Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ በማኅበራት ላይ ያለውን ስጋት በተደጋጋሚ በመግለጽ ላይ ነው

ከመንበረ ፓትርያርክ ጀምሮ እስከ አጥቢያ ድረስ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ ግብሮችን እያካሄደ ነው፡፡

በመምህር ይቅርባይ እንዳለ

የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ከቅዱስ ሲኖዶስ በተጣለበት ኃላፊነት ሰንበት ት/ቤቶችን ማደራጀትና በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም የሚዋቀሩትን ልዩ ልዩ ማኅበራት መምራትና መቆጣጠር ስራው እንደሆነ በተለያዩ መድረኮች ከመግለጹም በላይ ሃይማኖትንና ሀገርን በመወከል የሚከበሩት እንደ መስቀልና ጥምቀት ያሉት ታላላቅ ብሔራዊ በዓላት ከፍተኛ ምስክሮች ናቸው፡፡ ይሁንና ማደራጃ መምሪያው የተሰጠውን ኃላፊነት በአግባቡ እንዳያከናውን የሚያደርጉትን የውስጥና የውጭ ችግሮች በማለት ጥናት አድርጐ በ22/7/2003ዓ.ም ቅዱስ ፓትርያርኩ እና የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያው ኃላፊዎች ባሉበት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስብሰባ አድርጓል፡፡ የማደራጃ መምሪያው ዋና ኃላፊ ቆሞስ አባ ሠረቀብርሃን ወልደ ሳሙኤል በስብሰባው ላይ እንደገለጹት ማኅበረ ቅዱሳን ለቤተ ክርስቲያኒቱ ሁለገብ አገልግሎት ከፍተኛ ስጋት ከመሆኑም በላይ በሕግ የማይመራና በቅዱስ ሲኖዶስ የጸደቀለትን ሕገ ደንብ የማይጠብቅ ከሆነ በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ ከፍተኛ የኢኮኖሚ፣ የሃይማኖታዊ፣ የማኅበራዊ ውድቀት እንደሚያስከትል በስፋት አትተው ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪ ያንብቡ…

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኙ የአድባራትና ገዳማት ኃላፊዎች ታላቅ ሃገራዊ ጉባኤ አካሄዱ፡፡

የሚሊኒየመ ታላቅ ፕሮጀክት የአባይ ግድብን ለመደገፍ ባለ 6 የአቋም መግለጫ አስተላልፋል፡፡

በመምህር ሙሴ ኃይሉ (B.TH, MA IN PHILO)

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጠሪነት የአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፣ የሰበካ ጉባኤ ም/ሊቃነ መናብርት፣ ጸሐፊዎች፣ ሰባክያነ ወንጌልና የሰንበት ትምህርት ቤት ተወካዮች በተገኙበት በጠቅላይ ቤተ ክህነት ስብከተ ወንጌል አዳራሽ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያይርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተ/ሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንት ሰብሳቢነት በ04/08/2003 ዓ.ም የአባይ ግድብን አጀንዳ ያደረገ ሰፊ አገራዊ ጉባኤ ተካሄደ፡፡

በጉባኤው ብዛት ያላቸው ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያው ኃላፊዎችና ሠራተኞችም ጭምር በተገኙበት በመልካም መደማመጥና በሀገራዊ ወኔ የተካሄደ ሲሆን መርሐ ግብሩን የመሩት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ንቡረዕድ አባ ገ/ማርያም ጉባኤው የተዋጣለትና ግቡን እንዲመታ አደርገው በጥበብ በመምራታቸው በሁሉም ተሳታፊዎች አደናቆትን አትርፏል፡፡

በቅዱስ ፓትርያኩ መልካም ፈቃድ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የብፁዕ ወቅዱስ ረዳት ሊቀ ጳጳስና የሰላሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የአባይ መገደብ የጥንታውያን አባቶቻችን ፍጹም ምኞትና ፍላጐት እንደነበረ የታሪክ ተዋረዱን በሚገባ ዘርዝረው ካስረዱ በኋላ አሁን በዘመናችን የመሠረት ድንጋይ ተጥሎ ማየታችን ግን እደለኞች ነን፡፡ የዚህ ፕሮጀክት ሥራ ያለዳት በሙሉ የሚሠራው በእኛ በኢትዮጵያውያን ብቻ መሆኑ ደግሞ ታሪክ ለመሥራት እግዚአብሔር የፈቀደልን ዘመን መሆኑ መረዳት ይገባናል፡፡

በተጨማሪ ያንብቡ…

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን

በ72 አህጉረ ስብከት የሠመረ አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆንዋ ተገለጸ

     በመምህር ሙሴ ኃይሉ /B.TH.MAIN PHILO/

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሀገር ውስጥ 48በውጭ ዓለም በ24አህጉረ ስብከት ተቋቁመው በሊቃነ ጳጳሳት መሪነት በመደበኛ ካህናት የሠመረ መንፈሳዊና ማህበራዊ አገለግሎት እየተካሄደ እንደሚገኝ የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ ለዝግጅት ክፍላችን በላከው መግለጫ አስታወቀ፡፡

የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያው መልካም አስተዳደር የሰፈነባት፣ ድህነት ያልተቆራኛት፣ የውጭ ርዳታ ሳትጠብቅ ራሷን ችላ ሁሉን የምትረዳ የበለጸገችና ኢኮኖሚዋ ያደገ ከሁሉ በላይ የሆነች ቤተ ክርስቲያን ለማድረግ እንደ ራዕይ አስቀምጦ አሁንም የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሐዋርያዊ፣ መንፈሳዊና ማህበራዊ አገልግሎት በተሟላ ሁኔታ እንዲቀጥል ጠንክሮ በመሥራት ዘወትርም ክትትል በማድረግ ላይ መሆኑ በላከልን መግለጫ አስምሮበታል፡፡ የተከበራችሁ አንባቢዎች ከዚህ ቀጥሎ የሰበካ ጉባዔ ማደራጃ መምሪያ የላከልንን ሙሉ መግለጫ እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡

በተጨማሪ ያንብቡ…

የመካኒሳ ቅ/ሚካኤል ቤተክርስቲያን ወደ ካቴድራል አደገ በካቴድራሉ የሚገነባው ት/ቤት በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ስም ተሰየመ

                                      እስክንድር ገ/ክርስቶስ

የመካኒሳ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ከመጋቢት 05ቀን 2ሺህ3ዓ.ም ጀምሮ ወደ ካቴድራልነት ማደጉን ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ጽ/ቤት በ02/7/2ሺህ3ዓ.ም የወጣው ደብዳቤ ያመለክታል፡፡ ደብሩ ወደ ካቴድራልነት ያደገው በተለይ በልማት ሥራ እያስመዘገበ ባለው ተጨባጭ ውጤት መሆኑን ያመለከተው ደብዳቤው የሥራ እንቅስቃሴውንና ውጤቱን በመመዘን ቀደም ሲል ይጠራበት የነበረው የመካኒሳ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የሚለው ስያሜ ቀርቶ የመካኒሳ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል በሚል እንዲለወጥና ስያሜውም ከላይ ከተገለጸው ዕለት አንስቶ ተግባራዊ እንዲሆን መፈቀዱ ተገልጾአል፡፡

በተጨማሪ ያንብቡ…

ዜና ዕረፍት

የጠቅላይ ቤተ ክህነት አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ ዐረፉ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጠቅላይ ቤተ ክህነት አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ የነበሩ አቶ ነገደ ሥዩም መጋቢት 22ቀን 2003ዓ.ም ለ23 አጥቢያ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡ አቶ ነገደ ሥዩም በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የአስተዳዳር መምሪያ ኃላፊ ሆነው ከተሾሙበት ቀን አንስቶ ቤተ ክርስቲያን በአስተዳደራዊ ሂደቷ የተሳካ አገልግሎት እንዲኖራት ሌት ከቀን በማገልገል ላይ ሳሉ ድንገት ባደረባቸው ህመም ዐርፈዋል፡፡ የቀብር ሥነ ሥርዓቱም በዛሬው ዕለት መጋቢት 23ቀን 2003ዓ.ም.በደብረ አሚን አቡነ ተ/ሃይማኖት ገዳም እነደሚፈጸም ከወጣው መርሐ ግብር ለመረዳት ተችሎአል፡፡ የአቶ ነገደ ሥዩም ሕይወት ታሪክና የቀብር ሥነ ሥርዓት ተከታትለን እናቀርባለን፡፡

የአቶ ነገደ ሥዩም አጭር የሕይወት ታሪክ

አቶ ነገደ ሥዩም ከአባታቸው ከአቶ ሥዩም ኃ/ማርያምና ከእናታቸው ከወ/ሮ ማሚቴ ከበደ በ1957ዓ/ም በትግራይ ክልል ራያና አዘቦ አካባቢ በሚገኘው ወይራ ውሃ ከተማ ተወለዱ፡፡ እድሜአቸው ለትምህርት ሲደርስ የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸው በማይጨው ት/ቤት አጠናቀው፣ በደሴ መምህራን ማሠልጠኛ ተቋም በመምህርነት ሰልጥነው በደሴ ዙሪያ እስከ 1990ዓ/ም ድረስ በመምህርነት አገልግለዋል፡፡

በተጨማሪ ያንብቡ…

የቅርሳቅርስ መምሪያና የቤተ መጻሕፍት ወመዘክር ድርጅት የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት እየተዘጋጀ መሆኑን ገለጸ

በመምህር ሙሴ ኃይሉ (B.TH, MA IN PHILO)

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ የቅርሳ ቅርስ መምሪያና የቤተ መጻሕፍት ወመዘክር ድርጅት የቤተ ክርስቲያኗ ማዕከላዊ ቤተ መዛግብትና የቤተ መጻሕፍት አገልግሎት የሚሰጥና የቅርስ ጥበቃ፣ እንክብካቤ፣ ምዝገባ፣ እና ማስተዋወቂያ ተቋም መሆኑ በማስታወስ አሁንም ለበለጠ አልግሎት መዘጋጀቱን ገለጸ፡፡

የቅርሳ ቅርስ መምሪያና የቤተ መጻሕፍት ወመዘክር ድርጅቱ ከዚህ ቀደም ይሰጠው ከነበረው የሙዝየም አገልግሎት የበለጠ ለማስፋፋት የስዕል ኤግዚብሽን ከፍቶ አገልግሎት ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን ገልጾአል፡፡ ከዚህ ቀጥሎ ድርጅቱ የላከልንን ሙሉ መግለጫ አቅርበነዋል፡፡

በተጨማሪ ያንብቡ…

 

 

 

 

 

Letter Expressing condolences for the Earthquake that struck Japan by His Holiness Abune Paulos, Patriarch  of Ethiopian Orthodox Tewahedo Church, Ichege of the See of St. Tekle Haymanot, Archbishop of Axum, President of the World Council of Churches.

Read more...

ዜና ሕይወቱ ወዕረፍቱ ለብፁዕ አቡነ ይስሐቅ ሊቀ ጳጳስ

“ወፍናዊሁኒ ለሞት ዘእግዚአብሔር ውእቱ”
“የሞት ጐዳና የእግዚአብሔር ጎዳና ነው”
መዝ.67፡20

የባሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው ሲሠሩ የቆዩት ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ በቀድሞ አጠራር በሸዋ ክፍለ ሀገር በየረርና ከረዮ አውራጃ በአድአ ወረዳ ከአባታቸው ከመምሬ ዘውዴ ወልደ ዮሐንስ፣ ከእናታቸው ከወ/ሮ ሸዋንግዛው ደምሴ (አሁን እማሆይ)በ1927ዓ.ም ተወለዱ፡፡ ዕድሜያቸው ለትምህርት እንደደረሰ በተወለዱበት ደብር በየረር ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ከመምህር ገብረ ሚካኤል አባተ ንባብና ዳዊት ተምረዋል፡፡ ከዚያም የሰሜን ኢትዮጵያ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከነበሩት ከብፁዕ አቡነ ይስሐቅ የዲቁናን ማዕርግ ተቀብለው እየቀደሱ እያለ አያታቸው ቀኝ ጌታ ደምሴ ሀብተሥላሴ ወደ አዲስ አበባ ደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን አምጥተው ከቀኝ ጌታ ገሪማ ፀዋትወ ዜማ እንዲማሩ ትምህርት ቤት አስገብተዋቸዋል፡፡ በዚሁ ደብር ከውዳሴ ማርያም ዜማ እስከ ጾመ ድጓና ምዕራ እንዲሁም የአንድ ዘመን ድጓ ዘልቀዋል፡፡

በተጨማሪ ያንብቡ…

የባሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ ዐረፉ

በመምህር ሙሴ ኃይሉ

የባሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በመሆን በቅንነትና በትጋት ሲያገለግሉ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ ለሐዋርያዊ ተልእኮ አዲስ አበባ መጥተው በማገልገል ላይ እያሉ የካቲት 24ቀን 2003ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡ ስርዓተ ቀብራቸውም በመንበረ ጻባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቅዳሜ የካቲት 26 ቀን 2003ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንት፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣የጠቅላይ ቤተክህነት መላ ሠራተኞች፣ የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አገልጋዮች በተገኙበት ይፈጸማል፡፡ ሥርዓተ ቀብራቸውንና የሕይወት ታሪካቸውን በተመለከተ በቀጣይ እናቀርባለን፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ ከመጽሐፍ ቅዱስ ማህበር ጋር በመተባበር “ሚዲያና ሥነ ምግባር” በሚል ርዕስ ዐውደ ጥናት አካሄደ

በመምህር ይቅርባይ እንዳለ


ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝዳን ት የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንት ጉባኤውን ባርከው የከፈቱ ሲሆን በሚዲያ በኩል ሕዝብን የሚጻረር ወይም የሚነቅፍ ነገር ከክርስትና የሚመነጭ አለመሆኑን ገልጸው አንድ ጊዜ ሕዝቡ ውስጥ ተጽፎ የተሰራጨውን ነገር ተሳስቼ ነው ማለት አይቻልም ሲሉ ከሚዲያ በስተጀርባ የሚደረገውን የስም ማጥፋት ተግባር ኮንነዋል፡፡ በመቀጠልም ነጻነት የሰውን መብት ሳይነኩ መንቀሳቀስ እንደሆነ ገልጸው በሚዲያም የሚሠሩ ሰዎች ነፃነታቸውን ተጠቅመው የሰውንም መብት እና ስም ሳያጠቁ እንዲንቀሳቀሱ በመምከር ይልቁንም በሐይማኖት ሚዲያ ላይ የሚሠሩ ምሁራን ለሌሎች አርአያ መሆን እንዳለባቸው በመምከር ጉባኤው እንዲቀጥል አመራር ሰጥተው በብዙ ሺህ ሕዝብ ወደሚጠበቁበት ወደ እንጦጦ ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን ሄደዋል፡፡

በተጨማሪ ያንብቡ…

የቅዱስ ፓትርያርኩ ሐዋርያዊ ጉዞ በጋምቤላ

በመምህር ይቅርባይ እንዳለ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንት ሐዋርያዊ ጉዞ አደረጉ፡፡

በተጨማሪ ያንብቡ…

ቅዱስ ፓትርያርኩ ወደ ጋምቤላ ሀገረ ስብከት
ሐዋርያዊ ጉዞ ማድረጋቸው ተገለጸ

በመምህር ይቅርባይ እንዳለ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክር ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵተያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንት ወደ ተለያዩ ሀገረ ስብከቶች ሐዋርያዊ ጉዞ በተደጋጋሚ ያለመሰልቸት ሲያደርጉ እንደኖሩ ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጂ እንደ ጋምቤላ የመሳሰሉትን እጅግ በረሀማ አየር ያለባቸውን ሀገሮች መጐብኘት እና ለትውልድ ቅርስ የሚሆኑ ሥራዎችን መሥራት ለታላላቅ አባቶቻችን ቀርቶ ለወጣቶችም ውጣ ውረዱ የበዛ እንደሆነ መገመት አያዳግትም፡፡ቅዱስነታቸው አሁን በሚያደርጉት ሐዋሪያዊ ጉዞ በርከት ያሉ አብያተ ክርስቲያናትን እንዲሁም የአብነት ትምህርት ቤቶችን እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በጋምቤላ ያስገነባችውን ዘመናዊ ሙዚየም እንደሚመርቁ ይገመታል፡፡የጋምቤላ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መ/አዕላፍ ቆሞስ አባ ተ/ሐይማኖት በስልክ እንደገለጹልን ቅዱስነታቸው ከዋናው ከተማ ወደ ወረዳዎችም ወርደው ሕዝቡን ባርከው እንድሚመለሱ የገለጹልን ሲሆን አጠቃላይ ዝርዝሩን እንደደረሰን በአየር ላይ የምናውል መሆናችንን እንገልጻለን፡፡

More Articles...

የፎንት ልክ መቀየሪያ