Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

‹‹ለሐኮ ለሰብእ በአርአያከ ወበአምሳሊከ፤ ሰውን በአርአያህና በአምሳልህ አበጀኸው›› /ዘፍ.1፡26፣ ቅዱ ያሬድ/


ፈጣሬ ፍጥረታት እግዚአብሔር ሰውን ሲፈጥር በሦስት ነገሮች ከሌሎች ፍጥረታት የተለየ አድርጎ ፈጥሮታል፤
ይኸውም እንደሌሎች ፍጥረታት ይሁን በማለት በቃል - ትእዛዝ ሳይሆን ከምድር አፈር አበጅቶ ፈጥሮታል፣ ይህም ማለትም ፡-

 • በእጁ አከናውኖ፣ አሳምሮና አክብሮ የፈጠረው በመሆኑ፤
 • ከሌሎች ፍጥረታት በተለየ ሁናቴ በአርአያውና በአምሳሉ የፈጠረው በመሆኑ፣
 • ከፍጥረታት ሁሉ ለይቶ የሕይወት እስትንፋስን እፍ ያለበት ሕያው ፍጡር በመሆኑ ከሌሎች ፍጥረታት የተለየ ያደርገዋል፡፡

በኃላፊነት ደረጃም ምድርንና በምድር ያሉትን ፍጥረታት ሁሉ እንዲያስተዳድር፣ እንዲያዝና እንዲገዛ ባለሙሉ ሥልጣን ሆኖ በእግዚአብሔር ተሹሞአል፡፡
ይህ ሁሉ የሚያመለክተው ሰው በፈጣሪ ዘንድ እጅግ በጣም የተከበረና የተወደደ ፍጡር ከመሆኑም በላይ አርአያ እግዚአብሔር፣ አምሳለ እግዚአብሔር የሆነ ክቡር ፍጥረት መሆኑን ነው ፡፡
ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለሰው ክብር - ታላቅነት በሚያስተምርበት ጊዜ ‹‹በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል›› ብሎአል፤ /ማቴ.5፡21-22/
ጌታችን በዚህ ትምህርቱ የሰው ልጅን መግደል ይቅርና መሳደብና መቆጣት እንደማይቻል አበክሮ አስተምሮአል፤ ሰውን መግደል አርአያ እግዚአብሔርን፣ አምሳለ እግዚአብሔርን ማፍረስ ስለሆነ በፈጣሪ ዘንድ ትልቅ በደል ነው ፡፡


ከዚህ አንጻር በእግዚአብሔር የተሰጠውን የሰው ክብር በተግባር ለመጠበቅና ለማስከበር፣ በአሁኑ ጊዜ ሀገራችን ኢትዮጵያ በሁሉም አቅጣጫ ያሉትን ልጆቿን በእኩልነትና በአንድነት አስተባብራ ለዘመናት ተጭኖን የቆየውን ድህነት ለመቀነስ ብሎም ለማስቆም ከዳር እስከ ዳር እየተጋች ያለችና ብሩህ ተስፋ የሰነቀች ሀገር እንደሆነች ዓለም የተገነዘበበት ወቅት ላይ እንገኛለን ፡፡
ይሁን እንጂ አልፎ አልፎ በሰው ልጆች ሕይወት ላይ እየተከሠቱ ያሉት ግድያዎች የሰውን ክቡርነት በግልጽ የሚጋፉ ናቸው፤ በመሆኑም የግድያ ድርጊት፣ ለዚያም ዓቅም በሌላቸውና መከላከል በማይችሉ ሕጻናትና እናቶች የሚፈጸሙትን ግድያዎች፣ ሁሉም አምርሮ ሊያወግዛቸውና ሊመክታቸው ይገባል፤

በተለይም በዚህ ሰሙን በጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ በንጹሐን ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመው ግድያ፣ ዘረፋና የንብረት ውድመት ቤተ ክርስቲያናችንን በእጅጉ አሳዝኖአል ፡፡
ይህን ግድያ ልዩ የሚያደርገው በተለይ በሕጻናትና እናቶች ላይ ያነጣጠረ በመሆኑ ነው፣ ይህ ኅሊናን የሚያቆስልና ሕገ እግዚአብሔርን የሚጥስ የጭካኔ ተግባር በመሆኑ ቤተ ክርስቲያናችን አጥብቃ ታወግዘዋለች ፡፡
ሀገራችንም ሆነች የዓለም ማኅበረ ሰብ በአጠቃላይ የሰው ልጅ በሕይወትና፣ በነጻነት የመኖር ዋስትና ኖሮት፣ በሀገሩ ሠርቶ የመሻሻል መብቱ እንዲከበር ተግተው በሚሠሩበት ወቅት እንዲህ ያለ ድርጊት መፈጸሙ ሀገራችንን ወደኋላ የሚጎትት ስለሆነ እንዲህ ያለው ድርጊት ድጋሚ እንዳይከሠት ተገቢውን ጥንቃቄ ከማድረግ ጋር አስተማሪ የሆነ ሥራ ሊሠራ ይገባል ፡፡

አሁን የተከሠተው ዓይነት ችግር፣ ይብዛም ይነስ በጋምቤላ አካባቢ በተደጋጋሚ እየታየ የቆየ ከመሆኑ አንጻር ችግሩ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲያከትም ለማድረግ የኢትዮጵያና የደቡብ ሱዳን መንግሥታት በጋራ ቢሠሩ የተሻለ ውጤት ማምጣት እንደሚቻል ቤተ ክርስቲያናችን ታምናለች፤ ለዚህም ድጋፏን ትሰጣለች ፡፡
በመጨረሻም
በጋምቤላ ክልል በሚገኙት ልጆቻችንና ወገኖቻችን በተፈጸመው የግድያ፣ የዘረፋና የንብረት ውድመት ምክንያት የተሰማንን ጥልቅ ኃዘን በራሳችንና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስም እየገለጽን የመዋች ቤተሰቦችንና የጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥትን እግዚአብሔር እንዲያጽናናቸው እንጸልያለን በዚህ አጋጣሚ ቤተ ክርስቲያናችን አሁንም ሆነ ወደፊት ከክልሉ ሕዝብና መንግሥት ጎን እንደማትለይ እናረጋግጣለን ፡፡


እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ
አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ሚያዝያ 12 ቀን 2008 ዓ.ም.
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

የፎንት ልክ መቀየሪያ