Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

በመምህር ሙሴ ኃይሉ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን አስከትለው የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል መጋቢት 22 ቀን 2008 ዓ.ም በመጎብኘት በሆስፒታሉ ውስጥ እየታከሙ ለሚገኙት የቲቢ ሕሙማንም ልጆቻቸውም ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ አስተላለፉ፡፡

ጉብኝቱ የተጀመረው ሆስፒታሉ አዲስ እያሠራው በሚገኝ ሕንጻ ሲሆን በአዲሱ ሕንጻ ውስጥ የማዋለድ አገልግሎትን ጨምሮ የድንገተኛ እና ሁለገብ ሕክምና እንሚሰጥ በሆስፒታሉ የሥራ ኃላፊዎች እየተገለጸ ከጎበኙ በኋላ በወቅቱ በሆስፒታሉ ውስጥ አገልግሎት እያገኙ ለነበሩት እናቶች እና ሐኪሞች የሰው ሕይወትን ክቡርነት አስመልክተው ሰፋ ያለ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ሰጥተው ይህንን ክቡር የሆነ የሰው ልጅ ሕይወት ለመታደግ ደፋ ቀና ለሚሉ ሐኪሞችም ሆነ ሕይወታቸውን ለማዳን ሕክምና ተቋምን ምርጫ አድርገው ለመጡ ታካሚዎች ጸሎት እና ቡራኬ ሰጥተው አበረታትተዋል፡፡

stpeterhosp1 stpeterhosp2 stpeterhosp3

የጉብኝቱ ሁለተኛ ምዕራፍ የቲቢ ሕሙማን የሚታከሙበት ክፍል የጎነኙ ሲሆን በዚሁ ክፍል ስለሚሰጠው የሕክምና አገልግሎት እና ጊዜ ቆይታ አስመልክተው የሕክምና ባለሙያዎች ለቅዱስ ፓትርያርኩ ገለጻ አድርገዋል፡፡ ቅዱስ ፓትርያርኩም በሆስፒታሉ የሕክምና አገልግሎት እያገኙ ለነበሩት ታካሚዎች ስለ በሽታው መንስኤ እና የሚያስከትለውን ጉዳት በተመለከተ ሰፊ ምክር ሰጥተው የሕክምና ጥበብ እግዚአብሔር ለሰዎች ገልጾ የሰጠው የአምላክ በረከት መሆኑን አምናችሁ የሐኪሞቻችሁን ትእዛዝ አክብራችሁ የተሰጣችሁ መድኃኒትም አበግባቡ ወሰዳችሁ ከሕመማችሁ በመዳን ለራሳችሁ እና ለቤተሰቦቻችሁ እንዲሁም ለሀገራችሁ የምትጠቅሙ መልካም ዜጎች መሆን እንደምትችሉ መገንዘብ ይኖርበችኋል፤ ከዚህም በተጨማሪ ሕመማችሁን ሊያባብሱ ከሚችሉት አላሰፈላጊ ሱሶች የጸዳችሁ መሆን ይኖርባችኋል፤ እንዲህ ስታደርጉ ለሌሎች ወንድሞቻችሁም መልካም ምሳሌ ለመሆን ትበቃላች.... በማለት ምክርና ጸሎት አድርገውላቸዋል፡፡

 

የጉንኝቱ ሦስተኛ ክፍል የተለማመደ ቲቢ የታመሙ ሕሙማን የሚታከሙበት ክፍል ሲሆን በዚህ ክፍል ውስጥ የቲቢ ታማሚዎች ሕክምናቸውን በአግባበ ሳይከታተሉ ቀርተው መድኃኒቱን ሲያቋርጡ የሚታመሙ ሕሙማን የሚታከሙበት ክፍል መሆኑ እና የሕሙማኑ የሕክምና ቆይታ እንዲሁም የሕክምናው ዘዴ በተመለከተ በሐኪሞቹ ሰፊ ገለጻ ለቅዱስ ፓትርያርኩ ተደርጎላቸዋል፡፡

ቅዱስ ፓትርያርኩም ለሕሙማ ሁሉ ዞረው ከጠየቁ በኋላ የዚህ ሕመም መንስኤው የቲቢ መድኃኒት በሥነ ሥርዓቱ ጊዜውና ሰዓቱ ጠብቆ ባለመውሰድ የሚመጣ መሆኑ በስፋት ገልጸው ከዚህ በተጨማሪም ሕመሙን ሊያባብሱ የሚችሉትን እንኳንስ ለታማሚ ለጤነኛ እንኳን የሚያሳብዱትን የተለያዩ ሱሶችን ከመውሰድ እንዲታቀቡ በእግዚአብሔር ስም አደራ ጭምር ትምህርት እና ቃለ ምዕዳን ሰጥተዋቸዋል፡፡ በመጨረሻም ይህንን የቲቢ ሕመም ሕክምና በተመለከተ ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ተሰባስበው ስለጠና በመውሰድ ላይ የነበሩት የሕክምና ባለሙያዎች ይህንን የተቀደሰ የሰው ልጅ ሕይወትን ለማዳን በሚያደርጉት መልካም ሥራ እግዚአብሔር እንዲረዳቸው፣ በሚሄዱበት ቦተ ሁሉ እግዚአብሔር እንዲጠብቃቸው ጸሎት፣ ትምህርተ ወንጌል እና ቡራኬ ሰጥተው የጉብኝቱ መርሐ ግብር ተጠናቋል፡፡

የፎንት ልክ መቀየሪያ