Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በቅርቡ በኢትዮጵያ የተሾሙት የግብፁ አምባሳደር መስከረም 6 ቀን 2008 ዓ.ም. በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ:: በውይይቱም ወቅት የሁለቱም ሀገራት ታሪካዊ ግንኙነቶችን በማውሳት አሁንም የበለጠ ተጠናክሮ የሚቀጥልበት ሁኔታ መፍጠር ለነገ የማይባል ተልዕኮ መሆኑን በሰፊው ተገልጿል ፡፡

ውይይቱን የጀመሩት አምባሳደር አቡበከር በኢትዮጵያ ተመድበው ከመጡ በኋላ ይፋዊ ጉብኝት በማድረግ ሥራቸውን የጀመሩት በኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ማግስት የኢትዮጵያ ቅዱስ ፓትርያርክን በማነጋገር መሆኑን ገልጸው ይህም ለወደፊት ሥራቸው የተባረከ እንደሚያደርግላቸው ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል ፡፡ በመቀጠልም አምባሳደሩ የኢትዮጵያና የግብፅ ግንኙነት ከዓባይ ወንዝ ባሻገር ባሉ ታሪካዊ ማኅበራዊና መንፈሳዊ እሴቶቻችንም የበለጠ በትኩረት በመስጠት መሥራት በጣም አስፈላጊ እና ዓብይ አጀንዳቸው መሆኑን ገልፀው ይህንን ለማጠናከር የተቻላቸውን ሁሉ ለማድረግ መዘጋጀታቸውን ለቅዱስ ፓትርያርኩ ገልጸውላቸዋል ፡፡


ከዚህ በተጨማሪም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና የግብፅ ኮፕቲክ ቤተ ክርስቲያን ታሪካዊ ግንኙነት ለማውሳት ይህንኑ ሃይማኖታዊና ታሪካዊ ግንኙነት ለማጠናከር የሚደረገው የብፁዕ ወቅዱስ ፖፕ ታዋድሮስ ፓትርያርክ ጉብኝትም በጣም እንደሚያደንቁና ቅዱስ ፓትርያርኩ ወደ አክሱም፣ ጎንደርና ላልይበላ የሚያደርጉት ታሪካዊ ጉዞም አብረው ለመጓዝ መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል፡፡ ቅዱስ ፓትርያርኩ ሲመጡ የግብፅ ኤምባሲ የእራት ግብዣ ማዘጋጀቱን አስታውሰው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያም እንዲገኙላቸው የጥሪ ግብዣ አቅርበዋል ፡፡
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በበኩላቸው የሁለቱም ሀገራት የግንኙነት ታሪክ ዘመን ተሻጋሪና ተፈጥሮአዊም ጭምር መሆኑን በሰፊው ካብራሩ በኋላ ይህንን ዘርፈ ብዙ ይዘት የተላበሰውን የሁለቱም ሀገራት ግንኙነት የበለጠ እንዲጠናከር ማድረግ የሁሉም ሰው ኃላፊነት መሆኑን ካስገነዘቡ በኋላ የዚህ ታሪክ ተሳታፊ ለመሆን በኢትዮጵያ በመመደብዎ በጣም ደስተኞች ነን፣ ከመጀመሪያ ቤትዎ ወደ ሁለተኛ ቤትዎ እንኳን በደህና መጡ በማለት የእንኳን ደህና መጡ መልካም ምኞታቸውን ገልጸውላቸዋል ፡፡
በመቀጠልም በሁለቱም ሀገራት ሕዝቦች የነበረውን ታሪካዊ ግንኙነት ከዓባይ ወንዝ ባሻገር ብዙ ማኅበራዊና መንፈሳዊ ግንኙነቶች የነበሩና ያሉ መሆናቸውን በመግለፅ ይህንን ሰላማዊና ወንድማዊ ግንኙነት ተጠብቆ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲሸጋገር ማድረግ በጣም አስፈላጊ መሆኑን አብራርተዋል ፡፡
የቅዱስ ፓትርያርኩ ፖፕ ታዎድሮስ ጉብኝትም የዚህ የቆየ ሃይማኖታዊ ግንኙነታችን አንዱ ማሳያ መሆኑን በሰፊው ካብራሩ በኋላ ቅዱስ ፓትርያርኩ በሚጎብኟቸው ታሪካውያን ቦታዎች እርስዎም ለመገኘት በመዘጋጀትዎ በጣም የሚያስደስትና የምናደንቀው ተግባር ነው በማለት አድናቆታቸውን ገልጸውላቸዋል ፡፡
በመጨረሻም አምባሳደሩ ይህንን የቆየ ታሪካዊ ግንኙነት እንዲቀጥልና እንዲጠናከር ለማድረግ የተሰጠዎትን ኃላፊነት ለመወጣት በሚያደርጉት ጥረት ከእኛ የሚጠበቀውን ሁሉ ለማድረግ መዘጋጀታችንን እያረጋገጥኩ መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንልዎ እንጸልያለን በማለት መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸው ተመኝተውላቸዋል ፡፡

 

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

 

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም
ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

 

 • ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት

 • ክቡራን ክቡራት የጠቅላይ ቤተ ክህነት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሠራተኞች፤

 • ክቡራን ክቡራት የየድርጅቶች ሠራተኞች

 • የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፤

 • ክቡራን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፤

 • ክቡራን ክቡራት የኢሉባቦርና የጋምቤላ አህጉረ ስብከት ተወካዮች፤

 • የተከበራችሁ የብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ቤተሰቦች፤

 • በአጠቃላይም በብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የቀብር ሥነ ሥርዓት አፈጻጸም መርሐ ግብር ላይ የተገኛችሁ ሁላችሁ!

ከዚህ በመቀጠል የብፁዕ አቡነ ፊልጶስን አጭር የሕይወት ታሪክ እናሰማለን፡፡

ክፍል አንድ

ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የኢሉባቦርና የጋምቤላ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከአባታቸው ከአቶ ፈለቀ ለውጤ ከእናታቸው ከወ/ሮ አዛልነሽ ሙሉ በ1928 ዓ.ም. በወሎ ክፍለ ሀገር በላስታ ቡግና አውራጃ ሠራብጥ ካህናተ ሰማይ ከሚባል ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ተወለዱ፡፡

ብፁዕነታቸው በተወለዱበት በካህናተ ሰማይ ቤተ ክርስቲያን አካባቢ መምሬ ኃይሉ ከሚባሉ መምህር ንባብና ዳዊት ሰዓታትና አምስቱን አእማደ ምሥጢር ተምረዋል ፤ እንዲሁም ወደገነተ ማርያም በመሔድ፤ መሪጌታ ኃይለ ማርያም ከሚባሉ ፀዋትወ ዜማን ተምረዋል፤ በመቀጠልም አርካ አቦ ቤተ ክርስቲያን በመሔድ ከአለቃ ኢሳይያስ ጾመ ድጓን በመማር ላይ እንዳሉ ወደግሸን ደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በመሔድ ከብፁዕ አቡነ ሚካኤል የዲቁናን ማዕርግ ተቀበሉ፤ በኋላም ወደ ትውልድ ቀበሌያቸው ተመልሰው ጥቂት እንደቆዩ ወደ ደሴ መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን በመሔድ ከመምህር ገብረ እግዚአብሔር መጻሕፍተ ሐዲሳትንና መጽሐፈ መነኰሳትን ተምረዋል፡፡

ከዚህ በኋላ ብፁዕነታቸው በፍፁም ሀሳባቸው ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገል የመረጡት መንገድ ምንኵስናን በመሆኑ እንደገና ወደ ግሸን ደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ተመልሰው ምንኵስናን ተቀበሉ፤ በተከታታይም ማዕርግ ቁምስና ከብፁዕ አቡነ ሚካኤል ከተሰጣቸው በኋላ ገደሚት ከምትባል ገዳም ገብተው ለጥቂት ጊዜ እንዳገለገሉ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ከአለቃ በዛብህ ወንድም ጋር ወደ ዞብል በመሔድ ከመምህር ወልደ ሰንበት ሰዋሰወ ቅኔን ተምረዋል ፡፡

ከዚያም ብፁዕነታቸው በአዲስ አበባ የወንጌል ትምህርት በማስተማር ሰፊ አገልግሎት ከመስጠታቸውም በላይ፡-

በተጨማሪ ያንብቡ

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አንዳንድ አድባራትና ገዳማት የመሬት፣ የሱቆችና የልዩ ልዩ ገቢ ማስገኛ ተቋማትን እንዲሁም በአንዳንድ አድባራት የሚደረጉ የመኪና ሽልማቶችን አስመልክቶ በቂ ጥናት እንዲደረግና ውጤቱ እንዲገለጽላቸው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፤ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም፤ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት እና ቋሚ ሲኖዶስ ባስተላለፉት መመሪያ መሠረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ጉባኤ ጥናቱን አዘጋጅተው የሚያቀርቡ 3 ከጠቅላይ ቤተ ክህነት፤ 2 ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት፤ ኮሚቴዎችን አቋቁሞ ሥራውን ጀመረ፡፡


የተቋቋመው ኮሚቴም የጥናቱ መሠረት ለቤተ ክርስቲያኒቱ የሚሰጠውን ጥቅም መነሻ በማድረግ ጥናቱን በተሳካ ሁኔታ ለማካሄድ ይረዳው ዘንድ በጥቅል ጥናቱ ሂደት ላይ ተደጋጋሚ ውይይትና ክርክር በማድረግ ቤተ ክርስቲያኒቱን ለመታደግ የሚያስችል ሥራ መስራትና ማቅረብ እንደሚገባው በማመን ግልጽ የጥናት ማስፈፀሚያ ዕቅድ እንዲዘጋጅ አድርጓል፡፡


የጥናቱ የማስፈጸሚያ ዕቅድ ምን ያህል አብያተ ክርስቲያናት በጥናቱ መካተት እንዳለባቸው ጥናቱን ለማካሄድ የሚከተለውን ስልት በጥናቱ ወቅት የሚያጋጥሙትን ፈተናዎችና መፍትሔዎቻቸውን በዝርዝር በማስቀመጥ ከማስፈጸሚያ ስልት (Action plan) ጋር በማዘጋጀት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ፤የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ በተገኙበት በማስፈጸሚያ ዕቅዱ ዙሪያ ውይይት በማድረግ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ዕቅዱ እንዲጸድቅ ካደረገ በኋላ ወደ ሥራ ገብቷል፡፡


በዚህ የማስፈጸሚያ ዕቅዱ ላይ ያጋጥማሉ ተብለው ከቀረቡ ችግሮች መካከል፤

 • የአጥኚ ቡድኑን ስም ማጥፋት
 • የአበልና በትራንስፖርት ስም መማለጃ መስጠት
 • በጥናቱና በጥናቱ ማጠቃለያ ወቅት ውጤቱን በፀጋ ከመቀበል ይልቅ ውዥንብርና የኰሚቴውን ስም የማጥፋት ሂደቶች በዋናነት በስፋት ሊካሄዱ እንደሚችሉ ተጠቅሷል፡፡

በውጤቱም በየአድባራቱ ለጥናት በተንቀሳቀሰበት ወቅት በውሎ አበልና በትራንስፖርት ስም ኮሚቴውን ለመደለል ተሞክሯል፡፡

Read more...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ የአርመን ቂልቅያ ካቶሊኮስ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ አራም ቀዳማዊ ባደረጉላቸው ግብዣ መሠረት ሊባኖስን ጎበኙ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በአርመን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የመንበረ ቂልቅያ ካቶሊኮስ የአርመን ሰማዕታትን መቶኛ ዓመት አከባበርን ምክንያት በማድረግና በሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት መካከል ያለውን ወዳጅነት ለማጠናከር ይቻል ዘንድ ባደረጉላቸው ይፋዊ ጥሪ መሠረት በቤይሩት- ሊባኖስ ሐዋርያዊ ጉብኝት አደርገዋል፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በሊባኖስ በነበራቸው ቆይታ የአርመን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ባዘጋጀችው ዓለም አቀፍና የተለያዩ መንፈሳዊ ሥርዓቶች ላይ የተሳተፉ ሲሆን የሁለቱም ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት የቆየ ግኑኝነት መሠረት በማድረግ ታሪካዊ ንግግር አድርገዋል፡፡

Picture 021 Picture 035 Picture 078 Picture 118 Picture 199 Picture 217 Picture 286 Picture 386 Picture 396 Picture 422 Picture 428 Picture 429 Picture 551 Picture 552 Picture 570 Picture 655 Picture 659 Picture 663 Picture 693 Picture 703 Picture 726

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በንግግራቸው የኢትዮጵያና የአርመን ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት በማኅበረሰባዊ ትስስር ላይ የተመሠረተ ጥንታዊ፣ ታሪካዊ፣ ሃይማኖታዊና ሀገራዊ የሆነ መልካም ግንኙነት ያላቸው መሆኑን በመግለጽ የአሁኑ ትውልድም ይህንኑ የቆየ መንፈሳዊና ማኅበራዊ ግኑኝነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የበኩሉነ አስተዋጽኦ በማድረግ እንዲተጋ አሳስበዋል፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ

ዜና ቤተ ክርስቲያን 63ኛ ዓመት ቁ.69

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች እግዚአብሔር ዝናመ ምሕረቱን እንዲያወርድ እና ወርሐ ክረምቱ የተባረከ እንዲሆንልን የአንድ ሳምንት ጸሎተ ምህላ እንዲደረግ አሳሰቡ፡፡

ዓመታዊ የቁልቢ ገብርኤል በዓለ ንግሥ በታላቅ መንፈሳዊ ድምቀት ተከብሯል፡፡

በመምህር ሙሴ ኃይሉ

በዓመት ሁለት ጊዜ በታላቅ መንፈሳዊ ድምቀት የሚከበረው የቁልቢ ገብርኤል ዓመታዊ በዓለ ንግሥት ሐምሌ 19 ቀነ 2007 ዓ.ም. ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምያ ኃላፊዎች፣ ከተለያዩ አህጉረ ስብከቶችና አድባራትና ገዳማት የመጡ የቤተ ክርስቲያናችን መሪዎች፣ ከመላ ዓለም የተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች በተገኙበት ዘንድሮም እጅግ ማራኪ በሆነ መንፈሳዊ አገልግሎት ተከብሮአል፡፡

በዓሉ በተለመደው ሁኔታ ከዋዜማም ጀምሮ በሊቃውንት ያሬዳዊ ዜማና በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ትምህርት እየተሰጠ የተከበረ ሲሆን ሌሊቱን በማኅሌትና በቅዳሴ በዓሉ ተከብሮአል፡፡ ታቦተ ሕጉ ሦስት ጊዜ ዑደት ካደረገ በኋላ የገዳሙ ሊቃውንትና የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች መዘምራን መዝሙር ያቀረቡ ሲሆን ከዚህ በመቀጠል ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ እና የምሥራቅ ጐጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሰፊ ትምህርተ ወንጌል ሰጥተዋል፡፡ የዕለቱ ሰማዕታት የሆኑት ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣን መነሻ በማድረግ ትምህርታቸውን የሰጡ ሲሆን ዘመኑን ማዕከል በማድረግ ታሪኩን ወደ ዘመኑ የምዕመናን ሕይወት በመመለስ ሰፊ ትምህርት እና ምክር አስተላልፈዋል፡፡

ከዚህ በመቀጠል ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ትምህርተ ወንጌል፣ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ እንዲያስተላልፉ ተጋብዘው ሕዝቡን ባርከዋል፡፡ ቅዱስ ፓትርያርኩ በቃለ ምዕዳናቸው ትኩረት የሰጡት ማንኛውም መንፈሳዊና ማኅበራዊ ሥራዎቻችን የሠመሩ የሚሆኑት እምነትንና ሐቀኛ አሠራርን ስንከተል ብቻ መሆኑን መነሻ በማድረግ ሰፊ ቃለ በረከት አስተላልፈዋል፡፡
ቀደምት የኢትዮጵያውያን መገለጫዎች የሆኑት መከባበር፣ መቻቻል፣ መፋቀር፣ መተዛዘን የመሳሰሉት ሁሉ በአንዳንድ ምክንያቶች እንዳይሸራረፉ ሁሉም ሰው ነቅቶ መጠበቅና ማዳበር እንዲሁም ለልጆቹ ማስተማር ይገባል ካሉ በኋላ እግዚብሔር በሁሉም ሀገራችን ዝናመ ምሕረቱን አውርዶ የተዘራውን አብቅሎ ለፍሬ እንዲያደርስልን፣ ወርሐ ክረምቱንም እንዲባርክልን በሁሉም አህጉረ ስብከት ዘንድ የአንድ ሱባኤ ጊዜ ጸሎተ ምህላ እንዲደረግ መመሪያ አስተላልፈዋል፡፡
ጸሎተ ምህላው እዚያው ቁልቢ ገብርኤል ቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ እንዲሁም በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ሊቃውንትና ምዕመናን ባሉበት ቅዱስ ፓትርያርኩ አስጀምረው ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ በመስጠት በዓሉ በጸሎት ተዘግቷል፡፡

የብፁዕ አቡነ መርሐ ክርስቶስ ጨለቆት የገጠር ኑሮ ማሻያ ፕሮጀክት በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ተመረቀ

እስክንድር ገ/ክርስቶስ

የኢትዮጵያ ኦርቶደክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን በብር 13,681,000 በደቡብ ምሥራቅ ትግራይ ዞን እንደርታ ወረዳ በጨለቆት የገጠር ቀበሌ የሚኖሩ 5,750 ሰዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ልዩ ልዩ የልማት ፕሮጀክቶች በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ሰኔ 26 ቀን 2007 ዓ.ም አስመርቀ፡፡

Picture 032 Picture 043 Picture 055 Picture 142

ኮሚሽኑ ብሬድ ፎር ዘወርልድ ኢኢዲ ከተባለ የጀርመን ግበረ ሠናይ ድርጅት ጋር በመተባባበር በጨለቆት የገጠር ቀበሌዎች ባከናወናቸው ሥራዎች በ80 ሄክታር ላይ የተለያዩ የአፈርና የውሃ ጥበቃ ሥራዎችን ያከናወነ ሲሆን 45 የእረሻ መሬት ለሌላቸው ወጣቶች ሥልጠና በመስጠትና ከ105 በላይ ዘመናዊ የንብ ቀፎዎችና ተያያዥ ቁሳቁሶች ገዝቶ በመስጠት ወጣቶቹን ውጤታማ እንዳደረገ በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገልጾአል፡፡

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቀነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ለፕሮጀክቱ እውን መሆን ታላቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ተቋማት ከኰሚሸኑ ቅርጫፍ ማስተባበሪያ ቢሮ የተዘጋጀላቸውን ሽልማት ከሰጡ በኋላ ባደረጉት አባታዊ ንግግር በዛሬው እለት በዚህ ወረዳ በተደረገ አቀባበል ሥነ ሥርዓት የሙስሊም ወንድሞቻችን መታደማቸው በእጅጉ የሚያስደስት ነው፡፡ ይህ የእርስ በርስ ስምምነትና መፈቃቀርን የሚያመለከት በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠልና በቀጣዩ ትውልድም ይህ የመከባበርና የመቻቻል ተምሳሌት እንደ ባህል ሆኖ መቀጠል ይገባዋል ብለዋል፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የመካነ ሕይወት ጭህ ገዳምን ጐበኙ

በገዳሙ ለሚሠራው ሙዝየም ሥራ ማስጀመሪያ የ100 ሺህ ብር ድጋፍ አደረጉ


እስክንድር ገ/ክርስቶስ


የመካነ ሕይወት ጭህ ገዳም ከተገደመበት ከ1864-1988 ዓ.ም 124 ዓመት ውስጥ ስምንት አበምኔቶች ያገለገሉት ሲሆን በገዳሙ ከነበሩ መናንያን መካከል ሁለት ፓትርያርኰች፣ ሦስት ሊቃነ ጳጳሳት በርካታ ሊቃውንትን ያፈራው ገዳሙ በገዳሙ ታሪክ ውስጥ ከ50 ዓመት በላይ ያገለገሉት አባላት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስን ያስተማሩት መምህር አሥራተ ጽዮን መሆናቸው በገዳሙ የሙዚየም አሠሪ ኮሚቴ በቀረበው ሪፓርት ተገልጾአል፡፡

አሁን ገዳሙን በማስተዳደር ላይ ባሉት አበምኔት መምህር ዘመንፈስ ቅዱስ ረዳ ከ1988 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ገዳሙን በአበምኔትነት በማገልገል ላይ መሆናቸውን የገለጸው ሪፓርቱ በአገልግሎት ዘመናቸዉ ገዳሙ የ24 ሰዓት የመብራት አገልግሎት በነጻ እንዲያገኝ ያደረጉ ሲሆን የገዳሙንም አመታዊ በጀት ለማስከበር ከፍተኛ መስዋዕትነትን የከፈሉ አባት መሆናቸው ተገልጾአል፡፡

Picture 250 Picture 257 Picture 275 Picture 290 Picture 408 Picture 519 Picture 550 Picture 574 Picture 588 Picture 660

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ጭህ ገዳም በደረሱ ጊዜ ቁጥራቸው እጅግ በርካታ የሆኑ የአካባቢው ምዕመናን፣ የገዳሙ መናንያን ፣ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችና ካህናት እጅግ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

በተጨማሪ ያንብቡ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 ላይ በተደነገገው ቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዓመት ሁለት ጊዜ ይካሄዳል፡፡

ከሁለቱ አንዱ ከጌታችን ከአምላካችንና ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ትንሣኤ በኋላ በሃያ አምስተኛው ቀን በዕለተ ረቡዕ የሚውለው የረክበ ካህናት ጉባኤ ነው ፡፡

በመሆኑም የረክበ ካህናቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሚያዝያ 27 ቀን ከሰዓት በኋላ በጸሎት ተከፍቶአል ፡፡

በመቀጠልም ሚያዝያ 28 ቀን 2007 ዓ.ም. መደበኛ ስብሰባውን በጸሎትና በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ የመክፈቻ ንግግር ተጀምሮ ለሦስት ቀናት ሲካሄድ ሰንብቶአል፤ ልዩ ልዩ ውሳኔዎችንና መመሪያዎችንም አስተላልፎአል ፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ለዐራት ቀናት ያህል ባካሄደው ቀኖናዊ ጉባኤ፤

 • ለቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን የሚጠቅሙትን፤

 • ለልማትና ለሰላም የሚበጁትን፤

 • ከሀገር ውጭ ለሚገኙና በሀገር ውስጥ ላሉ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ሁለንተናዊ ሕይወት መጠበቅ የሚስችሉትን ርእሰ ጉዳዮች በማንሣት በስፋትና በጥልቀት አይቶ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አሳልፎአል ፡፡

1. ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ በጉባኤው መክፈቻ ያደረጉት ታሪካዊ ንግግር የቤተ ክርስቲያንን ሁለንተናዊ ሕይወት የቃኘ የሀገራችን ዕድገትንና የሰላም አስፈላጊነትን በስፋት የገለፀ በመሆኑ ጉባኤው በሙሉ ድምፅ ተቀብሎታል ፡፡

2. ምልአተ ጉባኤው በቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ተዘጋጅቶ የቀረበውን ዓመታዊ የሥራ መግለጫ ሪፖርት አዳምጦ አንዳንድ ማስተካከያዎችን በማድረግ በሙሉ ድምፅ ተቀብሎታል ፡፡

3. ምንም ጥፋትና በደል ሳይኖርባቸው ክርስቲያኖች በመሆናቸው ብቻ በሊቢያ ሀገር አይ ኤስ በተባለ የአሸባሪዎች ቡድን በግፍና በሚዘገንን ሁኔታ የተገደሉ ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖችንና የግብፅ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖችን በተመለከተ ቋሚ ሲኖዶስ ቀደም ሲል በሟቾቹ መንፈሳዊ ሕይወት ላይ ተወያይቶ ባቀረበው ሐሳብ መሠረት ምልዓተ ጉባኤው ያለውን ሁኔታ በጥልቀት ከተረዳ በኋላ ሟቾቹ የዘመኑ ሰማዕት እንዲባሉ ተስማምቶ ወስኗል ፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

ዜና ቤተ ክርስቲያን መጋቢትና ሚያዘያ 2007 ዒ.ም 63ኛ ዒመት ቊ. 69

zenamiazyafront

 

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት

ምሕረትና ይቅርታ፣ ትዕግሥትና ቸርነት የባህርዩ የሆነ እግዚአብሔር አምላክ፣ ሰፊውን የወርኃ ጾም አገልግሎት በሰላም አስፈጽሞ ብርሃነ ትንሣኤውን በሰላም ስለአሳየን፣ እንደዚሁም ሃይማኖታዊ፣ ቀኖናዊና ዓመታዊ ከሆነ ከዚህ የረክበ ካህናት ጉባኤ በሰላም ስላደረሰን ክብርና ምስጋና ለእርሱ እናቀርባለን፡፡

‹‹ኀበ ሀለዉ ክልኤቱ ወሠለስቱ ጉቡአን በስምየ አነ እሄሉ ማእከሌሆሙ ህየ፤ ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁ›› (ማቴ፡ 18÷20)፡፡

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ከዚህ በላይ በተጠቀሰው የጌታችን፣ የአምላካችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሕያው ቃል ላይ የተመሠረተ እንደሆነ ሁላችንም እናውቃለን፡፡

የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ተልእኮ ጀማሪና ፈጻሚ ራሱ ጌታችን ቢሆንም ሥራው በአጠቃላይ በሰው ልጅ ድኅነት ላይ የሚከናወን ፍጹምና ምሉእ ተልእኮ በመሆኑ በአንድ ትውልድ ብቻ የሚያልቅ አይደለም ፡፡

በመሆኑም ተልእኮው እስከ ዓለም መጨረሻ ለሚነሣው ትውልድ ሁሉ እንዲዳረስ፣ እርሱን ተከትለው የድኅነት አገልግሎት የሚሰጡ ሐዋርያት እንደሚያስፈልጉ ግልጽ ነበረ ፡፡

ከዚህ አንጻር የቤተ ክርስቲያን ተልእኮ የቅብብሎሽ ሥራ በመሆኑ እነሆ አባቶች ሲያልፉ በልጆች እየተተኩ ሥራው እኛ ዘንድ ደርሶአል፤ በዚህም ‹‹ወናሁ አነ እሄሉ ምስሌክሙ እስከ ኅልቀተ ዓለም፤ እነሆ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ›› (ማቴ፡ 28÷20) ብሎ የገባልን ቃል ኪዳን በተግባር እየተፈጸመልን አገልግሎታችን ከሀገር ውስጥ አልፎ መላውን ዓለም ባካለለ መልኩ እያካሄድን እንገኛለን፤ በዚህም እግዚአብሔርን እናመሰግነዋለን፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ

አሜን!!

 • የተከበሩ አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የኤፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር

 • የተከበራችሁ የሃይማኖት አባቶች

 • ክቡራንና ክቡራት

 • የተወዳደችሁ የኢትዮጵያ ሕዝቦች

ሚያዝያ 11 ቀን 2007 ዓ/ም ራሱን አይ ኤስ በማለት የሚጠራው ሰብዓዊ ርኅራኄ የሌለው አሸባሪ ቡድን በወገኖቻችን ላይ ያደረሰውን አሰቃቂ የወንጀል ድርጊት ከሰማንበት ቀንና ሰዓት ጀምሮ በአምላካችን ዘንድ የወገኖቻችን ደም በከንቱ እንዳይቀር ልብን በሚሰብር ሐዘን በጸሎት በማሰብ ላይ እንገኛለን፡፡

ይህ በሰብአዊ ፍጡር ይፈጸማል ተብሎ የማይታሰብ ድርጊት አሳሳቢና ፍጹም ጭካኔ የተመላው በመሆኑ ከሐዘናችንና ሰማዕታቱን በጸሎት ከማሰብ በተጨማሪ ወጣቶቹ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አማኞች መሆናቸውን ስለተረዳን ስለጌታችን ስምና ስለቀናች ሃይማኖት፣ ስለ እግዚአብሔርም ፍቅር ዐላውያን በቅጣት የሚያሰቃዩትን ክርስቲያናዊ ቸል አትበሉ ተብሎ በዲድስቅልያ በተደነገገው ቀኖና መሠረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በተደጋጋሚ ልዩ ልዩ መግለጫዎች በማወጣት፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልታደርግ የሚገባትን ሃይማኖታዊና ቀኖናዊ ሥርዓት በማከናወን ላይ ትገኛለች፡፡

Picture 109 Picture 119 Picture 122 Picture 150 Picture 155

በሁሉም ዘንድ እንደሚታወቀው የሁሉም ሃይማኖቶች ተልእኮ ሰውን ማዳን እንጂ ሰውን መግደል እንዳይደለ ቢታመንም ንጹሐን ዜጎችን በሃይማኖት ምክንያት በአሰቃቂ ግድያ የመግደል ወንጀል በዓለማችን መታየት ከጀመረ ሰነባብቶአል፡፡ ኢትዮያውያን ወገኖቻችንም በተለያየ ጊዜና በተለያየ አካባቢ የዚህ ዓይነቱ ግድያ ሰለባ መሆናቸው አልቀረም፡፡

ከዚህ አንጻር በዚህ ሰሙን በሊቢያና በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አማኞች በሆኑት ልጆቻችን ላይ የተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ ከምንም ጊዜ በላይ ቤተ ክርስቲያናችንን፣ ሀገራችንንና ሕዝባችንን ያሳዘነና ያሳሰበ ጉዳይ ሆኖ ተገኝቶአል፡፡

የተፈጸመው አሰቃቂ ድርጊት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ ብቻ ሳይሆን በሁሉም የዓለም ሃይማኖቶች ላይ የተቃጣ የወንጀል ተግባር መሆኑን በማመን መላው የሀገራችን ሕዝቦችና የሃይማኖት ተቅዋማት እንደዚሁም መላው የዓለም መንግሥታት ይህን ድርጊት በጽኑ መቃወምና ማውገዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያናችንም የተፈጸመውን ድርጊት ፈጽሞ ታወግዛለች ከመንግሥትና ከሕዝብ ጋር ተሰልፋም የሚጠበቅባትን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን ታረጋግጣለች፡፡

ቀደም ሲል በመግለጫችን እንደተነገረው የአሸባሪዎች የጥፋት እልቂት ሃይማኖትን፣ ቀለምን፣ ፆታንና አካባቢን ሳይለይ በአጠቃላይ በሰው ዘር ላይ የዘመተ የጥፋት ተልእኮ ስለሆነ ሁሉም የሃይማኖት መሪዎችና የፀረ ሽብር ተቅዋማት ለዓለማችን ሰላም መረጋገጥና ለሰው ልጆች በሕይወት የመኖር መብት መከበር ተባብረው እንዲሠሩ ቤተ ክርስቲያናችን በአጽንኦት ትጠይቃለች፤

 በተጨማሪ ያንብቡ…

More Articles...

የፎንት ልክ መቀየሪያ