Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

ማኅበረ ቅዱሳን ባልተፈቀደለትና ባልተሰጠው ሥልጣን በቤተ ክርስቲያኗ ተመርምረውና ተፈቅደው በማይታተሙት የሕትመት ውጤቶች በሆኑትና በድረ ገጹ ላይ አጠናሁት ባለው ጽሑፍ የቤተ ክርስቲያን ዓበይት ኮሌጆችንና ደቀመዛሙርቶቻቸውን በጋራ መድፈሩን፣ መንቀፉን፣ ማዋረዱንና ማውገዙን ተከትሎ የቅዱስ ፍሬምናጦስ ከሳቴ ብርሃን አባ ሰላማ መንፈሳዊ ኮሌጅ፣ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ፣ የሰዋሰወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ሠራተኞች፣ መምህራንና ደቀመዛሙት በጋራ በመሆን ከፍተኛ የተቃውሞ የአቋም መግለጫ በማውጣት ይህ ሕጋዊ መተዳደሪያ ደንብ እንኳ የሌለው በቤተ ክርስቲያኒቷ ስም እየነገደ የሚገኝ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን›› የተባለ ማኅበር በቅዱስ ሲኖዶስ መልካም ፈቃድ የተቋቋሙትን የቤተ ክርስቲያኗ መካነ አእምሮ (የእውቀት ማእከላት) እና የኮሌጆቹ ማኅበረሰብ በማን አለብኝነት ስላዋረደና አለስልጣኑም ገብቶ ስላወገዘ ቅዱስ ሲኖዶስ በአስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጠን ሆኖ በቤተ ክርስቲያኒቷ እየተመረመሩ ኅትመት ላይ የማይውሉ ጋዜጦች፣ መጽሔቶችና ድረ ገጽም ቅዱስ ሲኖዶስ ይህንን አቤቱታችንን ተመልክቶ ፍትሐዊ ውሳኔ እስኪሰጠን ድረስ የሕትመት ውጤቶቹ እንዲታገዱልን በማለት አቤቱታ ይዘው ቅዱስ ፓትርያርኩ ቢሮ ድረስ በመምጣት የሁሉም ኮሌጆች አመራርና የደቀ መዛሙርት ተወካዮች በአካል ቀርበው መጠየቃቸውን ተከትሎ ይህ የማኅበረ ቅዱሳን አዲስ ትርምስ የማስነሳት ተልዕኮ ለማክሸፍ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት አዲስ መመሪያ አስተላለፉ ፡፡
የቅዱስ ፓትርያርኩ መመሪያ ቤተ ክርስቲያኗ የእውቀት ማእከላት የሆኑት ኮሌጆችና ደቀመዛሙርት ተረጋግተው በሰላም የመማር የማስተማር ሥራቸውን እንዲያከናውኑ የሚል ሆኖ ማኅበሩ ለርእሰ ቤተ ክርስቲያን ለቅዱስ ሲኖዶስና ለቅዱስ ፓትርያርኩ አልታዘዝ በማለት እየሄደበት ያለው የጥፋት መንገዶች በሙሉ ሁሉም ግንዛቤ አግኝቶ ለቤተ ክርስቲያን ህልውና ቅድሚያ ሰጥቶ ማኅበሩን ከጥፋት እንዲታረም የበኩሉን እንዲወጣ በማሰብ ሕገ ወጥ ድርጊቶችን ዘርዝሮ ያስቀመጠ ሲሆን በአድራሻ ለሦስቱ ኮሌጆች ሆኖ በግልባጭም የሚመለከታቸው መንግሥት ጽ/ቤቶችና ባለድርሻ አካላት እንዲያውቁት መደረጉ ከደብዳቤው መረዳት ይቻላል ፡፡
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በመመሪያቸው በዋናነት፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከጥንት ጀምሮ በቀኖናዋ መሠረት የቅዱስ ሲኖዶስ ሥርዓተ ቀኖና እተከተለች ተልዕኮዋን የምትፈጽም መሆንዋን፤ ውሳኔ የሚያስፈልገው ትምህርት፣ ሥርዓት ወይም ቀኖና ቢኖርም ውሳኔ የሚያገኘው በቅዱስ ሲኖዶስ እንጂ በማኅበራት አለመሆኑ፤ ማኅበረ ቅዱሳን ከማክበርና ከመታዘዝ ይልቅ የሲኖዶስ ሥልጣን በመጋፋት ቤተ ክርስቲያንን የማተራመስ ቀኖና የለሽ ሥርዓት እየተከተለ ያለ መሆኑ፤ በሌለው ሥልጣን የጾም አዋጅ እስከማወጅ መድረሱን፣ ቤተ ክርስቲያን የማትቆጣጠረው በቤተ ክርስቲያን ስም ከፍተኛ ገንዘብ በመሰብሰብ ለድብቅ ዓላማው ማስፈጸሚያ እያዋለ መሆኑን፣ በቤተ ክርስቲያኗ መዋቅሮች ውስጥ ጣልቃ በመግባት እያተራመሰ መገኘቱን፤ ያለ ሕጋዊ ደንብና መመሪያ እየሠራ መሆኑን በማለት በስፋት ከገለጹ በኋላ የሦስቱ ኮሌጆች ሠራተኞች፣ መምህራንና ደቀመዛሙርት ያቀረቡትን አቤቱታ በውሳኔ ሰጭ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ የሚሰጥ ሆኖ ኮሌጆቹና የኮሌጁ ማኅበረሰብም የተለመደ ሥራቸውን ተረጋግተው በመሥራት ማኅበሩ ባደረገው የትርምስ ድርጊት ሳይበገሩ አገልግሎቸውን እንዲቀጥሉ መመሪያ አስተላልፈዋል ፡፡ የተከበራችሁ አንባቢዎች ቅዱስ ፓትርያርኩ ለሦስቱ ኮሌጆች የጻፉትን የማረጋጊያ ደብዳቤ ከዚህ ቀጥለን አቅርበናል፡፡ መልካም ንባብ ፡፡

ቅዱስ ፓትርያርኩ ለሦስቱ ኮሌጆች የጻፉትን የማረጋጊያ ደብዳቤ PDF

የፎንት ልክ መቀየሪያ