Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

በደቡብ ሱዳን በጁባ ከተማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ደብረ ምህረት ቅዱሰ ሚካኤል ቤተ ክርሰቲያን ቅዳሴ ቤቱ ተከበረ

በዶ/ር አባ ኃ/ማርያም መለሰ
የጠቅላይ ቤተ ክህነት ም/ሥራ አስኪያጅ

የክርስትና እምነት በኢትዮጵያ የተሰበከው በመጀመሪያው ምዕት ዓመት ነው፡፡ ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መስፋፋት የጀመረውና ወንጌልም በመላዋ ኢትዮጵያ የተሰበከው በ4ኛው መቶ ዓመት በአባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ዘመነ ጵጵስና ነው፡፡ ይህች ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን እምነቷን፣ ሥርዓቷንና ትምህርቷን በተለያዩ ጊዜያት ለዓለም ስታስተዋውቅ ቆይታለች፡፡ አሁንም በተለያዩ የአፍሪካ፣ የአውሮፓና የጃማይካ ክፍለ ዓለማት በተለያየ መንገድ እምነቷን እያስፋፋች ትገኛለች፡፡ በቅርቡ በጎረቤት አገር በደቡብ ሲዳን በጁባ ከተማ የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርቲያን ተሠርቶ ቅዳሴ ቤቱን እንድናከብር በብፁዕ ወቅዱስ አባታችን አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት አባታዊ መመሪያ በ13/3/2007 ዓ.ም ወደ ቦታው ተጉዘን ጽላተ ሕጉን ይዘን እንድንሄድ የታዘዝነው፡-

 • ብፁዕ አቡነ አረጋዊ ሊቀ ጳጳስ የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የበላይ ኃላፊና

 • አባ ኃ/ማርያም መለሰ /ዶ/ር የጠቅላይ ቤተ ክህነት ም/ሥራ አስኪያጅ ስንሆን በ13/3/2007 ዓ.ም በ7፡30 ሰዓት ጁባ አየር ማረፊያ በደረስን ጊዜ አምባሳደር ፍሬ ተስፋሚካኤልና ምእመናን የአቀባበል ስነ ሥርዓት ተደርጐ ወደ ታነፀው ቤተ ክርስቲያን ጉዞ ተጀምሮ በግምት 1 ኪሎ ሜትር ሲቀረው ጽላቱን በመሸከም የእግር ጉዞ በማድረግ ወደ ቦታው እንደደረሰን በቤተ ክርክርስቲያኑ ሥርዓተ ጸሎት በማድረስና ትምህርተ ወንጌል በመስጠት የዕለቱን ፕሮግራም አጠናቀናል፡፡ በ14/3/2007 ዓ.ም ሥርዓተ ቅዳሴውን ካከናወን በኋላ ዑደት በማድረግ በዓለ ንግሡን አክብረናል፡፡ የቤተ ክርስቲያኑ አሠራር የሚደነቅ ሲሆን በዛው ቦታ የካቴድራል ያህል የሚቆጠር ቤተ ክርስቲያን መሠራቱ ከ200-500 የሚቆጠሩ ምእመናን አቅም መሠራቱ እንዲሁም የሚደንቀው ደግሞ በ6 ወር ሠርተው ማጠናቀቃቸው ነው አስደናቂ የሚሆነው፡፡

 • IMG_0796 IMG_0811 IMG_0829 IMG_0843 IMG_0844 IMG_0858 IMG_0988
 • በዕለቱ በተከናወነው ስነ ሥርዓት በኢፌድሪ የደቡብ ሱዳን አምባሳደር የደቡብ ሪፐብሊክ ሱዳን የፕሬዚዳንቱ አማካሪ የደቡብ ሱዳን የፀጥታና የፍትህ ጄኔራል፣ የኤርትራ ቤተ ክርቲያን ተወካይና አገልጋይ ካህናት እንዲሁም ምዕመናን የግብፅ ቤተ ክርስቲያን ተወካይ የደቡብ ሱዳን የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ተወካይ እና የደቡብ ሱዳን የጎሳ መሪዎች ተወካይ በበዓሉ የተገኙ ሲሆን አምባሳደር ፍሬ ተስፋሚካኤልና የደቡብ ሪፐብሊክ የፕሬዝዳንቱ ኣማካሪ በየተራ ንግግር አድርገዋል፡፡ በንግግራቸውም ቤተ ክርስቲያኗ የአፍሪካውያን እናት ቤተ ክርስቲያን እንደሆነችና የብሉይ ኪዳን የክርስትናው የነፃነት፣ የታሪክ መሠረት መሆኗን በሚያስደንቅ አገላለጽ አብራርተዋል፡፡ ለወደፊቱም ብዙ የአፍሪካ ሀገሮችን መድረስ እንደሚገባት ገልጸዋል፡፡ ሌላው ለሌላው አርአያ የሚሆን የኢትዮጵያውያንና የኤርትራውያን ምዕመናን በአገልግሎት የሚያዩት መረዳዳትና መደጋገፍ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ በኩል የደብረ ሳህል ቅዱሰ ሚካኤል ቤተ ክርቲያን በዓል ሲሆን፣ የኤርትራ ካህናትና ምዕመናን አገልግሎት በአንድ ላይ ያከናውናሉ፡፡ የቅድስት ማርያም ቤተ ክርቲያን የኤርትራ ስትሆን በበዓሉ ቀን የኢትዮጵያ ካህናትና ምዕመናን በአንድነት አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡ እንዲሁም ቤተ ክርቲያኑ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ ያሳዩት ተሳትፎ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱን የሚያጠናክር በመሆኑ እጅግ የሚደነቅ ነው፡፡ ለበዓሉ ታዳሚ የቅዱሰነታቸውን የመልዕክት ደብዳቤ ለተሰበሰበው ምዕመናን አንብበን የእንኳን ደስ አላችሁ የአባታዊ ቡራኬአቸውን አብስረናል፡፡

 • በ15/3/2007 ዓ.ም በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ አምባሳደር ጽ/ቤት በመሄድ ከኢምባሲው ሠራተኞች ጋር በመወያየት ለቤተ ክርስቲያኗ ድጋፍ እንዲያደርግ ሌሎችም የልማት ሥራዎች በሚሠሩበት ጊዜ ድጋፋቸው እንዳይለያቸው ተወያይተን የኢምባሲው ሠራተኞችም በደስታ እንደሚመለከቱት እገዛም እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል፡፡ ሰበካ ጉባኤውም ለወደፊቱ የልማት ሥራዎችን ለመሥራት የገዙትን መሬት በቦታው ተገኝተን ለማየት ችለናል፡፡ ቦታውም ሰፊና ብዙ ሊያሠራ የሚችል መሆኑን ተገንዝበናል፡፡ ቦታው ሥራውን የሚጀምረው ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የመሠረት ድንጋይ ካስቀመጡ በኋላ የሚጀመር መሆኑንም ለማወቅ ችለናል፡፡ ከቦታው ሀገረ ገዥ ጋር ባደረግነው ውይይት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መሠረታችን በመሆኗ ማንኛውንም እገዛ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸውልናል፡፡

 • በመጨረሻም ከግብፃውያን ጳጳሳት ጋር በአጭር ጊዜ ውይይት በማድረግ በቀጣዩ ጊዜ ወንጌል የሚስፋፋበትን ሁኔታ እንዴት ማድረግ እንዳለብን ተነጋግረናል፡፡ የሚገርመው ቤተ ክርስቲያናችን በውጩ ያላት ግርማና ክብር የተለየ ነው፡፡ ተግተን መሥራት እንዳለብን ትልቅ ቁጭትን ፈጥሮብናል፣ ቤተ ክርስቲያኗ ዓለም አቀፋዊ ተልዕኮዋን ማጠናከርና ማስፋፋት እንደሚኖርባትም በዚሁ አጋጣሚ እንገልጻለን፡፡

ይህን ሁሉ ላደረገ ለልዑል እግዚአብሔር ምስጋና ይድረሰው

ዶ/ር አባ ኃ/ማርያም መለሰ
የጠቅላይ ቤተ ክህነት ም/ሥራ አስኪያጅ

የፎንት ልክ መቀየሪያ