Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

የካቲት 22 ቀን 2008 ዓ.ም.

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
 • ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት
 • የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የመምሪያና የድርጅት ኃላፊዎችና ሠራተኞች
 • የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች
 • የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች
 • ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን
 • የሟች ቤተ ሰቦችና ዘመድ ወዳጅ
 • በአጠቃላይም በሊቀ ትጉሃን ገብረ ክርስቶስ ኃይለ ማርያም የቀብር ሥነ ሥርዓት አፈጻጸም መርሐ ግብር ላይ የተገኛችሁ ሁላችሁ

ከዚህ በመቀጠል የሊቀ ትጉሃን ገብረ ክርስቶስ ኃይለ ማርያምን አጭር የሕይወት ታሪክ እናሰማለን።

ሊቀ ትጉሃን ገብረ ክርስቶስ ኃይለ ማርያም ከአባታቸው ከአቶ ኃይለ ማርያም ገብረ ሥላሴና ከእናታቸው ከወ/ሮ ሰብለ ወንጌል ወልደ ሥላሴ በትግራይ ክልል በቀድሞ አጠራር በተምቤን አውራጃ በበግዐ ማርያም ገዳም አካባቢ ጥቅምት 16 ቀን 1931 ዓ.ም. ተወለዱ። ዕድሜአቸው ለትምህርት ሲደርስ በዚሁ በተወለዱበት አካባቢ በሚገኘው በበግዓ ማርያም ገዳም ከተመደቡት መምህራን መሠረታዊውን የቤተ ክርስቲያን የአብነት ትምህርት ተከታትለው ከተማሩ በኋላ ገና በወጣትነት ዕድሜ የማስተዋል ጸጋ የተቸራቸው በመሆኑ ለአካባቢው የአጥቢያ ጻኛ ዋና ጸሐፊ በመሆን አገልግለዋል።

 • ሊቀ ትጉሃን ገብረ ክርስቶስ ኃይለ ማርያም ትምህርታቸውን በመከታ ተልና የነበራቸውን የመንፈሳዊነት ዝንባሌ በማጠናከር በ1941 ዓ.ም. ዲቁናን ተቀብለው እስከ 1950 ዓ.ም. ድረስ በገዳማዊ ሕይወት ሲያገለግሉ ቆይተዋል።
 • ሊቀ ትጉሃን ገብረ ክርስቶስ ኃይለ ማርያም በ1952 ዓ.ም. ወደ አዲስ አበባ ከመጡ በኋላ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በወቅቱ የገዳሙ አስተዳዳሪ ከነበሩት ከመምህር ገብረ ማርያም ወርቄ መዝገብ ቅዳሴን እየተማሩ፥ የጸሎተ ማኅበር አገልግሎት እያደረሱ ቆይተዋል። በመቀጠልም በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት በኩል ተቀጥረው የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በነበሩት በብፁዕ አቡነ ሉቃስ ፈቃድ በአርሲ ሀገረ ስብከት መንበረ ጵጵስና ሥር ከላእካን አርድእት አንዱ በመሆን ሠርተዋል።
 • ሊቀ ትጉሃን ገብረ ክርስቶስ ኃይለ ማርያም እስከ 1955 ዓ.ም. ድረስ በዚያው በአርሲ ሀገረ ስብከት በአቡነ ቀሲስነት አገልግለዋል።
 • ከ1956 እስከ 1958 ዓ.ም. ድረስ በኤርትራ ሀገረ ስብከት በዚሁ በያዙት የአቡነ ቀሲስነት ሥራ እያገለገሉ ቆይተዋል።
 • ከ1959 ዓ.ም. እስከ 1963 ዓ.ም. ድረስ በወለጋ ሀገረ ስብከት በግብረ ገብነት መምህር ሆነው ተመድበው በማስተማር የተለያየ እምነት ያላቸ ውን ወደ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት መልሰዋል።
 • ሊቀ ትጉሃን ገብረ ክርስቶስ ኃይለ ማርያም እስከ 2006 ዓ.ም. ድረስ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ተመድበው፦
 • በሬድዮ ፕሮግራም
 • ተዘዋዋሪ የስብከተ ወንጌል ጓድ በመሆን
 • በሰበካ ጉባኤ አደራጅነት
 • በማዕዶት መጽሔት አዘጋጅነት አገልግለዋል።
 • የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ ዋና ጸሐፊና ምክትል ኃላፊ በመሆን፤ እንዲሁም የቅዱስ ሲኖዶስ ምክትል ጸሐፊ በመሆን ለረጅም ዘመናት ሰፊ አገልግሎት አበርክተዋል።
 • ሊቀ ትጉሃን ገብረ ክርስቶስ ኃይለ ማርያም እንደ ቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ የተለያዩ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሥልጠናዎችን በመው ሰድ፦
 • የመጽሐፍ ቅዱስን ምሥጢር በመመራመር
 • ቅዱሳት መጻሕፍትን በማመስጠር
 • አንብቦ በመረዳትና በማስረዳት ድርሻቸውን የተወጡ የስብከተ ወንጌል መምህርና የመድረክ ሰው ነበሩ።
 • ሊቀ ትጉሃን ገብረ ክርስቶስ ኃይለ ማርያም በቤተ ክርስቲያኒቱ ማእከላዊ አስተዳደር ዘርፍ፥ በሌሎችም ተዘዋውረው በሠሩባቸው አህጉረ ስብከት ሁሉ የቤተ ክርስቲያኒቱን መራሑተ ምግባር መሠረት በማድረግ ከበላይ አካል የሚሰጠውን መመሪያ ተቀብለው የሚተገብሩ፥ በቅን ኅሊና፥ በትሑት ሰብእና ሆነው ከመላ ሠራተኞች ጋር ተባብረው የሚሠሩ፥ ፍቅረ ቢጽ ያደረባቸው፥ ኦሆ በሃሊና ትጉህ ሠራተኛ በመሆናቸው «ሊቀ ትጉሃን» በሚል የማዕርግ መጠሪያ ስም እንዲጠሩ ተፈቅዶላቸው እስካ ሁን ድረስ ሲገለገሉበት ኖረዋል።

ሊቀ ትጉሃን ገብረ ክርስቶስ ኃይለ ማርያም ከወ/ሮ በላይነሽ ሐጎስ ጋር ሕጋዊ ጋብቻን በመፈጸም የሦስት ወንዶችና የሦስት ሴቶች ልጆች አባት ለመሆን በቅተዋል። ልጆቻቸውንም በሚገባ አስተምረው ለቁም ነገር አብቅ ተዋል። የልጅ ልጆችንም ለማየት የበቁ አባት ነበሩ።

ከጊዜ በኋላም የነበራቸውን የሥራ ፍቅር በማጐልበት ወደ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ተዛውረው የበለጠ አገልግሎት ማበርከት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቶ በተዛወሩበት ቦታ የኆኅተ ጥበብ ጋዜጣ አርታኢ በመሆን ምድብ ሥራቸውን በማከናወን ላይ እንዳሉ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው የካቲት 21ቀን 2008 ዓ.ም. በተወለዱ በ77 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

የሊቀ ትጉሃን ገብረ ክርስቶስ ኃይለ ማርያም አስከሬን ወደ መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተወስዶ ስብሐተ ማኅሌትና ጸሎተ ፍትሐት ሲደረስበት አድሮ ከተቀደሰበት በኋላ፤

 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
 • ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት
 • የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የመምሪያና የድርጅት ኃላፊዎችና ሠራተኞች
 • የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች
 • የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች
 • ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን
 • ቤተ ሰቦችና ወዳጅ ዘመድ በተገኙበት የካቲት 22 ቀን 2008 ዓ.ም. በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የቀብራቸው ሥነ ሥርዓት ተፈጽሟል።

እግዚአብሔር አምላካችን ነፍሳቸውን
ለቅዱሳን አበው ባዘጋጀው መካነ ዕረፍት ያሳርፍልን

ለቤተ ሰቦቻቸው መጽናናትን ይስጥልን

የፎንት ልክ መቀየሪያ