Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

ቅዱስነታቸው የአድዋ ከተማንና አካባቢዋን ጐበኙ

እስክንድር ገ/ክርስቶስ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በሆን ኅዳር 19 ቀን 2008 ዓ.ም አክሱም አውሮኘላን ማረፊያ ሲደርሱ ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ ፣ ብፁዕ አቡነ ኢሳይያስና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆስ የክልል ትግራይ ሊቃነ ጳጳሳት አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
በርዕሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ጸሎት ካደረጉ በኋላ ወደ አድዋ ከተማ የተጓዙት ቅዱስ ፓትርያርኩ የአቀባበል መርሐ ግብር ውስጥ በተካተተው መሠረት ከመኪናቸው ወርደው ወደ ጥንታዊውና ወደ ታላቁ የደበረ ብርሃን ሥላሴ ቤተክርስቲያን በሰረገላ ተጉዘዋል፡፡

Picture 104 Picture 107 Picture 137 Picture 147 Picture 167 Picture 187 Picture 205 Picture 242 Picture 354 Picture 393 Picture 412 Picture 416 Picture 455 Picture 457 Picture 480 Picture 500

በመንገዱ ግራና ቀኝ ተሰልፎ በእልልታ ፣ በሆታ ፣ ርጥብ ቄጤማና የፈንድሻ አበባ በሚበትኑ እናቶች ደምቆ የጠበቀቸውን የአድዋ ከተማ ሕዝብን ቅዱስ ፓትርያርኩ ባርከዋል፡፡ በአቀባበል ሥነ ሥርዓቱ ማጠቃለያ ላይም ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በአድዋ ደብረ ብርሃን ሥላሴ ቤተክርስቲያን ጸሎት ካደረጉ በኋላ በአውደ ምህረት ላይ ለተሰበሰበው ሕዝብ ትምህርትና ቡራኬ ሰጥተዋል፡፡ የአድዋ ከተማ ከንቲባም የእንኳን ደህና መጡ ንግግር አድርገዋል፡፡ከንቲባው የቅዱስ ፓትርያርኩ ጉብኝት ለጥንታዊቷና ለታሪካዊቷ የአድዋ ከተማ ሕዝብ ትልቅ ትርጉም ያለው መሆኑን ገልጸው ከተማችንን ለመባረክ እንኳን በደህና መጡልን የአድዋ ቆይታዎም የተሳካ እንዲሆን እመኛለሁ ብለዋል፡፡

በአዲ አቡን ቤተክርስቲያን በመገኘት በቤተክርስቲያኑ የሚገኘውን ቅርስ ተዛውረው የተመለከቱት ቅዱስ ፓትርያርኩ ታሪካችሁንና ሃይማኖታችሁን አጽንታችሁ በመኖራችሁ እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል በቅዱስ ፓትርያርኩ መልካም ፈቃድ ትምህርት የሰጡት በብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የምሥራቅ ሸዋ ሊቀ ጳጳስ በትምህርታቸው የዚህ አካባቢ ካህናትና ምዕመናን በታሪካችሁ ፣ በሃይማኖታችሁ ፣ በታሪክ ጠባቂነታችሁ፣ በእንግዳ አክባሪነታችሁ ከእናንተ እንማራለን እንጂ ምን ልናስታምራችሁ እንችላለን ፣ ካሉ በኋላ እናንተ የታሪክ ባለቤቶች ፣ የታሪክ ጠባቂዎች በመሆን ያቆያችሁትን ቅርስ ለመጪው ትውልድ ለማስከበር ትችሉ ዘንድ የጀመራችሁትን ታሪክና ቅርስ የመጠበቅ ሥራ አጠናክራችሁ መቀጠል ይገባችኋል ብለዋል፡፡
በመቀጠልም የመደራ አቡነ ገሪማ ገዳምን የጐበኙት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በገዳሙ የሚገኙትን ሁለት ሙዚየሞችን ተዛውረው ተመልክተዋል፡፡ በገዳሙ የሐሳብ መስጫ መዝገብ ላይም አስተያየትና ፊርማቸውን አኑረዋል፡፡በገዳሙ ለተሰበሰቡ ካህናትና ምዕመናንም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ አቡነ ገሪማ ራሳቸው ከጻፉአቸው መጻሕፍት በተጨማሪ በቀላሉ የማይገኙ ጥንታዊያን መጻሕፍት በገዳሙ እንደሚገኙ የተመለከቱ መሆኑን የተናገሩት ቅዱስ ፓትርያርኩ በዚህ ገዳም በሌላ ቦታዎች ያልተመለከትናቸው በርካታ ቅርሶች አይተናል፡፡ ስለሆነም ካህናትና ምዕመናን ቅርሱችን ጠብቃችሁ ለትውልድ ለማስተላለፍ በምታደርጉት ጥረት ሁሉ ቤተክርስቲያን ከጐናችሁ ነች ብለዋል፡፡
በገዳሙ የሚገኘውን የራስ አሉላ አባ ነጋ መካነ መዕብርን የተመለከቱት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በገዳሙ የሚገኘውንና ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ፕሬዝዳንትና የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንት የሰሩትን የብፁዓን አበውና ቅዱሳን ፓትርያርኮች ማረፊያ ጐብኝተዋል፡፡
የገዳሙ መናንያን ያቀረቡትን ሪፓርት ያዳመጡት ቅዱስነታቸውም በገዳማዊያኑ ሪፓርት የቀረቡ ችግሮች በቅዱስ ሲኖዶስ ታይቶ ምላሽ የሚያገኝ መሆኑን ጠቅሰው ለጊዜው ለካህናቱ መደጐሚያ የሚሆን የ30,000.00 ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡ በገዳሙ በእነ ዣክ መርስኤ ይደረግ የነበረውን ጥናትና ጥናቱን ተካትሎ በእነ ዣክ መርስኤ የቀረበውን ሪፓርት በተመለከተ በኢትዮጵያዊያን ሙሁራንና በእነዣክ መካከል ክርክር ሲደረግ መቆየቱን የተናገሩት ቅዱስነታቸው ገዳሙን በተመለከተ የቀረበው ሪፓርት አስቸጋሪ መሆኑን ጠቁመው አጠቃላይ ሁኔታውን በተመለከተ የቅርብ ክትትል እንደሚደረግ አሳስበዋል፡፡
በተያያዘ ዜና ቅዱስ ፓትርያርኩ በይሐ አቡነ አፍጼ ገዳም በመገኘት ገዳሙን የጐበኙ ሲሆን በገዳሙ የሚገኘውን ሙዚየምና ከክርስቶስ ልደት በፊት አንድ ሺህ ዓመት ቀድሞ የተገነባውን ሙኩራብ ጐብኝተዋል፡፡
ቅዱስነታቸው በገዳሙ አቀባበል ላደረጉላቸው ካህናት ፣ ምዕመናንና ወጣቶች ባስተላለፉት መልዕክት ገዳሙ ታላላቅ አባቶችን ፣ ታላላቅ ካህናትን ያፈራ የታሪክ ቦታ መሆኑን ገልጸው ይህን የመሠለ ታላቅ ቦታ፣በውስጡ የተቀመጡትን ቅርሶችና የገዳሙን ሁለንተናዊ ክብር በመጠበቅ ለዚህ ያበቃችሁ በመሆናችሁ ቤተክርስቲያን ታመሰግናችኋላች ብለዋል፡፡
ይህን ታሪካዊ ቦታ ወደነበረበት የሥልጣኔ ማማ ለመመለስ ጊዜ የሚወስድ ቢሆንም በውስጡ ያለውን የተቀበረ ታሪክ ወጥቶ ሕዝብ እንዲያውቀው ማድረግ ግን ተገቢ ነው ፡፡ስለሆነም ምሁራንን በማስተባበር አካባቢውን እንዲያጠኑ በማድረግ በከርሰ ምድር ተቀብሮ የቆየውን ቅርስ በማውጣት ለሕዝቡ ለማስተዋወቅ ያደረጋችሁት ጥረት የሚመሰገን ነው ብለዋል፡፡
በጥቅሉ በዚህ በተቀደሰ ቦታ (ተሰዓቱ ቅዱሳን በጸለዩበትና በባረኩት) ቦታ የሚገኙ ጥንታዊያን ቅርሶችን በመጠበቅና በመንከባከብ ለትውልድ ለማስተላለፍ የምታደርጉት ጥረት ሊመሰገን የሚገባው ነው ያሉት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ልጆቻችሁን ስለታሪካችሁና ስለ ባህላችሁ በሚገባ በማስተማር ቅርሶቻቸውን የሚጠብቁና የሚንከባከቡ እንዲሆኑ ማድረግ ይጠበቅባችኋል ብለዋል፡፡ ለገዳሙ የ30,000.00 ብር ድጐማም አድርገዋል፡፡
በገዳሙ ሙዚየም የአቡነ አፍዴ መስቀልና ልዩ ልዩ መገልገያ ቁሳቁሶች የሚገኙ ሲሆን ከ3000 ዘመን በላይ ዕድሜ ያላቸው እንስራዎች ፣ በንጉሥ ገ/መስቀል የተሰራ መስቀል ፣ ማኅተሞች ፣ ከ6ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የነበሩ የብራና መጻሕፍት ፣ ዳዊት ፣ ድጓ ፣ አረጋኖን ፣ አቡሻክርና ሌሎች ከ700-1000 ዓመት ያስቆጠሩ የብራና መጻሕፍት ይገኛሉ፡፡
በገዳሙ የሚገኘውና ከክርስቶስ ልደት 1000 ዓመት በፊት እንደተሰራ የሚነገርለት የሕንጻ ቅሪት የሚገኝ ሲሆን በሕንጻውና በስሪቱ ዙሪያ ምሁራን ጥናት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ይህ የጸሎት ቤት በቅርስነት መመዝገብ የሚገባውና ያልተመዘገበ መሆኑን የገዳሙ አበምኔት ያስታወቁ ሲሆን ቦታውን በቅርስነት ለማስመዝገብ ጥረቱ መቀጠል እንደሚገባው ቅዱስነታቸው ተናግረዋል፡፡
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ በአድዋ ከተማ የሚገኘውና ከአፍሪካ በአንዳኛነት የሚታወቀውን የአልመዳ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ጐብኝተዋል፡፡ በፋብሪካው 5,600 ሠራተኞች መኖራቸውን፣ ከእነዚህ ውስጥም 3,500 የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸውን የተናገሩት የፋብሪካው የሥራ ኃላፊዎች ፋብሪካው የ24 ሰዓት የምርት ሥራ የሚያከናውን መሆኑን ገልጸው በሦስት ሽፍት ሥራውን እንደሚያከናውን ተናግረዋል፡፡ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩም የፋብሪካውን የሥራ ሂደቶች ጐብኝተውና ሠራተኛውን ባርከው ጉብኝታቸውን አጠቃለዋል፡፡
ቅዱስነታቸው በርዕስ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን የሚከበረው ዓመታዊ በዓለ ንግሥ ላይ ለመገኘት ወደ አክሱም በተጓዙበት ጊዜ ካህናት ፣ ምዕመናን ፣ ወጣት የሰንበት ት/ቤት ዘማርያን ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡ አቶ ሚካኤል አብርሃ የማዕከላዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪም ቅዱስ ፓትርያርኩን እንኳን ይህና መጡ ብለዋቸዋል፡፡
የአክሱምና የአካባቢዋ ነዋሪዎችም በአቀባበል ሥነ ሥርዓቱ ላይ የታደሙ ሲሆን ቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በሰረገላ ተጭነው ወደ ቤተክርስቲያኒቱ አምረተዋል፡፡ የፓሊስ የማርሽ ቡድን ፣ ወጣቶችና የከተማዋ ነዋሪዎችም የአቀባበል ሥነ ሥርዓቱ አካላት ሁነው ውለዋል፡፡
በርዕሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ቤተክርስቲያን ካህናት ያሬዳዊ ዝማሬና ቅኔ ያቀረቡ ሲሆን ቅዱስነታቸውም በአቀባበል መርሐ ግብሩ ላይ የተሣተፉትን ሁሉ ባርከዋል፣ መክረዋል ፣ አስተምረዋል፡፡ ቅዱስነታቸው በቃለ ምዕዳናቸውም አክሱም የታሪካችን ፣ የቀደምትነታችን ፣ የሰው ዘር መገኛነታችን ምልክት ናትና የሚታየው ታሪካዊ ቅርስም ይህንን እውነታ የበለጠ የሚያጐላው ሆኖ ይታያል ያሉት ቅዱስ ፓትርያርኩ በእነዚህ ጥንታዊያን ቦታዎች የሚገኙ ጥንታዊ ቅርሶች በሚገባ ካሉበት ቦታ ወጥተውና ተሰብስበው ለታሪካዊነታችንና ለጥንታዊነታችን ማስረጃ እንዲሆኑ ማድረግ ይቻል ዘንድ በአግባቡ ተደራጀተው መቀመጥ ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡
በድጋሜ እንኳን ለኅዳር ጽዮን በዓለ ንግሥ በሰላም አደረሳችሁ ያሉት ቅዱስነታቸው በዚህ በቃል ኪዳኑ ታቦት መገኛ ቦታ የሚደረግ ጸሎት እግዚአብሔር ፊት መቅረቡና ዋጋ ማስገኘቱ አይቀርምና ለሀገር ሰላም ፣ ለሰው ልጆች ፍቅር ፣ ርሃብና ቸነፈር እንዲወገዱ ጠንከራችሁ መጸለይ ይገባችኋል ብለዋል፡፡
በዚሁ ዕለት ሀገረ ስብከቱ ለሚያስገነባው ባለ 5 ፎቅ ሕንጻ ግንባታ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የመሠረት ድንጋይ የተቀመጠ ሲሆን ሀገረ ስብከቱ ከመንግሥት ባገኘው 950 ካሬ ሜትር ቦታ ውስጥ በሚገነባው ሕንጻ የሀገረ ስብከቱን ጽ/ቤት ጨምሮ የገበያ ማዕከላትና መሰል የንግድ ተቋማትን አጠቃሎ እንዲይዝ ተደርጐ ዲዛይን መደረጉ በወቅቱ ተገልጿል፡፡
ኅዳር 21 ቀን 2008 ዓ.ም ዓመታዊው የኀዳር ጽዮን ክብረ በዓል ሃይማኖታዊ ሥርዓቱ በሚፈቅደው አግባብ ተከናውኖ የተከበረ ሲሆን ሙራደ ቃል በመባል በሚታወቀው ቦታ ላይ ካህናት ወረብና ቅኔ ያቀረቡ ሲሆን ወጣት የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎችም መዝሙር አቅርበዋል፡፡ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል የከፋ ሸካና ቤንች ማጂ አህጉረ ስብከት ፣ የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ መልካም ፈቃድ ሰፊ ትምህርት ሰጥተዋል፡፡ ብፁዕነታቸው በትምህርታቸው ፣ ስለታቦተ ጽዮን ክብር፣ ስለአክሱም ጥንታዊነትና ስለሕዝቡ እንግዳ ተቀባይነት ፣ ስለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ክብርና ቅድስና የሕዝበ ክርስቲያኑን ቀልብ የሳበና ከፍተኛ አድናቆትን ያገኘ ትምህርት ሰጥተዋል፡፡
የክልል ትግራር ርዕሰ መስተዳደር አቶ አባይ ወልዱ በበኩላቸው በዓሉን ለማክበር የተሰበሰበውን ሕዝበ እንኳን አደረሳችሁ ካሉ በኋላ በዓሉ ከሃይማኖታዊ ፋይዳው በተጨማሪ ለቱሪስት ፍሰት መጨመር ከፍተኛ ጠቃሜታ እየሰጠ ያለ መሆኑን ጠቅሰው ሕዝቡ ከበዓሉ የሚያገኙው ኢኰኖሚያዊ ጥቅም መጨመር ይችል ዘንድ እንግዶቹን በአግባቡ መቀበልና መሸኘት እንደሚገባው ተናግረዋል፡፡
በቅርቡ በክልል ትግራይ አንዳንድ ዞኖች የታየውን የድርቅ ሁኔታ ለማስተካከል መንግሥት የግብርና ሥርዓቱን የበለጠ ለማዘመንና በከተማ መስፋፋት እርሱን ተከትሎ በኢንዱስትሪዎች መበራከት ዙሪያ በመስራት ድርቅ የማይጐዳውና መቋቋም የሚያስችል ስልትን መከተል እንደሚገባና ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሉቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በበኩላቸው ከእኔ በላይ ሌላ አምላክ አይኑርህ በሚል ርዕስ ሰፊ ትምህርት ሰጥተዋል፡፡
ቅዱስ ፓትርያርኩ በትምህርታቸው ወጣቱ ትውልድ ሃይማኖቱን ፣ ቅርሱን መጠበቅና መንከባከብ ይጠበቅበታል፡፡ካሉ በኋላ ይህን ኃላፊነት ለመቀበል እና ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ ይችል ዘንድ ወጣቱ ራሱ ጤንነቱን መጠበቅ ፣ ትምህርቱን በአግባቡ መከታተል ፣ ሀገሩን በማልማት ፣ በሕገ - ወጥ መንገድ አለመሰደድ ፣ አምላኩን ማወቅ ፣ ቤተክርስቲያኑን መውደድ ፣ ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡
ወጣቱ ትውልድ ይህንን ሁሉ በአግባቡ ማከናወን ከቻለ ለሀገሩ ታማኝ መሆንና ለሀገሩ መስራት ይችላል ያሉት ቅዱስ ፓትርያርኩ ጥራችሁ ግራችሁ በወዛችሁ ሠርታችሁ ብሉ የሚለውን አምላካዊ ቃል መሠረት በማድረግ ሰርቶ መኖርና ሠርቶ መለወጥ የሚገባ ስለሆነ ከእግዚአብሔር ቃልና ትዕዛዝ ውጭ ሕገ - ወጥ በሆነ መንገድ ሀብት ለመሠብሰብ መሞከር ሐጢአት መሆኑን መገንዘብና ሰርቶ መለወጥ እንደሚገባ መክረዋል፡፡
ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በዚሁ ዕለት በገዳሟ ሥርዓተ ቅዳሴውን በመምራትና በማቁረብ ሐዋርያዊ ተግባራቸውን አከናውነው በማግስቱ ጠዋት ወደ አዲስ አበባ ተመልስዋል፡፡
በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የአክሱም ቆይታ ወቅት እንደታዘብ ነው አክሱምን በሚያክል ታላቅ ሀገር የቅዱስ ፓትርያርኩ አቀባበል ሥነ ሥርዓት የተዋጠለት እንዲሆን የተደረገው ጥረትና የተገኘውን ውጤት እስከ በዐሉ ማጠቃለያ ተጠናክሮ መቀጠል ሲገባ ሀገረ ስብከቱና ገዳሙ መናበብ ባለመቻላቸው በርካታ ክፍተቶች ታይተዋል፡፡
ከእነዚህ በርካታ ክፍተቶች መካከል ጥቂቶቹን ብንመለከት ቅዱስ ፓትርያርኩን ተከትለው ለሥራ የሔዱ ሊቀውንትና የመምሪያ ኃላፊዎች መኝታ ሳይያዝላቸው ወይም አንድ ጥግ መውደቂያ የሚያዘጋጅላቸው ጠፍቶ በአክሱም የክብረ በዐል ግርግር፣ በአክሱማዊያን ነጋዴዎች የወቅቱን የገቢያ ሁኔታ ለመጠቀም ከአቅም በላይ በሚጨመር ዋጋ ፣ በከተማዋ የአልጋ ፍላጐትና በምዕመናን ብዛት ያለመጣጣም ሁኔታ የፈለጉበት እንዲያድሩ ሲፈረድባቸው ችግሩን ለመፍታት ሀገረ ስብከቱም ሆነ የገዳሟ ኃላፊዎች መወያየት ተስኗቸው አይተው እንዳላዩ አውቀው እንዳላወቁ ሲሆኑ ለተመለከታቸው እነዚህ ሰዎች በትክክል ጺዎናዊያን እንግዳ ተቃባዮች ናቸው; ወይስ ሌሎች;እንድንል የሚያስገድዱ ናቸው፡፡
የገዳሟ ንቡረ ዕድ በመንበረ ጵጵስናው እንግዳ እንዲያስተናግዱ ያስቀመጧቸውን መነኩሲት ማዘዝ ሲገናቸው መነኩሲቷም የአለቃቸውን ትዕዛዝ መፈጸምና መቀበል ተስኗቸው የጠቅላይ ቤተ ክህነትን የመምሪያ ኃላፊዎች ሊያንጓጥጡ ለተመለከታቸው በእርግጥ ሴትየዋ በርዕሰ አድባራት ወገዳማት የሚያገለግሉ መነኩሲት ናቸው; ብሎ መጠየቁ አይቀርም፡፡
ከሁሉም የሚገርመው እኒሁ መነኩሲት ለገዳሟ ንቡረ ዕድ መታዘዝ ተስኗቸው የመምሪያ ኃላፊዎችን ለማስተናገድ ሲቸገሩ እንዳልታዩ ሁሉ ጓደኛቸው በመጡ ጊዜ የሚተኙበት ፍራሽና አንሶላ በመስጠት በቤተክርስቲያን ንብረት የቤተክርስቲያን አገልጋዮችን ከማስተናገድ ይልቅ ወዳጆቻቸውን ሲጠቅሙና ወዳጅነታቸውን ሲያጠናክሩበት ለተመለከተ የመነኩሲቷን ጥፋት ብቻ ሳይሆን ያለቦታቸው ያስቀመጧቸውን የገዳሟን አመራሮች ለትችት ይዳርጋቸዋል፡፡
ሌላውና ለወደፊቱ መታረም የሚገባው ነገር ቢኖር በገዳሟ እና በሀገር ስብከቱ መካከል ያለው ልዩነት ነው፡፡ በገዳሟና በሀገር ስብከቱ መካከል በየጊዜው የሚታየው ያለመግባበት ፣ የመናናቅና ያለመረዳዳት ችግር እርስ በእርሳቸው ለክስ የሚዳርጋቸውና አንዱን አሸናፊ ሌላውን ተሸናፊ በማድረግ በሕዝበ ክርስቲያኑ ፣በመንግሥት የዐጥታ አካላትና በጠቅላይ ቤተክህነት አማካኝነት ውዝግቡ እንዲቋጭ የሚደረግ ሲሆን ይህ ሁኔታ እንዲታረም ቦታው እንዲለማ አካባቢው እንዲለወጥ መሥራት ያስፈልጋል፡፡
በዘንድሮ በዓል ላይ አክሱማዊያኑ ሥራቸውን በተረጋጋና በሰከነ መንገድ መምራት እንደተሳናቸው ያመለከተ ሌላ አጋጣሚም ተስተውሏል፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ለሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤትና ሁለገብ ሕንጻ መሠረት እንዲጠሉ ወደ ቦታው የሚመሯቸው የሀገረ ስብከቱ የሥራ ኃላፊዎች መሠረት የሚጣልበትን ቦታ የማያውቁት፣ በመሆኑ ቅዱስ ፓትርያርኩንና ብፁዓን አበው ሊቀነ ጳጳሳትን በአክሱም ከተማ ለመንከራተት ዳረገዋቸዋል፡፡
በወቅቱ ተፈልጐ በተገኘው ቦታ ላይ ቅዱስ ፓትርያርኩ የመሠረት ድንጋይ ሲያስቀምጡ የተመለከቱም በሰው ቦታ እንዳይሆን መሠረት የሚያስጥላቸው በማለት አለመረጋጋታቸውን ገልጸአል፡፡
ሌላው የታዘብነው ነገር በቅዱስነታቸው የአክሱም ቆይታ ሁሉ ባለቅኔዎቹ በቅኔአቸው የአክሱም ሙዚየም የግንባታ ሂደት እንዲቀጥል ሲወተውቱ ሰንብተዋል፡፡ ይህ ጥሩ ነው የአክሱም ካህናትና ሕዝብ የአክሱም ባለሃብቶችና የአክሱም ጽዮን ወዳጆች በእኛ በኩል ይህን እናደርጋለን ቤተክርስቲያኒቱ ይህን ታደርግ የሚል ሐሳብ ማቅረብ አለመቻላቸው ግን ትዝብት ላይ የጣላቸው ነበር፡፡
ሲጠቃለል አክሱማዊያኑ ፣ ለመተባበር ፣ ለመደማመጥ ፣ ለመከባበር ፣ ለመወያየት ፣ በጋራ ለመስራት ፣ እንግዶችን በአግባቡ ለማስተናገድ ፣ ኃላፊነትን በጋራ ለመወጣትና ሀገረ ስብከታቸውን ለማጠናከር ዘወትር ዝግጁ መሆን ይህን ለመፈጸም መንቀሳቀስ የማይችሉ ከሆነ የሃይማኖትና የሥልጣኔ ቀደምትነታቸውን /ብኩርናቸውን/ አሳልፈው ለሌላ መሰጠታቸው ስለሚሆን ሊያስቡበት ይገባል፡፡

የፎንት ልክ መቀየሪያ