Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሥራ ኃላፊዎችና ከገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች ጋር ምክክር አካሔዱ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሥራ ኃላፊዎች፣ የክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት የሥራ ኃላፊዎች፣ የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችና ጸሐፊዎች በተገኙበት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አዳራሽ መስከረም 27 ቀን 2007 ዓ.ም. ከፍተኛ የምክክር ጉባኤ አካሔዱ ፡፡

መርሐ ግብሩ በቅዱስ ፓትርያርኩ ጸሎተ ቡራኬ ከተጀመረ በኋላ ለዕለቱ የተዘጋጀው ትምህርታዊ የመወያያ መልእክት ‹‹የቤተክርስቲያን የአስተዳደር አሠራርን ማበልጸግ›› በሚል መሪ ርእሰ ጉዳይ አንስተው ሰፊ ማብራሪያና ትምህርት፣ ምክርና ምእዳን በመስጠት የተሰብሳቢውን ልብ በሚነካ አኳኋን መልእክታቸውን አስተላልፏል ፡፡

ቅዱስ ፓትርያርኩ በመልእክታቸው ዘመኑ ያልዋጀና ብልሹ አሠራርን ስለማስተካከል በተመለከተ፣ ዘረኝነትና አድሎአዊ አሠራርን ስለማስወገድ በተመለከተ፣ ሙስናን ስለመቃወምና ሕገ ወጥ ማኅበራትን ሥርዓት ስለማስያዝ በተመለከተ ሰፊ ገለፃ በማድረግ መድረኩን ለውይይት ክፍት አድርገዋል፡፡

ጉባኤውም በቅዱስ ፓትርያርኩ ትምህርታዊ መልእክት ላይ ጥልቅ የሆነ ምክክር ካካሔደ በኋላ የጋራ የአቋም መግለጫ በማውጣት በከፍተኛ አድናቆት ተጠናቅቋል፡፡

የተከበራችሁ አንባቢዎቻችን ከዚህ ቀጥሎ ቅዱስ ፓትርያርኩ ያቀረቡትን መልእክትና የጉባኤው የአቋም መግለጫ በተመለከተ በተከታታይ የምናቀርብ መሆናችንን እንገልፃለን ፡፡በዕለቱ የተደረገው ወይይትና የአቋም መግለጫ ድምፅና ምስል ከዘህ ቀጥልን እናቀርባለን፡፡

ማስታወሻ፡-

 የህን ድምፅና ምስል በከፊልም ሆነ በሙሉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ፍቃድ ውጪ ማስተለፍ በሕግ ያስጠይቃል !!!

ክፍለ 1 ክፍለ 2

ክፍለ 3 ክፍለ 4
ክፍለ 5  
 

 

 

 

የፎንት ልክ መቀየሪያ