Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

በመ/ር ዕንቈባሕርይ ተከስት

ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት በቁጥር ል/ጽ/248/382/2008 በቀን 16/6/2008 ዓ.ም የወጣው መመሪያ የሚገልጸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በኦርቶዶክሳዊ ትምህርተ ሃይማኖትና ሥርዓተ ቀኖና፣ ሐዋርያዊ ትውፊትና ባህል ጸንታ ለሁለት ሺህ ዓመታት መዝለቅ የቻለችው፣ እንደሌላው የኦርቶዶክሱ ዓለም በውሉደ ክህነት፣ በሊቀ ጳጳስ፣ ከዚያም እንደየደረጃው በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ በቀሳውስትና ዲያቆናት መዋቅራዊ አስተዳደርና አገልግሎት እንደሆነ የማይካድ ሐቅ መሆኑን ይገልጻል፤ ይሁን እንጂ በቤተ ክርስቲያን ሥር የተቋቋመው ማኅበረ ቅዱሳን ከላይ የተጠቀሱትን መሠረታዊ የቤተ ክርስቲያን መዋሮችን በመሻማትና ሌላ ሁለተኛ መዋቅር በማደራጀት እንደዚሁም ሌላ የገንዘብ ቋት በመፍጠር ቤተ ክርስቲያኗ ለሁለት የሚከፍል የአሠራር ስህተት ከፈጸመ ውሎ ማደሩን፡፡

በተለይም ከቤተ ክርስቲያን የበላይ አመራር የሚሰጠውን መመሪያ አለመቀበል፣ ይልቁንም ሕገ ወጥና ሥርዓት አልባ ደብዳቤዎችን አሻቅቦ ወደላይ በመጻፍ መሪዎችን መቃወም እያስፋፋና እያሰራጨ መምጣቱ የቤተ ክርስቲያን አጋርነቱን ጥያቄ ውስጥ ከቶታል፡፡

ከዚህም አልፎ ተርፎ የቤተ ክርስቲያንዋ ከፈተኛ የትምህርት ተቋማት፣ የአብነት ትምህርት ቤቶች፣ ማሠልጠኛዎችና ሰንበት ትምህርት ቤቶች፣ ገዳማትና የአስተዳደር መዋቅሮች በአጠቃላይ የተሐድሶ መፈልፈያና መሰግሰጊያ ሆነዋል በማለት በሕትመትና የኤሌክትሮኒክስ ሚድያዎቹ በማሰራጨት በቤተ ክርስቲያኗ ህልውና ላይ ያካሄደውን የስም ማጥፋት ዘመቻ እንዲሁ በቀላሉ የሚታለፍ አለመሆኑን በመግለጽ ማኅበረ ቅዱሳን ደብዳቤ ከደረሰው ቀን ጀምሮ ሊያደርጋቸው የሚገባ ከ1-4 ተራ ቁጥር የተዘረዘሩት በማሳወቅ ደብዳቤው ከተላለፈበት ቀን ጀምሮ ባሉት አምስት ቀናት መመሪያውን ተቀብሎ ተግባራዊ ካላደረገ በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት የማስተካከያ ሥራ ለመሥራት የሚገደድ መሆኑን በጥብቅ አስታውቋል፡፡

በሌላ በኩል የደብረ ብርሃን የማኅበረ ቅዱሳን ንዑስ ማዕከል በቀን የካቲት 13 ቀን 2008 ዓ.ም በቁጥር ደ/ብ/ማ/01/111/2008 የጠራው ሕገ ወጥ ስብሰባ በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ኤፍሬም የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ታገደ፣ ብፁዕነታቸው በቁጥር 349/34/2008 በቀን 11/06/2008 ዓ.ም በጻፉት ደብዳቤ ከሀገረ ስብከቱም ሆነ ከመንበረ ፓትርያርኩ ፈቃድ ሳይገኝ ስለሃይማኖት ጉዳይ በየሆቴሉ መሰብሰብ ሕገ ወጥ መሆኑን አስገንዝቦአል፡፡

ውድ አንባቢያን ቅዱስ ፓትርያርኩ ለመጨረሻ ለማሕበሩ የጻፉት የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ከዚህ በታች አቅርበናል ተከታተሉት፡፡

መልካም ንባብ

ቅዱስ ፓትርያርኩ ለመጨረሻ ለማሕበሩ የጻፉት የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ

የፎንት ልክ መቀየሪያ