Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ የአርመን ቂልቅያ ካቶሊኮስ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ አራም ቀዳማዊ ባደረጉላቸው ግብዣ መሠረት ሊባኖስን ጎበኙ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በአርመን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የመንበረ ቂልቅያ ካቶሊኮስ የአርመን ሰማዕታትን መቶኛ ዓመት አከባበርን ምክንያት በማድረግና በሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት መካከል ያለውን ወዳጅነት ለማጠናከር ይቻል ዘንድ ባደረጉላቸው ይፋዊ ጥሪ መሠረት በቤይሩት- ሊባኖስ ሐዋርያዊ ጉብኝት አደርገዋል፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በሊባኖስ በነበራቸው ቆይታ የአርመን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ባዘጋጀችው ዓለም አቀፍና የተለያዩ መንፈሳዊ ሥርዓቶች ላይ የተሳተፉ ሲሆን የሁለቱም ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት የቆየ ግኑኝነት መሠረት በማድረግ ታሪካዊ ንግግር አድርገዋል፡፡

Picture 021 Picture 035 Picture 078 Picture 118 Picture 199 Picture 217 Picture 286 Picture 386 Picture 396 Picture 422 Picture 428 Picture 429 Picture 551 Picture 552 Picture 570 Picture 655 Picture 659 Picture 663 Picture 693 Picture 703 Picture 726

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በንግግራቸው የኢትዮጵያና የአርመን ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት በማኅበረሰባዊ ትስስር ላይ የተመሠረተ ጥንታዊ፣ ታሪካዊ፣ ሃይማኖታዊና ሀገራዊ የሆነ መልካም ግንኙነት ያላቸው መሆኑን በመግለጽ የአሁኑ ትውልድም ይህንኑ የቆየ መንፈሳዊና ማኅበራዊ ግኑኝነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የበኩሉነ አስተዋጽኦ በማድረግ እንዲተጋ አሳስበዋል፡፡

በዓሉን አስመልክተው ባስተላለፉት መልእክትም፡- “ከዛሬ መቶ ዓመት በፊት ስለ ሃይማኖታቸው ሰማዕትነት የተቀበሉት አርመኖችን ስናስብም በወቅቱ የተፈጸመውን ድርጊት ያስታወሱ አሁን ለመበቀልና ጥላቻን ለማስፋፋት ሳይሆን ሰማዕታቱን በክብር በመዘከር ተመሳሳይ እልቂት እንዳይፈጸም፤ ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ሕይወት የሚገባውን ክብር እንዲሰጠውና ከፍተኛ ጥበቃ እንዲደረግለት ለማሳሰብ ነው” በማለት ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም በቅርቡ በሊቢያ የሜድትራንያን ባህር ዳርቻ በኢትዮጵያውንና በግብፃውያን ክርስቲያኖች ላይ የተፈጸመው አሰቃቂ ተግባር የዚህ ማሳያ ስለሆነ ከታሪክ መማርና ለሰው ልጅ ሕይወት ቅድሚያ መስጠት ይገባል ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ከዚሁ ይፋዊ ጉብኝታቸው ጎን ለጎን በሊባኖስ ቤይሩት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በመሠረቱት የደብረ ሲና ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል በመገኘት በዚያ ለሚገኙ ምዕመናን ትምህርተ ወንጌል፣ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ አስተላልፈዋል፡፡

በዚሁ ወቅትም በሊባኖስ ቤይሩት የኢትዮጵያ ኤምባሲ አምባሳደር እና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ በአካባቢው የሚገኙ የሃይማኖት መሪዎችና ምእመናን በተገኙበት ለሁለት ቀናት ያህል ልዩ ልዩ መንፈሳዊና ማኅበራዊ መልእክቶች ያስተላለፉ ሲሆን ወጣቶች በስደት በሚኖሩበት አካባቢ መልካም ስማቸውን በመጠበቅ፣ በምግባራቸው ታማኝ፣ በሥራቸውም ትጉሃን እንዲሆኑ በጥሩ ሥነ ምግባርና በሐቀኝነት የሚኖሩበትን ሀገር ሕግና ሥርዓት በደንብ በማወቅና በማክበር ራሳቸውን እንዲያስከብሩ በማለት አባታዊ ምክር አስተላልፈዋል፡፡ በተለይም የኢትዮጵያውያን መገለጫ የሆኑ ልዩ ዕሴቶቻችን መከባበርን፣ መተዛዘንን፣ መተሳብን.. ወዘተ አጥብቃችሁ በመያዝ ከራሳችሁ አልፋችሁ የሀገራችሁንም መልካም ገጽታ እንድታሳዩ፣ ወገኖቻችሁን እንድትጠቅሙ ምግባራችሁ የቀና፣ ባህላችሁን የምታከብሩ መሆን ይገባችኋል፤ ይህን ካደረጋችሁ የተከበራችሁና የተወደዳችሁ ትሆናላችሁ ብለዋል፡፡

“ብዙ ወገኖቻችን በሕገ ወጥ ስደት ምክንያት ለበርካታ ያልተጠበቁ አደጋዎች እየተጋለጡ፣ ሠርተው ያፈሩት ሀብትና ንብረት እየተቀሙ፣ ሕይወታቸውን እያጡ ስለሆነ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን መግታት ይገባል” ካሉ በኋላ “ከሀገር መውጣት ካለባቸውም በሕጋዊ መንገድ እንዲወጡ፣ አለበለዚያ በሀገራቸው ሠርተው እንዲለወጡ እንድትመክሩ እና የበኩላችሁን እንድትወጡ አደራየ የጸና ነው" ብለዋል፡፡

በሊባኖስ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ክብርት ወ/ሮ ሐሊማ በበኩላቸው በሊባኖስ የምትገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና ምእመናን አጠቃላይ ኮሚኒቲው ከኤምባሲው ጋር በመተባበር እጅግ የሚያስመሰግን ሥራ እየሠሩ እንደሆነ ገልጸው ብዛት ያላቸው ኢትዮጵያውያን በተለያየ መልኩ ድጋፍ ሲያስፈልጋቸው ወደ ቤተ ክርስቲያኑ በምንልክበት ጊዜ ያለ ምንም ልዩነት ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ሁሉ አቀፍ የሚያስፈልገውን በማድረግና በማስተባበር ወገኖቻችንን በማቀፍና በመደገፍ ተምሳሌታዊ ሥራ እየሠሩ ስለሚገኙ ቅዱስ አባታችን በተገኙበት የቤተ ክርስቲያንዋ አባቶችና ምእመናን ሁሉንም ማመስገን እወዳለሁ ካሉ በኋላ ለወደፊትም ይህንን ወገንን የማገዝ መንፈሳዊና ማኅበራዊ ድጋፋቸው ተጠናክሮ እንዲቀጥል አደራ በማለት አሳስበዋል፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በተጨማሪ የአኃት አብያተ ክርስቲያናት ፓትርያርኮችና የሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ልዩ ልዩ መሪዎችን ያነጋገሩ ሲሆን በአርመንና በኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት መካከል ያለው ግንኙነት ስለሚጠናከርበት ሁኔታ፣ ክብርት አምባሳደር፣ በቤይሩት የሚገኙት የቤተ ክርስቲያን ተወካዮች በተገኙበት ሰፊ ውይይት ካደረጉ በኋላ በቅዱስ ፓትርያርኩ የተመራውና በሊባኖስ-ቤይሩት ለ5 ቀናት የተደረገውን ይፋዊ ጉብኝት አጠናቀው ሐምሌ 14 ቀን 2007 ዓ.ም አዲስ አበባ ተመልሰዋል፡፡

የፎንት ልክ መቀየሪያ