Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

ማኅበረ ቅዱሳን የኦዲት ምርመራን አስመልክቶ ለጠቅላይ ቤተክህነት የጻፈው ደብዳቤ አግባብነት የሌለው መሆኑን ተገለጸ፡፡

ለቤተክርስቲያን ሁለገብ አገልግሎት ድጋፍ ሰጪ እንዲሆን በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሥር የተቋቋመው ማኅበረ ቅዱሳን ለ19 ዓመታት ያህል በቤተክርስቲያንዋ የሒሳብ ምርመራ /ኦዲት/ተደርጐ የማያውቅ ብቸኛ አካል መሆኑ በተደጋጋሚ ተገልጿል፡፡ ማኅበሩ በበኩሉ በውጭ ኦዲተሮችም ጭምር እንዳስመረመረ ቢገልጽም መረጃዎች እንደሚያስረዱት ግን ማህበሩ በውጭ ኦዲተር የተመረመረው የአንድ ዓመት ሒሳብ ብቻ እንደሆነ ነው፡፡ ይህም ቢሆን እንደጥሩ ጅምር በመቈጠር ቤተክርስቲያን ማኅበረ ቅዱሳን ከተመሠረተበት ጊዜ አንስቶ ሒሳቡ እንዲመረመር ባለሙያዎች አወዳድሬ እመድባለሁ ስትል፡-ማኅበሩ በበኩሉ በራሱ በውስጥ ኦዲተሮች እንደሚመረመርና በውጭ ኦዲተሮችም ጭምር እንደአስፈላጊነቱ እንደሚያስመረምር ገልጾ በቤተክርስቲያንዋ በኩል የሚደረግ የሒሳብ ምርመራ (ኦዲት)ግን እንደማይቀበል ከቃልም ባለፈ በጽሑፍ እምቢታውን ሲገልጽ መቆየቱ በዚሁ ገልጸን እንደነበር ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጂ ጠቅላይ ቤተክህነቱ ከማኅበሩ የተጻፈለትን ደብዳቤ በአግባቡ ከተመለከተ በኋላ ማኅበሩ በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሥር የተቋቋመ በመሆኑ ከጠቅላይ ቤተክህነቱ የሚሰጡትን መመሪያዎች ማክበርና መታዘዝ ሲገባው በራሳችን እንጂ በቤተክርስቲያንዋ የሚደረግ የሒሳብ ምርመራ ለመቀበል ያስቸግረናል በማለት የጻፈው ደብዳቤ አግባብነት የሌለውና መዋቅሩን ያልጠበቀ መሆኑን ገልጾ አሁንም ማኅበሩ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤቱ ገለልተኛ በሆኑ ወገኖች ኦዲት እንዲደረግ የማዘዝ ስልጣን ያለው መሆኑ ተገንዝቦ በተለያየ ዘዴ ከማመካኘት ይልቅ በመታዘዝ ሒሳቡን በአግባቡ እንዲያስመረምር፤ የቁጥጥር መምሪያም ይህንን ሂደት ተከታትሎ አሁንም እንዲያስፈጽም በጻፈው ደብዳቤ አስታውቋል፡፡ የተከበራችሁ አንባቢዎች ጠቅላይ ጽሕፈት ቤቱ ለማኅበሩ የጻፈው ደብዳቤ ከዚህ ቀጥለን አቅርበናል፡፡

ጠቅላይ ጽሕፈት ቤቱ ለማኅበሩ የጻፈው ደብዳቤ PDF

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የዓለም ሃይማኖቶች ምክር ቤት ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንት የ2003 ዓ.ም የቅድስት ድንግል ማርያም ጾመ ፍልሰታን ምክንያት በማድረግ በመላው ዓለም ለሚገኙ ምዕመናን ያስተላለፉት መልዕክት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቼ ምእመናንና ምእመናት !

እንኳን ለ2ዐዐ3 ዓ.ም. የቅድስት ድንግል ማርያም ጾመ ፍልሰታ በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፡፡

"ጾም ልጓም ፍሬሃ ጥዑም፤ ጾም ልጓም ናት፤ ፍሬዋም ጣፋጭ ነው" /ቅዱስ ያሬድ/

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በኦርቶዶክሳዊ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ድንጋጌ መሠረት ከምትጾማቸው ሰባት አጽዋማት አንዱ ጾመ ፍልሰታ ለማርያም ነው፡፡

በተጨማሪ ያንብቡ…

የጾመ ፍልሰታ የሱባዔ አገልግሎት ሰዓቱን ጠብቆ እንዲፈጸም ቅዱስ ፓትርያርኩ አባታዊ መመሪያ ሰጡ

በየዓመቱ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ ክርስቲያናዊ ምግባር ትሩፋት ከልሂቅ እስከ ደቂቅ በጾምና በጸሎት ለሁለት ሱባዔያት የሚከበረው የጾመ ፍልሰታ አገልግሎት በየደረጃው የሚገኙ የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ሰዓቱን አክብረው የሚጀመርበትንና የሚያልቅበትን የሰዓት ቀመር በማዘጋጀት ለተገልጋዩ ሕብረተሰብ በአግባቡ ትውፊቱን ጠብቀው አገልግሎታቸውን እንዲፈጽሙ በቀን 27/11/2003ዓ.ም በጠቅላይ ቤተክህነት ስብከተ ወንጌል አዳራሽ ለተገኙት ለአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፤ ለጸሐፊዎችና ለስብከተ ወንጌል ኃላፊዎች፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ኃለፊዎችና ሠራተኞች እንዲሁም የጠቅላይ ቤተክህነት የየመምሪያ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በተገኙበት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንት አባታዊ መመሪያ አስተላልፈዋል፡፡

ቅዱስነታቸው ይህንን ሲያብራሩም በዚህ በሱባኤያችን ወቅት አባቶችና እናቶች እንዲሁም ሕጻናት በተጨማሪ በሥራ ላይ የሚገኙ ምዕመናንም ሱባዔ የሚገቡበት የጾምና የጸሎት ጊዜ ስለሆነ በሰዓቱ ወደ ቤተክርስቲያን መጥተው በሰዓቱ ደግሞ ወደ ሥራቸው መመለስ እንዲችሉ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የተሰጣቸውን የአገልግሎት ኃላፊነት አክብረው እንዲንቀሳቀሱ በአጽንኦት አደራ ብለዋል፡፡

ከዚህ በመቀጠልም የታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ገዳም ነባር መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ወደ ኮሌጅ እንዲያድግ ቅዱስ ሲኖዶስ መወሰኑን አብራርተው በአባቶቻችን ረቂቅ ችሎታ የተሠራውን ጥንታዊው ሕንጻ በአዲስ መልክ ለመሥራት የመሠረት ድንጋይ የተቀመጠ ቢሆንም እስከ አሁን እንዳልተጀመረ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በመጨረሻም ቅዱስ ፓትርያርኩ አድባራቱና ገዳማቱ የዚህን ጥንታዊ ትምህርት ቤት ጠቀሜታ ከሁሉም የተሻለ ግንዛቤ ስላላቸው ይህንን መሠረት በማድረግ ሁሉም አድባራትና ገዳማት ኮሚቴ በማቋቋም ለሕንጻው ግንባታ ከአንድ ሚልዮን ብር ያላነሰ አስተዋጽኦ ማድረግ እንደሚገባቸው አደራ ጭምር መመሪያ ካስተላለፉ በኋላ ተሳታፊዎችም የድጋፍ ሐሳብ ሰጥተው የዕለቱ መርሐ ግብር በቅዱስ አባታችን ጸሎትና ቡራኬ ተጠናቅቋል፡፡

ሕግን፣ ሥርዓትንና ቀኖናን ሳይከተል እየተካሄደ የሚገኘው "የተሐድሶ" እወጃ የቤተክርስቲያንን ቀኖና ያልተከተለ በመሆኑ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግ ቅዱስ ፓትርያርኩ መመሪያ አስተላለፉ፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከጥንት ጀምሮ በኦርቶዶክሳዊ ትምህርተ ሃይማኖት የተራቀቁ ሊቃውንት የሚገኙባት ጥንታዊት ቤተክርስቲያን እንደ መሆንዋ መጠን ከሐዋርያት ጀምሮ በተዋረድ በቅዱሳን አባቶቻችን የተወሰኑትን ቀኖናዎች መሠረት አድርጋ ለዚህ ያህል ዘመን በአግባቡ ጥንታዊ ትውፊትዋን አውቃ፣ መንፈሳዊ እሴቷን ጠንቅቃ፣ የአበው ሲኖዶሳዊ አካሄድ ጠብቃ... የምትመራ እናት ቤተክርስቲያን መሆኗ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንት ገለጹ፡፡

ቅዱስ ፓትርያርኩ በቁጥር ልጽ/598/1604/03በቀን 25/11/2003ዓ.ም ለሁሉም አህጉረ ስብከትና ለሁሉም የጠቅላይ ቤተክህነት መምሪያዎች በአድራሻ ባስተላለፉት ሰርኩላር ደብዳቤ የቤተክርስቲያን ጥንታዊ ትምህርተ ሃይማኖት፣ ሥርዓት፣ ትውፊትና ቀኖና...ነቅቶ ከመጠበቅ በተጨማሪ የሃይማኖት ሕፀፅ ሲያጋጥምም ስለእውነትነቱ በሕጋዊ ማስረጃ የተደገፈ ጽሑፍ ቀርቦ፣ በሊቃውንት ጉባኤ ተመርምሮና ተጣርቶ ትክክለኛ መሆኑ ሲረጋገጥ በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔ ታይቶ የመጨረሻ ውሳኔ ማግኘት እንደሚገባ የሦስቱን ጉባኤያት ቀኖናዊ ሂደት ጠቅሰው በስፋት አትተዋል፡፡

ይሁን እንጂ አሁን የእምነት ሕጸጽ በትክክል አጋጥሞ ከሆነና በቂ ማስረጃ አለኝ የሚል ካለ በግል ስሜት ብቻ ተገፋፍቶ ቀኖናው በማይፈቅደው አካሄድና በሌለው ስልጣን ራሱ ወስኖ ከመሮጥ ይልቅ አለኝ የሚለውን ማስረጃ ቀኖናው በሚፈቅደው መርሕ መሠረት ለቅዱስ ሲኖዶስ ማቅረብ እንደሚገባ በስፋት አብራርተው ከዚህ ውጭ የሆነ አካሄድ ግን ሕገወጥ እንቅስቃሴ መሆኑ ታውቆ በሁሉም ባለድርሻ አካላት ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እንዲደረግ ቅዱስነታቸው መመሪያ አስተላልፈዋል፡፡ የተከበራችሁ አንባቢዎቻችን የቅዱስ አባታችንን ሙሉ የደብዳቤ ይዘት ሙሉ የደብዳቤ ይዘት ከዚህ ቀጥለን አቅርበናል፡፡

በቅዱስ ፓትርያርኩ በቁጥር ልጽ/598/1604/03 በቀን 25/11/2003 ዓ.ም የወጣው ደብዳቤ PDF

ማኅበረ ቅዱሳን የሒሳብ ምርመራን /ኦዲትን/ በማስመልከት ቤተክርስቲያኒቱ የወሰነችውን ውሳኔ አልቀበልም በማለት ገለጸ

ማኅበረ ቅዱሳን እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምንም እንኳ ተቀራራቢ እና አብረው የሚሠሩ ቢመስሉም መነታረክና መካሰስ ከጀመሩ አያሌ ዓመታት ማለፉን ሁሉም ሰው የሚያውቀው ጉዳይ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ቤተክርስቲያን አሁንም ቢሆን ማኅበረ ቅዱሳን ለሚያጠፋው ጥፋትና ለሚያደርገው አለመታዘዝ ከቅጣት ይልቅ ምክርን በማስቀደም የእናትነት ድርሻዋን በመወጣት ላይ በምትገኝበት በዚህ ወቅት ማኅበሩ አሁንም በቤተክርስቲያኒቱ ስም እንደፈለገ ገንዘብ ከማግበስበስ ውጪ ለቤተክርስቲያኒቱ መታዘዝን በፍጹም ሊሞክረው ፈቃደኛ አልሆነም፡፡ ባለፈው ሳምንት በድረ ገጻችን እንዳስነበብነው ቤተክርስቲያኒቱ ማኅበሩ ኦዲት እንዲደረግ ለዚህም እንቅስቃሴ አስፈጻሚ አካል እንዲሆን ለቁጥጥር መምሪያ አገለግሎት የጻፈችውን ደብዳቤ ጨምረን አስተላልፈን ነበር፡፡ ይሁን እንጂ በነጋታው ማኅበሩ የእምቢታውን ደብዳቤ በመጻፍ መልስ የሰጠበት ደብዳቤ በእጃችን ስለገባ የማኅበሩን ሀሳብ ልናቀርብላችሁ እንወዳለን፡፡ ማኅበሩ በላከው ደብዳቤ ላይ እንዳነበብነው ምንም እንኳ ቤተክርስቲያን ማኅበሩ ኦዲት እንዲደረግ ብትወስንም ይህንን ለመቀበል ግን መቸገሩን ከመግለጹም በላይ የቤተክርስቲያኒቱ ሀሳብ ግን ጥሩና ይበል የሚያሰኝ ነው በማለት የፌዝ ቃልም አካትቶበታል፡፡ ውሳኔውን ለመቀበል ያስቸግረኛል በማለት ማኅበሩ እንደ ዋና ምክንያት ያቀረባቸው ሦስት ምክንያቶች አሉ፡፡ እነዚህም ምክንያቶች፤

 1. ቅዱስ ሲኖዶስ በ1994ዓ.ም አጽድቆ በሰጠው መተዳደሪያ ደንብ ላይ ይህ ጉዳይ የለም የሚል ምክንያት፤
 2. ማኅበሩ በውጪ ኦዲተሮች ኦዲት ማስደረጉ በቂ ነው በሚል ምክንያት
 3. የ2003ዓ.ም የኦዲት ምርመራን ለማድረግ የውጪ ኦዲተሮችን በመጋበዝ ላይ በመሆኑ ምክንያት በማለት እነዚህን ከላይ የጠቀስናቸውን ምክንያቶች አስቀምጧል፡፡

በተጨማሪ ያንብቡ…

19ኛ በዓለ ሲመት በታላቅ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ተከበረ

በመምህር ሙሴ ኃይሉ

abune paulos 1የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንት 19ኛው ዓመት በዐለ ሢመት ማክሰኞ ሐምሌ 5 ቀን 2003ዓ.ም በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በታላቅ መንፈሳዊ ትሩፋት ተከብሮ ዋለ፡፡ በተለይ በአዲስ አበባ በመንበረ ጻባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንት፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ አምባሳደሮች፣ የመንግስት ባለሥልጣናት፣ የጠቅላይ ቤተክህነት የየመምሪያውና የየድርጅቱ ኃላፊዎችና መላው ሠራተኞች፣ የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን፣ ምእመናንና ምዕመናት በተገኙበት በዓሉ በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ውሏል፡፡

 s5

 s7

በዓሉ ከሌሊቱ ጀምሮ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ስብሐተ እግዚአብሔር በማድረስ የተጀመረ ሲሆን የቅዳሴው መርሐ ግብርም በቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት ከተከናወነ በኋላ ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ የበዓሉ ዓመታዊ መርሐ ግብር ተከናውኗል፡፡ በመርሐ ግብሩ መሠረትም ከአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት የተውጣጡ ሊቃውንት ለ20 ደቂቃ ያህል ያሸበሸቡ ሲሆን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የማዕከላውያን መዘምራንም ያሬዳዊ መዝሙር አቅርበዋል፡፡

ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የኢሉባቦርና የጋምቤላ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በዓሉን በሚመለከት አባታዊ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን በቅዱስ ፓትርያርኩ መልካም ፈቃድ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ በዓሉን በተመለከተ ሰፊ ትምህርት ሰጥቷል፡፡ ቀጥለውም የቤተክርስቲያን ሊቃውንት በዓሉን አስመልክተው መወድስ ቅኔ በማቅረብ ለበዓሉ ድምቀት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡

በመጨረሻም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንት ትምህርት፣ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ከሰጡ በኋላ የቅዳሴው ሰርሆተ ሕዝብ ተከናውኖ የበዓሉ መርሐ ግብር ተፈጽሞአል፡፡

የቤተክርስቲያኒቱ ሦስቱ ከፍተኛ መንፈሳውያን ኮሌጆች ደቀ መዛሙርቶቻቸውን አስመረቁ

በመምህር ሙሴ ኃይሉ

trintygrad2003የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከፍተኛ የመንፈሳዊ ትምህርት ተቋማት የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ፤ የቅዱስ ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅና የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ለአምስትና ለሦስት ዓመታት በመደበኛና በኤክስቴንሽን መርሐ ግብር ያስተማሯቸውን ደቀመዛሙርት በድኅረ ምረቃ (PGD)፣ በዲግሪ፣ በዲፕሎማና በሰርተፊኬት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንት፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የምሩቃን ቤተሰቦች በተገኙበት በየኮሌጆቹ አዳራሽ በታላቅ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት አስመረቁ፡፡

በተጨማሪ ያንብቡ…

ማኅበረ ቅዱሳን የሚያንቀሳቅሰውን ንብረት በሙሉ እንዲያስመረምር እና አፈጻጸሙንም የቁጥጥር መምሪያ አገልግሎት እንዲያስፈጽም ጠቅላይ ቤተክህነት ውሳኔ አስተላለፈ::

በመምሪያው ሕትመት ክፍል

ማኅበረ ቅዱሳን ለአያሌ ዓመታት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስም በተለያዩ አቅጣጫ ከልዩ ልዩ የንግድ ተቋማትና የገቢ ማሰባሰቢያ ማዕከል ሲሰበስብ የኖረውን ገንዘብ እንዲያስመረምር ቤተክርስቲያኒቱ በተደጋጋሚ ስታሳስብ መኖሯ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ ለ19 ዓመታት ማለትም እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ ቤተክርስቲያኒቱ የማኅበሩን ገቢና ወጪ አለማወቋ በተደጋጋሚ ብትገልጽም በተቃራኒው ማኅበሩ ግን በሥሩ ላሉት አባላት በሚድያዎቹ ሳይቀር ኦዲት እንደተደረገ መግለጹ ለብዙ ሰዎች ጥያቄ ሆኖ ቆይቷል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሰኔ 30 ቀን 2003ዓ.ም ተጽፎ በቁጥር 7205/16187/2003 ከጠቅላይ ቤተክህነት የወጣው ደብዳቤ እንደሚገልጸው "ማኅበሩ ለረጅም ዓመታት ኦዲት ሳያስደርግ የቆየው ሒሳብ አስቸጋሪ እና ውስብስብ ከመሆኑ የተነሳ የቁጥጥር መምሪያ አገልግሎት ለውጪ ኦዲተሮች ማስታወቂያ በማውጣት አወዳድሮ የምርመራውን ሥራ እንዲያስፈጽም" የሚገልጽ ደብዳቤ አስነብቦናል፡፡

ይህም ደብዳቤ ከዚህ በፊት በቤተክርስቲያን እና በማኅበሩ መካከል የነበረውን ክርክር እንደሚፈታ ብዙዎች በአስተያየታቸው ገልጸውልናል፡፡ ማደራጃ መምሪያውም ይህንን ምክንያት በማድረግ በቤተክርስቲያኒቱ እና በማኅበረ ቅዱሳን መካከል ያለውን አለመግባባት እውነቱን ግልጽ አድርጎ ለአንባቢያን ለማቅረብ ይረዳ ዘንድ ከጠቅላይ ቤተክህነት ለቁጥጥር መምሪያ አገልግሎት የተጻፈውን ደብዳቤ ከዚህ ቀጥሎ አቅርቦአል፡፡

ለቁጥጥር መምሪያ አገልግሎት እንዲያስፈጽም ጠቅላይ ቤተክህነት የወጣው ደብዳቤ PDF

የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሐመር መጽሔትና የስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ ሕትመት እንዳላገደ አስታወቀ

ከመምሪያው ሕትመት ክፍል

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ በማኅበረ ቅዱሳን ተዘጋጅተው የሚሠራጩ የሐመርና የስምዐ ጽድቅ ሕትመት አለማገዱን አስታወቀ፡፡ ማደራጃ መምሪያው ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጀምሮ በተዋረድ ማኅበሩ ሕትመቶቹን ቅድመ ምርመራ /ኢዲት/ እንዲያስደርግ የተወሰኑ ውሳኔዎች ለመተግበርና የተሰጠውን መመሪያ ተግባራዊ አድርጐ የሕትመቶቹን ጤናማ አካሄድ ለመምራት እንዲቻል ለማኅበሩ በተደጋጋሚ ደብዳቤ ቢጻፍለትም እሰከ አሁን ድረስ ፈቃደኛ መሆኑን ባለመግለጹ ለሁሉም ማተሚያ ቤቶች ከማደራጃ መምሪያው የፈቃድ ደብዳቤ ካልተጻፈላቸው በቀር "በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን" በሚል ስም የሚቀርብላቸውን ማንኛውንም የሕትመት ጥያቄ በአለማስተናገድ ትብብር እንዲያደርጉለት መጻፉን ገልጾአል፡፡

የዚህ ዓይነቱን አካሄድ ማደራጃ መምሪያው እንዲከተል ምክንያት የሆነው የማኅበሩ ሕገወጥነትና አልታዘዝ ባይነት መሆኑን የገለጸው ማደራጃ መምሪያ የቅድመ ምርመራው ጉዳይ ከ87ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ተግባራዊ እንዲያደርግ ማደራጃ መምሪያው ያለመሰልቸት በተደጋጋሚ ቢጠይቅም ማኅበሩ አንድም ቀን ፈቃደኛ ሆኖ ሕትመቶቹን በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንዲታዩ አለማድረጉን ገልጿል፡፡

በተጨማሪ ያንብቡ…

በማህበረ ቅዱሳን የቀረበው የአክሲዮን ሽያጭ እና ግዢ ጥያቄ አግባብ አለመሆኑን ማደራጃ መምሪያው ገለጸ

ከመምሪያው ሕትመት ክፍል

ማኅበረ ቅዱሳን እንደ መንፈሳዊ ማኅበር ሆኖ የተደራጀው በ1984ዓ.ም ሲሆን በቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ መተዳደሪያ ደንብ ወጥቶለት ወጣቶችን ለማስተማር እና እንዲሁም ለሰንበት ትምህርት ቤቶች እንዲሰጥ በሚል ዓላማ የተደራጀ ማኅበር ነው፡፡ ይህ ማኅበር ሲደራጅ ግን ሙሉ በሙሉ ተጠሪነቱ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሥር ሆኖ እንዲመራ በውስጠ ደንቡ መሠረት ታዝዟል፡፡ ይሁን እንጂ ምንም እንኳ ውስጠ ደንቡ ተጽፎ በወረቀት ቢኖርም የማህበሩ አካሄድ እና በወረቀቱ ላይ ያለው ውስጠ ደንብ የሰማይና የምድር ያህል እንደሚራራቅ ብዙ ምዕመራንም ሆኑ የቤተ ክርስቲያኒቱ የየመምሪያው ኃላፊዎች በሚገባ ያውቁታል፡፡ ይሁን እንጂ ማደራጃ መምሪያው እስከ አሁኗ ሰዓት ድረስ ይህንን የማኅበረ ቅዱሳንን ያፈነገጠ አካሄድ ለማስተካከል ሌት እና ቀን እየሠራ ነው፡፡ ይህ የማደራጃ መምሪያው እንቅስቃሴ ያሰጋው ማኅበረ ቅዱሳን ግን ከቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ መዋቅር ለመውጣት በማሰብ እንዲሁም በብልጣ ብልጥ አካሄድ በማለሳለስ፤

 • የባንክ ሂሳብ
 • የቦንድ ግዢ ፈቃድ
 • እንዲሁም የተለያዩ ማኅበሩን የሚመለከቱ ጉዳዮች ሁሉ በአንድ ሰው ፊርማ ብቻ እንዲንቀሳቀስ ይፈቀድለት ዘንድ ደብዳቤ እንዲጻፍለት ለማደራጃ መምሪያው ጥያቄ አቀረበ፡፡ ማደራጃ መምሪያው ይህንን ጥያቄ ሲመለከት እጅግ ከማዘኑም በላይ አስቦት የማያውቀው የማኅበሩ ከቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ መዋቅር የመገንጠሉ ስሜት በዚህ መልኩ መምጣቱ በጣም አሳፍሮታል፡፡ ይህ ራሱን ከቤተ ክርስቲያን ጉያ የማውጣት እንቅስቃሴም አግባብ አለመሆኑን እየገለጸ የማህበሩን የአመራር ሁኔታ በጥልቀት የማያውቁ ወይም ያልተረዱ የማህበሩ አባላት ከቅድስት ቤተ ክርስቲያናቸው ሳያውቁ በማህበር ስም እንዳይወጡ ቆመው የት እንዳሉ ሊያጤኑ እንደሚገባ በተደጋጋሚ ጥሪውን አስተላልፏል አሁንም እያስተላለፈ ነው፡፡

በተጨማሪ ያንብቡ…

ማኅበረ ቅዱሳን ከሰኔ 1 ቀን 2003ዓ.ም ጀምሮ ሕትመቶቹን ሳያስመረምር ስርጭት ላይ እንዳያውል በድጋሚ ታዘዘ፡፡

የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ለብዙ ዓመታት ማኅበሩ በማሳተም የሚያሰራጫቸውን ሕትመቶች በሙሉ በቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት አስቀድሞ እንዲያስመረምር በተደጋጋሚ ቢጠየቅም ማኅበሩ አንድም ጊዜ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ለሁሉም ማተሚያ ቤቶች ደብዳቤ በመጻፍ የማኅበሩ ሕትመቶች ቅድመ ምርመራ ማድረጋቸውን የሚገልጽ ከማደራጃ መምሪያው ደብዳቤ ካልደረሳቸው ሕትመቶቹን ተቀብለው እንዳያስተናግዱ ደብዳቤ መጻፉ ይታወቃል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ማኅበሩ በለመደው ሕገ ወጥ አካሄዱ ተጠቅሞ ብፁዓን አባቶችን በማታለል ማደራጃ መምሪያው ሕትመቶቹን እንዳገደ በማስመሰል የእዝ ሰንሰለቱን ሳይጠብቅ ቅድመ ምርመራን (ኢዲት) እንዲያደርግ አስቀድሞ ከጻፈለት ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ቀደም ብሎ ለማተሚያ ቤቶች የተጻፈ ደብዳቤ አስነስቷል፡፡ ይሁን እንጂ ማደራጃ መምሪያው በግልባጭ ሲደርሰው በዚህ ጉዳይ ላይ ከጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ጋር ሰፊ ውይይት ካደረገ በኋላ የደብዳቤው አወጣጥ ስሕተት መሆኑን የጋራ ስምምነት ላይ ከተደረሰ በኋላ የተጻፈው ደብዳቤ እንዳለ ሆኖ በአስቸኳይ በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ በኩል የቅድመ ምርመራ ሥራን ተግባራዊ እንዲያደርግ አሁንም በድጋሚ ለማደራጃ መምሪያው አዲስ ደብዳቤ ተጽፎአል፡፡

ደብዳቤው ከሰኔ 1 ቀን 2003ዓ.ም ጀምሮ ሕትመቶቹና የሕትመቶቹ ስርጭት በሊቃውንት እየታዩና እየታረሙ ሥራ ላይ እንዲውሉና ሕትመቶቹም ለማደራጃ መምሪያው ቀርበው አስቀድሞ ማረጋገጫ ካልሰጠ በቀር ሕትመት ላይ እንዳይውሉ ጠቅላይ ቤተ ክህንት ዛሬ ለሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ አሳውቋል፡፡

ማኅበሩ እየሄደበት ያለው መንገድ አግባብ አለመሆኑን መምሪያው ገልጾ "ለምን ቤተ ክርስቲያን ትቆጣጠረናለች፣ ለምን ጥያቄ ይቀርብብኛል፣ እስከ ዛሬ ያልነበረ ቁጥጥር ነው .... ወዘተ" በሚል የተሳሳተ ምክንያት እንደለመደው ከቤተ ክርስቲያን አጥር ውጭ በመሆን የሚያደርገውን እንቅስቃሴ በአስቸኳይ እንዲያርም አሳስቦ ዘጠና ከመቶ የሚሆኑትን ንጹሐን የቤተ ክርስቲያን ልጆች አባላቱ ማኅበሩ የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት እንዲጠብቅ በሚደረገው ሁለገብ እንቅስቃሴ ከማደራጃ መምሪያው ጎን እንዲቆሙ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ ማኅበሩ በማታለል ያጻፈው ደብዳቤና ለማስተካከያው ተብሎ የተጻፈውን ደብዳቤ ከዚህ ቀጥለን እናቀርባለን፡፡

ሙሉ ደብዳቤው በ PDF

"በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት

ከሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የተሰጠ መግለጫ፤

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በታሪክ ራስዋን ችላ ሁለገብ አገልግሎት መስጠት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በሁለተኛው ፓትርያርክ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ጊዜ ወጣቶችን አሰባስቦና አደራጅቶ በትምህርተ ቤተ ክርስቲያን አንጾ የቤተ ክርስቲያንና የሀገር ተረካቢ እንዲሆኑ ዝግጁ የማድረጉ ጉዳይ ከምንም ጊዜ በላይ ትኩረት ተሰጥቶት በቃለ ዐዋዲ ሕገ ደንብ ተዘጋጅቶ ከረቀቀ በኋላ በሦስተኛው ፓትርያርክ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት ኅዳር 29 ቀን 1970ዓ.ም በቅዱስ ሲኖዶስ ጸድቆ አገልግሎት ላይ ውለዋል፡፡

ይህ ሕገ ደንብ እስከ 1986ዓ/ም ድረስ ሲያገለግል ከቆየ በኋላ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ዘመኑንና ጊዜውን ያገናዘበ መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት እንዲሰጡና እንዲያገኙ ለማስቻል ውስጠ ደንቡን ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ ስለተገኘ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንት መልካም ፈቃድ በ1986ዓ.ም አዲስ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ውስጠ ደንብ ተቀርጾ በቅዱስ ሲኖዶስ ጸድቆ ሥራ ላይ እንዲውል ስለታዘዘ በዚሁ መሠረት ከመንበረ ፓትርያርክ ጀምሮ እስከ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ድረስ አስተዳደራዊ መዋቅሩን ዘርግቶ ዘርፈ ብዙ መንፈሳዊና ማሕበራዊ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

በተጨማሪ ያንብቡ…

More Articles...

የፎንት ልክ መቀየሪያ