Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51
 • የደብረ መድኃኒት መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤቱን አክብረዋል፤
 • ለተለያዩ ጥንታውያን ገዳማትና አድባራት ከሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

በመምህር ሙሴ ኃይሉ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን አስከትለው ከጥቅምት 25-29 ቀን 2008 ዓ.ም. ድረስ በምሥራቅ ትግራይ ሀገረ ስብከት ሐዋርያዊ ጉዞ አደረጉ፡፡
የሐዋርያዊ ጉዞው ዋና ምክንያት በዓዲግራት ከተማ የሚገኝ በአዲስ መልክ የተገነባውን የደብረ መድኃኒት መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ለመባረክ ሲሆን ከዚሁ አገልግሎት ጎን ለጎን በሀገረ ስብከቱ ሥር የሚገኙ ጥንታውያን አድባራትና ገዳማትን በመጎብኘት ለገዳማውያኑንና በአጠቃላይ ለሕዝበ ክርስቲያኑን ትምህርተ ወንጌል፤ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ሰጥተዋል፡፡
ቅዱስነታቸው ከመቀሌ አየር ማረፊያ ተነስተው ውቅሮ ከተማ ሲደርሱ ሕዝቡ በከፍተኛ አባታዊ አቀባበል የተቀበላቸው ከተማ ከመድረሳቸው በፊት ጀምሮ ሲሆን የአቀባበል ሥነ ሥርዓት የተከናወነውም በደብረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ በበዓሉም የከተማዋ ሊቃውንት፣ ካህናት፣ ምእመናንና ወጣቶች የተገኙ ሲሆን በሥነ ሥርዓቱ ጊዜ ሊቃውንቱና ወጣቶች ያሬዳዊ መዝሙርና ቅኔ በማቅረብ ለአባታቸው ያላቸውን ክብር ገልጸዋል፡፡
በመቀጠልም ለዕለቱ የሚገባ ትምህርተ ወንጌል ከተሰጠ በኋላ ቅዱስ ፓትርያርኩ ለተሰበሰበው ሕዝበ ክርስቲያን ትምህርተ ወንጌል፣ ቃለ ምእዳንና ቡራኬ አስተላልፈዋል፡፡ በቃለ ምእዳናቸው ትኩረት ከሰጡት ውስጥ "ስደት ተመራጭ የሕይወት አቅጣጫ አለመሆኑና በትውልድ ሀገርህ ወጥተህ ወርደህ ሠርተህ መበልጸግ ትልቅ ብልህነትና ዘመኑ የሚፈቅደው ጥበብ መሆኑ፣ በተለይ ግን የሕይወት፣ የሃይማኖትና የንብረት ዋስትና ወደ ሌላቸው ሀገሮች ከመሰደድ በተለይ ወጣቶች እንዲቆጠቡ፤ ወላጆችም የዚህን ሕገ ወጥ ስደት አስከፊነት ለልጆቻቸው እንዲመክሩ፣ በሀገራችን አልፎ አልፎ የታየው የድርቅ ሁኔታ ለብቻችን የመጣ መቅሰፍት ሳይሆን ዓለም አቀፍ የአየር መዛባት ያመጣው ክስተት መሆኑን በመገንዘብ ሕዝቡ በትዕግሥት ፈጣሪውን እየለመነ በመረዳዳትና በመተሳሰብ እንዲያሳልፍ፣ ቤተ ክርስቲያንም ከመንግሥት ጎን ተሰልፋ ይህንን የተከሰተውን ድርቅ ለመቋቋም የበኩሏን ለማድረግ መዘጋጀትዋን፣ ሕዝቡ የቆየ የሃይማኖት ጽናቱን አጥብቆ እንዲቀጥል..." በሚሉና ተዛማች መንፈሳዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች በማንሳት ሰፊ ትምህርት ሰጥተዋል፡፡ በመጨረሻም ለቤተ ክርስቲያኑ የብር የእጅ መስቀል በማበርከት አገልጋዮቹን ካበረታቱ በኋላ ቡራኬ በመስጠት የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል፡፡

ከሰዓት በኋላ በደጃች ስባጋድስ ተሠራውን ጥንታዊውን የአፅቢ ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ጎብኝተዋል፡፡ በአቀባበሉም ሕዝቡ ከሕጻን እስከ አዋቂ ተሰልፎ የተቀበላቸው ሲሆን በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ የሚገኙ ጥንታውያን ቅርሶችን በሙሉ በቅዱስ ፓትርያርኩና በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ተጎብኝተዋል፡፡
ቅዱስ ፓትርያርኩም ለተሰበሰበው ሕዝበ ክርስቲያን ሰፊ ትምህርትና ቃለ ምእዳን ሰጥተዋል፡፡ በዋናነት ያተኮሩት፡- "ሃይማኖታውያን አባቶቻችን ያቆዩትን ጥንታዊ ጥበብ ያረፈበትን ቤተ ክርስቲያንና በገንዘብ ተመን የማይወጣለት ቅርስ ተረክባችሁ በአግባቡ ጠብቃችሁ የምትገኙ በመሆናችሁ ሁሌም ቢሆን በሰውም በእግዚአብሔር ትመሰገናላችሁ፡፡ ይህንን ቅርስ በዋጋ የማይተመን የቤተ ክርስቲያን ሀብት ስለሆነ የበለጠ ተጠንቅቃችሁ እንድትይዙት፣ እንድትጠብቁት አደራ" በማለት ቅርሱ በሥርዓት ተጠብቆ እንዲኖር ትኩረት ሰጥተው አደራ በማለት አስተምረዋል፡፡ በመቀጠልም ከጥንታዊው ቤተ ክርስቲያን አጠገብ በዘመናዊ መልክ እየተሠራ ላለው ግዙፍ ቤተ ክርስቲያን የአንድ መቶ ሺህ ብር ድጋፍና ለቤተ ክርስቲያኑ አንድ የብር የእጅ መስቀል ካበረከቱ በኋላ ጉባኤው በጸሎትና በቡራኬ ተዘግቷል፡፡ ከዚህ በመቀጠል ቅዱስ ፓትርያርኩ ጉብኝታቸውን እስከ ደብረ አላማ አሲራ መቲራ ቅድስት ማርያም ገዳም ድረስ አጠናክረው በመቀጠል ትምህርተ ወንጌል፣ ቃለ ምእዳንና ቡራኬ ሰጥተዋል፡፡
በነጋታው ቅዱስ ፓትርያርኩ በውቅሮ አካባቢ የሚገኙ ጥንታውያን ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ጎብኝተዋል፡፡ የቅዱስነታቸው ጉብኝት የጀመረው በአራተኛው ክፍለ ዘመን በአብርሃ ወአጽብሃ የታነጸው በውቅሮ ቂርቆስ ቤተ ክርስቲያን ሲሆን ቀጥሎም በዓለም አቀፍ ከፍተኛ አድናቆት የተቸረው የደብረ ነገሥት አብርሃ ወአጽብርሃ ታሪካዊ ቤተ ክርስቲያንን ጎብኝተዋል፡፡ በገዳሙ የሚገኙት ልዩ ልዩ ቅርሶችን ከተመለከቱ በኋላ ቅዱስነታቸውን ለመቀበል ለተሰበሰበው ሕዝብ ትምህርተ ወንጌል፣ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ አስተላልፈው ለካህናቱ መደጎሚያ የሚሆን ሠላሳ ሺህ ብር ለቤተ ክርስቲያኑ ደግሞ በሙዝየም የሚቀመጥ አንድ የብር የእጅ መስቀል አበርክተዋል፡፡ ከዚህ በመቀጠል በከተማዋ መሀል የሚገኘውና በዘመናዊ መልክ የተሠራው የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያንም በተመሳሳይ ጎብኝተዋል፡፡
ጥቅምት 26 ቀን 2008 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ በዋናነት ወደ ተዘጋጀው የቤተ ክርስቲያን ቡራኬ ለማክበር ጉዞ የተደረገው ወደ ዓዲግራት ከተማ ነበር፡፡ የዓዲግራት ሊቃውንት፣ ካህናት፣ መዘምራን ወጣቶች፣ የተለያዩ የሃይማኖት መሪዎች፣ ተማሪዎች በአጠቃላይ ሕዝቡ ሁሉ ከከተማ መዳረሻ ጀምሮ እስከ ሚባረክ ቤተ ክርስቲያን ድረስ ሰልፍ በማድረግ ለሃይማኖት አባታቸው ያላቸውን አክብሮት በሚገልጽ መልኩ ደማቅ አቀባበል አድርገዋል፡፡
የቤተ ክርስቲያኑ ሥርዓተ ቡራኬ ከተፈጸመ በኋላም ሊቃውንትና ወጣቶች እንዲሁም መስማት የተሳናቸው በምልክት ቋንቋ ያሬዳዊ መዝሙር አቅርበዋል፡፡ ትምህርተ ወንጌልም በብፁዕ አቡነ እንጦንስና በብፁዕ አቡነ ሙሴ የተሰጠ ሲሆን ሕዝቡም እስከ ማታ ድረስ የአባቶቹ ትምህርት እጅግ በትልቅ አክብሮት ሲከታተል አምሽቷል፡፡
በመጨረሻም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ለተሰበሰበው ሕዝበ ክርስቲያን ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ሰጥተዋል፡፡ በትምህርታቸውም ለአባቶች የተደረገውን ደማቅ አቀባበል አመስግነዋል፡፡ የሌላ የሃይማኖት መሪዎች አብረው ከሕዝቡ ጋር በመተባበራቸው አመስግነው ይህንኑ የመቻቻል ባህል ይበልጥ እንዲጎለብት መክረዋል፡፡ ይህን የመሰለ የሃይማኖት ጽናት ለልጆች እንዲተላለፍ መምህራን እንዲያስተምሩ፣ ወላጆችም እንዲመክሩ አደራ ብለዋል፤ አልፎ አልፎ የታየው የድርቅ ክስተትም በመረዳዳትና በጸሎት ችግር እንዳይደርስ እንዲያደርግ መክረዋል፡፡ በአጠቃላይ የቆየ የመፈቃቀርና የመተሳሰብ ሃይማኖታዊ ሥነ ምግባር እንዲጎለብት መክረው በመባረክ ጉባኤው በጸሎት ተዘግቷል፡፡
በነጋታው የቤተ ክርስቲያኑን ቅዳሴ ቤት በማክበር ቅዱስ ፓትርያርኩ ቀድሰው በማቁረብ ትምህርተ ወንጌልና ቡራኬ ሰጥተዋል፡፡
ከሰዓት በኋላ በከፍተኛ ሁኔታ በማደግ ላይ የሚገኘው የዓዲግራት ዩኒቨርስቲን ጎብኝተው የሚጠቀሟቸው ዘመናዊ ቴክኖሎጂም ተመልክተዋል፡፡ ለዩኒቨርስቲው ማኅበረሰብ ማበረታቻ ምክር ሰጥተው አጠገቡ በሚገኘው ደብረ ፀሐይ ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን በመሔድ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ትምህርተ ወንጌል፣ ቃለ ምእዳንና ቡራኬ ሰጥተው የደብረ ጎልጎታ መድኃኔ ዓለም ካቴድራልን ጎብኝተዋል፡፡
ቅዱስ ፓትርያርኩ ሐዋርያዊ ጉዞአቸውን በመቀጠል በነጋታው ጥቅምት 28 ቀን 2008 ዓ.ም. ወደ ጥንታዊው ቤተ ክርስቲያን ወደ ወልዋሎ ደብረ ብርሃን ቅዱስ ቂርቆስ በመሔድ ጎብኝተዋል፡፡ የወረዳው ሕዝብም በከፍተኛ ሁኔታ በመዘጋጀት ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል፡፡ ቅዱስነታቸውም ለአቀባበል ለመጣው ሕዝበ ክርስቲያንና ለወረዳው ካህናት በአጠቃላይ ትምህርተ ወንጌል፣ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ከሰጡ በኋላ በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ስምንት አብያተ ክርስቲያናት ከሰማንያ ሺህ ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል፡፡ የቅዱስ ቂርቆስ ቤተ ክርስቲያንም የመቀደሻ አልባሳት፣ የብር የእጅ መስቀልና ለጧፍና ለዕጣን መግዣ የሚሆን ተጨማሪ ገንዘብ ሰጥተዋል፡፡ ቅዱስነታቸው ጥንታዊው የደብረ ሲና ሰውነ ቅድስት ማርያም ገዳምን ጎብኝተዋል፤ አንድ የዕፅ አንድ የብር የእጅ መስቀል ሰጥተዋል፡፡ ለአቡነ ዘርአ ብሩክ ቤተ ክርስቲያንም አንድ የዕፅና አንድ የብር የእጅ መስቀል ሰጥተዋል፡፡
ከዚህ በመቀጠል በዕዳጋ ሐሙስ ወረዳ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ደብረ ፀሐይ ቅድስት ሥላሴና ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያንን ጎብኝተዋል፡፡ ቅዱስነታቸው ሐዋርያዊ ጉዞአቸው ያጠናቀቁት ሐውዜን ከተማ በመጎብኘት ነበር፡፡ የአቀባበል ሥነ ሥርዓቱ የተከናወነው በጥንታዊው ቤተ ክርስቲያን በሐውዜን ተክለ ሃይማኖት ሲሆን ሊቃውንቱና ወጣቶች ያሬዳዊ መዝሙርና ቅኔ በማቅረብ በዓሉን አድምቀውታል፡፡ ቅዱስነታቸውም በግፍ የፈሰሰው የወገኖቻችን ደም ዳግም እንዳይደገም ሁሉም ሰው ሰላሙንና ልማቱን ተጠናክሮ እንዲቀጥል በማድረግ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ጥሪ በማድረግ ሰፊ ትምህርተ ወንጌል፣ ቃለ ምእዳንና ቡራኬ ከሰጡ በኋላ በግፍ የተገደሉ ወገኖቻችን በተቀበሩበት መቃብር በመገኘት ጸሎተ ፍትሐት አድርገው የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ጋር ያደረጉትን ሐዋርያዊ ጉዞ አጠናቀው ጥቅምት 29 ቀን 2008 ዓ.ም. አዲስ አበባ ተመልሰዋል፡፡

የፎንት ልክ መቀየሪያ