Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

የብፁዕ አቡነ መርሐ ክርስቶስ ጨለቆት የገጠር ኑሮ ማሻያ ፕሮጀክት በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ተመረቀ

እስክንድር ገ/ክርስቶስ

የኢትዮጵያ ኦርቶደክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን በብር 13,681,000 በደቡብ ምሥራቅ ትግራይ ዞን እንደርታ ወረዳ በጨለቆት የገጠር ቀበሌ የሚኖሩ 5,750 ሰዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ልዩ ልዩ የልማት ፕሮጀክቶች በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ሰኔ 26 ቀን 2007 ዓ.ም አስመርቀ፡፡

Picture 032 Picture 043 Picture 055 Picture 142

ኮሚሽኑ ብሬድ ፎር ዘወርልድ ኢኢዲ ከተባለ የጀርመን ግበረ ሠናይ ድርጅት ጋር በመተባባበር በጨለቆት የገጠር ቀበሌዎች ባከናወናቸው ሥራዎች በ80 ሄክታር ላይ የተለያዩ የአፈርና የውሃ ጥበቃ ሥራዎችን ያከናወነ ሲሆን 45 የእረሻ መሬት ለሌላቸው ወጣቶች ሥልጠና በመስጠትና ከ105 በላይ ዘመናዊ የንብ ቀፎዎችና ተያያዥ ቁሳቁሶች ገዝቶ በመስጠት ወጣቶቹን ውጤታማ እንዳደረገ በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገልጾአል፡፡

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቀነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ለፕሮጀክቱ እውን መሆን ታላቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ተቋማት ከኰሚሸኑ ቅርጫፍ ማስተባበሪያ ቢሮ የተዘጋጀላቸውን ሽልማት ከሰጡ በኋላ ባደረጉት አባታዊ ንግግር በዛሬው እለት በዚህ ወረዳ በተደረገ አቀባበል ሥነ ሥርዓት የሙስሊም ወንድሞቻችን መታደማቸው በእጅጉ የሚያስደስት ነው፡፡ ይህ የእርስ በርስ ስምምነትና መፈቃቀርን የሚያመለከት በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠልና በቀጣዩ ትውልድም ይህ የመከባበርና የመቻቻል ተምሳሌት እንደ ባህል ሆኖ መቀጠል ይገባዋል ብለዋል፡፡

በልማትና ክርስቲያናዊ ተራጽኦ ኰሚሽን የተሰራው ሥራ የወረዳውን ሕዝብ ተጠቃሚ የሚያደርግ በመሆኑ ሕዝቡ በአግባቡ ሊጠብቀቸው ፣ ሊንከባከባቸውና ሊጠቀምባቸው ይገባል፡፡ ያሉት ቅዱስ ፓትርያርኩ የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኣ ኰሚሽን ይህን የመሰለ ገጠርን ተጠቃሚ ሊያደርግ የሚችል ፕሮጀክት በመቅረጽ ይህን አካባቢ ለመጠቀም ያደረገው እንቅስቃሴ የሚደነቅና የሚከበር ነው ብለዋል፡፡

ዛሬ የተገኘንበት ይህ ቦታ የታላላቅ ሰዎች መካነ መቃብር፣ የሊቃውንትና የቃለ እግዚአብሔር መፍለቂያ በጥቅሉ የቤተክርስቲያን መገልገያ የሆኑት የእግዚአብሔር ቃላት መገኛ ነው፡፡ ያሉት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በዚህ ቤተክርስቲያን የሚገኙ ጥንታዊያን ዘውዶች ፣ መስቀሎችና መጻሕፍት እስከ አሁን በክብር ተጠብቀው መቀመጣቸው በእጅጉ አስደሳች ስለሆነ ይህ ታሪካዊ ቤተክርስቲያን አሁን ያለውን ክብርና ሞገስ እንደጠበቀ ለትውልድ ለማስተላለፍ ሁላችንም ጠንክረን መሥራት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

ቅዱስነታቸው በመልዕክተቸው ማጠቃለያ ላይ ለወጣቱ ትውልድ ባስተላለፉት መልዕክት ወጣቱ ትውልድ ይህን የመሠለ የአባቶቹን ቀርስ በአግባቡ መጠበቅና የመንከባከብ፣ በሀገርና በወገኑ ፊት ጥሮ ግሮ ፣ ተፍጨረጭሮ በመሥራት ራሱን መለወጥና ቤተሰቡን መጠቀም የሚገባው መሆኑንን ተገንዝቦ የሕይወት ዋስትናና የመኖር ነጻነት በሌለው በሰው ሀገር በሕገ ወጥ መነገድ በመጓዝ ራሱንና ቤተሰቡን ብሎም ሀገሩን ለችግር ማጋለጥ የለበትም ብለዋል፡፡

በምረቃ ሥነ ሥረዓቱ ላይ የተገኙትና ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ አባታዊ ንግግር ቀደም በለው መልዕከታቸውን ያስተላለፉት የደቡብ ምሥራቅ ትግራይ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ወ/ሮ አረጋሽ በየነ ባስተላለፉት መልዕክት የኢትዮጵያ ኣርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሀገራችን በልማቱ ዘርፍ በምታከናውናቸው ተግባራት ሁሉ ግንባር ቀደም ተሰላፊ መሆኗን ጠቁመው በተለይም ለድህነት ቅነሣ መርሐ ግብሩ መሳካት ወሳኝ ሚና የሚጫወቱ ሥራወችን በገጠር ተግባራዊ በማድረግ የልማት አጋርነቷን አሳይታለች ብለዋል፡፡

ዛሬ የተመረቁ የልማት ሥራዎች በወረዳችን የሚገኙ በርካታ የሕበረተሰባችን ክፍሎችን ተጠቃሚ በማድረግ ረገድ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው የሉት ዋና አስተዳዳሪዋ በቀጣይም የሀገራችንን ሕዳሴ በማረጋገጥ ተግባር ዙሪያ አንደ እስከ ዛሬው ሁሉ ቤተክርስቲያኒቱ ከመንግሥት ጐን እንደምትቆም አልጠራጠርም ብለዋል፡፡

ከዞኑ የቤተክርስቲያኒቱ መዋቅር /ከሀገረ ስብከቱ/ ጋር እጅና ጓንት በመሆን ሥራቸውን በማከናወን ላይ መሆናቸውን የተናገሩት ወ/ሮ አረጋሽ በተለይም ባህላዊና ጐጂ አስተሳሰቦችን ለማረም ጐጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለማስወገድና የገጠሩን ሕዝብ የምርት አቅም ለማሳደግ በሚደረጉ ጥረቶች ሁሉ ቤተክርስቲያን ሁሌም የሚጠበቅባትን በመፈጸም ላይ መሆኗን ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ወደ ዞናችን እንኳን በደህና መጣችሁ ያሉት ዋና አስተዳዳሪዋ በቅዱስነትዎ የሚመራው ከፍተኛ የቤተክርስቲያኒቱ አመራር አካላት በዚህ መገኘት ለአካባቢያችንና ለሀገራችን ሰላምና ልማት በጸሎተችሁ ዋጋ የምናገኝበት ስለሆነ ከፍተኛ ደሰታ የተስማኝ መሆኑን በዞን አስተዳዳራችንና በራሴ ስም ለመግለጽ እወዳለሁ በማለት ንግባራቸውን አጠናቀዋል፡፡

ክቡር ዶ/ር አግደው ረዴ የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ኰሚሽነር በበኩላቸው ባደረጉት ንግግር የአቡነ መረሐ ክርስቶስ ጨለቆት የገጠር ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት 13 ሚሊየን ብር በጀት የተመደበለት መሆኑን ገልጸው ሰፊ የመሰኖ ግንባታ ፣ ድልድይ ፣ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ፣ የመነገድ ሥራ፣ የወጣቶች ኝሮግራም የገቢ ማስገኛ ተቋምና የገበሬዎች ሁለገብ የሕበረት ሥራ ማበርን ለማጠናከር የተለያዩ ግንባታና የማንቀሳቀሻ ገንዘብ ልገሳ ተደርጓል በለዋል፡፡

ብፁዕ አቡነ መርሐ ክርስቶስ በሕይወት በነበሩበት ወቅት ይህ ሥራ እንዲሰራ ሚስ ሞኒካ ከተባሉ የጀረመን የርዳታ ባለሙያ ጋር ንግግር አድርገው እንደነበር ያስታወሱት ዶ/ር አግደው የርዳታ ባለሙያዋ ብፁዕነታቸው በሥጋ ከተለዩን በኋላ ጥያቄያቸውን የልማት ኰሚሽን አስታውሶ ከክልሉ ማሰተባበሪያ ጽ/ቤት ጋር በመሆን ፕሮጀክቱን አጥንቶ በማቅረብ አስፈላጊው ድጋፍና በጀት እንዲያዝ ማድረጉን ገልጸዋል፡፡

የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኰሚሽን ለብዙ ዘመናት በመንገድ ሥራ ፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ በጤናና በትምህርት አገልገሎት እንዲሁም ሕጻናትና ወጣቶችን በመንከባከብ በክልል ትግራይ ከ50 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ተግባራዊ ማድረጉን ያሰታወሱት ኰሚሽነሩ ሥራዎቹን በምንሠራበት ወቅት የትግራይ ክልላዊ መንግሥትና ሕዝብ እንዲሁም የክልሉ አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት አስፈላጊውን ትብብር ሁሉ ስላደረጉልን በኰሚሽኑ ስም ልባዊ ምሰጋናዬን አቀርባለሁ በማለት ንግግራቸውን አጠቃለዋል፡፡

በኰማሽኑ የክልል ትግራይ ማሰተባበሪያ ኃላፊ የሆኑት አቶ ዘሚካአል ቦጋለ በበኩላቸው ልማት ኰሚሽን በተጠናና ገጠሩን የትግራይ ሕዝብ ማዕከል ባደረገ መልኩ በርካታ የልማት ሥራወችን ሲሰራ መቆየቱን አስታውሰው በዚህ በዛሬው እለት በሚመረቀው የብፁዕ አቡነ መርሐ ክርስቶስ ጨለቆት የገጠር ኑሮ ማሻሻያ ኘሮጀክት ቀደም ሲል ከተገለጹት በተጨማሪ የሕብረትሰቡን የጤና ችግር ለመቀረፍ ለአንድ የጤና ጣቢያ የማዋላጃ አልጋዎች፣ የሕክምና መሣሪያዎችን ፣ የመጀመሪያ ርዳታ ቁሳቁሶች ተገዝተው ተሰጥተዋል ብለዋል፡፡

የኰሚሽኑ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በዚሁ ወረዳ የአርሶ አደሮችን የአገልግሎት የሕብረት ሥራ የግብይት አቅም ለማጐልበት አንድ የግብርና ምርትና ግብዐት ማከማቻ መጋዘን እና አንድ ሱቅ ገንብቶ ለማኀበራቱ አስረክቧል ያሉት የማስተባበሪያ ጽ/ቤቱ ኃላፊ በተጨማሪም ማኀበሩን ለማጠናከር የ150,000 ብር የመነሻ ካፒታል እገዛ ማድረጉን ጠቁመው የሕብረተሰቡን አቅም ለማጐልበትም ለ150 አርሶ አደሮች የተለያዩ የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎች ተሰጥቷል ብለዋል፡፡

ከመቀሌ ጨለቆት የመኪና መንገድ ባለመኖሩ የግብርና ምርታቸውን ወደ ገብየ በማውጣት ለመሸጥና ወደ ሕክምና ለመሐድ የተቸገሩትን የጨለቆት ነዋሪዎችን ጥያቄ ምላሸ ለመሰጠት ኰሚሸኑ ባደረገው ጥረት ከክልሉ መንግሥት የገጠር መንገድ ሥራ ቢሮ ጋር በመተባበር 2 ድልድዮችን እና 26 ፎርደሮችን፣ በመገንባት 10.2 ኪሎ ሜትር መንገድ ጠርጐ ጠጠር አልብሷል፡፡ ያሉት አቶ ዘሚካኤል የ1.55 ኪሎ ሜትር ዘመናዊ የመሰኖ ቦይ ሰርቶ 40 ኪ.ግ የተለያዩ የአትክልት ዘር እና 900 የፍሪፍሬ ችግኞችን በመሰጠት በርካታ አርሶ አደሮችን የመሰኖ ተጠቃሚ አድረጓል ብለዋል፡፡

በአጠቃላይ ኰሚሽኑ በአሁኑ ወቅት በትግራይ ክልል 51,126,173 ብር በመመደብ የልማት ሥራዎችን እያከናወነ ሲሆን በዓለፉት ዓመታት በክልሉ በብር 400 ሚሊየን ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክልሉ የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ካሚሽን ማስተባበሪያ ቢሮ ኃላፊ በሪፓርታቸው ገልጸዋል፡፡

የፎንት ልክ መቀየሪያ