Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ

አሜን!!

 • የተከበሩ አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የኤፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር

 • የተከበራችሁ የሃይማኖት አባቶች

 • ክቡራንና ክቡራት

 • የተወዳደችሁ የኢትዮጵያ ሕዝቦች

ሚያዝያ 11 ቀን 2007 ዓ/ም ራሱን አይ ኤስ በማለት የሚጠራው ሰብዓዊ ርኅራኄ የሌለው አሸባሪ ቡድን በወገኖቻችን ላይ ያደረሰውን አሰቃቂ የወንጀል ድርጊት ከሰማንበት ቀንና ሰዓት ጀምሮ በአምላካችን ዘንድ የወገኖቻችን ደም በከንቱ እንዳይቀር ልብን በሚሰብር ሐዘን በጸሎት በማሰብ ላይ እንገኛለን፡፡

ይህ በሰብአዊ ፍጡር ይፈጸማል ተብሎ የማይታሰብ ድርጊት አሳሳቢና ፍጹም ጭካኔ የተመላው በመሆኑ ከሐዘናችንና ሰማዕታቱን በጸሎት ከማሰብ በተጨማሪ ወጣቶቹ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አማኞች መሆናቸውን ስለተረዳን ስለጌታችን ስምና ስለቀናች ሃይማኖት፣ ስለ እግዚአብሔርም ፍቅር ዐላውያን በቅጣት የሚያሰቃዩትን ክርስቲያናዊ ቸል አትበሉ ተብሎ በዲድስቅልያ በተደነገገው ቀኖና መሠረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በተደጋጋሚ ልዩ ልዩ መግለጫዎች በማወጣት፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልታደርግ የሚገባትን ሃይማኖታዊና ቀኖናዊ ሥርዓት በማከናወን ላይ ትገኛለች፡፡

Picture 109 Picture 119 Picture 122 Picture 150 Picture 155

በሁሉም ዘንድ እንደሚታወቀው የሁሉም ሃይማኖቶች ተልእኮ ሰውን ማዳን እንጂ ሰውን መግደል እንዳይደለ ቢታመንም ንጹሐን ዜጎችን በሃይማኖት ምክንያት በአሰቃቂ ግድያ የመግደል ወንጀል በዓለማችን መታየት ከጀመረ ሰነባብቶአል፡፡ ኢትዮያውያን ወገኖቻችንም በተለያየ ጊዜና በተለያየ አካባቢ የዚህ ዓይነቱ ግድያ ሰለባ መሆናቸው አልቀረም፡፡

ከዚህ አንጻር በዚህ ሰሙን በሊቢያና በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አማኞች በሆኑት ልጆቻችን ላይ የተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ ከምንም ጊዜ በላይ ቤተ ክርስቲያናችንን፣ ሀገራችንንና ሕዝባችንን ያሳዘነና ያሳሰበ ጉዳይ ሆኖ ተገኝቶአል፡፡

የተፈጸመው አሰቃቂ ድርጊት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ ብቻ ሳይሆን በሁሉም የዓለም ሃይማኖቶች ላይ የተቃጣ የወንጀል ተግባር መሆኑን በማመን መላው የሀገራችን ሕዝቦችና የሃይማኖት ተቅዋማት እንደዚሁም መላው የዓለም መንግሥታት ይህን ድርጊት በጽኑ መቃወምና ማውገዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያናችንም የተፈጸመውን ድርጊት ፈጽሞ ታወግዛለች ከመንግሥትና ከሕዝብ ጋር ተሰልፋም የሚጠበቅባትን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን ታረጋግጣለች፡፡

ቀደም ሲል በመግለጫችን እንደተነገረው የአሸባሪዎች የጥፋት እልቂት ሃይማኖትን፣ ቀለምን፣ ፆታንና አካባቢን ሳይለይ በአጠቃላይ በሰው ዘር ላይ የዘመተ የጥፋት ተልእኮ ስለሆነ ሁሉም የሃይማኖት መሪዎችና የፀረ ሽብር ተቅዋማት ለዓለማችን ሰላም መረጋገጥና ለሰው ልጆች በሕይወት የመኖር መብት መከበር ተባብረው እንዲሠሩ ቤተ ክርስቲያናችን በአጽንኦት ትጠይቃለች፤

የኢትዮጵያ መንግሥት ከዓለም አቀፍ ማኅበረ ሰብና ከየሀገሩ መንግሥታት ጋር በመሆን የሚያካሂደውን የፀረ ሽብር እንቅስቃሴ አጠናክሮ በመቀጠል የዜጎቻችን ሕይወት በአሸባሪዎች እንዳይቀጠፍ ከእስከአሁኑ በበለጠ እንዲንቀሳቀስ፤ ሕዝቡም ከአሁን በፊት በበጎ ታሪካችን እንደሚታወቀው በሃይማኖትና በሌላው ሁሉ ሳንለያይ ጠብቀን ያቆየነውን በአንድነት፣ በፍቅርና በመቻቻል የመኖር ዕሴት አሁንም አጥብቀን በመያዝ የጋራ ጠላት የሆነውን ግብረ ሽብር በመመከት ራሱንና ሀገሩን ከአሸባሪዎች ነቅቶ እንዲጠብቅ ቤተ ክርስቲያናችን ታሳስባለች፤

የመዋች ቤተ ሰቦች የሆናችሁ ወገኖቻችን ሁሉ በዚህ ግፍ የተሞላበት ጭካኔ የተገደሉት ልጆቻችን በዚህ ዓለም የመኖር ተስፋቸው ባጭሩ ቢቀጭም ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተገፉ መንግሥተ ሰማያትን ይናጠቋታል ማለትም ይወርሱአታል ባለው አምላካዊ ቃል መሠረት እግዚብሔር ዕንባቸውን አብሶ በመንግሥቱ የሚቀበላቸው መሆኑን አውቃችሁ፣ ቤተ ክርስቲያንም ለሰማዕታቱ የአንድ ሳምንት የጸሎተ ፍትሐት ያወጀች መሆኑንና ሰማዕታቱን በሚገባቸው ክብር ለማክበር የሚገባትን ሥርዓት የምታከናውን መሆኑን ተረድታችሁ ልትጽናኑ ይገባችኋል፡፡

ከዚሁ ጋር ለማሳሰብ የምንወደው ጉዳይ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ በሕገ ወጥ መንገድ ከሀገር ከመውጣት፣ አስተማማኝ የሕይወትና የንብረት ዋስትና ወደሌለበት ሀገር ከመሄድ ተቆጥቦ በሀገሩ ሠርቶ ኑሮውን እንዲመራ ቤተ ክርስቲያን የምትመክር መሆኑን እናስገነዝባለን፤

ክቡራንና ክቡራት
የተወደዳችሁ የሀገራችን ሕዝቦች

ሞትን ለመጀመሪያ ጊዜ የቀመሰው አቤል የተገደለው በወንድሙ በቃየል እጅ ነበር፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ግን በአመጽና በክፋት ተመልቶ ወንድሙን አቤልን የገደለ ቃየልን ከነጥፋቱ እንዲሰወር አልፈቀደም፡፡ ይልቁንም ገዳዩን #ወንድምህ አቤል ወዴት ነው? አቤል ምን አደረገህ? የወንድምህ የአቤል የደሙ ድምጽ ከምድር ወደ እኔ ይጮሃልና ብሎ ጠይቆታል፡፡ (ዘፍ 4፡10)

ስለዚህ ዛሬም በግፍና በጭካኔ የተመሉ አሸባሪዎች ከፈጣሪን ጥያቄና ፍርድ ፈጽመው እንደማያመልጡ እናምናለን፡፡ ምክንያቱም ፈጣሪ የወንድሙን ደም ያፈሰሰውን ቃየልን የወንድምህን ደም ከእጅህ ለመቀበል አፍዋን በከፈተች በምድር ላይ አንተ የተረገምህ ነህ፣ በምድር ላይ ኮብላይና ተቅበዝባዥ ትሆናለህ በማለት በቃየል ላይ ፈርዷልና ነው፡፡ ይህ አምላካዊ ፍርድ ዛሬም ወንድሞቻቸው የሚሆኑ የንጹሐን ወጣቶችን ሕይወት ያለርኀራኄ የቀጠፉ አሸባሪዎች ከዚህ ሰማያዊና ምድራዊ ፍርድ እንደማያመልጡ እምነታችን የጸና ነው፡፡

ስለዚህ እኛም በዛሬው ዕለት በወገኖቻችን የደረሰውን አሰቃቂ ወንጀል ልባችንን ስለነካው አቤል ወዴት አለ ብሎ የተገደለውን እንደፈለገው ፈጣሪ ወንድሞቻችን ወዴት አሉ ብለነን ሁላችንም ከመኖሪያ ቤታችን ከሥራችን ወጥተን ይህንን አሰቃቂ የወንጀል ድርጊት ለመቃወምና ለማውገዝ ወደ አደባባይ መውጣታችን ሰውን በሚወድ በፈጣሪ ፊት የሚያስመሰግን ነው፡፡

ክቡራንና ክቡራት
የተወደዳችሁ የሀገራችን ሕዝቦች

ይህ በወገኖቻችን ላይ ደረሰውን አሰቃቂ የወንጀል ድርጊት ከሰው ልጅ ተፈጥሮአዊ ተግባር የወጣ ደረቅ ወንጀል ስለሆነ፣ ልንቃወምና ልንመክት የምንችለው በጥልቀትና በተረጋጋ መንፈስ በመሆን በመላው ዓለም ካሉ ከፀረ ሽብረ ግብር ኃይሎች ጋር በመተባበር ስለሆነ በትዕግስትና በጥበብ የሰው ልጅ ሉዓላዊ ክብር እንዳይጣስ በነፃነት ሊኖርባት በተሰጠችው ምድር የሕይወት ዋስትና እንዲኖረው ለማስቻል ሁሉም ነቅቶና ተግቶ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

ወስብሐት ለእግዚብሔር
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ሚያዝያ 13 ቀን 2007 ዓ.ም.
አዲስ አበባ፡ ኢትዮጵያ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
አሜን!!

 

የፎንት ልክ መቀየሪያ