Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ከብፁዕ ወቅዱስ ፖፕ ፋራንሲስ በተደረገላቸው ሐዋርያዊ የጉብኝት ጥሪ መሠረት ወደ ቫቲካን ከተማ በመጓዝ የአራት ቀናት ሐዋርያዊ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

በዚሁ ጉብኝት ቅዱስ ፓትርያርኩ ከብፁዕ ወቅዱስ ፖፕ ፋራንሲስ ጋር እንዲሁም ከሌሎች የቫቲካን ከተማና የቤተ ክርስቲያኒቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር በልዩ ልዩ ሃይማኖታዊና ማኅበራዊ ርዕሰ ጉዳዮች ሰፊ ውይይቶችን አድርገዋል፡፡

Picture 003 Picture 034 Picture 087 Picture 172 Picture 217 Picture 247 Picture 259 Picture 265 Picture 285 Picture 440 Picture 446 Picture 467 Picture 470 Picture 512 Picture 515 Picture 523 Picture 530 Picture 535 Picture 539 Picture 556

በውይይታቸው በሁለቱ ጥንታውያን ዓለም አቀፍ አብያተ ክርስቲያናት መካከል የነበሩ ቀደምት ግንኙነቶች ስለሚቀጥሉበትና ስለሚጠናከሩበት፣ እንዲሁም በጋራ በመሆን በዓለም ሰላም፣ በሰው ልጆች ደኅንነት በአካባቢ ጥበቃ፣ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ስለተከሰቱ የድርቅ አደጋዎችና አክራሪነትን በተመከከቱ ጉዳዮች አብረው ስለሚሠሩበት ሁኔታ ተወያይተዋል፡፡
በሁለቱ ቅዱሳን አባቶች መካከል በተደረገው በዚሁ ውይይት አስቀድመው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ለፖፕ ፍራንሲስ ባደረጉት ንግግር ጉብኝታቸው ቀደም ሲል የነበሩ አባቶች ያደርጉት የነበረውን መልካም ግንኙነት ፈለግ በመከተል የተደረገ፣ በሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት መሪዎች መካከል ያለውን ወንድማዊ ግንኙነት ለማጠናከር፣ በጋራ ሁነው ስለ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ለማሰማት እንደሆነ ሲገልጹ፤ ፖፕ ፍራንሲስ በቅርቡ በአክራሪ ሽብርተኞች የተገደሉ ስደተኞች ኢትዮጵያውያን አስመልክተው ላስተላለፉት ፈጣን የማጽናኛ መልእክትና በሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት መካከል ያለው ግንኙነት ለሚያደርጉት ልባዊ ድጋፍ ያላቸውን ምስጋና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ፖፕ ፋራንሲስ በበኩላቸው ለቅዱስ ፓትርያርኩ ባደረጉት ንግግር በቅዱስነታቸው ጉብኝት ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው በመግለጽ ቅዱስ ፓትርያርኩ በሀገር ውስጥ የሃይማኖት ነፃነት፣ መከባበርና መቻቻል፣ እንዲሆን በሃይማኖት ተቋማት መካከል የሚደረጉ መልካም ግንኙነቶች እንዲጠናከሩ የሚያደርጉትን ጥረት አድንቀዋል፡፡


የሮም ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ፖፕ በንግግራቸው እንደገለጹት ኢትዮጵያውያን በአሁኑ ጊዜ ሀገራቸውን ከድኅነት ለማላቀቅና የሕዝቡን የኑሮ ሁኔታቸውን ለማሻሻል የሚያደርጉትን ጥረት አድንቀው፣ ለፍትሕና እኩልነት መረጋገጥ በተለይም የሕግ በላይነትንና የጾታ እኩልነትን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት እንደሚያደንቁ ገልጸዋል፡፡

ከአየር ንብረት መለወጥ ጋር በተያያዘ የተፈጠረው የውሃ እጥረት በሀገሪቱ በጋራ የተያዘውን በርካታ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ የዕድገት እንቅስቃሴ በመጠኑም ቢሆን እንቅፋት እንደሚመጣ ቢታመንም አሁንም የተሻለ ለውጥ ለማምጣት ብዙ አማራጭ እንዳለ፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም በዚሁ ጥረት የበኩሏን ለማድረግ፤ በቅዱስነታቸው መሪነት የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በጋራ የሚጠበቅባትን ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል፡፡

ፖፕ ፍራንሲስ እንደገለጹት በቀጣይም በሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት መካከል ያለው ግንኙነት ጠንክሮ እንደሚቀጥል፣ የቅዱስ ፓትርያርኩ ጉብኝትም ለዚህ አዲስ ምዕራፍ እንደሚከፍት እምነታቸው መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ከፖፕ ፍራንሲስ ጋር ከነበራቸው ውይይት በኋላ "የጉብኝቱና የዚህ ሐዋርያዊ ጉዞ ዋና ዓላማ በሁለቱ አብያተ ክርስያናት መካከል የቆየውን ግንኙነት በይበልጥ ለማጠናከር፣ በአሁኑ ጊዜ በመላው ዓለም ያለውን አለመረጋጋትና የሰላም መደፍረስ አስመልክቶ የሃይማኖት አባቶች ማድረግ ስለሚገባቸው ጥረትና በሰው ልጆች አጠቃላይ ደኅንነት ዙሪያ ስለሚያደርጉት ጥረት መጠናከር የጋራ ምክክርና ውይይት ለማድረግ ነው" በማለት በሮም ለሚገኙ ዓለም አቀፍና የኢጣሊያ ብሔራዊ የብዙኀን መገናኛዎች ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ቅዱስነታቸው በነበራቸው የአራት ቀናት ሐዋርያዊ ጉብኝት በርካታ ቅዱሳት መካናትን እና ታሪካውያን ቦታዎችን ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ከአራት መቶ ዓመታት በፊት ወደ ሮም ተጉዘው በነበሩ ኢትዮጵያውያን የተመሠረተውንና በአሁኑ ጊዜ "ቅዱስ እስጢፋኖስ በቫቲካን የኢትዮጵያ ኮሌጅ" በመባል የሚታወቀውን ጥንታዊ ኮሌጅ ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝታቸው በቫቲካን የውጭ ግንኙነት ዋና ጽ/ቤት ተገኝተው ባደረጉት ንግግርም በአሁኑ ጊዜ ቤተ ክርስቲያኒቱ በልማት፣ በማኅበራዊ አገልግሎት፣ በዓለም አቀፍ ግንኙነት፣ በትምህርትና በበጎ አድራጎት ሥራዎች ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገች መሆኑን፣ በሀገሪቱ የሚገኙ የሃይማኖት ተቋማት የጋራ ጉባኤ በመመሥረት የሃይማኖት ተቋማት በሰላምና በአንድነት ለሚያበረክቱት አስተዋጽኦ የበኩሏን ድርሻ እየተወጣች መሆኗል ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም በዚሁ ጉብኝት በፈረንሳይና በቫቲካን እንዲሁም በኢጣሊያ ሮም የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ መንግሥት አምባሳደሮች፣ በኢጣሊያና በሌሎች የአውሮፓ ሀገሮች የሚገኙ የቤተ ክርስቲያኒቱ አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ የተገኙ ሲሆን ቅዱስነታቸው በኢጣሊያ ልዩ ልዩ ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን በሮም ከተማ ሰብስበው አነጋግረዋል፡፡ ቅዱስ ፓትርያርኩ ለኢትዮጵያውያን ባተላለፉት መልእክት "በአሁኑ ጊዜ ሀገራችን ኢትዮጵያ በከፍተኛ የጋራ እድገት ድኅነትን በመቅረፍ ጥረት ላይ እንደምትገኝ ገልጸው በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለዚህ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የሚጠበቅባቸውን ግዴታ በመወጣት የትውልድ ግዴታቸውን እንዲያበረክቱ፣ መንፈሳዊ ሕይወታቸውንና አንድነታቸውን ጠብቀው በትብብር ሀገራቸውን እንዲያሳድጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የተመራው የቅዱስ ሲኖዶስ አባላትን ያካተተው ልዑክ ከየካቲት 18 እስከ 21 ቀናት 2008 ዓ/ም በጣሊያን ሮም ቫቲካን ያደረገውን የዐራት ቀናት ጉብኝታቸውን ፈጽመው ዛሬ ጥዋት የካቲት 22 ቀን 2008 ዓ/ም አዲስ አበባ ገብቷል፡፡

የፎንት ልክ መቀየሪያ