Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

የካቲት 3 ቀን 2008 ዓ/ም


እኛ የኢትዮጵያ ኣርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የመምሪያና የድርጅቶች ኃላፊዎችና ምክትል ኃላፊዎች እንዲሁም የኮሌጆች ኃላፊዎች ዛሬ የካቲት 3 ቀን 2008 ዓ.ም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በተገኙበት በቤተክርስቲያኒቱ ሁለንተናዊ ችግሮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት አድርገናል፡፡

በውይይታችንም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሃይማኖታዊ፣ በማኅበራዊና በኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ዙሪያ የሚታዩ ጠንካራና ደካማ ጐኖች ተገምግመው በአፈጻጸም ወቅት የታዩ ጠንካራ ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ፣ በአፈጻጸም ወቅት የታዩ ደካማ ሥራዎችም ተገቢው ክትትልና ድጋፍ እየተደረገላቸው የተጠናከረ ውጤት እንዲያመጡ ለማድረግ የሚያስችል ሥራ እንዲሠራ ማድረግ እንደሚገባ አምነንበታል፡፡ ቤተክርስቲያኒቱ አገልግሎቷን የበለጠ ለማስፋፋትና ለማዘመን ትችል ዘንድም መከተል በሚገባት የለውጥ ሂደት ዙሪያ በተደረገው ውይይት የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

Picture 023 Picture 025 Picture 026 Picture 027 Picture 028 Picture 029 Picture 030 Picture 031 Picture 032 Picture 033 Picture 034 Picture 035 Picture 036 Picture 037

ከዚህም ጋር በእለቱ ከታዩት ጉዳዮች መካከል ማኅበረ ቅዱሳን በኀዳር ወር አጋማሽና በጥር ወር የመጀመሪያ አጋማሽ ቀናት ላይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ኰሌጆችና በቤተክርስቲያኒቱ ተቅዋማት በአጠቃላይ በጻፈው ጋዜጣ በጀምላ በቤተክርስቲያኒያት ተቅዋማት በጅምላ በመናፍቅነት የፈረጀና የኮሌጆቹን ህልውና የተፈታተነ በመሆኑ በየኮሌጅቹ ያሉ አመራሮችና ደቀ መዛሙርትን በእጅጉ ያሳዘነ፣ ያስቆጣና ለፍትሕ ጥያቄ እንዲነሣሡ ያደረገ ጉዳይ መፈጠሩን ጉባኤው ተገንዝቧል፡፡

በዚህም ማኅበሩ የኮሌጆቹን ስም በማጥፋትና ሰድቦ ለሰዳቢ በመስጠት ኮሌጆቹ በሕዝበ ክርስቲያኑ ዘንድ በጥርጣሬ እንዲተዩ ለማድረግ በሌለው ሥልጣን በመናፍቅነት መፈረጁ አግባብነት የሌለው መሆኑን ጉባኤው በመገንዘብ ድርጊቱን በጽኑ ያለአንዳች የድምጽ ልዩነት አውግዞታል፡፡

ማኅበሩ ከኀዳር 16-30 ቀን 2008 ዓ.ም ባወጣው ጽሑፍ ኮሌጆቹን በጅምላ በመናፍቅነት ከፈረጀ በኋላ ጥር 1-15 ቀን 2008 ዓ.ም ባወጣው ጽሑፍ ደግሞ የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳደር መዋቅር ፣ የአብነት ት/ቤቶች ፣የሰንበት ት/ቤቶች ፣ ማሠልጠኛዎች ፣ የቤተክርስቲያኒቱ ኮሌጆች በመናፍቃን ተሰግስገውበታል፡፡ ሲል ጽፎአል፡፡ ይህ ሁሉ ድርጊትም ቤተክርስቲያኒቱን ለማፈራረስ ሆን ተብሎ የተከናወነ ድርጊት መሆኑን ጉባኤው ተገንዝቧል፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን ስምዐ ጽድቅ በተጻፈ ጋዜጣ ያወጣው ጽሑፍ ቤተክርስትያኒቱን ሰድቦ ለሰዳቢ የሰጠ ብቻ ሳይሆን በቤተክርስቲያኒቱ ተቋማትና በሕዝበ ክርስቲያኑ መካከል መተማመንና መደማመጥ እንደይኖር የሚያደርግ አደገኛ አካሔድ በመሆኑ ቤተክርስቲያኒቱን ፈተና ላይ ጥሏታል፡፡ማኅበሩ ይህን ዓይነት ስልት በመጠቀም ቤተክርስቲያኑን ከሕዝበ ክርስቲያኑ ለማለያየት የተጠቀመበት መንገድ ምን ትርፍ ለማግኘት እንደሆነ ጉባኤው ግልጽ ሆኖለታል፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን ከሥነ ምግባር ውጭ በሌለው ሥልጣንና መዋቅሩን ባልጠበቀ ከቅዱስ ፓትርያርኩ አቻ ለአቻ ሆኖ የጻፈው ደብዳቤና እርሱን ተከትሎ አመራሮቹ በየግል ጋዜጣውና ማኅበራዊ ድረ -ገጾች የሰጧቸው ቃለመጠይቆችና የለቀቋቸው ጽሑፎችም ጉባኤውን በእጅጉ አሳዝኗል፡፡ የዚህችን ታላቅ ቤተክርስቲያን መሪን በዚህ መልኩ መጋፋቱ በቤተክርስቲያኒቱ ታሪክ ታይቶም ሆነ ተስምቶ የማይታወቅ መሆኑን ጉባኤው አውስቷል በቤተክርስቲያኒቱ ሥርዓት የቤተክርስቲያኒቱን የመጨረሻ ሉዓላዊ ሥልጣንና ክብር ማረጋገጫ የሆነውን ቅዱስ መንበር መዳፈር ከኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮና ቀኖና አንጻር ተቀባይነት ያለው ባለመሆኑ ጉባኤው በጽኑ አውግዞታል፡፡
በአጠቃላይ በቤተክርስቲያኒቱ ሁለንተናዊ ጉዳይ ዙሪያ የተወያየው ጉባኤው የሚከተለውን የአቋም መገለጫ አውጥቶ ጉባኤውን በጸሎት አጠናቋል፡፡

መግለጫ

 1. ማኅበረ ቅዱሳን በቤተክርስቲያኒቱ ተቋማት የመናፍቃን እንቅስቃሴ መኖሩን ካረጋገጠ ኦርቶዶክሳዊውን ሥርዓት በጠበቀ መልኩ ለሚመለከተው አካል በማቅረብ መፍትሔ እንዲሰጥበት ማድረግ ሲገባው በራስዋ ጋዜጣ ገዳማት ፣ የአብነት ት/ቤቶችን ፣ ኮሌጆችን ፣ የሰንበት ት/ቤቶችን ፣ በጀምላ በመናፍቅነት በመፈረጁ ካህናትን፣ ምእመናንንና ቤተክርስቲያኒቱን አደጋ ላይ ሊጥል በሚችል አኳኋን ከኀዳር 16-30 ቀን 2008 ዓ.ም 23ኛ ዓመት ቁጥር 5 ቅጽ 23 ቁጥር 333 "መንፈሳዊ ኮሌጆች እና ደቀ መዛሙርቱ ምን እና ምን ናቸው" በሚል ርእሰ እንዲሁም ከጥር 1-15 ቀን 2008 ዓ.ም 23ኛ ዓመት ቁጥር 2 ቅጽ 23 ቁጥር 330 "ገርፎ የመጮኽ የተሐድሶዎች የማደናገሪያ ስልት" በሚል ርእስ ባወጣው ጽሑፍ በሁሉም የቤተክርስቲያኒቱ መዋቅር መናፍቃን እንደተሰገሰጉ በመግለጽ ቤተክርስቲያኒቱን ሰድቦ ለሰዳቢ በመስጠቱ በጥብቅ አውግዞ የቤተክርስቲያኒቱን መዋቅር በአጠቃላይ በጀምላ በመናፍቅነት በመፈረጅ ለጻፈው ጽሑፍ በአስቸኳይ በጽሑፍ ይቅርታ እንዲጠይቅና በሁሉም ሚዲያዎቹም ለጻፈው ጽሑፍ ማስተባበያ እንዲሰጥ ይህን ማድረግ ካልቻለ ጋዜጣው እንዲታገድና በሕግ እንዲጠየቅ፤
 2. የማኅበሩ አመራር አካላት በማን አለብኝነት በየግል ጋዜጣው የቤተክርስቲያኒቱን መሪ በመዳፈር የሚያወጡት ጽሑፍ ተገቢነት የሌለውና ኢ-ክርስቲያናዊ ከመሆኑም በላይ ማኅበሩ ለቤተክርስቲያኒቱ ክብር ግድ የሌለውና አሁንም ቤተክርስቲያኒቱን ሰድቦ ለሰዳቢ ለመስጠት ቆርጦ የተነሣ መሆኑን የሚያመለክት ሆኖ ይታያል በተለይም ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በቁጥር ል/ጽ/179/336/2008 በቀን 16/5/2008 ዓ.ም ለሦስቱ ኮሌጆች በጽሑፍ የሰጡትን መመሪያ በመቃወም ማበረ ቅዱሳን በቁጥር ማቅሥ አመ1239/02/ለ/08 በ24/05/2008 ዓ.ም የጻፈው ሥርዓት አልባና ሕገ ወጥ ጽሑፍ የቤተክርስቲያኒቱን ሉዓላዊ ክብር የተዳፈረ ለቤተክርስቲያን አበው የመታዘዝ ባህልና እምነትን የጣሰ መሆኑን በጽኑ ተቃውሞ ማበሩ በድፍረት የጻፈውን ደብዳቤ በአስቸኳይ እንዲያነሣና ቅዱስ ፓትርያርኩን እና ቤተክርስቲያኒቱን በጽሑፍ ይቅርታ እንዲጠይቅ ይሕንንም በሚዲያዎቹ ለሕዝቡ በይፋ እንዲገልጽ፤
 3. ማኅበሩ ቤተክርስቲያኒቱ ለሃይማኖት አስተምህሮ በፈቀደችለት የራስዋ ጋዜጣና መጽሒት "የእናት ጡት ነካሽ ሆኖ"በቤተክርስቲያኒቱ ዙሪያ የሚያወጣውን መሠረተቢስ የስም ማጥፋት ዘመቻ ከዛሬ ጀምሮ እንዲያቆም ፤
 4. ቤተክርስቲያናችን ማኅበሩ በሚከተለው የትንኮሳ ተግባር በአሁኑ ጊዜ ያለችበት ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ እየሆነ ስለመጣ የመምሪያ ኃላፊዎች ፣ የድርጅት ኃላፊዎች ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትና የመንግሥት አካላት በቤተክርስቲያኒቱ ሁለንተናዊ ችግሮች ዙሪያ የምንወያይበት ሁኔታ እንዲመቻች ፤
 5. ቅዱስ ሲኖዶስ ቤተክርስቲያኒቱ በአሁኑ ወቅት ያለችበትን አሳሳቢ ሁኔታ በመገንዘብ እና በሒደት የሚያስከትለውን አደጋ በማጤን የቤተክርስቲያኒቱን ክብር የማስጠበቅ ሥራ ሊሠራ ይገባል በማለት ልዩነት በሌለው በአንድ ድምፅ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

የካቲት 3 ቀን 2008 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የፎንት ልክ መቀየሪያ