Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አንዳንድ አድባራትና ገዳማት የመሬት፣ የሱቆችና የልዩ ልዩ ገቢ ማስገኛ ተቋማትን እንዲሁም በአንዳንድ አድባራት የሚደረጉ የመኪና ሽልማቶችን አስመልክቶ በቂ ጥናት እንዲደረግና ውጤቱ እንዲገለጽላቸው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፤ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም፤ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት እና ቋሚ ሲኖዶስ ባስተላለፉት መመሪያ መሠረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ጉባኤ ጥናቱን አዘጋጅተው የሚያቀርቡ 3 ከጠቅላይ ቤተ ክህነት፤ 2 ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት፤ ኮሚቴዎችን አቋቁሞ ሥራውን ጀመረ፡፡


የተቋቋመው ኮሚቴም የጥናቱ መሠረት ለቤተ ክርስቲያኒቱ የሚሰጠውን ጥቅም መነሻ በማድረግ ጥናቱን በተሳካ ሁኔታ ለማካሄድ ይረዳው ዘንድ በጥቅል ጥናቱ ሂደት ላይ ተደጋጋሚ ውይይትና ክርክር በማድረግ ቤተ ክርስቲያኒቱን ለመታደግ የሚያስችል ሥራ መስራትና ማቅረብ እንደሚገባው በማመን ግልጽ የጥናት ማስፈፀሚያ ዕቅድ እንዲዘጋጅ አድርጓል፡፡


የጥናቱ የማስፈጸሚያ ዕቅድ ምን ያህል አብያተ ክርስቲያናት በጥናቱ መካተት እንዳለባቸው ጥናቱን ለማካሄድ የሚከተለውን ስልት በጥናቱ ወቅት የሚያጋጥሙትን ፈተናዎችና መፍትሔዎቻቸውን በዝርዝር በማስቀመጥ ከማስፈጸሚያ ስልት (Action plan) ጋር በማዘጋጀት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ፤የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ በተገኙበት በማስፈጸሚያ ዕቅዱ ዙሪያ ውይይት በማድረግ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ዕቅዱ እንዲጸድቅ ካደረገ በኋላ ወደ ሥራ ገብቷል፡፡


በዚህ የማስፈጸሚያ ዕቅዱ ላይ ያጋጥማሉ ተብለው ከቀረቡ ችግሮች መካከል፤

 • የአጥኚ ቡድኑን ስም ማጥፋት
 • የአበልና በትራንስፖርት ስም መማለጃ መስጠት
 • በጥናቱና በጥናቱ ማጠቃለያ ወቅት ውጤቱን በፀጋ ከመቀበል ይልቅ ውዥንብርና የኰሚቴውን ስም የማጥፋት ሂደቶች በዋናነት በስፋት ሊካሄዱ እንደሚችሉ ተጠቅሷል፡፡

በውጤቱም በየአድባራቱ ለጥናት በተንቀሳቀሰበት ወቅት በውሎ አበልና በትራንስፖርት ስም ኮሚቴውን ለመደለል ተሞክሯል፡፡


የአጥኚ ቡድኑን አባላት በተናጠል በመወንጀል ሥራቸውን ለማጣጣል ተሞክሯል፡፡


ማስፈራራትና ዛቻም ደርሶበታል፡


ይሁንና አጥኚ ቡድኑ ይህ ቀድሞ እንደሚሆን ያወቀ በመሆኑ የእያንዳንዱ ደብር የጥናት ውጤት በየጊዜው ቅዱስ ፓትርያርኩ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጁና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት በማቅረብ ግልጽነት እንዲፈጠር ያደረገ ከመሆኑም በላይ መማለጃ የነዳጅና የትራንስፖርት አበል ለመስጠት የሞከሩ አድባራትን ስም ዝርዝር ለቅዱስ ፓትርያርኩ በማቅረብ ሥራው ነጻ በሆነ መልኩ እንዲካሄድ አድርጓል፡፡


አጥኚ ቡድኑ በእያንዳንዱ ደብር የተሠሩ ሥራዎችና ውጤታቸውን ከላይ በተገለፀው መልኩ ለፓትርያርኩ፣ ለጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጁና ለሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በማቅረብ ግልፅ አሠራር ከመከተል ባለፈ በጊዜያዊነት መፍትሔ በሰጠባቸው ከ5 በላይ ጥናቶች ላይም በኮሚቴው ሰብሳቢ እየተመራ ውይይቶችን በማድረግና የመፍትሔ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ በቤተ ክህነት በኩል አመራር እንዲሰጥበትና በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በኩል እንዲፈፀም አድርጓል፡፡


ከዚህ በተረፈም በየአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናቱ ችግሮች በሙሉ እንዲገለፁ በማድረግ የመፍትሔ አቅጣጫዎችንም አመላክቷል፡፡ በጥናቱ የታዩ ሠፋፊ ችግሮች በዘላቂነት ከቤተ ክርቲያኒቱ ይወገዱ ዘንድም የተተነተነ የሚሳካና ውጤት ሊያመጣ የሚችል የመፍትሔ ሀሳብ አስቀምጧል፡፡


ጥናቱን መነሻ በማድረግም ቤተ ክርስቲያኒቱ የመሬትና የገቢ ማስገኛ ተቋማቷን ሊያስተዳድር የሚችል የገቢ ማስገኛ ፓሊሲን ተቋማቱን በበላይነት የሚያስተዳድር አካል ማቋቋም እንደሚያስፈልግ በመግለጽ የሠለጠነ መፍትሔ አስቀምጧል፡፡
በዚህ መልኩ አግባብነት ባለው የጥናት ዝግጅት መርህ በ33 ገጽ ተቀምሮ የቀረበውን ጥናት በሚገባ የገመገመው የጠቅላይ ቤተ ክህነት አስተዳደር ጉባኤም ጥናቱን ሙሉ በሙሉ በመቀበል አጽድቆታል፡፡


በመሠረቱ የጠቅላይ ቤተ ክህነት አስተዳደር ጉባኤ የቀረበለትን ጥናት የመቀበል፤ በከፊል የመቀበልና ጭራሹኑ ያለመቀበል መብት ያለው መሆኑ ልብ ሊባል ይገባዋል፡፡ ይሁንና በዚህ በቀረበለት ጥናት ከልብ በመደሰት በሙሉ ድምጽ ተቀብሎ ካፀደቀ በኋላ ባለ 10 ነጥብ የውሳኔ ሃሳብ እንዲካተትበት በማድረግ ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ እንዲቀርብ አድርጓል፡፡


የጥናት ቡድኑን ሪፖርት ከውሳኔ ሃሳብ ጋር ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ያቀረበው የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት አስተዳደር ጉባኤ ቤተ ክርስቲያኒቱ ብልሹ አሠራርና ሙስናን ለማስወገድ በተግባር የተደገፈ ትግል ማድረግ የሚገባት ወቅት አሁን መሆኑን በመግለጽ የጥናቱን መነሻ ሀሳቦች መሠረት ያደረገ የፀረ ሙስና ትግል እንዲጀመርና በትግሉ ሂደት ግንባር ቀደም ተሰላፊ በመሆን ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር እንደሚሠራ በማረጋገጥ ሠነዱን ለቅዱስነታቸው አቅርቧል፡፡


ቅዱስ ፓትርያርኩም የዝርዝር ጥናቱን ሂደትና ውጤት በማድነቅ ቤተ ክርስቲያኒቱን ወደ ቀደመ ክብሯ ለመመለስ አስተዳደር ጉባኤውን የወሰነውን ውሳኔ ከልብ በመቀበል ለተግባራዊነቱም አስተዳደር ጉባኤው ከቅዱስነታቸው ጋር በጋራ መስራት እንደሚጠበቅበት ጠቁመው የጥናት ሰነዱን በአዎንታዊነት ተቀብለውታል፡፡


ይህ ከሆነና የጸረ ሙስና ትግሉ እንደሚቀጣጠል እርግጥ ከሆነ በኋላ የጥናቱ ሂደት ውጤትና ዓለማ በቅጡ ያልገባቸው በሌላ አገላለጽ አጥኚ ቡድኑ በጥናት ማስፈጸሚያ ስልቱ ላይ የጠቀሳቸው ችግር ፈጣሪዎች ብቅ ብቅ ማለት ጀምረዋል፡፡ እነዚህ ወገኖች የጥናት ሂደቱን በማጣጣል የአጥኚ ቡድን አባላቱን በተናጠል በማሞገስና በመወንጀል የጥናቱን ውጤት ለማደናቀፍ ደፋ ቀና ሲሉ በጥናቱ ወቅት የታዩ ችግሮች ሁሉ ባለቤቶች መሆናቸውን በማረጋገጥ ራሳቸውን ሲያጋልጡ በሌላ መልኩ ደግሞ የጸረ ሙስና ትግሉ ተግዳሮቶች መሆናቸውን እያሳዩ ይገኛሉ፡፡


በመሠረቱ እነዚህ የጥናት ውጤቱ ተቀዋሚዎች የጥናቱን ውጤት ተከትሎ ቤተ ክርስቲያን የምትወስደውን ርምጃ ሳያውቁ የጥናቱን ውጤት ለማጣጣል የሚሞክሩት ለማን በማሰብነው ለቤተ ክርስቲያኒቱ ወይስ ለግል ስብዕናቸው? የሚለውን በመመልከት ብቻ ማንነታቸውን ማየት ይቻላል፡፡


በዚህ ጥናት የታዩ ውጤቶች በአንዱ ደብር የታዩና በሌላው ያልታዩ መስሎ የሚሰማቸው ወገኖችም ተሳስተዋል ችግሩ በጥቂት አድባራት ቢገለጽም ድምር ውጤቱ የቤተ ክርስቲያኒቱ ነው፡ ስለሆነም በሁሉም ደረጃ የሚገኝ የጥፋቶቹን ውጤት ተከትሎ የሚታዩ የአሠራርና የአፈጻጸም ክፍተቶችን ለማስተካከል መሥራትና በውጤቱ ቤተ ክርስቲያን ወደ ጥንቱ ልዕልናዋ እንድትመለስ የሚደረገውን ጥናት ሁሉ የውዴታ ግዴታችን መሆኑን ማወቅ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ሲጠቃለልም ይህ ጥናት እና ውጤቱ በቤተ ክርስቲያን የሚታዩ ችግሮችን ይፋ ማድረጉ እና ችግሮቹን ለመፍታት የመፍትሔ ሀሳብ ማስቀመጡ ቤተ ክርስቲያኒቱ የመሬትና የገቢ ማስገኛ ተቋማት ፓሊሲ እንዲኖራት በማድረግ ዳግም ጥፋቶች እንዳይከሰቱና ሥራዎች ሁሉ ለሕግና በሥርዓት እንዲመሩ ለማድረግ የሚያስችል ጥናት በመሆኑ ጥናቱንና የጠቅላይ ቤተ ክህነት አስተዳደር ጉባኤ ያስተላለፋቸውን ውሰኔዎች በሙሉ ተግባራዊ እንዲሆኑ በማድረግ ሁሉም የቤተ ክርሰቲያኒቱ የሥራ ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት የጎላ ሚና መጫወት ይገባቸዋል፡፡ ይህን ውሳኔ ውጤታማ በማድረግ ሌሎች የቤተ ክርስቲያን ችግሮችን የሚቀርፉ ፖሊስዎችን ማዘጋጀት ይቻላልና፡፡


በሰንበት ት/ቤቶች ስር የሚገኙም ሆኑ የቤተ ክርስቲያኒቱ ተከታይ የሆኑ ወጣቶች ቤተ ክርስቲያኒቱ በራሱዋ ተነሳሽነት በራስዋ የመዋቅር ሠራተኞች አስጠንታ በውስጧ የሚታዩ የአሠራር የአደረጃጀትና የአፈፃፀም ችግሮችን በመለየት እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ የምታደርገው ጥረት ሁሉ ተገቢ እና ትክክለኛ መሆኑን በመገንዘብ ቤተ ክርስቲያኒቱ ለጀመረችው የፀረ ሙስና ትግል ሕግና ሥርዓትን በተከተለ አግባብ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ በማድረግ ቤተ ክርስቲያን በሥነ ምግባር የታነፀ ሙስናን የሚፀየፍና ከአድሎ የፀዳ ትውልድ የምትፈጥር እንጂ የሙሰኞች መገኛ መሆን እንደማይገባት በመረዳት በቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት የተጀመረውን ቤተ ክርስቲየኒቱን ወደ ጥንተ ማንነቷ የመመለስ ሥራ በማገዝ ረገድ ወጣቱ ትውልድ የበኩሉን ማበረከት ይጠበቅበታል፡፡


በሌላ በኩልም ወጣቱ በቤተ ክርሰቲያኒቱ የመሬት የሕንጻና የመሰል ገቢ ማሰገኛ ተቋማት ጥናትን ተከትሎ የተሠራውን ውጤታማ ሥራ ለማጣጣል አጥኚ ቡድኑን በተናጠልና በቡድን ለመወንጀልና ስም ለማጥፋት በመሞከር የጥናት ሥራውንና እርሱን ተከትሎ የቤተ ክርስቲያኒቱን ክብር ወደ ጥንተ ዘመኑ ለመመለስ ይቻል ዘንድ በቅዱስነታቸው በጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጁና በአስተዳደር ጉባኤ አባላቱ የተጀመረውን ጥረት ለማስተጓጎል የሚጥሩትን ሁሉ በማጋለጥና በመታገል የሚጠበቅበትን ሚና መጫወት ይገባዋል እንላለን፡፡


የቀጥላል.....................

 

"ወስብሐት ለእግዚአብሔር"

የፎንት ልክ መቀየሪያ