Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት

 • ክቡራን ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣
 • ክቡራን የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር እንግዶች
 • ክቡራን የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች
 • ክቡራን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን
 • በአጠቃላይ በዚህ በዓል የተገኛችሁ ሕዝበ ክርስቲያን ምእመናን ወምእመናት

ሠያሜ ካህናት የሆነው ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለሦስተኛው ዓመት በዓለ ሢመተ ፓትርያርክና በሰላም አደረሳችሁ፡፡
ሁሉንም ማድረግ የሚችልና ከኅሊናት ሁሉ በላይ የሆነ እግዚአብሔር አምላካችን በሥራችን ሁሉ እየመራንና እየደገፈን ከዚህ ዕለትና ሰዓት ስላደረሰን ከሁሉ በፊት ክብርና ልዕልና፣ አምልኮና ምስጋና ለእርሱ እናቀርባለን ፡፡
‹‹መነ እፌኑ ኀበ ሕዝብየ እሥራኤል፤ ወደ ሕዝቤ ወደ እሥራኤል ማንን እልካለሁ?›› (ኢሳ.6፡8)፤

Picture 003 Picture 008 Picture 080 Picture 105 Picture 108 Picture 114 Picture 120

ይህ ቃል በክፋት፣ በዓመፅና በኃጢአት የተጎዱትን የእሥራኤል ሕዝብ የሚያስተምር የሚመክርና የሚገሥጽ ጠንካራ ነቢይ ለመላክ በፈለገ ጊዜ እግዚአብሔር የተናገረው ኃይለ ቃል ነው ፡፡
እግዚአብሔር ለማንም የማያዳላ ፈታሒ በርትዕ ኰናኒ በጽድቅ ቢሆንም መሐሪ፣ መዝገበ ርኅራኄና መፍቀሬ ሰብእ ነውና ሰዎች የእርሱን መንገድ ስተው ወደጥፋት ሲያዘነብሉ ለንሥሐ ዕድል ለመስጠት በትዕግሥት ይጠብቃቸዋል ፡፡
በአጥፊዎች ላይ ከመፍረዱ በፊትም በተለያየ መንገድ እንዲመከሩ፣ እንዲማሩና እንዲመለሱ ዕድል ይሰጣቸዋል፤ ይህም የሚያደርገው በጥንተ ፍጥረት የሰጣቸውን ነጻ ፈቃድ በአምላክነቱ ኃይል ሳይጋፋ ነው፡፡

በመሆኑም እግዚአብሔር በክፋት፣ በበደል፣ በአምልኮ ጣዖትና በገቢረ ኃጢአት ባህር ወዲያና ወዲህ የሚዋልሉ ሕዝበ እሥራኤልን የሚያስተምር፣ የሚመክርና የሚገሥጽ ጥቡዕ ነቢይን መላክ ፈለገ፤ ይህንም ፈቃዱ ወደ ሕዝቤ ወደ እሥራኤል ማንን እልካለሁ? ማንስ ይሄድልናል? በማለት ለነቢዩ ለኢሳይያስ አስታወቀ፡፡
ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስም በሕይወቱ ውስጥ ያለውን ክፍተት ከመግለፅ ጋር ችግሩ ከተወገደለት እርሱ መልእክተኛ ሆኖ ለማገልገል ፈቃደኛ እንደሆነ በትሕትና ገለፀ፡፡
እግዚአብሔር የኢሳይያስን ፈቃደኝነት ተመልክቶ የነበረበትን የለምፅ በሽታ ካስወገደለት በኋላ ቃሉን በእርሱ በኩል ለሕዝበ እሥራኤል እንዲደርስ አድርጎአል ፡፡
ከዚህም የተነሣ በኢሳይያስ ነቢይ በኩል የተላለፈው የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ድረስ ዓለም እየተማረበት፣ እየተመከረበትና እየተገሠፀበት ይገኛል፡፡
ይህ ጽዋዔ እግዚአብሔር ዛሬም በዚህ ዘመን ለሚገኝ ትውልድ የሚጣራ የእግዚአብሔር ሕያው ድምፅ ነው፤ ብዙ ክፋት፣ አስመሳይነት፣ አታላይነት፣ ጥቅመኝነት፣ አድላዊነት፣ ኝየፍትሕ መዛባትና ነውረ ኃጢአት ከመቼውም ጊዜ በባሰ ሁኔታ ያጥለቀለቀው የዘመናችንን ዓለም የሚያስተምር፣ የሚመክርና የሚገሥፅ ጠንካራ የወንጌል ልኡክ ዛሬም እግዚአብሔር ይፈልጋል፡፡
በኢሳይያስ ጊዜ የነበረ የመምህራን እጥረት ዛሬም እንዳለ ነው፤ ልዩነቱ በዚያን ጊዜ ይጣራ የነበረ እግዚአብሔር ብቻ ነው፤ ዛሬ ግን እግዚአብሔርም ሕዝቡም በጥምር ሆነው እየተጣሩ ነው፤ አስተምሩን የሚሉ ወገኖች በዓለም ዙሪያ ዛሬም ብዙ ናቸው፤ ሆኖም ለዚህ የሚሆን በቂ መልስ ሲሰጥ አይታይም ፡፡
ምክንያቱም ‹‹በመልእክተ ወንጌል›› ዙሪያ ብዙ ሊያሠሩ የሚችሉ ተግባራት በሚገባ አለመሠራታቸው ነው ፡፡ ዛሬ በከፍተኛ ደረጃ እያከበርነው ያለ በዓለ ሢመተ ክህነት ይህን ጽዋዔ እግዚአብሔር ወሰብእን በትክክል ማዳመጥ የምንችልበት በዓል ሊሆን ይገባል፡፡
ዛሬ በቂ ባልሆኑ አንዳንድ ምክንያቶች ከቤተ ክርስቲያናችን ጉያ እያፈተለኩ የሄዱ ውሉደ ክርስቲያን ቀላል ናቸው የሚል እምነት ባይኖረንም አሁንም ቢሆን በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር የቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ ፈላጊዎች እጅግ ብዙ ናቸው፤ ይህ መልካም ዕድልና ክፍት በር ቤተ ክርስቲያናችን ሊያመልጣት አይገባም፤ የቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ ቀኖና እና ባህል በአሁኑ ጊዜ ካለው የክርስትና ዓለም በተሻለ ሁኔታ የዘመነ ሐዋርያትን አስተምህሮና ቀኖና ይዞ መገኘቱ ቤተ ክርስቲያናችንን በእጅጉ የሚያኮራ ነው ፡፡
ይህ እውነተኛ ኩነት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት በሙሉ ያውቁልናል፤ ይህንን ሐቅ የተገነዘቡና በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን ወገኖቻችን የቤተ ክርስቲያናችንን እምነት፣ ቀኖናና ባህል ማወቅ ይፈልጋሉ፤ ልታስተምራቸውም ይፈልጋሉ በመሆኑም ቤተ ክርስቲያናችን ይህን ኃላፊነት መውሰድና መወጣት አለባት ፡፡
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ክቡራን እንግዶች !
የዘመናችን አሠራር በተደራጀና በተጠና ሁኔታ፣ መነሻ ዓላማና መድረሻ ግብ ባለው ጥናት የሚካሄድ ከመሆኑ አንጻር ቤተ ክርስቲያናችን በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር ወጥነት ባለው አፈጻጸምና በተደራጀ አሠራር መልእክተ ወንጌልን ለዓለም ሁሉ ለማዳረስ መነሣት አለባት ፡፡
ውሉደ ክህነት በአጠቃላይ ማለትም ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጀምሮ እስከ ንፍቀ ዲያቆን ያሉት ሁሉ ሊያጤኑት የሚገባ ዓቢይ ነገር ከሁሉ በፊት ተቀዳሚ የቤተ ክርስቲያን ሥራ ስብከተ ወንጌል መሆኑን ነው፤ ስብከተ ወንጌልን መደበኛና ቀዋሚ ተግባር አድርጋ የማትንቀሳቀስ ቤተ ክርስቲያን ህልውናዋ አስተማማኝ አይሆንም ፡፡
ቤተ ክርስቲያናችን ለሁለት ሺሕ ዘመናት ያህል በየዘመኑ በልዩ ልዩ ኃይሎች የተጋረጡባትን እንቅፋቶች ሁሉ በመቋቋም እዚህ ልትደርስ የቻለችው በስብከተ ወንጌል ኃይል ነው፤ ስብከተ ወንጌል ለቤተ ክርስቲያናችን ህልውና መቀጠል መተኪያ የሌለው ኃይል ነውና፡፡
ስለሆነም ሁላችንም ውሉደ ክህነት ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹ሑሩ ውስተ ኵሉ ዓለም ወስብኩ ወንጌለ ለኵሉ ፍጥረት፣ ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ›› ያለውን ዓቢይ መልእክት ለአፍታ ያህል እንኳ ከአእምሮአችን እንዲወጣ መፍቀድ የለብንም፡፡
የስብከተ ወንጌል ዕውቀት ማእከላት የሆኑት በየገዳማቱ፣ በየአድባራቱና በየቤተ ክርስቲያኑ ለዘመናት ተጠብቀው የኖሩት የአብነት ትምህርት ቤቶቻችን፣ በየሀገረ ስብከቱ የሚገኙ ማሰልጠኛዎቻችንና መንፈሳዊ ኮሌጆቻችን ሁሉ ስብከተ ወንጌልን ተኮር ያደረገና ሁሉንም ተማሪዎች ለመልእክተ ወንጌል ዝግጁ የሚያደርግ ሥርዓተ ትምህርት በመቅረጽ የቤተ ክርስቲያናችንን ህልውና ለማስጠበቅ የበኩላቸውን ሊወጡ ይገባል ፡፡
የቤተ ክርስቲያናችን ዕድገት ወደፊት እንዳይገሠግሥ መሰናክል ሆኖ የሚገኘው የመልካም አስተዳደር እጦት ተወግዶ ከብክነት፣ ከምዝበራና ከአድልዎ የፀዳ አሠራር መረጋገጥ አለበት ፡፡
ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን ዓበይት ነገሮች አስተካክለን ካልሠራን ቀጣዩ ውጤት የሚያምር አይሆንም ፡፡
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ክቡራን እንግዶች፡፡
የበዓለ ሢመተ ፓትርያርክ በዓል የግብረ ክህነት ሥራ በምን ደረጃ ላይ ይገኛል ብለን በማጤን ያሉብንን ክፍተቶች ለመሙላት የምንጠቀምበት መሣሪያ ነው ፡፡
የቤተ ክርስቲያን ሥራ የተደራረበ እንደመሆኑ መጠን ሕዝባችን በሥጋዊም ሆነ በመንፈሳዊ ኑሮው የበለፀገና ያደገ እንዲሆን ደጋግመን ማስተማርና መምከር አርአያ መሆንም ከሁላችን ይጠበቃል፡፡
ቤተ ክርስቲያን ልታድግና ልትለማ የምትችለው ሕዝቡ ሲለማና ሲበለፅግ እንደሆነ መዘንጋት የለበትም፤ ስለሆነም የሀገራችን የልማትና የሕዳሴ ጉዞ በምንም ምክንያት ሳይደናቀፍ የታለመለትን ግብ እንዲመታ ጠንክሮ ማስተማር ከውሉደ ክህነት ሁሉ ይጠበቃል ፡፡
በዚህ ዓመት በዝናም እጦት ምክንያት በሀገራችን የተከሠተው የምግብ እጥረት በወገኖቻችን ላይ አስከፊ ጉዳት እንዳያደርስ ሕዝቡ ወገኑን እንዲረዳ፣ በሚችለውም ሁሉ እንዲያግዝ ማስተማርና መቀስቀስ ይገባናል ፡፡
እንግዲህ እግዚአብሔር ‹‹ወደ ሕዝቤ ማንን እልካለሁ? ማንስ ይሄድልናል?›› በማለት መልእክተኛ ሲፈልግ ያየነው፣ በሕዝቡ መካከል ገብቶ የሕዝቡን ሃይማኖታዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ሊቀርፍ የሚችል አስተምህሮ በመስጠት ሕዝቡን ከልዩ ልዩ ችግሮች የሚገላግል አስተማሪ፣ ሰባኪና መካሪ ፈልጎ እንደሆነ እናስተውል ፡፡
እነሆ እኛም በዚያ ቃል ተጠርተንና ተሹመን ዛሬ በመድረኩ ተገኝተናልና ከእግዚአብሔር የተሰጠንን ዓቢይ መልእክት ተቀብለን ወደሥራ እንሠማራ ፡፡
በመጨረሻም
ሁሉም እንደሚገነዘበው በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ያለውን ሰፊ የአሠራር ክፍተት በወሳኝ መልኩ ለማስተካከል፣ በምትኩም መልካም አስተዳደርን በአስተማማኝ ሁኔታ ለማስፈን በተጀመረው እንቅስቃሴ ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተ ክርስቲያናችንን ሁለንተናዊ ችግር በጥልቀት በማጥናትና በመፈተሸ ከመፍትሔ አቅጣጫ ጋር የሚያቀርብ ዓቢይ ኮሚቴ ሰይሞአል፡፡
በመሆኑም ከአሁን ጀምሮ ኮሚቴው በቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠውን የሥራ ተልእኮ ስለሚጀምር በየደረጃው የምትገኙ የቤተ ክርስቲያናችን ኃላፊዎች፣ የሥራ አመራሮች፣ ካህናትና ምእመናን፣ ለቤተ ክርስቲያናችን መልካም አስተዳደር መረጋገጥ ከኮሚቴውና ከቅዱስ ሲኖዶስ ጎን በመሰለፍ በሚቻላችሁ ሁሉ ቀና ትብብር እንድታደርጉ ጥሪያችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን ፡፡


እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝባችንን ይባርክ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
አሜን
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
የካቲት 24 ቀን 2008 ዓመተ ምሕረት
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

የፎንት ልክ መቀየሪያ