Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

በማህበረ ቅዱሳን የቀረበው የአክሲዮን ሽያጭ እና ግዢ ጥያቄ አግባብ አለመሆኑን ማደራጃ መምሪያው ገለጸ

ከመምሪያው ሕትመት ክፍል

ማኅበረ ቅዱሳን እንደ መንፈሳዊ ማኅበር ሆኖ የተደራጀው በ1984ዓ.ም ሲሆን በቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ መተዳደሪያ ደንብ ወጥቶለት ወጣቶችን ለማስተማር እና እንዲሁም ለሰንበት ትምህርት ቤቶች እንዲሰጥ በሚል ዓላማ የተደራጀ ማኅበር ነው፡፡ ይህ ማኅበር ሲደራጅ ግን ሙሉ በሙሉ ተጠሪነቱ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሥር ሆኖ እንዲመራ በውስጠ ደንቡ መሠረት ታዝዟል፡፡ ይሁን እንጂ ምንም እንኳ ውስጠ ደንቡ ተጽፎ በወረቀት ቢኖርም የማህበሩ አካሄድ እና በወረቀቱ ላይ ያለው ውስጠ ደንብ የሰማይና የምድር ያህል እንደሚራራቅ ብዙ ምዕመራንም ሆኑ የቤተ ክርስቲያኒቱ የየመምሪያው ኃላፊዎች በሚገባ ያውቁታል፡፡ ይሁን እንጂ ማደራጃ መምሪያው እስከ አሁኗ ሰዓት ድረስ ይህንን የማኅበረ ቅዱሳንን ያፈነገጠ አካሄድ ለማስተካከል ሌት እና ቀን እየሠራ ነው፡፡ ይህ የማደራጃ መምሪያው እንቅስቃሴ ያሰጋው ማኅበረ ቅዱሳን ግን ከቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ መዋቅር ለመውጣት በማሰብ እንዲሁም በብልጣ ብልጥ አካሄድ በማለሳለስ፤

 • የባንክ ሂሳብ
 • የቦንድ ግዢ ፈቃድ
 • እንዲሁም የተለያዩ ማኅበሩን የሚመለከቱ ጉዳዮች ሁሉ በአንድ ሰው ፊርማ ብቻ እንዲንቀሳቀስ ይፈቀድለት ዘንድ ደብዳቤ እንዲጻፍለት ለማደራጃ መምሪያው ጥያቄ አቀረበ፡፡ ማደራጃ መምሪያው ይህንን ጥያቄ ሲመለከት እጅግ ከማዘኑም በላይ አስቦት የማያውቀው የማኅበሩ ከቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ መዋቅር የመገንጠሉ ስሜት በዚህ መልኩ መምጣቱ በጣም አሳፍሮታል፡፡ ይህ ራሱን ከቤተ ክርስቲያን ጉያ የማውጣት እንቅስቃሴም አግባብ አለመሆኑን እየገለጸ የማህበሩን የአመራር ሁኔታ በጥልቀት የማያውቁ ወይም ያልተረዱ የማህበሩ አባላት ከቅድስት ቤተ ክርስቲያናቸው ሳያውቁ በማህበር ስም እንዳይወጡ ቆመው የት እንዳሉ ሊያጤኑ እንደሚገባ በተደጋጋሚ ጥሪውን አስተላልፏል አሁንም እያስተላለፈ ነው፡፡

እንደ ማደራጃ መምሪያው አቋም ማኅበረ ቅዱሳን ሕግ እንዲይዝ እንጂ እንዲፈርስ ወይም እንዲገነጠል አስቦ አያውቅም፡፡ ይሁን እንጂ ማኅበረ ቅዱሳን በመንፈሳዊ ማኅበር ስም ተደራጅቶ ለትርፍ የተቋቋመ ማኅበር አለመሆኑን እየገለጸ ነገር ግን ከሀገር ውጪ እሰከ ሀገር ውስጥ በብዙ ሚሊዮን የሚያንቀሳቅሰው ገንዘብ በቤተ ክርስቲያኒቷ ስም እስከ ሆነ ድረስ ቤተ ክርስቲያኒቷ ልታውቀው ይገባል ብሎ ማደራጃው በማሳሰብ ማኅበረ ቅዱሳን በቤተ ክርስቲያኒቷ ስም ያግበሰበሰውን ገንዘብ ለማሸሽ የአክስዮን ግዢ መጠየቁና ሁሉም ሂሳብ በአንድ ግለሰብ ፊርማ ብቻ እንዲንቀሳቀስ መፈለጉ ለቤተ ክርስቲያን ጥቅም ሳይሆን ለንግድ ያለውን ፍቅር ያሳያል የሚል አቋም አለው፡፡

ማደራጃ መምሪያው አሁንም የሚያሳስበው ጉዳይ በየአህገረ ስብከቱ ያሉት የቤተ ክርስቲያናችን ልጆች አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገል ካለባቸወ ጥማት የተነሣ የማኅበረ ቅዱሳን አባል በመሆን ከዕለት ጉርሳቸው እየቀነሱ የሚልኳት 2 ፐረሰንት የደሞዛቸው ተቆራጭ ቤተ ክርስቲያንን ሳይሆን የአበላል ስትራቴጂ /ዘዴ/ በቀየሱ ምሁራን ወንድሞቻቸው ኪስ እየገባ እንደሆነ እንዲያውቁ እና ቢያንስ የቤተ ክርስቲያኒቱን ካርኒ ወይም የወጪና የገቢ ደረሰኝ እንደማይነካ እና ገንዘባቸው ለራሳቸውም ለቤተ ክርስቲያናቸውም ሳይሆን መሀል ላይ በተደራጁ ግለሰቦች እጅ እየተባ መቅረቱን እንዲያውቁት በማለት ይገልጻል፡፡

ቤተ ክርስቲያኒቷ ገቢና ወጪአችሁን አሳውቁኝ ስትል ያለውን አጠቃላይ የማኅበረ ቅዱሳንን የሂሳብ መዝገብ አመራሩ በግለሰብ ስም ለማዞር መንቀሳቀስ ጀመረ በማለት እውነታውን የሚገልጸው ማደራጃ መምሪያው ማኅበረ ቅዱሳን አክሲዮን ቢገዛ እና አጠቃላይ የማኅበሩ ጉዳይ በግለሰብ ፊርማ ቢንቀሳቀስ ያስከትላል የሚለው ችግር፤

 1. በቤተ ክርስቲያኒቷ ስም ማኅበሩ ያካበተው ንብረት ሁሉ የግለሰብ መጫወቻ ይሆናል ብሎ በመስጋቱ ማኅበሩ ቢፈርስም እንኳ ወራሹ በግልጽ በውስጠ ደንቡ ላይ የተገለጸ ስላልሆነ የቤተ ክርስቲያን ንብረትተበዝብዞ ይቀራል ብሎ በመስጋት፤
 2. አጠቃላይ የማኅበሩ አሠራር ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን የእዝ ሰንሰለት ወይም መዋቅር ይወጣል ስሎ በማሰቡ፤
 3. ከዚህ በፊት ፈጽሞ በውስጠ ደንቡ ያልተካተተ አዲስ ሀሳብ እና አሰራር በመሆኑ እና ይህን መሰል ችግሮችን በውስጡ ያዘለ ስለሆነ በአክሲዮን ጉዳይ ላይ የቀረበውን የማኅበረ ቅዱሳንን ጥያቄ ሙሉ በሙሉ ውድቅ አድርጓል፡፡ ማደራጃ መምሪያውም ይህንን ሁኔታ የሚገልጸው የቤተ ክርስቲያንን ገንዘብ ከመበዝበዝ አኳያ ነው፡፡ ማደራጃ መምሪያው የተቃወመውን የማኅበረ ቅዱሳንን የአክስዮን ግዢ ጥያቄ መጠየቂያ ደብዳቤ ምዕመናን አንብበው ይረዱት ዘንድ ከዚህ በታች ለማስረጃ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

 

PDF  1.ማኅበሩን የሚመለከቱ ጉዳዮች ሁሉ በአንድ ሰው ፊርማ ብቻ እንዲንቀሳቀስ ይፈቀድለት ዘንድ የጠየቀበት ደብዳቤ  ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት

PDF 2.ማኅበሩን የሚመለከቱ ጉዳዮች ሁሉ በአንድ ሰው ፊርማ ብቻ እንዲንቀሳቀስ ይፈቀድለት ዘንድ የጠየቀበት ደብዳቤ ለሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ

የፎንት ልክ መቀየሪያ