Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

ቅዱስ ፓትርያርኩ ጉባኤውን በፀሎት ከፍተዋል በዕለቱ የደብረ ፅጌ ቅ/ዑራኤል ሰ/ት/ቤት ወጣቶችም የመክፈቻ ወረብ አቅርበዋል፡፡

በ34ኛ ጠቅላላ የሰበካ ጉባኤ ስብሰባ ላይ ከሁሉም አኅጉረ ስብከት እና እንዲሁም ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የተጋበዙ እድምተኞች እንዲሁም ከመንግስታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች የተጋበዙ ክቡራን እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬ የእንኳን አደረሳችሁ ንግግር /መልእክት/ አስተላልፈዋል፡፡ ይህ የሰበካ ጉባኤ ስብሰባ የሚዘጋው ረቡዕ በ10/2/08 ዓ.ም ሲሆን በመጨረሻ ላይም የተሰብሳቢው የአቋም መግለጫ ይቀርባል፡፡
በዚህ ጉባኤ ላይ እንደ ከዚህ ቀደሙ የጋምቤላ ሀገረ ስብከት በጣም አስደሳች እና ልዩ የሆነ ሥራ ሠርቷል፡፡ 7 የክክሉ ከፍተኛ አመራ ባለሥልጣናትን ይዞ የመጣ ሲሆን እነዚህም ሰባቱ ወንጌልን በመማር ለጥምቀት የተዘጋጁ እንደሆነ ከሊቀ አእላፍ ቆሞስ አባ ተክለኃይማኖት የጋምቤላ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ አንደበት ልንረዳ ችለናል፡፡
ከጋምቤላ ክልል የመጡት
1. አቶ ጋርዌች ዊዩዋል የዋንቱዋ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ
2. አቶ ኮንግ ጆክ የማኩዌይ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ
3. አቶ ጆን ኬክ የዋንቱዋ ወረዳ ምክትል ዋና አስተዳዳሪ እና ሲቪል ሰርቪስና መልካም አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ
4. ወ/ሮ ጥበዎል ቲያንግ የላሬ ወረዳ ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ
5. አቶ ዋጅኔ ታሮ የማጆንግ ዞን ዋና አፈ ጉባኤ
6. አቶ አሙሉ ኡቻንግ በጋምቤላ ክልል መስተዳደር ምክር ቤት የዳያስፓራ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ
7. ዴንግ ሬስ የጋምቤላ ክልል የኢ/ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሲሆኑ ከዚህ ቀጥሎ የሚቀርቡትን ሪፖርቶች እና አንዳንድ ግርምት ሊጭሩ ይቸላሉ ብለን የምንገምታቸውን ነገሮችን በየሰዓቱ እየለቀቅን እናስነብባችኋለን፡፡

Picture 028 Picture 029 Picture 032 Picture 033 Picture 034 Picture 036 Picture 038 Picture 039 Picture 040 Picture 042 Picture 043 Picture 046 Picture 047 Picture 052 Picture 053 Picture 054 Picture 056 Picture 057 Picture 058

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

 • ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት
 • የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያው ኃላፊዎችና፣ የየድርጅቱ ሥራ አስኪያጆች፤
 • የየአህጉረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጆች
 • የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች
 • የካህናት፣ የምእመናንና የሰንበት ት/ቤት ተወካዮች
 • ክቡራን የዚህ ታላቅ ጉባኤ ተሳታፊዎች፤

ሁሉን ፈጥሮ የሚገዛ አምላካችን እግዚአብሔር ያለፈውን የ2007 ዓ.ም. የሥራ ዘመን በሰላም አስፈጽሞ በአዲሱ የ2008 ዓ.ም. ልንሠራው የሚገባንን ሥራ ለመሥራት አንድ ላይ ስለሰበሰበን ከሁሉ በፊት እርሱን እያመሰገን እንኳን ለሠላሣ ዐራተኛው ዓመታዊ መደበኛ አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በሰላም አደረሳችሁ እንላለን ፡፡

‹‹ቃለ እግዚብሔር ቃል ንጹሕ፣ የእግዚአብሔር ቃል ንጹሕ ቃል ነው›› (መዝ.11፡6)

ስለ ቃል አንሥተን ስንመረምር በፍጡራን ዘንድ የተለያዩ ቃላት እንዳሉ ከቅዱስ መጽሐፍ እንመለከታለን፡፡

ከነሱ መካከል የተወሱትን ለመጥቀስ የአዕዋፍን ቃል ‹‹ቃለ ማዕነቅ›› የውሀን ቃል ‹‹ቃለ ማያት ብዙኅ›› የደመናትን ቃል ‹‹ቃለ ወሀቡ ደመናት›› እየተባለ በቅዱስ መጽሐፍ ተጽፎአል ፡፡

ከምድራውያን ፍጡራን ሁሉ የተሻለ ቃለ ሰብእም እንዳለ ሁላችን የምናውቀው ጉዳይ ነው ፡፡

ነገር ግን ከዚህ ሁሉ የበለጠና ሕያው የሆነው ቃል የእግዚአብሔር ቃል ነው፤

ቃለ እግዚአብሔር በሰማይም ሆነ በምድር ያሉትን ማለትም የሚታዩትንና የማይታዩትን ሁሉ የፈጠረ፤

ኃይላተ ሰማያት ወምድር ጸንተው የሚኖሩበት፣

ሁሉን የሚያሳልፍ እንጂ እርሱ የማያልፍ ቃል ነው፤

የእግዚአብሔር ቃል እውነት እንጂ ሐሰት የማይቀላቀልበት፤

ኃይል እንጂ ድካም የማይፈራረቅበት በመሆኑ ንጹሕ ቃል ይባላል ፡፡

በዚህ ዓለምም ሆነ በወዲያኛው ዓለም የእግዚአብሔር ቃል ያልተናገረለት ፍጡር የለም፤

ይሁን እንጂ የእግዚአብሔር ቃል ከሁሉም በላይ አብዝቶ የተናገረላት ብትኖር ቤተ ክርስቲያን ብቻ ናት፣

በተለያየ ኅብረ ትንቢት ወአምሳል፣ በተለያየ ኊልቈ ሱባዔ ወቀመር ተጽፎ የሚገኘው ቃለ እግዚአብሔር የመጨረሻ መዳረሻው ቤተ ክርስቲያን ናት፤

ቤተ ክርስቲያን በጥንተ ፍጥረት ከመጀመሪያ ጀምሮ ነበረች፤ ከዓለም ፍጻሜ በኋላም የእግዚአብሔር መንግሥት ርእሰ ከተማ ሆና ማኅለቅት በሌለው ኊልቈ ዘመን ትቀጥላለች ፡፡

የእግዚአብሔር ቃል በብሉይ ኪዳን ስለ ቤተ ክርስቲያን ሲናገር

‹‹ይሰግዱ ለኪ ኵሎሙ ነገሥታተ ምድር ወይልሕሱ ፀበለ እግርኪ፤
ወትሰመይ ጽዮንሃ ሀገረ እግዚአብሔር፤
ወአስተጋብኦሙ ለውሉድኪ በውስቴትኪ፣
ያመጽኡ አምኃኪ እምርኁቅ ብሔር ወነገሥት ክብረ ሊባኖስ›› ብሎአል

ይህም ማለት ሁሉም የምድር ነገሥታት ላንቺ ይሰግዳሉ፤ የእግርሽንም ትቢያ ይልሳሉ፤

አንቺ የእግዚአብሔር ከተማ ጽዮን ነሽ ትባያለሽ፤

ልጆችሽን በአንቺ ውስጥ እሰበስባቸዋለሁ፤

መባውን፣ ቀዳምያቱን፣ ዐሥራቱን፣ በኵራቱን ከሩቅ አገር ይዘውልሽ ይመጣሉ፤

ነገሥታትም የሊባኖስን ክብር ያመጡልሻል ማለት ነው ፡፡ (ኢሳ. 49፡23)

በውስጧ ሆነው ሲያገለግሉ የሚኖሩ ልጆችዋም ‹‹ወይትወኃውሁ በአዝማን ዘአልቦ ኊልቁ፤ ፍጻሜ በሌላቸው አዝማነ መንግሥተ ሰማያት ሲመላለሱ ይኖራሉ›› ተብሎ በተነገረላቸው ቃል መሠረት ማኅለቅትና ፍጻሜ በሌለው ሕይወት በውስጧ ለዘላለሙ በደስታና በክብር ይኖራሉ ፤

እንግዲህ የእግዚአብሔር ቃል ይህን ሁሉ የተናገረው ለንጽሕትና ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ነው፤

ዛሬ በዚህ ዓቢይ ጉባዔ እግዚአብሔር የሰበሰበን ኃይል ‹‹ልጆችሽን በአንቺ ውስጥ እሰበስባቸዋለሁ›› ብሎ ከዛሬ ሁለት ሺሕ ሰባት መቶ ዓመታት በፊት የተናገረው የእግዚአብሔር ቃል ነው፤

ዛሬ መባውን፣ ቀዳምያቱን፣ በኵራቱን፣ ዐሥራቱን፤ ወይም በዘመናችን አነጋገር የሰበካ ጉባኤ አስተዋጽኦውን ከሩቅ አገር ይዘን ወደዚህ የመጣንበት ምክንያት ‹‹መባሽን ከሩቅ ይዘውልሽ ይመጣሉ›› የሚለው የእግዚአብሔር ቃል አስተምሮን ነው፤

ይህ ሕያውና የማይታበል ቃል ዛሬም በእኛ ውስጥ ሥራውን እየሠራ የሚገኝ በመሆኑና እኛም የቃሉ መሣሪያ ሆነን በመገኘታችን እጅግ፤ ደስ ሊለን ይገባል፡፡

ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት
ክቡራን የጉባኤው ተሳታፊዎች፤

በዓለም ውስጥ እጅግ ሀብታምና ኃያል የሆነ ማን ነው? ተብሎ ቢጠየቅ ትክክለኛ መልስ ሊሆን የሚችለው ቤተ ክርስቲያን ናት የሚለው መልስ ነው ፡፡

እርግጥ ነው፤ ቤተ ክርስቲያን ለሰዎች ኃይል ቀርቶ ለሰይጣንና ለሠራዊቱ እንኳ የማትበገር ኃያል ናት፤

በዚህም የእግዚአብሔር ቃል ‹‹ወአናቅጸ ሲኦል ኢይኄይልዋ፣ የሲኦል በረኞች ሰይጣንና ሠራዊቱ አያሸንፉአትም›› ብሎ ተናግሮላታል፤

ይህ ቃል የማይሸነፍ ኃያልና ንጹሕ የእግዚአብሔር ቃል ስለሆነ እነሆ ጠላቶቿ ሁሉ እየተሸነፉ እርስዋ ግን በድል አድራጊነት በዘመኑ ሁሉ ወደፊት እየገሠገሠች ከዘመናችን ደርሳለች፤ ወደፊትም በዚሁ ትቀጥላለች ፡፡

በሌላም በኩል ቤተ ክርስቲያን እጅግ የበለፀገች ባለሀብት መሆንዋን የእግዚአብሔር ቃል ሲናገር ‹‹ወይበውእ ኀቤኪ ብዕለ አሕዛብ፤ የሕዝቡና የአሕዛቡ ብዕል ወዳንቺ ይገባል ›› ይላል፡፡

ቤተ ክርስቲያን ይህ ቃል መሠረተ ሀብቷ ሆኖ አስገዳጅ ምድራዊ ኃይል ሳይኖር በቃሉ ቀስቃሽነት ብቻ ሕዝበ እግዚአብሔር የሆኑ ክርስቲያኖች ያላቸውን በደስታ፣ በፈቃደኝነትና በልግስና ዐውደ ምሕረቷ ድረስ እየመጡ ከከበረው የወርቅ ጌጥ ጀምሮ ስጦታውን በየዓይነቱ ሲያፈሱላት ይኖራሉ ፡፡

እንግዲህ ይህን ሁሉ በዓይናችን እየተመለከትን የምንገኝ እኛ ‹‹በአማን ኢይሔሱ ቃሎ ዘነበበ፣ በእውነት የተናገረውን ቃል አይዋሽም›› ብለን እርሱን ከማመስገን ጋር በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሆነን ልንፈጽመው የተሰጠንን ተልእኮ በደስታ፣ በፈቃደኝነት፣ በትጋትና በቅንነት ከመወጣት በቀር ሌላ ምን ሥራ ሊኖረን ይችላል ፤

ከዚህ ተነሥተን ስናይ እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያን የተናገረው ቃሉን እንዳላጠፈብን እናረጋግጣለን፡፡

በአንጻሩ ደግሞ እኛስ ቃላችንን አክብረናል፤ ወይስ አጥፈናል፤ የሚለውን መመርመር ከእኛ ይጠበቃል ፡፡

በአሁኑ ጊዜ ያለው የቤተ ክርስቲያናችን ገቢ በቂ ነው ባይባልም ቤተ ክርስቲያናችን በሰበካ ጉባኤ መደራጀት ስትጀምር ገቢዋ በመቶ ሺሕ ብር ደረጃ የነበረው ዛሬ ወደመቶ ሚሊዮኖች መድረሱ በሀገር አቀፍ ደረጃ አጠቃላይ ሲታይ ደግሞ ወደ ቢሊዮኖች መድረሱ ትልቅ ዕድገት ነው፤

ነገር ግን የምእመናን ዕድገትስ የት ነው ያለው የሚለውን አይተነዋል ወይ?፤

በዚህ በኩል ያለው ዕድገት የኋልዮሽ መሆኑ የማያውቅስ በመካከላችን ይኖር ይሆን?

ይህን ችግር በሚገባ ተገንዝበንና በቁጭት ተነሣሥተን ነገሩን ለመቀልበስ ያደረግነው ሙከራስ ይኖር ይሆን? ለዚህ ጥያቄአችን ከዚህ ጉባኤ መልስ እንፈልጋለን ፡፡

ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፤
ክቡራን የጉባኤው ተሳታፊዎች፤
መቼም ቢሆን ተልእኮአችን ሰማያዊ እንጂ ምድራዊ እንዳይደለ ሁላችንም እናውቃለን፤
ሰማያዊውና ታላቁን ተልእኮአችን በተገቢው ሁኔታ ለመወጣት ከኅሊና መቈርቈር ጀምሮ እስከ ኅልፈተ ሕይወት የሚዘልቅ የመሥዋዕትነት ዋጋ እንደሚጠይቅ ምንጊዜም አንዘነጋውም፤
ይህ መሥዋዕትነት ብዙዎቹ የሃይማኖት መስተጋድላን አባቶቻችን ያለፉበት ስለሆነ ለኛ ለቤተ ክርስቲያን ልጆች አዲስ አይሆንም ፡፡

ይሁንና እኛ ባለንበት በአሁኑ ዘመን ከፍተኛ መሥዋዕትነትን እየጠየቀን ያለው የደምና የሕይወት መሥዋዕትነት ሳይሆን ራስን የመካድ ወይም ያልተገባ ጥቅምን የመጸየፍና ኃላፊነትን በሚገባ ለመወጣት የመነሣሣት ጉዳይ ነው ፡፡

ቤተ ክርስቲያናችንን ከሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ጋር ስናነጻጽር በቊጥር እጅግ የላቀ የውሉደ ክህነት ብዝኅነት ያላት ስትሆን ‹‹ታላቁን የቅዱስ ወንጌል ተልእኮን›› ለውሉደ ሰብእ በማዳረስ ረገድ ያለን ውጤት ግን አናሳ ነው ማለት ይቻላል፡፡

ባህርን አቋርጦ፣ ድንበርን ተሻግሮ፣ እስከ ጽንፈ ምድር ተጉዞ፣ አስተምሮና ያላመነውን፣ አሳምኖ የቤተ ክርስቲያን ልጅ ማድረጉ ይቅርና በሀገር ውስጥ ያሉትን ወገኖች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አሰባስቦ ምእመናንን ማብዛት ብዙ ያልተሄደበት እንደሆነ ማወቅ አለብን ፡፡
ከሁሉም በላይ የሚያስቆጨው ደግሞ ትናንት ቤተ ክርስቲያን ‹‹ሀብተ ወልድና ስመ ክርስትና›› ሰጥታ በአባልነት የተቀበለቻቸው ልጆችዋ ዛሬ እናት ቤተ ክርስቲያናቸውን እየካዱ ወደሌላው ጎራ የመቀላቀሉ ጉዳይ እጅግ በጣም እየናረ መምጣቱን ነው ፡፡

የምእመናን ፍልሰት በየጊዜው እየጨመረ የመሄዱ መነሻ ምሥጢር ምንድን ነው? የሚለውን ጥያቄ ቤተ ክርስቲያናችን በአጽንዖት ልታጤነው ይገባል፤

በዚህ ዙሪያ የሚታየው ክፍተት ፈጣን ምላሽ በመስጠት መግቻ ካላበጀንለት ነገ ከባድ የሃይማኖትና የታሪክ ወቀሳ ማስከተሉ እንደማይቀር ልብ እንበል ፡፡

ለመሆኑ ምእመናን ከቤተ ክርስቲያናችን እየወጡ ወደ ሌላ ካምብ ለመግባት ለምን መረጡ?

የሚያስተምራቸው ካህን አጥተው ነው?

የቤተ ክርስቲያናችን ትምህርተ ሃይማኖት ክፍተት ኖሮት ነው?

የቤተ ክርስቲያናችን አስተዳደር የማያረካ ሆኖ ነው?

የካህን እጥረት ስላለ ነው?

ወይስ ሌሎች ከእኛ የተሻሉ ሆነው ስለተገኙ ነው፤?

የዚህ ሁሉ መልስ በእያንዳንዳችን ኅሊና ውስጥ ቁልጭ ብሎ ስለሚታወቅ የጥያቄው መልስ ለእናንተው ሰጥተናል፡፡

ይሁን እንጂ ይህ ዓቢይ ጉባዔ በሁለት ዓበይት የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንዲነጋገርባቸው ሳንጠቁም አናልፍም ይኸውም፡-

ምእመናንን የመጠበቅ ተልእኮ በሚገባ እየተወጣን አይደለምና ባዶአችንን ከመቅረታችን በፊት ለተደራጀና ለድንበር የለሽ ትምህርተ ወንጌል ብንነሣ፤

የአስተዳደር ሥራችን ለምእመናን ኅሊና እንቅፋት እየሆነ ነውና የሃይማኖቱን መርሕ ጠብቀን አስተዳደራችን የሕግ የበላይነትን ያረጋገጠ፣ ግልጽ፣ ተአማኒና ተጠያቂነትን ያሰፈነ የምእመናንን ልብ የሚያረካ፣ ምእመናን በቤተ ክርስቲያናቸው ኵራት እንዲሰማቸው የሚያስችል አሠራር ብናረጋግጥ ተጨባጭ ለውጥ ማስመዝገብ እንችላለን፤

 • ይህ ሲሆን ነው የሰበካ ጉባኤ ዓላማ ግቡን የሚመታው በእርግጠኝነት ለመናገር እንደ ጌታችን አስተምህሮ ሕጻናትን፣ ወጣቶችንና አዋቂዎችን በአግባቡ ጠብቃ የምትኖር ቤተ ክርስቲያን ለሃይማኖት ቅሰጣ አትጋለጥም ፡፡
  ስለሆነም የሰበካ ጉባኤ ዋና ምንጭ ምእመናን መሆናቸውን አውቀን በዚህ ዙሪያ በሰፊው እንሥራ፤ ቢቻል አሁን አለን ከምንለው የላቀ የምእመናን ቁጥር በበለጠ ለማሳደግ ከፍተኛ ጥረት ማድረግ፣ ባይሆን ደግሞ ባለበት ጠብቆ ለማቆየት በርትተን መሥራት ይጠበቅብናል ፡፡
 • በመጨረሻም

 • ይህ ዓለም አቀፋዊ የቤተ ክርስቲያን ጉባኤ ከየአቅጣጫው የሚቀርቡትን ሪፖርቶች በመገምገም፣ ለበጀት ዓመቱ ሥራችን መሠረት የሚሆኑ የዕቅድ አመላካች አስተያየቶችና ሐሳቦችን በማስቀመጥ፣ እንደዚሁም የሀገራችንን የሕዳሴ ጉዞ በተያዘለት መርሐ ግብር መሠረት ግቡን እንዲመታ ሕዝቡን ለማነሣሣት ቃል በመግባት የሚጠበቅበትን ሁሉ እንዲያደርግ መልእክታችንን በቤተ ክርስቲያን ስም እናስተላልፋለን ፡፡

እግዚአብሔር ጉባኤያችንን ይባርክ፣ ይቀድስ

 አሜን

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ጥቅምት 8 ቀን 2008 ዓ.ም.
አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

-      ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት

-      የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያው ኃላፊዎችና፣ የየድርጅቱ ሥራ አስኪያጆች፤

-      የየአህጉረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጆች

-      የገዳማትና  አድባራት አስተዳዳሪዎች

-      የካህናት፣ የምእመናንና የሰንበት ት/ቤት ተወካዮች

-      ክቡራን የዚህ ታላቅ ጉባኤ ተሳታፊዎች፤

ሁሉን ፈጥሮ የሚገዛ አምላካችን እግዚአብሔር ያለፈውን የ2007 ዓ.ም. የሥራ ዘመን በሰላም አስፈጽሞ በአዲሱ የ2008 ዓ.ም. ልንሠራው የሚገባንን ሥራ ለመሥራት አንድ ላይ ስለሰበሰበን ከሁሉ በፊት እርሱን እያመሰገን እንኳን ለሠላሣ ዐራተኛው ዓመታዊ መደበኛ አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በሰላም አደረሳችሁ እንላለን ፡፡

‹‹ቃለ እግዚብሔር ቃል ንጹሕ፣ የእግዚአብሔር ቃል ንጹሕ ቃል ነው›› (መዝ.11፡6)

ስለ ቃል አንሥተን ስንመረምር በፍጡራን ዘንድ የተለያዩ ቃላት እንዳሉ ከቅዱስ መጽሐፍ እንመለከታለን፡፡

ከነሱ መካከል የተወሱትን ለመጥቀስ የአዕዋፍን ቃል ‹‹ቃለ ማዕነቅ›› የውሀን ቃል ‹‹ቃለ ማያት ብዙኅ›› የደመናትን ቃል ‹‹ቃለ ወሀቡ ደመናት›› እየተባለ በቅዱስ መጽሐፍ ተጽፎአል ፡፡

ከምድራውያን ፍጡራን ሁሉ የተሻለ ቃለ ሰብእም እንዳለ ሁላችን የምናውቀው ጉዳይ ነው ፡፡

ነገር ግን ከዚህ ሁሉ የበለጠና ሕያው የሆነው ቃል የእግዚአብሔር ቃል ነው፤

ቃለ እግዚአብሔር በሰማይም ሆነ በምድር ያሉትን ማለትም የሚታዩትንና የማይታዩትን ሁሉ የፈጠረ፤

ኃይላተ ሰማያት ወምድር ጸንተው የሚኖሩበት፣

ሁሉን የሚያሳልፍ እንጂ እርሱ የማያልፍ ቃል ነው፤

የእግዚአብሔር ቃል እውነት እንጂ ሐሰት የማይቀላቀልበት፤

ኃይል እንጂ ድካም የማይፈራረቅበት በመሆኑ ንጹሕ ቃል ይባላል ፡፡

በዚህ ዓለምም ሆነ በወዲያኛው ዓለም የእግዚአብሔር ቃል ያልተናገረለት ፍጡር የለም፤

ይሁን እንጂ የእግዚአብሔር ቃል ከሁሉም በላይ አብዝቶ የተናገረላት ብትኖር ቤተ ክርስቲያን ብቻ ናት፣

በተለያየ ኅብረ ትንቢት ወአምሳል፣ በተለያየ ኊልቈ ሱባዔ ወቀመር ተጽፎ የሚገኘው ቃለ እግዚአብሔር የመጨረሻ መዳረሻው ቤተ ክርስቲያን ናት፤

ቤተ ክርስቲያን በጥንተ ፍጥረት ከመጀመሪያ ጀምሮ ነበረች፤ ከዓለም ፍጻሜ በኋላም የእግዚአብሔር መንግሥት ርእሰ ከተማ ሆና ማኅለቅት በሌለው ኊልቈ ዘመን ትቀጥላለች ፡፡

የእግዚአብሔር ቃል በብሉይ ኪዳን ስለ ቤተ ክርስቲያን ሲናገር

‹‹ይሰግዱ ለኪ ኵሎሙ ነገሥታተ ምድር ወይልሕሱ ፀበለ እግርኪ፤

ወትሰመይ ጽዮንሃ ሀገረ እግዚአብሔር፤

ወአስተጋብኦሙ ለውሉድኪ በውስቴትኪ፣

ያመጽኡ አምኃኪ እምርኁቅ ብሔር ወነገሥት ክብረ ሊባኖስ›› ብሎአል

ይህም ማለት ሁሉም የምድር ነገሥታት ላንቺ ይሰግዳሉ፤ የእግርሽንም ትቢያ ይልሳሉ፤

አንቺ የእግዚአብሔር ከተማ ጽዮን ነሽ ትባያለሽ፤

ልጆችሽን በአንቺ ውስጥ እሰበስባቸዋለሁ፤

መባውን፣ ቀዳምያቱን፣ ዐሥራቱን፣ በኵራቱን ከሩቅ አገር ይዘውልሽ ይመጣሉ፤

ነገሥታትም የሊባኖስን ክብር ያመጡልሻል ማለት ነው ፡፡ (ኢሳ. 49፡23)

በውስጧ ሆነው ሲያገለግሉ የሚኖሩ ልጆችዋም ‹‹ወይትወኃውሁ በአዝማን ዘአልቦ  ኊልቁ፤ ፍጻሜ በሌላቸው አዝማነ መንግሥተ ሰማያት ሲመላለሱ ይኖራሉ›› ተብሎ በተነገረላቸው ቃል መሠረት ማኅለቅትና ፍጻሜ በሌለው ሕይወት በውስጧ ለዘላለሙ በደስታና በክብር ይኖራሉ ፤

እንግዲህ የእግዚአብሔር ቃል ይህን ሁሉ የተናገረው ለንጽሕትና ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ነው፤

ዛሬ በዚህ ዓቢይ ጉባዔ እግዚአብሔር የሰበሰበን ኃይል ‹‹ልጆችሽን በአንቺ ውስጥ እሰበስባቸዋለሁ›› ብሎ ከዛሬ ሁለት ሺሕ ሰባት መቶ ዓመታት በፊት የተናገረው የእግዚአብሔር ቃል ነው፤

ዛሬ መባውን፣ ቀዳምያቱን፣ በኵራቱን፣ ዐሥራቱን፤ ወይም በዘመናችን አነጋገር የሰበካ ጉባኤ አስተዋጽኦውን ከሩቅ አገር ይዘን ወደዚህ የመጣንበት ምክንያት ‹‹መባሽን ከሩቅ ይዘውልሽ ይመጣሉ›› የሚለው የእግዚአብሔር ቃል አስተምሮን ነው፤

ይህ ሕያውና የማይታበል ቃል ዛሬም በእኛ ውስጥ ሥራውን እየሠራ የሚገኝ በመሆኑና እኛም የቃሉ መሣሪያ ሆነን በመገኘታችን እጅግ፤ ደስ ሊለን ይገባል፡፡

ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት

ክቡራን የጉባኤው ተሳታፊዎች፤

በዓለም ውስጥ እጅግ ሀብታምና ኃያል የሆነ ማን ነው? ተብሎ ቢጠየቅ ትክክለኛ መልስ ሊሆን የሚችለው ቤተ ክርስቲያን ናት የሚለው መልስ ነው ፡፡

እርግጥ ነው፤ ቤተ ክርስቲያን ለሰዎች ኃይል ቀርቶ ለሰይጣንና ለሠራዊቱ እንኳ የማትበገር ኃያል ናት፤

በዚህም የእግዚአብሔር ቃል ‹‹ወአናቅጸ ሲኦል ኢይኄይልዋ፣ የሲኦል በረኞች ሰይጣንና ሠራዊቱ አያሸንፉአትም›› ብሎ ተናግሮላታል፤

ይህ ቃል የማይሸነፍ ኃያልና ንጹሕ የእግዚአብሔር ቃል ስለሆነ እነሆ ጠላቶቿ ሁሉ እየተሸነፉ እርስዋ ግን በድል አድራጊነት በዘመኑ ሁሉ ወደፊት እየገሠገሠች ከዘመናችን ደርሳለች፤ ወደፊትም በዚሁ ትቀጥላለች ፡፡

በሌላም በኩል ቤተ ክርስቲያን እጅግ የበለፀገች ባለሀብት መሆንዋን የእግዚአብሔር ቃል ሲናገር ‹‹ወይበውእ ኀቤኪ ብዕለ አሕዛብ፤ የሕዝቡና የአሕዛቡ ብዕል ወዳንቺ ይገባል ›› ይላል፡፡

ቤተ ክርስቲያን ይህ ቃል መሠረተ ሀብቷ ሆኖ አስገዳጅ ምድራዊ ኃይል ሳይኖር በቃሉ ቀስቃሽነት ብቻ ሕዝበ እግዚአብሔር የሆኑ ክርስቲያኖች ያላቸውን በደስታ፣ በፈቃደኝነትና በልግስና ዐውደ ምሕረቷ ድረስ እየመጡ ከከበረው የወርቅ ጌጥ ጀምሮ ስጦታውን በየዓይነቱ ሲያፈሱላት ይኖራሉ ፡፡

እንግዲህ ይህን ሁሉ በዓይናችን እየተመለከትን የምንገኝ እኛ ‹‹በአማን ኢይሔሱ ቃሎ ዘነበበ፣ በእውነት የተናገረውን ቃል አይዋሽም›› ብለን እርሱን ከማመስገን ጋር በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሆነን ልንፈጽመው የተሰጠንን ተልእኮ በደስታ፣ በፈቃደኝነት፣ በትጋትና በቅንነት ከመወጣት በቀር ሌላ ምን ሥራ ሊኖረን ይችላል ፤

ከዚህ ተነሥተን ስናይ እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያን የተናገረው ቃሉን እንዳላጠፈብን እናረጋግጣለን፡፡

በአንጻሩ ደግሞ እኛስ ቃላችንን አክብረናል፤ ወይስ አጥፈናል፤ የሚለውን መመርመር ከእኛ ይጠበቃል ፡፡

በአሁኑ ጊዜ ያለው የቤተ ክርስቲያናችን ገቢ በቂ ነው ባይባልም ቤተ ክርስቲያናችን በሰበካ ጉባኤ መደራጀት ስትጀምር ገቢዋ በመቶ ሺሕ ብር ደረጃ የነበረው ዛሬ ወደመቶ ሚሊዮኖች መድረሱ በሀገር አቀፍ ደረጃ አጠቃላይ ሲታይ ደግሞ ወደ ቢሊዮኖች መድረሱ ትልቅ ዕድገት ነው፤

ነገር ግን የምእመናን ዕድገትስ የት ነው ያለው የሚለውን አይተነዋል ወይ?፤

በዚህ በኩል ያለው ዕድገት የኋልዮሽ መሆኑ የማያውቅስ በመካከላችን ይኖር ይሆን?

ይህን ችግር በሚገባ ተገንዝበንና በቁጭት ተነሣሥተን ነገሩን ለመቀልበስ ያደረግነው ሙከራስ ይኖር ይሆን? ለዚህ ጥያቄአችን ከዚህ ጉባኤ መልስ እንፈልጋለን ፡፡

ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፤

ክቡራን የጉባኤው ተሳታፊዎች፤

መቼም ቢሆን ተልእኮአችን ሰማያዊ እንጂ ምድራዊ እንዳይደለ ሁላችንም እናውቃለን፤

ሰማያዊውና ታላቁን ተልእኮአችን በተገቢው ሁኔታ ለመወጣት ከኅሊና መቈርቈር ጀምሮ እስከ ኅልፈተ ሕይወት የሚዘልቅ የመሥዋዕትነት ዋጋ እንደሚጠይቅ ምንጊዜም አንዘነጋውም፤

ይህ መሥዋዕትነት ብዙዎቹ የሃይማኖት መስተጋድላን አባቶቻችን ያለፉበት ስለሆነ ለኛ ለቤተ ክርስቲያን ልጆች አዲስ አይሆንም ፡፡

ይሁንና እኛ ባለንበት በአሁኑ ዘመን ከፍተኛ መሥዋዕትነትን እየጠየቀን ያለው የደምና የሕይወት መሥዋዕትነት ሳይሆን ራስን የመካድ ወይም ያልተገባ ጥቅምን የመጸየፍና ኃላፊነትን በሚገባ ለመወጣት የመነሣሣት ጉዳይ ነው ፡፡

ቤተ ክርስቲያናችንን ከሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ጋር ስናነጻጽር በቊጥር እጅግ የላቀ የውሉደ ክህነት ብዝኅነት ያላት ስትሆን ‹‹ታላቁን የቅዱስ ወንጌል ተልእኮን›› ለውሉደ ሰብእ በማዳረስ ረገድ ያለን ውጤት ግን አናሳ ነው ማለት ይቻላል፡፡

ባህርን አቋርጦ፣ ድንበርን ተሻግሮ፣ እስከ ጽንፈ ምድር ተጉዞ፣ አስተምሮና ያላመነውን፣ አሳምኖ የቤተ ክርስቲያን ልጅ ማድረጉ ይቅርና በሀገር ውስጥ ያሉትን ወገኖች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አሰባስቦ ምእመናንን ማብዛት ብዙ ያልተሄደበት እንደሆነ ማወቅ አለብን ፡፡

ከሁሉም በላይ የሚያስቆጨው ደግሞ ትናንት ቤተ ክርስቲያን ‹‹ሀብተ ወልድና ስመ ክርስትና›› ሰጥታ በአባልነት የተቀበለቻቸው ልጆችዋ ዛሬ እናት ቤተ ክርስቲያናቸውን እየካዱ ወደሌላው ጎራ የመቀላቀሉ ጉዳይ እጅግ በጣም እየናረ መምጣቱን ነው ፡፡

የምእመናን ፍልሰት በየጊዜው እየጨመረ የመሄዱ መነሻ ምሥጢር ምንድን ነው? የሚለውን ጥያቄ ቤተ ክርስቲያናችን በአጽንዖት ልታጤነው ይገባል፤

በዚህ ዙሪያ የሚታየው ክፍተት ፈጣን ምላሽ በመስጠት መግቻ ካላበጀንለት ነገ ከባድ የሃይማኖትና የታሪክ ወቀሳ ማስከተሉ እንደማይቀር ልብ እንበል ፡፡

ለመሆኑ ምእመናን ከቤተ ክርስቲያናችን እየወጡ ወደ ሌላ ካምብ ለመግባት ለምን መረጡ?

-      የሚያስተምራቸው ካህን አጥተው ነው?

-      የቤተ ክርስቲያናችን ትምህርተ ሃይማኖት ክፍተት ኖሮት ነው?

-      የቤተ ክርስቲያናችን አስተዳደር የማያረካ ሆኖ ነው?

-      የካህን እጥረት ስላለ ነው?

-      ወይስ ሌሎች ከእኛ የተሻሉ ሆነው ስለተገኙ ነው፤?

-     የዚህ ሁሉ መልስ በእያንዳንዳችን ኅሊና ውስጥ ቁልጭ ብሎ ስለሚታወቅ የጥያቄው መልስ ለእናንተው ሰጥተናል፡፡

ይሁን እንጂ ይህ ዓቢይ ጉባዔ በሁለት ዓበይት የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንዲነጋገርባቸው ሳንጠቁም አናልፍም ይኸውም፡-

-     ምእመናንን የመጠበቅ ተልእኮ በሚገባ እየተወጣን አይደለምና ባዶአችንን ከመቅረታችን በፊት ለተደራጀና ለድንበር የለሽ ትምህርተ ወንጌል ብንነሣ፤

-      የአስተዳደር ሥራችን ለምእመናን ኅሊና እንቅፋት እየሆነ ነውና የሃይማኖቱን መርሕ ጠብቀን አስተዳደራችን የሕግ የበላይነትን ያረጋገጠ፣ ግልጽ፣ ተአማኒና ተጠያቂነትን ያሰፈነ የምእመናንን ልብ የሚያረካ፣ ምእመናን በቤተ ክርስቲያናቸው ኵራት እንዲሰማቸው የሚያስችል አሠራር ብናረጋግጥ ተጨባጭ ለውጥ ማስመዝገብ እንችላለን፤

-       ይህ ሲሆን ነው የሰበካ ጉባኤ ዓላማ ግቡን የሚመታው በእርግጠኝነት ለመናገር እንደ ጌታችን አስተምህሮ ሕጻናትን፣ ወጣቶችንና አዋቂዎችን በአግባቡ ጠብቃ የምትኖር ቤተ ክርስቲያን ለሃይማኖት ቅሰጣ አትጋለጥም ፡፡

ስለሆነም የሰበካ ጉባኤ ዋና ምንጭ ምእመናን መሆናቸውን አውቀን በዚህ ዙሪያ በሰፊው እንሥራ፤ ቢቻል አሁን አለን ከምንለው የላቀ የምእመናን ቁጥር በበለጠ ለማሳደግ ከፍተኛ ጥረት ማድረግ፣ ባይሆን ደግሞ ባለበት ጠብቆ ለማቆየት በርትተን መሥራት ይጠበቅብናል ፡፡

በመጨረሻም

ይህ ዓለም አቀፋዊ የቤተ ክርስቲያን ጉባኤ ከየአቅጣጫው የሚቀርቡትን ሪፖርቶች በመገምገም፣ ለበጀት ዓመቱ ሥራችን መሠረት የሚሆኑ የዕቅድ አመላካች አስተያየቶችና ሐሳቦችን በማስቀመጥ፣ እንደዚሁም የሀገራችንን የሕዳሴ ጉዞ በተያዘለት መርሐ ግብር መሠረት ግቡን እንዲመታ ሕዝቡን ለማነሣሣት ቃል በመግባት የሚጠበቅበትን ሁሉ እንዲያደርግ መልእክታችንን በቤተ ክርስቲያን ስም እናስተላልፋለን ፡፡

እግዚአብሔር ጉባኤያችንን ይባርክ፣ ይቀድስ

አሜን

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

አባ ማትያስ ቀዳማዊ

ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ

ሊቀ  ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

ጥቅምት 8 ቀን 2008 ዓ.ም.

አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ   

የፎንት ልክ መቀየሪያ