Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ዛሬ ተጀመረ፡፡

የቤተ ክርስቲያን ቀኖና በሚደነግገው መሠረት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በዓመት ሁለት ጊዜ የሚካሄድ ሲሆን አንዱ በጥቅምት አንዱ ደግሞ በዓለ ትንሣኤ በዋለ በሃያ አምስት ቀን በርክበ ካህናት ይካሄዳል፡፡ ይኽንን ሐዋርያዊ ትውፊት መሠረት በማድረግ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ለማካሄድ ትናንትና 05/09/2006 ዓ.ም በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ገዳም በቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት የተለመደው የጸሎት መርሐ ግብር ተካሂደዋል፡፡

በዛሬው ዕለት የምልዓተ ጉባኤው መደበኛ ጉባኤ የተጀመረ ሲሆን ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላትና ጋዜጠኞች በተገኙበት ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን የቅዱስ ሲኖዶስ የመክፈቻ ንግግርና ቃለ በረከት አስተላልፎአል፡፡

የመክፈቻ ቃለ በረከቱም በአጠቃላይ የቤተ ክርስቲያናችን ጥንተ ቅድስናና ንጽሕና ተጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ፣ መልካም አስተዳደርና ብልሹ አሠራር እንዲወገድ ቅዱስ ሲኖዶስ የበኩሉን አስተዋጽኦ ማድረግ አለበት በማለት አደራ ጭምር አስተላልፎአል፡፡

የቅዱስ ሲኖዶስ መደበኛ ምልዓተ ጉባኤ ከዛሬ ጀምሮ የሚካሄድ ሲሆን ጉባኤውን በተመለከተና ውሳኔዎቹ እየተከታተልን እናቀርባለን፡፡

የተከበራችሁ አንባቢዎቻችን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በቅዱስ ሲኖዶስ መክፈቻ ላይ ያቀረቡት ቃለ በረከት እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

 

ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት

ሞትን በሞቱ ድል አድርጎ፣ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ፣ በኃይለ መለኮቱ ከሙታን ተለይቶ የተነሣው ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሁላችንንም በልዩ አጠራሩ ጠርቶ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት በሚካሄደው በዚህ ክርስቶሳዊና ሐዋርያዊ የቅዱስ ሲኖዶስ ዓቢይ ጉባኤ ስለሰበሰበን ክብርና ምስጋና ለእርሱ ይሁን፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ …

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ አቡነ ማትያስ ፓትሪያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሐዋርያዊ ጉዙ በጎንደር

ክፍል 1

  

ክፍል 2

ክፍል 3

ክፍል 4

 ክፍል 5

 

zena64

ዜና ቤተክርስቲያን 62ኛ ዓመት ቊ. 64

 

ማኅበረ ቅዱሳን "ጥንታዊ የብራና መጻሕፍት ዓይነትና የይዘት ትንተና እንዲሁም አያያዝና አጠባበቅ" በሚል የጥናት ርእስ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም ያዘጋጀው ሕገ ወጥ ጥሪ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት ታገደ

ከዚህ ቀደም ማኅበረ ቅዱሳን ከየካቲት 7-9 ቀን 2006 ዓ.ም በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ የአብነት መምህራን ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ሳያስፈቅድ በራሱ መንገድ ሀገር አቀፍ ጥሪ በማድረግ ሊያካሂደው የነበረውን ስብሰባ መታገዱን መግለጻችን ይታወሳል፡፡

አሁንም ማኅበረ ቅዱሳን በተመሳሳይ ከመንበረ ፓትርያርክ ሳያስፈቅድ "ጥንታዊ የብራና መጻሕፍት ዓይነትና የይዘት ትንተና እንዲሁም አያያዝና አጠባበቅ" በሚል የጥናት ርእስ የቤተክርስቲያን አባቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት እና ምሁራንን ሚያዝያ 23 ቀን 2006 በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም የጥናት ጉባኤ ተዘጋጅቷል ብሎ የሥልጣን ተዋረድንና የእዝ ሰንሰለትን ባልተከተለ መልኩ በመጥራቱ ቤተክርስቲያን ሳታውቅና ሳትፈቅድ ሊያካሂደው የነበረው ስብሰባ አሁንም በድጋሚ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት በቁጥርል/ጽ/392/384/2006 ዓ.ም በቀን 21/08/2006 ዓ.ም ቤተክርስቲያን የማታውቀውና ፈቃድም ያልሰጠችበት ስለሆነ ሲል በጻፈው ደብዳቤ በድጋሚ አግዶታል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም "ማህበረ ቅዱሳን ከመንበረ ፓትርያርክ  ልዩ ጽ/ቤት ፈቃድ ሳያገኝ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን ጋር ተያያዠነት ባላቸው ጉዳዮች በሙሉ ስብሰባም ሆነ በከፊል ጉባኤ ማድረግ የማይችል መሆኑን" ደብዳቤው በጥብቅ አስታውቋል፡፡

ይህንና ተያያዥ ዝርዝር ሐሳብ የያዙትን ደብዳቤዎች ከዚህ በታች በዝርዝር አቅርበናል፡፡፤

1.  ማኅበሩ በራሱ መንገድ ጥሪ ያስተላለፈበት፤
2. የብፁዕ ወቅዱስ ልዩ ጽ/ቤት ጉባኤውን ያገደበት ደብዳቤ
3. የብፁዕ ወቅዱስ ልዩ ጽ/ቤት ጉባኤውን አስመልክቶ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም የገለጸበት ደብዳቤ 

ከሀገር ወጥቶ የቆየው የመድኃኔ ዓለም ታቦት ወደ ሀገሩ ተመለሰ

ሚያዝያ 17ቀን 2006 ዓ.ም ከ17 ዓመታት በፊት በህገ ወጥ መንገድ ከሀገር ወጥቶ የቆየው የመድኃኔ ዓለም ታቦት ከጅቡቲ አዲስ አበባ ገባ።

ታቦቱ አዲስ አበባ ቦሌ አለም ዓቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናት፣ምእመናን፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችና የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን የሥራ ሃላፊዎች አቀባበል አድርገውለታል፡፡

ባልታወቀ ምክንያት ከቤተክርስቲያኒቱ የሸዋ ሃገረ ስብከት ከአፄ ዋሻ ማርያም ገዳም የጠፋው ይህ ታቦት በግለሰቦች ጥቆማ እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንና በቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ትብብር ወደ ሀገር ቤት ሊመለስ ችሏል።

 በተጨማሪ ያንብቡ …

የአራት ጉኤያት መምህር የነበሩት የመምህር ቆሞስ አባ ገ/ጊዮርጊስ ሥርዓተ ቀብር ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ተፈጸመ፡፡

አራት ዓይና መምህር የነበሩት የዕውቀትና የዕድሜ ባለጸጋ ቆሞስ አባ ጊጊዮርጊስ ገ/መድኅን ከኅጻንነታቸው ጀምሮ ቤተ ክርስቲያንን ለአንድ መቶ አስራ ሁለት ዓመታት ያህል ከረድእነት እስከ መምህርነት ካገለገሉ በኋላ ባደረባቸው ሕመም ምክንያት መጋቢት 16 ቀን 2006 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ፤ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የመቀሌ ሀገረ ስብከት ኃላፊዎችና መላ ሠራተኞች፣ የመቐለ አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፣ካህናት.ዲያቆናት፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችና ባጠቃላይ ምዕመናን፣ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በመቐለ ደብረ ገነት መድኃኔ ዓለም፣ቅድስት ኪዳነ ምሕረት እና ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ተፈጽሞአል፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ …

የብፁዕ አቡነ ቶማስ ዜና ዕረፍትና የሕይወት ታሪክ

ብፁዕ አባታችን አቡነ ቶማስ በቀድሞው አጠራር በጎጃም ጠቅላይ ግዛት በቆላ ደጋ ዳሞት አውራጃ በደጋ ዳሞት ወረዳ በመንበረ ስብከት ዝቋላ 4ቱ እንስሳ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ውስጥ ከአባታቸው ብላታ ተገኘ ይልማ ገ/ሕይወት እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ውድነሽ ቸሬ መጋቢት 14 ቀን 1935 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ "በእንበለ እፍጥርከ አእመርኩከ ወዘንበለ ትጻእ እምከርሠ እምከ ቀደስኩከ ወረሰይኩከ መምህረ ለአህዛብ" ተብሎ ለነቢዩ ኤርምያስ እንደተነገረለት (ኤር. 14) ብፁዕ አባታችን በብፁዓትና በፈቃደ አምላክ የተገኙ ማኅደረ መንፈስ ቅዱስ በመሆናቸው በወላጆቻቸው ቤት "ወልህቀ በበህቅ እንዘ ይትኤ ዘዝ ለአዝማዲሁ ወለይእቲ እሙ" (ሉቃስ 2፡51) እንደተባለው ለወላጆቻቸው በመታዘዝና በማገልገል ካደጉ በኋላ እድሜያቸው ለትምህርት እንደደረሰ በተወለዱ በ7 ዓመታቸው በደጋ ዳሞት ወረዳ ጉድባ ቅ/ማርያም ከሚገኙት ከታላቁ ሊቅ መምህር እንዱ ዓለም አስረስ ከመልክዐ ፊደል ጀምሮ ፀዋትወ ዜማን ተምረዋል በመቀጠልም ከቀደሙት ከብፁዕ አቡነ ማርቆስ ሊቀ ጳጳስ ዘጎጃም በ1948 ዓ.ም ማዕረገ ዲቁና ተቀብለዋል፡፡ በተሰጠው የመመዘኛ ፈተናም ችሎታቸውንና ብቃታቸውን ከአዩ በኋላ የትምህርት ቤት መጠሪያ መዘምር፣ ወላጆቻቸው ባለህ ተገኘ ብለው ያወጡላቸውን ስም ለውጠው በመንፈስ ቅዱስ የብፁዕነታቸውን የወደፊት አባትነት የተረዱት ሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ ከዛሬ ጀምሮ ስምህ ጸሐይ ነው ብለው ሰይመዋቸዋል፡፡ በኋላም በመምህራቸው ፈቃድ ከመምህር ገብረ ሥላሴ፣ ከመምህር ለይኩን እና ከተለያዩ መምህራን ቅኔ ተምረዋል፡፡ በእውቀትና በእድሜ እየበሰሉም በሄዱ ጊዜ ቅኔውን የበለጠ ለማዳበር የቅኔው ማዕበል ከሚፈስባት ታላቋ ገዳም ደ/ምዕራፍ ዋሸራ ማርያም ሂደው ከታላቁ ሊቅ ከመምህር ማዕበል ፈንቴ ቅኔውን ከእነ አገባቡ ግሱን ከእነአረባቡ ቅምሩ ተምረው በመምህርነት ተመርቀዋል፡፡ በኋላም ወደ ጸዋትወ ዜማ ት/ቤት ተመልሰው በደጋ ዳሞት ወረዳ ከሚገኙት ከታወቁት ሊቅ መ/ጋ ካሳ መንገሻ ከጾመ ድጋ እስከ ድጓ ያለውን ትምህርት አጠናቀዋል፡፡ በመቀጠልም የአቋቋም ትምህርታቸውን በዚያው በደጋ ዳሞት ከሚገኙት ከመምህር ዋሴ አስረስ ዝማሬ መዋሥዕት ከመምህር ወልዴ ማን አምኖህ ተምረው ተመርቀዋል፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ …

ማኅበረ ቅዱሳን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ይቅርታ እንዲጠይቅ፣ በቤተ ክርስቲያን ሞዴላ ሞዴሎች እንዲጠቀምና መዋቅሩን ሳይጠብቅ ማንኛውም ጥሪ እንዳያስተላልፍ በደብዳቤ ታዘዘ፤

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የጥቅምቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ውሳኔን መሠረት በማድረግ ማኅበረ ቅዱሳን ማንኛውም የማህበሩ ገቢና ወጪ በተመለከተ በቤተ ክርስቲያኗ ሕጋውያን ሞዴላ ሞዴሎች ከዋና ማዕከል ጀምሮ እስከ ንዑስ ማዕከልና የግኑኝነት ጣብያዎች ድረስ በማሰራጨት እንድትገለገሉ በማለት በቁጥር 2331/7628/2006 በቀን 28/06/2006 ዓ.ም በጻፈው ደብዳቤ አስታውቋል፡፡

መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤቱ ማኅበረ ቅዱሳን ሊገለገልባቸው ይገባል ያላቸው ሞዴላሞዴሎች በዝርዝር ያሳወቀ ሲሆን የቤተ ክርስቲያኗን ሞዴሎች ከሚያሣትም ከትንሣኤ ማሣተሚያ ድርጅት በሕጋዊ መንገድ ተረክበው ሥራ እንዲጀምሩ ሆኖ የሒሳብ ምርመራ ውጤታቸውም ለጽ/ቤቱ እንዲያቀርቡ መመሪያ አስተላልፎአል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ማኅበረ ቅዱሳን ቤተ ክርስቲያኗን ሳያስፈቅድ የጠራው ሀገር አቀፍ የመምህራን የምክክር መድረክ በጠቅላይ ቤተ ክህነት መታገዱን ተከትሎ እና ከዚህ ቀደምም ለፈጸማቸው አጠቃላይ የመዋቅር ጥሰቶች ማኅበሩ በይፋ ባሉት ሚድያዎቹ ቤተ ክርስቲያኗን ይቅርታ እንዲጠይቅ ጠቅላይ ቤተ ክህነት በደብዳቤ መምሪያ አስተላልፎአል፡፡

ምክንያቱ ሲያስረዳም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ራሱን የቻለ ሕግና ደንብ ያላት ከመሆኑም ሌላ ባላት ደንብና መመሪያ መሠረት የሥራ ዕዝ ሰንሰለት መዋቅሯን ጠብቃ እየሠራች ባለችበት ጊዜ ማኅበሩ እያደረገው ያለው የመዋቅር ጥሰት ተገቢ ሆኖ ባለመገኘቱ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት አስተዳደር ጉባኤ ማኅበሩ በይፋ ባለው የሚድያ ሽፋን ሁሉ ግልጽ በሆነ ሁኔታ ቤተ ክርስቲያኗን ይቅርታ እንዲጠይቅ ውሳኔ ማስተላለፉን ይገልጻል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ማኅበረ ቅዱሳን የዕዝ ሰንሰለቱን ሳይጠብቅ ከዋና መሥርያ ቤትና ከመምሪያዎች ይሁንታ ሳያገኝ በቀጥታ ለአኅጉረ ስብከት ደብዳቤ በመጻፍ ስብሰባም ሆነ መሰል ድርጊቶች እንዳይፈጽም ለሁሉም አኅጉረ ስብከት ሰርኩላር ደብዳቤተላልፎአል፡፡

የተከበራችሁ አንባቢዎቻችን ሦስቱን ደብዳቤዎች ማለትም፡-
1. ማኅበረ ቅዱሳን በቤተ ክርስቲያኗ ሞዴላሞዴሎች እንዲጠቀም የተጻፈለት ደብዳቤ
2. ማኅበረ ቅዱሳን ባለው የሚድያ ሽፋን ቤተ ክርስቲያኗን ይቅርታ እንዲጠይቅ የተጻፈለት ደብዳቤ
3. ማኅበረ ቅዱሳን ጣልቃ ገብቶ ለአኅጉረ ስብከት ደብዳቤ እንዳይጽፍ የተጻፈለትን ደብዳቤ ከዚህ ቀትሎ ቀርቦአል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሀገር አቀፍ የምክክር ጉባኤ መካሄድ ጀመረ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ከኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ሀገር አቀፍ የግንዛቤ ማስጨበጫ የምክክር ጉባኤ ዛሬ የካቲት 21 ቀን 2006ዓ.ም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር ዋና ጸሐፊና የቦርድ አባላት፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያው ኃላፊዎችና ምክትል ኃላፊዎች፣ የየአኅጉረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጆችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በስብከተ ወንጌል አዳራሽ ተጀመረ፡፡

 በተጨማሪ ያንብቡ…

የዓለም ዓብያተ ክርስቲያናት ጉባኤና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የነበራት ተሳትፎ በሚመለከት አጭር ሪፖርት

አባ ኃ/ማርያም መለሰ /ዶ/ር/
የጠቅላይ ቤተ ክህነት ም/ሥራ አስኪያጅና
የዓለም አብያተ ክርስቲያናት የማዕከላዊና
የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል

በሃያኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት ደርሶበት ከነበረው ከፍተኛ አደጋ ማውጣት ግዙፍ ጫና ነበር፡፡ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ በግፍ መገደል የፈጠረው ጥርጣሬ ቀላል አልነበረም፡፡ በተለይም የዓለም የአብያተ ክርስቲያናት ሕብረት መሥራች ከመሆኗም በላይ የአፍሪካ የሃይማኖት ጋሻ ተብላ በተሰየመችበት ሀገር ደርግ ሁለተኛውን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስን በግፍ በመግደሉ ምክንያት የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን በዓለም አቀፍ ደረጃ ደርሳበት ከነበረው ከፍተኛ ደረጃ ወደ ዝቅተኛ ሁኔታ አድርሷት ነበር፡፡ ስለዚህ የቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት በሃያኛው ክፍለ ዘመን ከውጭ ሳይሆን ወሳኝ ፈተናዎችን ከውስጥ ያስተናገደችበት ዘመን ነበር፡፡ ያን የመሰለ ታሪካዊ ጉባኤ ባካሄደችበት ሀገርና ቤተ መንግስት እግዚአብሔር የለም የሚል ርዕዮት በመስፋፋቱ እነዚህን ታላላቅ የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎችን የማስተናገድ አቅም የነበራት ቤተ ክርስቲያን ንብረቷ ተቀምቶ ሊቃውንቷ በየሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱና በየዩኒቨርስቲው ተበትነዋል፡፡ ይሁንና ከለውጥ በኋላ በቀድሞው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያኗ ወደ ቀድሞ የውጭ ግኑኝነት ተመልሳ ተሳትፎዋን ቀጥላለች፡፡ በአሁኑ ዘመን ጥንት የነበረው የክርስቲያን የትብብር መንፈስ ዛሬም እንዲኖር ታላቅ ፍላጎት መኖሩን ስንመለከት በጣም ደስ ይለናል፡፡ በዚህም መንፈስ ከልባችን እናከብራለን፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዓለም አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት (WCC) ከጥቅምት 20 እስከ ህዳር 3 ቀን 2006 ዓ.ም ደቡብ ኮሪያ በተደረገው አጠቃላይ ስብሰባ ቤተ ክርስቲያናችን በማዕከላዊ ኮሚቴና በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መሰየሟ የሚታወስ ነው፡፡ በመሆኑም ለመጀመሪያ ጊዜ ከጥር 29 እስከ የካቲት 6 ቀን 2006 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ በጄኔቫ ቦሲ በተሳተፈችበት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ውይይት የተደረገ ሲሆን፣ ሳውዝ ኮርያ ስለተደረገው ስብሰባ አፈጻጸም፣ አዳዲስ አባል ለመሆን ስለጠየቁ አብያተ ክርስቲያናት፣ ስለ 2014 ዓ.ም የማዕከላዊ ኮሚቴ መወያያ አጀንዳ፣ ስለ ስትራቴጂክ ፕላን፣ ከ2014 -2017፣ የተለያዩ ንዑሳን ክፍሎችን በማቋቋምና መንፈሳዊ ጉዞ ለሰላምና ለፍትህ በሚል ርዕስ ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡ ሌሎችም በርካታ ጉዮች በስብሰባው ላይ በአጀንዳ የቀረቡና ውይይት የተደረገባቸው ጉዳዮች ነበሩ፡፡ እሁድ ጠዋት ሎዛን በተባለች ከተማ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በምትተዳደረው የቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በመገኘት የቅዳሴና የትምህርተ ወንጌል አገልግሎት አከናውነናል፡፡ ደስ ከሚያሰኘው ነገር አንዱ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን በአንድነት ሥርዓተ ቅዳሴውን ሲከታተሉና ሲፈጽሙ እንዲሁም ልጆቻቸውን ሲያቆርቡ በማየታችን እጅግ ደስ ብሎናል፡፡

በጄኔቫ የምትገኘው የመድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ለምእመናን ጥሩ አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆኗንና በዛ የሚገኙት አስተዳዳሪ አባት በጥሩ ሁኔታ እየመሩት እንደሆነ ለማወቅ ችለናል፡፡ በጄኔቫ የሚገኘው የኢምባሲ ሠራተኞች ከተማውን በማስጎብኘት በማስተናገድ ቀና ትብብር አድርገውልናል፡፡ የሚያስመሰግን ነው፡፡ በጄኔቫ ለረጅም ጊዜ ኗሪ የሆኑት ባልና ሚስት በቤታቸው በመጋበዝ የኢትዮጵያውያንን የእንግዳ ተቀባይነት ተግባር ማከናወናቸውን ስናይ በጣም ተደስተናል፡፡ በሀገሪቷ ያለው ሰላምና ጸጥታ እንዲሁም የስልጣኔ፣ የዕድገት ደረጃና የተረጋጋ አኗኗር ወደዚህ የኑሮ ደረጃ ለመድረስ ለሚጥሩ ሀገራት ጥሩ ተሞክሮ ነው፡፡ በመጨረሻም ስብሰባው በሽኝት ጸሎት ተጠናቆ ወደየመጣንበት ተመልሰናል፡፡

"ይህን ሁሉ ላደረገና ለረዳን እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይድረሰው"

የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ "ማኅበረ ቅዱሳን" የማዘዣ ወረቀቱንና ማኅተሙን እንዲያስተካክል ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ደብዳቤ ጻፈ፡፡

የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማህበረ ቅዱሳን በማዘዣ ወረቀቱና በማኅተሙ ሚገኘውን የመምሪያውን ስም እንዲያነሳ በዛሬው ዕለት ጠይቋል፡፡ መምሪያው በደብዳቤው ማኅበረ ቅዱሳን ከተመሠረተ አንስቶ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሥር ሆኖ ሲመራ ማለትም ተጠሪነቱ ለሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ እያለ የማዘዣ ወረቀቱም ሆነ ማኅተሙ በማደራጃ መምሪያ ስም በማድረግ ሲገለገል መቆየቱን አስታውሶአል፡፡

አሁን ግን በግንቦት 2004 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተጠሪነቱ ከማደራጃ መምሪያው ወጥቶ በጊዜያዊነት ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ እንዲሆን በማለት ከተወሰነ ዓመታት ቢያልፍም እስካሁን ድረስ በቆየው የማደራጃ መምሪያ ስም በማዘዣ ወረቀቱም ሆነ በማኅተሙ እየተገለገለ መገኘቱ አለአግባብና ሕጋዊ አካሄድ አለመሆኑን ገልጾ ለጠቅላይ ቤተ ክህነት በዛሬው ዕለት በቀን 14/05/2006 ዓ.ም ደብዳቤ ጽፏል፡፡

በመሆኑም ከዛሬ ጀምሮ በሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሚለውን ስም ከማዘዣ ወረቀቱንም ሆነ ከማኅተሙ በማንሳት የተፈቀደለትን ስምና መዋቅር ብቻ እንዲጠቀም አግባባዊ መመሪያ እንዲሰጠው የሚጠይቅ ደብዳቤ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ጽፎአል፤ ደብዳቤውም እነሆ አቅርበነዋል፡፡

"ማኅበረ ቅዱሳን" የማዘዣ ወረቀቱንና ማኅተሙን እንዲያስተካክል የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ለጠቅላይ ቤተ ክህነት የጻፈው ደብዳቤ

በማኅበረ ቅዱሳን የተዘጋጀው የአብነት መምህራን የምክክር መድረክ እና ሁኔታው፤

በማኅበረ ቅዱሳን የተጠራውንና እንዳይካሄድ የተከለከለውን ጉባኤ በሚመለከት እውነታውን ምን እንደሚመስል ግለጹልን በማለት የድረ ገጻችን አንባቢዎች ተደጋጋሚ ጠይቀውናል፡፡ በመሆኑም የጉባኤውን አጠቃላይ ሁኔታ እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን ከየካቲት 7-9 ቀን 2006 ዓ.ም በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ የአብነት መምህራን ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ሳያሳውቅና ሳያስፈቅድ በራሱ መንገድ ሀገር አቀፍ ጥሪ በማድረግ በአዲስ አበባ በግዮን ሆቴል፣ በብሔራዊ ሙዝየም ትልቁ አዳራሽ እና በስብሰባ ማዕከል ለሦስት ተከታታይ ቀናት ሀገር አቀፍ የአብነት መምህራን ጉባኤ ለማድረግ አስቦ ያዘጋጀው ጉባኤ ለማካሄድ ለሁሉም የጠቅላይ ቤተ ክህነት መምሪያዎችና ሊቃነ ጳጳሳት የግብዣ ደብዳቤ ያስተላልፋል፡፡
ይህንን ሀገር አቀፍ ጉባኤ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ዕውቅናና ፈቃድ ውጭ ብቻም ይሆን ከማኅበሩ ስልጣንና ኃላፊነት በላይ ሆኖ በመገኘቱ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጉባኤው እንዳይካሄድ በማለት የካቲት 4 ቀን 2006 ዓ.ም በአድራሻ ለማኅበሩ በግልባጭ ለሚመለከታቸው መንግስታዊ አካላት ደብዳቤ በመጻፍ እንዲታገድ ያደርጋል፡፡

በወቅቱም ማኅበሩ ከተሰጠው የአገልግሎት ድርሻ በላይ ማንንም ሳያስፈቅድ የቤተ ክርስቲያንዋ አጠቃላይ መዋቅር ወደ ጎን በመተው ራሱን ችሎ ቤተ ክርስቲያኒቷ ይሁንታ ባልሰጠችበት ሁኔታ በቀጥታ በራሱ መንገድ ሀገር አቀፍ ጥሪ አድርጎ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት መሰብሰብ እንደማይችል እያወቀና ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከተው የትምህርትና ማሰልጠኛ መምሪያ ምንም ሳያውቅ፣ አኅጉረ ስብከቶችና የወረዳ ቤተ ክህነት ጽ/ቤቶች ምንም በማያውቁት ሁኔታ ጥሪ አስተላልፎ ጉባኤ ማዘጋጀት በዋናነት የሚመለከታቸው የቤተ ክርስቲያንዋ የበላይ ኃላፊዎች ዕውቅና መስጠት፣ መፍቀድና ማዘዝ ሲገባቸው እንደታዛቢ ቆጥሮ በክብር እንግድነት እንዲገኙ መጋበዙ ማኅበሩ ከሕጋዊ የቤተ ክርስቲያን መዋቅራዊ አሠራር የቱን ያህል እንደራቀ የሚያሳይ መሆኑን አንዳንድ የመምሪያ ኃላፊዎች የገለጹ ሲሆን ጠቅላይ ቤተ ክህነት የወሰደው አስቸኳይ የእርምት እርምጃም ተገቢ መሆኑ አስምረውበት ነበር፡፡

ጠቅላይ ቤተ ክህነት በበኩሉ ማኅበሩ በጊዜያዊነት ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ ሆኖ እያለ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በማያውቁትና ባልፈቀዱት ሁኔታ በሕገ ወጥ መንገድና በማን አለብኝነት ዋናው መስሪያ ቤት ሳይጠይቅና ሳያስፈቅድ ከተሰጠው ሥልጠናና መመሪያ ውጪ ሀገር አቀፍ የስብሰባ ጥሪ ማድረጉ አለአግባብ መሆኑን በመግለጽ ከዚህ በኋላ ይህ ስብስባ ቤተ ክርስቲያናችን የማታውቀው በመሆኑ እንድታስቆሙ በማለት፤ ለወደፊትም በቤተ ክርስቲያኒቱ ዙርያ ለምታደርጉት ማንኛውም እንቅስቃሴ ጠቅላይ ቤተ ክህነትና የሚመለከታቸው የየመምሪያ ኃላፊዎች ሳያውቁት የምታከናውኑት እንቅስቃሴ ሁሉ ተቀባይነት የሌለውና ሕግንና ሥርዓትን ያልጠበቀ አካሄድ በሕግ የሚያስጠይቃችሁ መሆኑን እንድታውቁ በማለት ምክር አዘል የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ይጽፍላቸዋል፡፡

በነጋታው የማኅበሩ ነባርና አሁን ያሉ ከፍተኛ አመራሮች ወደ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ በመግባት በድርጊቱ ተጸጽተናል፣ ይቅርታ ይደረግልን፣ ከዚህ በኋላ ይህንን ትምህርት ሆኖን እናስተካክላለን በማለት በቃል ከዋና ሥራ አስኪያጁ ጋር ከተስማሙ በኋላ የይቅርታ ደብዳቤ የካቲት 5 ቀን 2006 ዓ.ም ጽፈው ለጠቅላይ ቤተ ክህነት በማስገባት በይፋ ይቅርታን ይጠይቃሉ፡፡
ጠቅላይ ቤተ ክህነቱም ይህንን የይቅርታ ደብዳቤ ተመልክቶ በዚሁ ቀን ይቅርታ በማድረግ ቀደም ብሎ ጽፎት የነበረውን የእገዳ ደብዳቤ እንደገና መነሳቱን በዋናነት ለማኅበሩ በግልባጭ ለሚመለከታቸው አካላት ይጽፋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ሁኔታውን በትዕግስት ሲከታተሉት ከቆዩ በኋላ የእገዳ ደብዳቤውን መነሳት ተከትሎ የማስተካከያ ደብዳቤ በቀን 06/06/06 ዓ.ም ለብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ በአድራሻ በግልባጭ ለሚመለከታቸው አካላት ጽፈዋል፡፡
የማስተካከያ ደብዳቤውም ማኅበረ ቅዱሳን የቤተ ክርስቲያን የበላይ አባቶች ሳያውቁትና ሳይፈቅዱት እንዲሁ በራሱ ስልጣን ሀገር አቀፍ ጥሪ አድርጎ መሰብሰብ አይችልም፤ ስለሆነም ጉባኤው መታገዱ አግባብና ትክክል መኖሩን አስታውሶአል፡፡ ምክንያት ሲገልጽም ማኅበረ ቅዱሳን እንዲህ ዓይነቱ ሀገር አቀፋዊ የቤተ ክርስቲያንን ሊቃውንት ያለበላይ አመራር አካላት ፈቃድ መጥራትና መሰብሰብ ማለት ቤተ ክርስቲያኒቱ ሕግና ሥርዓት እንደሌላት፤ ከነጭራሹም የበላይ ኃላፊዎች እንደሌሏት የሚያስቆጥር ሕገ ወጥ ስለሆነ በቸልተኝነት ወይም በዝምታ የሚታለፍ ስላልሆነ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕጋዊ መብትና ክብር ለመጠበቅ ሲባል ዕገዳውን እንዲጸና የሚያስገነዝብ ነበር፡፡
ሀገር አቀፍ ጉባኤው የታገደበት ዋና ምክንያት

ሀገር አቀፍ ጉባኤው የታገደበት ዋና ምክንያት ማኅበረ ቅዱሳን በቤተ ክርስቲያን ከተሰጠው ሥልጣንና ኃላፊነት በላይ በመሆን በየደረጃው የሚገኙ የቤተ ክርስቲያን የበላይ አመራር አካላት ሳያሳውቅና ሳያስፈቅድ በማዘጋጀቱ ብቻ ነው፡፡ ይኸውም አሠራር ስሕተት መሆኑን ማኅበሩ ለጠቅላይ ቤተ ክህነት በጻፈው የይቅርታ ደብዳቤ ገልጿል፡፡ የተከበራችሁ አንባቢዎቻችን ከዚህ ቀጥሎ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ለማኅበሩ የጻፈለትን ደብዳቤ፣ ማኅበሩ ለጠቅላይ ቤተ ክህነት የጻፈው የይቅርታ ደብዳቤ እና የቅዱስ ፓትርያርኩ ደብዳቤ ከዚህ እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡

1. ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጉባዔውን ያገደበት ደብዳቤ፣

2. ማኅበሩ ለጠቅላይ ቤተ ክህነት የጻፈው የይቅርታ ደብዳቤ 

3. ጠቅላይ ቤተ ክህነት እገዳውን ያነሳበት ደብዳቤ፣

4 . የቅዱስ ፓትርያርኩ ደብዳቤ

 

More Articles...

የፎንት ልክ መቀየሪያ