቅ ጉባዔውን በተለመደው መንፈሳዊ ትውፊት መሠረት በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የየአኅጉረ ስብከት የሰንበት ት/ቤት ተጠሪዎች ጋር ምክከር በማድረግ የጋራ መግለጫ በመስጠት ተጠናቀቀ፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ አዘጋጅነት በመንበረ ፓትርያርክ የየአኅጉረ ስብከቱ የሰንበት ት/ቤት ክፍል ተወካዮች /ኃላፊዎች/ ጋር በተደረገው ውይይት ሁሉም የአኅጉረ ስብከቱ የሰንበት ት/ቤት ክፍል በበጀትና በሰው ኃይል መጠናከር እንዳለበት፤ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያውም ወጥ የሆነ ሥርዓተ ትምህርትና የመዝሙረ ማኅሌት መጻሕፍት በማሳተም ለሁሉም አኅጉረ ስብከት ማሰራጨት እንዳለበት፤ ከዚህ በተጨማሪም የወጣቱን መሠረታዊ ችግር በአግባቡ ለመፍታት ይቻል ዘንድ መምሪያው ራሱን ችሎ የውይይት መርሐ ግብር በማዘጋጀት መፍትሔ እንዲያበጅ፤ የጠቅላይ ቤተክህነትም ማደራጃ መምሪያው የወጣት ኃይል የሚያንቀሳቅስና ማኅበራትን የሚቆጣጠር መምሪያ እንደመሆኑ መጠን በሰው ኃይልና በበጀት እንዲያጠናክር በጋራ በመጠየቅና የጋራ የአቋም መግለጫ በማውጣት ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

More Articles...

የፎንት ልክ መቀየሪያ