Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ካርዲናል ሊዮናርዶ ሳንድሪን ተቀብለው አነጋገሩ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአከCስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በመሆን የምስራቃውያን ካቶሊክ አብያተ ክርሰቲያናት የበላይ ኃለፊ የሆኑትን ካርዲናል ሊዮናርዶ ሳንድሪ ልዩ የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል በማድረግ በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ፡፡

ካርዲናል ሊዮናርዶ ሳንድሪ፣ ብፁዕ አቡነ ብርሃነ ኢየሱስንና ሌሎች ከፍተኛ የካቶሊክ ጳጳሳትና የሥራ ኃላፊዎችን ያጠቃለለ ልዑክ መርተው የመጡ ሲሆን፣ ከቅዱስ ፓትርያርኩና ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ጋር ውጤታማና ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል፡፡

Picture 013 Picture 017 Picture 028 Picture 030 Picture 031 Picture 032 Picture 034

በቅድሚያ ንግግር ያደረጉት የዕለቱ የክብር እንግዳ የሆኑት ካርዲናል ሊዮናርዶ ሳንድሪ ናቸው፡፡ ካርዲናል ከንግግሬ ሁሉ አስቀድሜ የቀድሞውን ፓትርያርክ ተከትለው ይህችን ጥንታዊትና አንጋፋ ቤተ ክርስቲያን ለመምራት በመመረጥዎ እንኳን ደስ አለዎ በማለት መልካም ምኞታቸውን ለቅዱስነታቸው ከገለፁላቸው በኋላ ኢትዮጵያን ተዘዋውረው መጎብኘታቸውን ገልጸውላቸዋል፡፡ ካርዲናሉ በተለያዩ የሀገራችን ከተሞች ጉብኝት ማድረጋቸውን ገልጸው ይልቁንም በውቅሮ የጐበኙት ውቅር ጥንታዊ ቤተ ክርስቲያን የበለጠ እንደመሰጣቸው ገልፀው ለዚህች ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን ያላቸውን አድናቆት ለቅዱስ ፓትርያርኩ ገልጸውላቸዋል፡፡


በመቀጠልም በተለይ በአዲግራት የኦርቶዶክስና የካቶሊክ የሃይማኖት መሪዎች የሰላም ጉባኤ ማድረጋቸውንና በዚህ ጉባኤ ወቅትም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ያሰሙት ጣዕመ ዝማሬ እጅግ በጣም የሚመስጥና በዓለም ከሚገኝ የዜማ ስልት ግሩም ቃና የለበሰ በመሆኑ በእጅጉ መደሰታቸውንና በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ያደረጉት ጉብኝት በጣም ውጤታማና አስደሳች መሆኑን ገልጸውላቸዋል፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በበኩላቸው የተከበሩ ካርዲናል ሊዮናርዶ ሳንድሪ ሀገራችን ኢትዮጵያን ለመጐብኘት፣ ያላትን ታሪካዊ ገጽታ በዓይን ለማየትና ለማረጋገጥ እንዲሁም ምስክር ለመሆን እንኳን ደህና መጡ ብለው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልካም ምኞት ከገለፁላቸው በኋላ ስለ ኢትዮጵያና ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ፣ ትውፊት፣ ገዳማትና አድባራት የአሠራር ጥበብ፣ ጥንታዊነት፣ ስለ ብራና መጻሕፍት፣ ስለ አብነት መምህራንና ተማሪዎች በአጠቃላይ ስለ ቤተ ክርስቲያናችን አጠቃላይ ታሪካዊና ወቅታዊ ገጽታ ሰፊ ገለጻ አድርገውላቸዋል፡፡

በመቀጠልም ኢትዮጵያ ሀገራችን ኦርቶዶክስና ካቶሊክ ብቻም ሳይሆን ሁሉም ሃይማኖቶች በመፈቃቀር፣ በመከባበርና በመስማማት በሰላምና በፍቅር በእኩልነት የሚኖሩባት ሀገር መሆንዋንና በዚህ ረገድም በዓለም አቀፍ ደረጃ ሊጠቀስ የሚችል ታሪክና መልካም ተሞክሮ ያላት መሆኑን ሰፋ አድርገው ገልጸውላቸዋል፡፡

ስለ ሁለቱም አብያተ ክርስቲያናት በተመለከተም ልዩነታችን እንደተጠበቀ ሆኖ የጋራ በሆኑ እሴቶቻችን ዙርያ ዓለም አቀፍ አንድነት መሥርተን መሥራት ይኖርብናል፤ ክርስትና ሃይማኖት ለማስፋፋትና ከጥፋት ለመጠጠበቅ፣ በዓለማችን እየታዩ ያሉትን ማኅበራዊ ችግሮች ለማስወገድ ተባብረን በጋራ መሥራትና መጸለይ ይገባናል ብለው ከገለጹላቸው በኋላ በዛሬው ቀን እግዚአብሔር ፈቅዶ በመገናኘታችን ደስ ብሎኛል በማለት ደስታቸውን ገልጸውላቸዋል፡፡

ካርዲናል ሊዮናርዶ ከዚህ ቀጥለው የተለያየን ብንሆንም በወንጌል አንድ መሆናችንን ገልጸው በካቶሊክና በኦሬንታል ኦርቶዶክስ የሚደረግ የጋራ የምክክር ጉባኤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በኩል እየተደረገለት ያለው ድጋፍና የመምራት አገልግሎት በጣም በአድናቆት የሚመለከቱት መልካም ተግባር መሆኑንና ተጠናክሮም እንዲቀጥል አደራ ብለዋል፡፡

አያይዘውም ቤተ ክርስቲያናቸው የኦሬንታል አብያተ ክርስቲያናት ጥናት የሚያደርጉበት የትምህርት ተቋም ያላት መሆኑን ከገለጹ በኋላ በቅዱስነትዎ መልካም ፈቃድ ለሚላኩ የቤተ ክርስቲያናችሁ ልጆች ስኮላርሽፕ ለመስጠት ዝግጁዎች ነን በማለት የነፃ ትምህርት ዕድል ሰጥተዋቸዋል፡፡

በመጨረሻም የምክከር ጉባኤው ተጠናክሮ እንዲቀጥል በጋራ ተስማምተው የማስታወሻ ልውውጥ ካደረጉ በኋላ የመርሐ-ግብሩ ፍጻሜ ሆኗል፡፡

የፎንት ልክ መቀየሪያ