Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የመካነ ሕይወት ጭህ ገዳምን ጐበኙ

በገዳሙ ለሚሠራው ሙዝየም ሥራ ማስጀመሪያ የ100 ሺህ ብር ድጋፍ አደረጉ


እስክንድር ገ/ክርስቶስ


የመካነ ሕይወት ጭህ ገዳም ከተገደመበት ከ1864-1988 ዓ.ም 124 ዓመት ውስጥ ስምንት አበምኔቶች ያገለገሉት ሲሆን በገዳሙ ከነበሩ መናንያን መካከል ሁለት ፓትርያርኰች፣ ሦስት ሊቃነ ጳጳሳት በርካታ ሊቃውንትን ያፈራው ገዳሙ በገዳሙ ታሪክ ውስጥ ከ50 ዓመት በላይ ያገለገሉት አባላት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስን ያስተማሩት መምህር አሥራተ ጽዮን መሆናቸው በገዳሙ የሙዚየም አሠሪ ኮሚቴ በቀረበው ሪፓርት ተገልጾአል፡፡

አሁን ገዳሙን በማስተዳደር ላይ ባሉት አበምኔት መምህር ዘመንፈስ ቅዱስ ረዳ ከ1988 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ገዳሙን በአበምኔትነት በማገልገል ላይ መሆናቸውን የገለጸው ሪፓርቱ በአገልግሎት ዘመናቸዉ ገዳሙ የ24 ሰዓት የመብራት አገልግሎት በነጻ እንዲያገኝ ያደረጉ ሲሆን የገዳሙንም አመታዊ በጀት ለማስከበር ከፍተኛ መስዋዕትነትን የከፈሉ አባት መሆናቸው ተገልጾአል፡፡

Picture 250 Picture 257 Picture 275 Picture 290 Picture 408 Picture 519 Picture 550 Picture 574 Picture 588 Picture 660

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ጭህ ገዳም በደረሱ ጊዜ ቁጥራቸው እጅግ በርካታ የሆኑ የአካባቢው ምዕመናን፣ የገዳሙ መናንያን ፣ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችና ካህናት እጅግ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

ቅዱስ ፓትርያርኩ በአቀባበል ሥነ ሥርዓቱ ላይ ለተገኙና ደማቅ አቀባበል ላደረጉላቸው ሁሉ ልባዊ ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን ከዛሬ 50 ዓመት በፊት በተለዩት በዚህ ታላቅ ገዳም ከብዙ አባቶች መካከል ተመርጠውና በሕይወት ቆይተው በመገኘታቸው ከፍተኛ ደስታ እንደተሠማቸው ገልጸዋል፡፡

የዛሬዋ እለት ሰንበት የተባረከችና የተቀደሰች እለተሰንበት ነች ያሉት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ከ50 ዓመት በኋላ በመንፈስ ቅዱስና በቤተክርስቲያን ትምህርት ወደተወለድኩበት ወደዚህ ታላቅ ገዳም በመምጣቴ አብረውኝ የመጡ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትንና አቀባበል ያደረጋችሁልኝን ሁሉ በልዑል እግዚብሔር ስም ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ብለዋል፡፡
በዚህ ታላቅ ገዳም ታላላቅ አባቶች አገልግለው አልፈዋል፡፡ ይህ ገዳም በርካታ ጥንታዊ ቅርሶችና ንዋየተ ቅድሳት የሚገኙበት እጅግ በጣም በርካታ መናንያንን ያፈራ አንጋአፋ ገዳም ነው ያሉት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ እነዚህን ጥንታዊያን ቅርሶች በሚገባና በክብር በመጠበቅ ለመጪው ትውልድና ለታሪክ ተመራማሪዎች በሚመጥን መልኩ በዘመናዊ እቃቤት (በሙዚም) በማስቀመጥ ለጥናትና ምርምር ምቹ ሁኔታን መፍጠርና ቅርሶቹንም በአስፈላጊው ሁኔታ ማስቀመጥ ተገቢ በመሆኑ እነሆ ዘመናዊ የቅርስ መጠበቂያ ሙዚየም የሚገነባበት ሁኔታ እየተመቻቸ ይገኛል ብለዋል፡፡ገዳማት የግብረገብ ፣ የትምህርት ፣ የሰላምና የፍቅር መገኛ ማዕከላት ናቸው ያሉት ቅዱስነታቸው ጥንታዊ ገዳማትን በአግባቡ ልንጠብቃቸውና ልንንከባከባቸው ይገባል፡፡ ተንቤን የታላላቅ ነገሥታትና የቀደምት ገዳማት መገኛ ታላቅ ሀገር በመሆኑ በተንቤን ያሉት ታሪካዊያን ገዳማት፣ ታሪካቸው ተጠብቆ መኖር ይችሉ ዘንድ የሚመለከተው ሁሉ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት አጥብቄ ለማሳሰብ እወዳለሁ ብለዋል፡፡

ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ መልዕክት ቀደም ብሎ አቶ ተወልደብርሃን የጣንቋ አበርገለ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ባደረጉት ንግግር ጭህ ፣ ቀቅማና መነወን የመሳሰሉ ጥንታዊያን ገዳማት ወደ ሚገኙበት ወረዳችን ቅዱስ አባታችንና ብፁአን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እንኳን በሰላም መጣችሁ ካሉ በኋላ ይህ ወረዳ በጣም በርካታ ጀግኖችና የሀገራችንን ታሪክ የለወጡ ሰዎችን ያፈራ አገር በመሆኑ በተለይም በፀረ ሕዝብና በፀረ እምነት የሚታወቀውን የደግር መንግሥትን ለመደምሰስ በተደረገው ጥረት ውስጥ ይህ ገዳም ካለው እየቀነሰና እየካፈለ ለትግሉ ውጤታማነት ታላቅ አስተዋጽኦ ያበረከተ ገዳም ነው ብለዋል፡፡

ቤተክርስቲያን ይህንን ታላቅ ገዳም የቱሪስት መዳረሻ ማዕከል ለማድረግ በምታደርገው ጥረት ሁሉ የወረዳ አስተዳዳሩና ሕዝባችን ከቤተክርስቲያኒቱ ጐን በመሠለፍ የታሰበው የሙዚየም ግንባታ እስከ ሚጠናቀቅ ድረስ የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማበርከት ዝግጁ ነው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው የሙዚየም አሠሪ ኮሚቴ ለሚያከናውኑው ሁሉን አቀፍ እንቅስቃሴ መንግሥት ከጐኑ የሚቆም መሆኑን በድጋሜ ለማረጋገጥ እወዳለሁ ብለዋል፡፡

በገዳሙ ለሚገነበው ዘመናዊ ሙዚየም ተግባራዊነት በብፁዕ ወቀዱስ ፓትርያርኩ መልካም ፈቃድ የተቋቋመው ኮሚቴ አስተባባሪ ከቅዱስ ፓትርያርኩ አባታዊ ንግግር ቀደም ብሎ ባቀረቡት ሪፓትርት እንደገለጹት የፌዴራል መንግሥት የቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን በገዳሙ የሚገኙ ጥንታዊያን ንዋየ ቅድሳትና ቅርሶች ፣ብዛትና ያሉበትን ሁኔታ በማስረዳት አዲስ ዘመናዊ ሙዝየም ለመገንባት በከፍተኛ ጥረት ላይ መሆናችንን ገልጸን ባቀረብነው የርዳታ ጥያቄ ለግንባታው ሥራ ማሰጀመሪያ 80,000.00ብር በመስጠቱ ለቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን ፈጣን ምላሽ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በበኩላቸው ኮሚቴው የታሰበውን የሙዚየም ግንባታ ተግባራዊ ለማድረግ በማድረግ ላይ ያለውን ጥረት አጽድቀው ለሙዚየሙ ግንባታ ሥራ ማስጀመሪያ የብር 100,000.00ድጋፍ አድርገዋል ቅዱስ ፓትርያርኩ ለጭህ ፣ ለቀቀማና ለመነወ ገዳማት ማጠናከሪያ ለእያንዳንዳቸው የ10 ሺህ ብር ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን በተንቤን ለሚገኙ 10 ጥንታዊያን ገዳማት ለእየንዳንዳቸዉ የ5 ሺህ ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡ ቅዱስ ፓርያርኩ በድምሩ 55,000.00ብር በተንቤን አካባቢ ለሚገኙ ጥንታዊያን ገዳማት ለግሰዋል፡፡በተጨማሪም ለገዳሙ አንድ የብር መስቀል ፣ ለገዳሙ አበምኔት አይከንና የእጅ መስቀል አበርክተዋል፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በመነወ ገዳም በመቀሌ ዩንበርሲቲ ለሚያስገነባው የራሱ አሉላ አባነጋ ሙዚየም ሥራ የመሠረት ድንጋይ ካኖሩ በኋላ ባደረጉት ንግግር መንግሥት ለሀገርና ለቤተክርስቲያን ጠቃሚ ሥራዎችን ሠርተው ያለፉ ታላላቅ ሰዎችን በማሰብ ይህን የመሠለ ኘሮጀክት ቀርጾ ተግባራዊ ለማድረግ መንቀሳቀሱ የሚያስመሰግንና ለታሪክ ተመራማሪዎችና ለመጪው ትውልድ የቀደምት አባቶቹን ታሪክ የበለጠ እንዲያውቅ እድል የሚፈጥር በመሆኑ የመቀሌ ዩንቨርሲቲ ምስጋና ይገባልዋ ብለዋል፡፡ ቅዱስ ፓትርያርኩ በመነወ የነበረውን ፕሮግራም ካጠናቀቁ በኋላ በእንዳ ማርያም ቆራር ገዳም ለተሰበሰቡ ቁጥራቸው እጅግ በጣም በርካታ ሕዝበ ክርስቲያን ትምህርትና ቡራኬ ሰጥተዋል፡፡ ቀደም ሲልም ቅዱስ ፓትርያርኩ ከመቀሌ ወደ ጭህ በተጓዙ ጊዜ በሀገረ ሰላም ከተማ እጅግ በጣም ደማቅ አቀባበል ተደርጐላቸዋል፡፡ በሀገረ ሰላም ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ለተሰበሰበው እጅግ በጣም ብዙ ሕዝበ ክርስቲያንም ሰፊ ትምህርትና ቡራኬ ሰጥተዋል፡፡ የደቡብ ምሥራቅ ትግራይ ሀገረ ስብከትም ለቅዱስ ፓትርያርኩ የብር መስቀል ሸልማት አበርክቷል፡፡

ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሬዎስ የደቡብ፣ የደቡብ ምሥራቅና የምሥራቅ ትግራይ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ሀገረ ሰላም ከተማ በደረሱ ጊዜ ለቁጥር ከሚያተክት ሕዝብ ጋር አቀባበል ካደረጉላቸውና በሀገረ ሰላም ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲየን ለተሰበሰበው ሕዝበክርስትያን በሰጡት ሰፊ ትምህርት ቅዱስ ፓትርያርኩንና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን እንዲሁም አብረዋቸው በሀገረ ሰላም የተገኙ የቅዱስነታቸውን ተከታዮች በሙሉ እንኳን ደህና መጣችሁ ካሉ በኋላ በደጋ ተንቤን ወረዳ ከ17 በላይ ጥንታዊያን ገዳማት እንደሚገኙ፣ሀገሩ የእነ አፄ ዮሐንስ፣የእነ አፄቴዎድሮስ፣ የእነ አፄ የማነ ክርስቶስና የእነ ራስ አሉላ መገኛ ሀገር በመሆኑ ጥንታዊና ታሪካዊ ሀገር ነው ብለዋል፡፡

የደጋ ተንቤን ሕዝብ ለሃይማኖቱ ቀናሂ፣ጀግና ፣ ሃይማኖቱን ጠባቂና ታሪኩን አክባሪ ሕዝብ ነው፡፡ያሉት ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሬዎስ ራስ አሉላ አባ ነጋ ለሃይማኖታቸውና ለሀገራቸው በጀግንነት ታሪክ የሰሩ አባት በመሆናቸው ይህን ታሪካቸውን ለመዘከር በመነወ ገዳም በመቀሌ ዩንቨርሲቲ ወጪ ታላቅ ሙዝየም የሚገነባ በመሆኑ በሚገነባው ሙዝየም ልጀቻችን እንዲጠቀሙበት ታሪካቸውን እንደያውቁበት ያወቁትን ታሪካቸውን የሚጠብቁበትና ተጨማሪ ታሪክ ሰፊዎች የሚሆኑበት እድልን የሚፈጥር በመሆኑ እንኳን ደሰ አላችሁ ብለዋል፡፡

ወ/ሮ አረጋሽ በየነ የደቡብ ምሥራቅ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በበኩላቸው ብፁዕ ወቅዱስ አባታችንና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ወደ ሀገረ ሰላም እንኳን በደህና መጣችሁ ካሉበኋላ የትግራይ ሕዝብ ያለምንም የሃይማኖት ልዩነት ፣ አሁን የተረጋገጠውን ሰላምና ልማት ለማምጣት ከባድ መሰዋዕትነትን የከፈለ ሕዝበ ነው ካሉ በኋላ እነ አፄ ዮሐንስንና ራስ አሉላ የተወለዱበት ሀገር ላይ በተለይም ደግሞ ራስ አሉላ በተወለዱበት በመነወ ገዳም የራስ አሉላን ሙዚየም ለማስገንባትየመቐሌ ዩንቨርሲቲ የመሠረት ድንጋይ በሚያስቀምጥበት ወቅት ቅዱስ አባታችንና ብፁዓን አባቶች በመምጣታችሁ ደስታችን እጥፍ ድርብ ይሆናልና እንኳን በደህና መጣችሁልን ብለዋል፡፡

የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ሐዋርያዊ ጉብኝትን ተከትሎ በተለይም በደቡብ ምሥራቅ ትግራይ ሀገረ ስብከት በሀገረ ሰላም ፣ በእንዳማረያም ቆራር ፣ በመነወና በጭህ ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የተደረገው ደማቅ አቀባበል በጉዞው ላይ የተሳተፉትን አባቶች ያስደነቀ ሲሆን የሀገረ ስብከቱን የማሰተባበር፣ የማደራጀትና በእውቀት የመምሪትን ጥበብ የሚያመላክት ሆኖ አጊንተነዋል፡፡

በዚህ ጉብኝት መላው የደጋተንቤን ሕዝብ በተለይም ደግሞ የመንግሥት ባለሥልጣናትን ያስገረመና ያስደመመው ክስተት ደገሞ ለወራት ዝናብ ጠፍቶ ሲያስጨንቅ በከረመበት ወቅት ቅዱስ ፓትርያርኩ እና ብፁዓን አባቶች በጭህ ገዳም ተገኝተው አሰፈላጊው መርሐ ግብር ከተከናወነ በኋላ የፕሮግራሙን መጠናቀቅ ይጠብቅ የነበረ በሚመሰል ሁኔታ ለ2 ሰዓታት ያክል የጣለው ከባድ ዝናብ የቅዱስነታቸውን ፍጹም ቅድስና ያመለከተ እንደሆነ በበዓሉ ላይ የታደሙ ሁሉ በደስታ ሲገልጹት ተደምጠዋል፡፡

በአጠቅላይ ቅዱስነታቸው በመቐለና በተንቤን ያደረጉት ሐዋርያዊ ጉዞ በደማቅ አቀባበል የታጀበ ጠቃሚ መልዕክቶችና ሰፊ ትምህርተ ወንጌል የተሰጠበትና የተሳካ ጉዞ ነበር፡፡

 

የፎንት ልክ መቀየሪያ