Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

በመ/ር ዕንቈባሕርይ ተከስተ

ከየካቲት 1 ቀን 1987 ዓ.ም ጀምሮ እስከ የካቲት 7 ቀን 2008 ዓ.ም ድረስ ለቤተ ክርስቲያኒቱ የተመለሱ ቤቶችና ሕንጻዎች፤
መግቢያ፤
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከመንፈሳዊ ተልዕኮ ጋር ለሀገር አንድነትና ሰላም ዕድገትና ብልጽግና ነፃነትና ሉዓላዊነት መከበር እጅግ በጣም አስፈላጊ የሆነ ማሕበራዊ አገልግሎት የሚፈጸምባት ሕዝባዊ ተቋም መሆንዋ ለሁሉም የተሰወረ አይደለም፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በማናኛቸውም በየተኛው ጊዜ ከሕዝቡ ተለይታ የኖረችበት ለአንድ አፍታ እንኳን የለም፡፡
በመከራ ጊዜም በጦርነት ጊዜም በሰላም ጊዜም ሁሉ በሕዝቦችዋ መካከል የምታበራ ፋና ወጊ ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለብዙ ዘመናት ትውልዱን በሃይማኖት አንድ አድርጋና አስተባብራ ለነጻነቱ፣ ለሃይማኖቱ፣ ለሀገሩ፣ ለአንድነቱ፣ ለታሪኩ፣ በተቀደሰ ባሕሉና ሕልውናው እንዲታገል ብዙ ከፍተኛ ድካምንና ጥረትን አድርጋለች፡

የውጭ ወራሪ ጠላት በሚመጣበት ጊዜም ሕዝቡ ነጻነቱን አሳልፎ እንዳይሰጥ ለሀገሩ፣ ለመሬቱ ለወገኑ፣ ለሃይማኖቱ፣ መስዋዕትነት እንዲከፍል ታቦታቱ ጭምር በጦር ሜዳ እንዲዛመቱ አድርጋለች፡፡
ይሁንና ኢትዮጵያ በደርግ አገዛዝ ሥር ከወደቀች በኋላ የደርግ መንግሥት ቤተ ክርስቲያኒቱን ለማዳከምና ብሎም ለማጥፋት በነበረው ዓላማ በ1967 ዓ.ም ሀብቷንና ንብረቷን ወርሶ ብር 4883276.00 ብቻ በድጎማ መልክ በመፍቀድ ቤተ ክርስቲያኒቱን ለ18 ዓመታት ያህል በችግር ውስጥ እንድትቆይ ማድረጉን የቅርብ ትዝታችን ነው፡፡
ነገር ግን በሕዝብ ልጆች የተገረሰሰው የደርግ መንግሥት ከተወገደ ወዲህ ሀገሪቱን በሰላምና በዲሞክራሲ ለመምራት የተረከበው የኢህአዴግ መንግሥት የቤተ ክርስቲያንዋን ቤቶችና ሕንጻዎች ለመመለስ ከየካቲት 1 ቀን 1987 ዓ.ም ጀምሮ እንዲመለስላት በቁርጠኝነት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
በዚህ መሠረት ውሳኔው ከተላለፈበት የካቲት 1 ቀን 1987 ዓ.ም እስከ የካቲት 7 ቀን 2008 ዓ.ም ድረስ የተመለሱ ቤቶችና ሕንፃዎች ሕዝቡ እንዲያውቀው ማድረጉ አስፈላጊ በመሆኑ እንደሚመለከተው ቀርቧል፡፡
1. በጠቅላይ ሚኒስትር ውሳኔ መሠረት በኪራይ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር የነበሩት ከ600 በላይ ቤቶችና ሕንጻዎች ለቤተ ክርስቲያንዋ ተመልሰዋል፡፡
ሀ/ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣
ለ/ የፌዴሬሽን ምክር ቤት፣
ሐ/ ኦሮሚያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን፣
መ/ የፍል ውሃ ድርጅት በቢሮነትና በሆቴልነት የሚገለገልባቸው የአራት ሕንጻዎች ካሣ ብር 71,051,517.80 ከምትክ መሥሪያ ቦታ አንደኛ ደረጃ 22,856 ካሬ ሜትር ጋር ለቤተክርስቲያንዋ እንዲሰጥ በመንግሥት በተወሰነው መሠረት ከላይ የተጠቀሰው ገንዘብ ከገንዘብና የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ቤተ ክርስቲያኒትዋ መረከብዋ፤ ቦታውን በተመለከተ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለመረከብ በዝግጅት ላይ መሆኑዋ፤
2. በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እስከ አሁን ድረስ የነበሩት 283 የቤተ ክርስቲያንዋ ቤቶችና ሕንፃዎች የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤትና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ባለ ሥልጣናት ባደረጉት ውይይት ቤተ ክርስቲያንዋ 283 ቤቶችና ሕንጻዎች መረከብ የሚያስችላትን ደብዳቤ የካቲት 7 ቀን 2008 ዓ.ም በቁጥር አ.አ/ከፅ/01/16.4 በቀን 07/06/2008 ዓ.ም ለቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ ሲጻፍ ለቤተ ክርስቲያንዋ የተመዘገበውን ግልባጭ ደብዳቤ ከምስጋና ጋር ተቀብላ በመጋቤ ካህናት ኃይለ ሥላሴ ዘማርያም የሚመራው የቤቶችና ሕንጻዎች አስመላሽ ኮሚቴ በመከታተል የሚገኝ መሆኑ፤
3. በሐረር ከተማ የሚገኙትና እስከ አሁን ድረስ ለቤተ ክርስቲያናችን ያልተመለሱት 22 ቤቶችና ሕንጻዎች ጥናታቸው አልቆ ጉዳዩ ለሐረር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ካብኔ ቀርቦ ውሳኔ ማግኘት ይችል ዘንድ ኮሚቴው በመከታተል የሚገኝ መሆኑ፤
4. የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ማግኘት ይችሉ ዘንድ ከነሐሴ 18 ቀን 2001 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 8 ቀን 2008 ዓ.ም ድረስ ከ220 በላይ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ በመጋቤ ካህናት ኃይለ ሥላሴ ዘማርያም የተመራው ኮሚቴ ካርታዎችን ተረክቦ ለገዳማትና አድባራት ማስረከቡን መረጃዎች የሚገልጽ መሆናቸው፤
5. ከመስከረም 9 ቀን 1998 ዓ.ም በኋላ የተተከሉ ከ36 በላይ የሆኑ ገዳማትና አድባራት የይዞታ ካርታ እንዲያገኙ ጥረቱ ቀጥሏል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ከ76 በላይ ባሕረ ጥምቀቶች ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ባሕረ ጥምቀቶች ታቦታተ ሕጉ የሚያድርባቸው ሥጋሁ ወደሙ የሚፈተትባቸው፡፡ ስብሐተ እግዚአብሔር የሚደርስባቸው፤ ሕዝበ ክርስቲያኑ መንፈሳዊ አምልኮቱን የሚገልጽባቸው፣ ከድህነት ለመውጣት ለሚደረገው ርብርብ በልማት እና በቱሪዝም መስሕብነታቸው የታወቁና ዓለም የመሰከረላቸው፤
6. የመላው ዓለምን ሕዝብ ቀልብ የሳቡ ቅዱሳት መካናት ናቸው፡፡እነዚህ ብርቅየና ድንቅ የሆኑ የሀገር ሃብቶች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ በቤተ ክርስቲያን ስም ተዘጋጅቶ እንዲሰጥ ኮሚቴው ጥረቱን ቀጥሏል፡፡
7. ከተሰጡት ከ220 በላይ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታዎች መካከል 55 የይዞታ ማረጋገጫ ካርታዎች በግሪን ኤሪያ ውስጥ በመሆናቸው የገዳማትና አድባራት የልማት ሥራ እንዳይሠሩ እንቅፋት እየሆነባቸው መምጣቱና የተረጋገጠ ሲሆን ይህንን ችግር ለመፍታት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለ ሥልጣናት ጋር በመነጋገር ላይ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡

የፎንት ልክ መቀየሪያ