Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

የርዕሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን
ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር ዶክመንተሪ ፊልም ምረቃ

ዳንኤል ሰይፈሚካኤል ፈለቀ (መ/ር)

በመጀመሪያ ከሁሉ አስቀድመን ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለዚህች ቀን አደረሰን እያልኩ ረጀም ጊዜ የፈጀውንና ለርዕሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር መግለጫ እንዲሆን ለተዘጋጀው የዶክምንተሪ ፊልም ምረቃ በዓል ላደረሰን አምላክ ምስጋናን እናቀርባለን፡፡

ዶክምንተሪ ፊልም ወይም አንዳንድ ጊዜ ዘጋቢ ፊልም ማለት በልቦልድ ላይ ያልተመሠረተ፣ ኢ-ልቦለዳዊ፣ ምናባዊ ወይም አሉባልታዊ ያላሆነ፣ በአውነተኛና ተጨባጭ መረጃዎች፣ ታሪካዊ ክስተቶች፣ ወይም ድርጊቶች ላይ የተመሠረተ ለማስተማር፣ ለማሳወቅ፣ ቅስቀሳ ለማድረግ፣ ታሪክን ለመዘገብ፣ መሠረታዊ የሆኑ መልእክቶችን ለሕዝብ ለማስተላለፍና ለትውልድ ለማውረስ ሲባል የሚዘጋጅ ፊልም ነው፡፡ ዶክምንተሪ ፊልም በፊልም ሥነጥበብ ትምህርት ውስጥ ከፍተኛ ቦታ ያለው ጥበብ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ በመላው ዓለም ያሉ የብዙኀን መገናኛ ሥርጭት መሥመሮች ከመደበኛ የዜና እና የወቅታዊ መረጃ ሥርጭቶች ቀጥሎ ተጨባጭ መልእክትን በማስተላለፍ ከፍተኛውን ቦታ ይዟል፡፡ ዶክምንተሪ ፊልም እንደአስፈላጊነቱ በሲኒማ ወይም በተውኔት መልክ በገጸ ባህርያት እየተተወነ ወይም በታማኝ እና ሕያው ዘጋቢ መቅርብ የሚችል ሲሆን በአብዛኛው ተግባራዊ እየሆነ ያለውና የተመደው ግን ታሪካዊ ምስሎችንና ተንቀሳቃሽ ሥዕሎችን በመጠቀም በጥናትና ምርምር የተዘጋጀ ልዩ ዘገባ ወይም ትረካን በማዘጋጀት በትረካ መልክ አቀናብሮ ማቅረብ ነው፡፡ ባለፉት ሃያና ሠላሳ ዓመታት ውስጥ ዲክምነተሪ ፊልም ዕድገት ወደላቀ ደረጃ የደረሰ ሲሆን በተለይ እንደሌሎቹ የፊልም ጥበቦች እጅግ ብዙ ገንዘብ የማይጠይቅ፣ ከልቦለድ ይልቅ በእውነተኛና ገሐዳዊ ክስተቶች ላይ የሚያተኩር፣ በጥናትና ምርምር ላይ ተመረኮዘ መሆኑ፣ የሚያስተምርና የሚያሳውቅ ተደርጎ መዘጋጀቱ፣ አንዳንድ ጊዜም ተመልካቾችን ወይም አድማጮችን የሚያሳትፍ መሆኑ ተወዳጅ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ ስለ ዶክምንተሪ ፊልም በርካታ ትንታኔዎች ያሉ ቢሆንም የዚሁኑ ዘመናዊ የማስተማሪያና ቅስቀሳ የማድረጊያ ዘዴ በመጠቀም ለቤተ ክርስቲያን አንዳንድ መርሐ ግብሮች ያለውን አወንታዊ ጠቀሜታ ከግምት ውስጥ በማስገባት የርዕሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ቤተ መጻሕፍት ወመዘክርን ለማስተዋወቅና የሀገራችንን ረጅም ዘመን ያስቆጠረ ታሪክ ለማሳያት፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በሀገራችን ማኅበራዊ፣ ሥነ ጥበባዊና እና ሁለንተናዊ ታሪክ ውስጥ የነበራትን ጉልህ ድርሻ በመጠኑ የሚያስገነዝበው ይኽ የመጀመሪያው ዶክምንተሪ ፊልም ተዘጋጅቷል፡

ዶክምንተሪ ፊልም ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አሁን ያለውን ትውልድ በደረሰበት የሥልጣኔ እና የአስተሳሰብ ደረጃ ማገልገል ስላለባት፣ ትውልዱም ያለፈውን የአባቶቹንና እናቶቹን ታሪክ፣ የቅዱሳን እውነተኛ መንፈሳዊ የሕይወት ተጋድሎ፣ የሰማእታት ገድል፣ የሊቃወንተ ቤተ ክርስቲያንን የእምነትና የቀኖና ትምህርት፣ ተምሳሌትነት ያላቸው የምእመናን መንፈሳዊ ሕይወት፣ የአንዲት፣ ቅድስት፣ ሐዋርያዊትና ዓለም አቀፋዊት ቤተ ክርስቲያን በየዘመናቱ የገጠማትን ታሪካዊ ክስተቶችና በድል የተሞሉ ሉዓላዊ ታሪኮች በምስል አስደግፎ፣ በታሪካዊ መረጃ እያጣቀሱ፣ በልዩ ሙያዊ ቅንብር፣ በተለያዩ ሕዝቡ ሊሰማውና ሊረዳው በሚችለው ቋንቋ እያዘጋጁ ማቅረብ አሁን ያለውን ትውልድ ለማስተማርና በመንፈሳዊ ሕይወት ለማጽናት ወደር የማይግኝለት የማስተማሪያ መንገድ ነው፡፡ ስለዚህ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በሥነ ጽሑፍ፣ በሥነ ጥበብ፣ በታሪክ፣ በሥርዓት፣ በትምህርተ ሃይማኖት፣ በዜማ፣ በሥርዓተ አምልኮት፣ በትርጓሜ ቅዱሳት መጻሕፈት፣ በተፈጥሮና በሥነ ልቦናው ምርምሮች እና ወዘተርፈ ያላትን ሰፊ ሀብት በዚሁ በዶክምንተሪ ፊልም አቀራረብ እንዳስፈጊነቱ በማሰናዳት ለትውልዱ ማቅረቡ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡ ወቅታዊ ጉዳዮችንም ቢሆን በተለይ በአሁኑ ጊዜ ዘመን ተሻግረው ታሪክ ጠብቀው ከዚህ ትውልድ ደርሰው የቀደመውን ዘመን የክርስትና ሕይወት የሚመሰክሩ ጥንታውያን ገዳማትን፣ አድባራትን ታሪክ በመዘገብና፣ እነሱንም ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ሊደረግ የሚገባውን ኃላፊነት ለትውልዱ በማስተዋወቅ የዶክምንተሪ ፊልም ልዩ ጥቅም አለው፡፡ በዚሁ አንጻር የርዐሰ አድባራት አክሱም ጽዮን ኮሚቴም የዚሁን ጥበብ አስፈላጊነት በመረዳት ይህን ዘጋቢ ፊልም፣ ወይም ዶክምነታሪ ፊልም አዘጋጅቶ ለማስመረቅ አቅርቧል፡፡

የርዕሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ማርያም ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር ዘጋቢ ፊልም (ዶክመንተሪ ፊልም)

ርእሱ ‹‹አክሱም ጽዮን የሁለቱ ኪዳናት ማኅደር›› የሚል ነው፣ ትርጉሙ በጣም ከባድ አይደለም ሀገራችን ኢትዮጵያ በተለይም ጥንታዊቷ አክሱም የኪዳነ ኦሪት ብሉይ ኪዳን እና የኪዳነ ሐዲስ መጀመሪያ መሆኗን ለማሳየት የተመረጠ ርዕስ ነው፡፡ ስያሜው በአንድ በኩል አንድ ልዩ ቦታ የአሁኗን አክሱምን የሚመመለከት ይሁን እንጅ በአጠቃላይ የሚመለከተው ሀገራችን ኢትዮጵያን ነው፣ ምክንያቱም በአክሱም የተወጠኑት የሁለቱም ኪዳናት ትምህርቶችና ሥርዓቶች ብዙም ሳይቆዩ በመላ ሀገራችን ተዳርሰዋል፡፡ ስለዚህ የሁለቱ ኪዳናት ማኅደር የሚለው ስያሜ በአንድ በኩል መላዋን ኢትዮጵያን የሚመለከት ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ለዚህ ታሪክ ቋሚ ምስክር፣ ታሪኩ መገኛ፣ የሥልጣኔው ምንጭ፣ የሥርዓተ መንግሥቱ ማዕከል፣ የሥርዓተ አምልኮቱ ቀዳሚ መንበር አክሱምን ይመለከታል ማለት ነው፡፡

ዶክምነተሪ ፊልሙ ዋና ዓላማ
የርዕሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር ዘጋቢ ፊልም (ዶክመንተሪ ፊልም) በዓይነቱ፣ በይዘቱ፣ እና በአመሠራረቱ በሀገራችን ለየት የሚለውና የመጀመሪያ የሆነውን የሙዚየሙን ወይም የቤተ መጻሕፍት ወመዘክሩን ግንባታ በሰፊው ለማስተዋወቅ እና ከሚመለከታቸው አካላት በሙሉ የሐሳብ፣ የሙያ፣ የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ለማግኘት ተብሎ የተዘጋጀ ነው፡፡
በዚህ ሂደትም፣ አክሱም ከጥንት ጀምሮ ጥንታዊት የአፍሪካ የሥልጣኔ፣ የእምነትና የመንግሥት መናኸሪያ መሆኗ፣ አክሱም ቅድመ ልደተ ክርስቶስ ጀምሮ ለብዙ ሽ ዓመታት የሀገራችን የብሉይ ኪዳን በኋላ ደግሞ ሐዲስ ኪዳን ብሥራት የተሰማባት፣ ሥርዓተ መንግሥት ከሥርዓተ አምልኮት ጋር የተከናወነባት፣ ሥነ ጥበብ ከማኅበራዊ ዕድገት ጋር አብሮ የኖረባት፣ የንግድ፣ ሉዓላዊ የመንግሥት አስተዳደር፣ ዓለም አቀፍ ግንኙነት፣ የተከናወነባት፣ ከኢትዮጵያውያን አልፎ የአፍሪካውን ሁሉ መኩሪያ እንደሆነች ለማሳየት ተሞክሯል፡፡ ከዚህም ጋር ተያዞ የቤተ መጻሕፍት ወመዘክር መሠራት እነዚህ አኩሪ ታሪኮች ለመጠበቅ፣ ለማጥናት፣ ለማስተዋወቅ፣ ለማስተማር፣ ያለውን ተቀሜታ፣ በሕዝቦች መካከል የርስ በርስ መተዋወቅ እንዲኖር፣ ለሥነ ጥበብና ለባህል ዕድገት ያለውን አስተዋጽኦ ለማሳየት ተችሏል፡፡ በተለይም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በሀገራችን ሁለንተናዊ የእምነትና የሥልጣኔ ታሪክ የነበራትን ማዕከላዊ አስተዋጽኦ ለማስተዋወቅ ከፍተኛ አጋጣሚን ፈጥሯል፡፡

የዶክምነተሪ ፊልሙ የአሠራር ሂደት

የዶክምንተሪ ፊልም አሠራር በአንድ ባለሙያ የሚጀመርና የሚፈጸም ሳይሆን በርካታ ባለሙያዎችን የሚያሳትፍ፣ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚጠይቅ፣ ተከታታይ የሆኑ ምክሮችንና ጥናቶች የሚጠይቅ ስለሆነ በዚህ የዲክምንተሪ ፊልም ሥራ በርካታ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፣ ብዙ ጊዜ የፈጀ ምክክርና ውይይተ ተደርጓል፣ እንዲሁም ታሪካዊ መረጃንና የቃል ትውፊትን ያማከሉ አስፈላጊ ጥናቶች ተከናውነዋል፡፡ በመጀመሪያ አስፈላጊ ናቸው የሚባሉ የታሪክ ቅደም ተከተሎች ዳሰሳ ጥናት ተከናውኗል፤ በመቀጠልም ከዓቢይ ኮሚቴው በታዘዘው መሠረት የመጀመሪያው ዶክምንተሪ በአንድ ሲዲ እንዲጠናቀቅ የተወሰነ በመሆኑ ምን ዓይነት ይዘት ይኑረው የሚለውን ውይይት በማድረግ የመጀመሪያው ዶክምንተሪ የታሪክን ሂደት የሚያሳይ፣ በአክሱም በየዘመኑ የተከሰቱ ታሪኮች በአጭር በአጭሩ የሚዳስስ፣ መጠነኛ ቃለ መጠይቆችን የያዘ፣ የሙዚየሙን ግንባታ አጀማማርና አሁን የደረሰበትን ደረጃ የሚጠቁም እንዲሆን ስምምነት ላይ በመደረሱ በዚሁ መሠረት ዝግጅቱ ቀጠለ፤ ከዚያም በተደረጉት ውይቶችና ምክክሮች ላይ የተመሠረተ የመጀመሪያ ደረጃ የዶክምንተሪ ፊልም ወይም የዘጋቢ ፊልም ጥናታዊ ጽሑፍ ተዘጋጂቶ ለኮሚቴው ቀረበ፤ በዚህ ጽሑፍ መሠረትም የመስክ ጉብኝት እና መረጃ ማሰባሰብ ሥራ እንዲሁም አስፈላጊ የሆኑ የታሪካዊ ቦታዎች የቪዲዮ ቀረጻ ተከናውኗል፣ በዚህም በተለይ ወቅታዊ የሆኑ የሙዚየሙን ግንባታ እንቅስቃሴ የሚያሳዩ ምስሎች ከአባ ኪሮስ ገብረአብ አግኝተናል፣ የመስክ ቀረጻው በአቶ ወንድ ወሰን ስቱዲዮ ተከናውኗል፡፡

ከዚያም የቀረበው ጥናታዊ ጽሑፍ ለትረካ በሚመች መልኩ እንደገና ተዘጋጅቶ ለእርማት ቀረበ፣ እርማቱንም ብፁዕ አቡነ ገሪማ እና ክቡር ንቡረ ዕድ ኤልያስ አብርሃ በሚገባ አይተውና መርምረው እንዲተረክ ፈቃድ ሰጡ፤ በቀረበው እርማት መሥረት ጽሑፉ የትረካ ባለሙና የድምጽ ስጦታ ያላቸው ሰዎች ተፈልገውና ተመርተው የትረካው ቀረጻ ተከናውነዋል፡፡ በመጨረሻም ምስሎቹን፣ የተሰበሰቡትን ስዕላዊና ተንቀሳቃሽ ምስሎች፣ የተቀረጸውን ትረካ በአንድነት ወደማቀናጀቱ ሥራ በመግባት ቅንበሩ ተከናውኗል፡፡ ለዚሁ ሥራ ክትትል ኮሚቴው አባላቱን የወከለ ሲሆን እነሱም ከፊልም ቅንብርና አርትኦት ባለሙያዋ ጋር በመሆን የጎደለውን እየሞሉ የመጀሪያውን ተቀናበረ የዶክምንተሪ ፊልም በማጠናቀቅ እንደገና ለአስተያየት የኮሞቴው አባላትና ባለሙያዎች ባሉበት እንዲታይ ተደርጓል፡፡ በመጨረሻም በየደረጃው የቀረቡ አስተያየቶችንና ሙያዊ ምክሮችን በማካተት ሥራው ተጠናቆ ለምረቃ ሊደርስ ችሏል፡፡
ቀደም ሲል እንደተጠቀስኩት በዚህ ሥራ ውስጥ፣ የታሪክ ምርምርና ጥናታዊ ጽሑፍ ዝግጅት፣ የቪዲዮ ቀረጻ፣ የዶክምንተሪ ፊልም ጽሑፍ ዝግጅት፣ የእርማት፣ የድምጽ ትረካና ቀረጻ፣ የፊልም ቅንብር፣ የክትትልና ዳይሬክቲንግ ባለሙየዎችን፣ ሊቃውንትንና አባቶችን ተካተቱ ሲሆን አስተያየት በመስጠትና መረጃ በማሰባሰብም በርካታ ባለሙያዎች ተካፍለውበታል፡፡ እንግዲህ አንድ ሥራ ለመሥራት፣ የገንዘብ አቅም፣ ሥራ መስክ፣ የባለሙያ ስብስብ፣ የመረጃዎች መገኘት እና የመሳሰሉት ሁሉ አስፈላጊ ቢሆኑም ከሁሉ በላይ ደግሞ በቅን ሕሊናና ከልብ መነሣትን ጥረትን ሁሉ ለስኬት እንደበቃ፣ ትውድም እንዲማርበት ያደርጋል፡፡ በዚህ ረገድ ምንም እንኳ ከአምስት ሺ በላይ ዕድሜ ያስቆጠረችን የአክሱምን እምነትና የሥልጣኔ ታሪክ ሙሉ በሙሉ አጥንቶ፣ ከዚያ ውስጥ ለሚፈለገው አገልግሎት የሚሆነውን መርጦ፣ ተርኮ፣ አቀናብሮ ለፍሬ ማብቃት፣ በአጭሩ መከናወን የሚችል ነገር ባይሆንም ልባዊ ጥረትና መተበር ካለ ማይሳካ ነገር የለምና በአባቶቻችን ጸሎትና አመራር ሰጭነት በኮሚቴው ክትትልና ማስተባበር የዶክምንተሪ ፊልም ሥራው ለፍሬ ሊበቃና በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በከፍተኛ ክብር ሊመረቅ ችሏል፡፡
ከሁሉ በላይ ደግሞ የእመቤታችን ጸሎት ረድቶን የጌታችን ፈቃድ ሆኖ ይህ ዶክምንተሪ ፊልም ታትሙ ለሥርጭት ደርሷል፣ ዋናው ጉዳይ ቀደም ሲል በመግቢያው ላይ ስለ ዓላማው እንደገለጸኩት እየተሠራ ያለውን ከፍተኛ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ሥራ ማስተዋወቅ፣ ይህ ሥራ የዩኔስኮ ባለሙያዎች ሳይቀሩ አይተው አድናቆታቸውን የቸሩት፣ ለወደፊቱም ግንባታው ሲጠናቀቅ የበኩላቸውን ድጋፍ ለማድረግ ቃል የገቡበት፣ ከሀገር አቀፍ ደረጃናት አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና እያገኘ የመጣ፣ ቅርስን በመጠበቅ፣ በማስተዋወቅ፣ በአግባቡ ለትምህርት፣ ለጥናትና ምርምር ለማቅረብ፣ የቱሪዝም እንቅስቃሴን ለማስፋፋት፣ ታሪክን በባለቤቱ ሳይሸራረፍና ሳይዛባ ለማቅረብ፣ ወደፊት የሚደረጉ የታሪክና የቅርስ ምርምሮችን ለማገዝ፣ ቤተ ክርስቲያናችን ያለፈውን ትውልድ ታሪክ በመጠበቅ፣ የአሁኑን በማስተማር፣ የወደፊቱን ትውልድ መንገድ በማመቻቸት ልትፈጽመው የሚገባትን ኃላፊነት እየተወጣች መሆኑን በተጨባጭ መረጃ የሚያሳይ ምስክር ስለሆነ ወደፊት ለሚደረጉት የሥርጭት አንቅስቃሴዎችና በቀጣይነት ለሚሠሩት ሌሎች የዚሁ ተከታታይ ዶክምንተሪ ፊልሞ ሁላችንም የበኩላችንን እንወጣ እላለሁ አመሰግናለሁ፡፡

ዳንኤል ሰይፈሚካኤል ፈለቀ (መ/ር)
ከመንበረ ፓትርያርክ ጠ/ጽ/ቤት
አዲስ አበባ፣ የካቲት 5 ቀን 2007 ዓ/ም

የፎንት ልክ መቀየሪያ