Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት አክሱም ጽዮን የሁለቱ ኪዳናት ማኅደር" በሚል ርእስ የተዘጋጀውን ዶክምንተሪ ፊልም መረቁ


በዓይነቱ፣ በይዘቱ፣ እና በአመሠራረቱ በሀገራችን ለየት የሚለውና የመጀመሪያ የሆነውን የርዕሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር ግንባታ በሰፊው ለማስተዋወቅ እና ከሚመለከታቸው አካላት በሙሉ የሐሳብ፣ የሙያ፣ የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ለማግኘት ‹‹አክሱም ጽዮን የሁለቱ ኪዳናት ማኅደር" በሚል ርእስ የተዘጋጀውን ታሪካዊ ዶክመንተሪ ፊልም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያ ሓላፊዎች፣ የቅርስና ጥናት ባለሥልጣን ተወካዮች፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ምሁራን፣ የርዕሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ተወካዮች፣ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፣ ምክትል ሊቃነ መናባርት፣ እና አጥቢያው ልዩ ልዩ ሃላፋችና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በተገኙበት በጠቅላይ ቤተ ክህነት ስብከተ ወንጌል አዳራሽ የካቲት 5 ቀን 2007 ዓ.ም. ተመረቀ፡፡

አክሱም ከጥንት ጀምሮ ጥንታዊት የአፍሪካ የሥልጣኔ፣ የእምነትና የመንግሥት መናኸሪያ መሆኗ፣ አክሱም ቅድመ ልደተ ክርስቶስ ጀምሮ ለብዙ ሽ ዓመታት የሀገራችን የብሉይ ኪዳን በኋላ ደግሞ ሐዲስ ኪዳን ብሥራት የተሰማባት፣ ሥርዓተ መንግሥት ከሥርዓተ አምልኮት ጋር የተከናወነባት፣ ሥነ ጥበብ ከማኅበራዊ ዕድገት ጋር አብሮ የኖረባት፣ የንግድ፣ ሉዓላዊ የመንግሥት አስተዳደር፣ ዓለም አቀፍ ግንኙነት፣ የተከናወነባት፣ ከኢትዮጵያውያን አልፎ የአፍሪካውን ሁሉ መኩሪያ ስትሆን፡፡ እነዚህ ዘመን ተሸጋሪ አኩሪ ታሪኮች ለመጠበቅ፣ ለማጥናት፣ ለማስተዋወቅ፣ ለማስተማር፣ በሕዝቦች መካከል የርስ በርስ መተዋወቅና መቀራረብ እንዲኖር፣ ለሥነ ጥበብና ለባህል ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዲኖረው ተደርጎ የታቀደውን ሙዚየም ቀደም ሲል በአምስተኛው ፓትርያርክ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ቀዳማዊ አቅራቢነት በቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ ግናባታው የተጀመረ ሲሆን ሙዚየሙ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን በሀገራችን ሁለንተናዊ የእምነትና የሥልጣኔ ታሪክ የነበራትን ማዕከላዊ አስተዋጽኦና በአክሱም ያሉትን በራካታ ተንቀሳቃሽና የማይንቀሳቀሱ ቅርሶች በመጠበቅ የሚኖረውን አገልግሎት በመረዳት ግንባታው ቀጥሎ አሁን የደረሰበት ደረጃ ላይ መገኘቱ በምረቃው ዕለት የኮሚቴው ሥራ አስፈጻሚ ሰብሳቢ ቀሲስ ሰሎሞን በቀለ አስታውቀዋል፡፡

በመቀጠልም የዶክምነተሪ ፊልሙ ጥናታዊ ጽሑፍና የትረካ ጽሑፍ አዘጋጅ መ/ር ዳንኤል ሰይፈሚካኤል ስለ ዶክምንተሪ ፊልም ዝግጅትና የአሠራር ሂደት፣ በውስጡ ስለአካተተቻው ይዘቶችና ዓላማ አጠቃላይ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ መ/ር ዳንኤል በመግለጫቸው በዶክምነተሪ ፊልም ሥራ ላይ የታሪክ ምርምርና ጥናታዊ ጽሑፍ ዝግጅት፣ የቪዲዮ ቀረጻ፣ የዶክምንተሪ ፊልም ጽሑፍ ዝግጅት፣ የእርማት፣ የድምጽ ትረካና ቀረጻ፣ የፊልም ቅንብር፣ የክትትልና ዳይሬክቲንግ ባለሙየዎችን፣ ሊቃውንትንና አባቶችን ተካተቱ ሲሆን አስተያየት በመስጠትና መረጃ በማሰባሰብም በርካታ ባለሙያዎች ያካተተ እንደነበር ገልጸዋል፡፡

ከመግለጫው በመቀጠልም የዶክምንተሪ ፊልም በቅዱስነታቸው በይፋ የተመረቀ ሲሆን ከፊልሙ የተወሰነው ክፍል ለዕይታ ቀርቧል፡፡ የሙዚየሙ ሥራ አሁን ለደረሰበት ደረጃ እንዲበቃ አስተዋጽኦ ያደረጉ በርካታ ሰዎች በክቡር ንቡረ ዕድ ኤልያስ አብርሃ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጸሐፊ አቅራቢነት የማበረታቻ ምስክር ወረቀት ከቅዱስነታቸው ዕጅ ተቀብለዋል፡፡

በመጨረሻም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በሰጡት ቃለ ምእዳን የሙዚየሙ ግንባታ ያለውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ "እስመ አብ ዘወሃበነ እግዚአብሔር መንፈስ ፍርሐት አላ ወሃበነ መንፈሰ ጥብዓት" እግዚአብሔር የፍርሐት መንፈስ አልሰ0ንም አላሳደረብንም የጥብዓት መንፈስ ሰጠን እንጂ በሚል መነሻ የእናት ስም ጽዮን ቤተ መዘክር የመላ ኢትዮጵያን ኩራትና የታማኝነትን፣ የማንነትን መገለጫ ነው፡፡ ዘመን የማይሽረው ልዩ ልዩ ታላላቅ የብራና መጻሕፍት በአግባቡ የሚጠበቁበት ነው፡፡

ቅርስታችን ለታላቅነታችን ለደደሚነቶችን ምስክሮች ናቸው፡፡ ለቅርሶቻችን ሕልውና መጠበቅ ቀናተኞች ሆነን መነሳት አለብን፡፡ የሕዳሴው ግድብ ጀምረን እንጨርሰዋለን በማለት ሕዝባችን እየተረባረበ ነው፡፡ እንዲሁም ማሕበረ ምዕመናንና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን የተጀመረው የአኲሱም ቤተ መዘክርና ሙዝየም በአንድ መንፈስ በአንድ ሐሳብ ሕዝብን በማስተባበር መጨረስ አለብን፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ ኃይል መንፈሳዊ ጥበብ መንፈሳዊ ጥብዓት አለና በማለት መመሪያና ቃለበረከት ሰጥቷል፡፡ መርሐ ግብሩም በጸሎት ተፈጽሞአል፡፡

የፎንት ልክ መቀየሪያ