Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

በመ/ር ዕንቈባሕርይ ተከስተ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከ1966 ዓ/ም በፊት በሀገሪቱ ብሔራዊ ሬዲዮና ቴሌቪዥን፣ እንዲሁም በሉተራን ፌደሬሽን እርዳታ ይሰራጭ የነበረው የብሥራተ ወንጌል፣ የምሥራች ድምጽ ሬዲዮ ጣቢያ በነበራት የነፃ የዓየር ሰዓት የሰላም፣ የእምነትና የማኅበራዊ ተልእኮ ትምህርቶቿን፣ ዓመታዊ በዓላቷንና ሥርዓተ አምልኮቷን በቀጥታ ሥርጭት የማስተላለፍ ዕድል ነበራት፡፡

ይኽ እንቅስቃሴ በወታደራዊው የደርግ ሥርዓተ መንግሥት ከተቋረጠ በኋላ የቤተ ክርስቲያኒቱ መልእክት በጥቂት የሕትመት ሚዲያ ሥርጭቶች ተወስኖ ቆይቷል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ደግሞ ምንም እንኳ የመናገርና ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት በሕገ መንግሥቱ የታወጀ ቢሆንም የሀገሪቱ የብሮድ ካስት አዋጅ በኢትዮጵያ ውስጥ በሃይማኖት ተቋማት ብዙኀን መገናኛ ጣቢያዎች እንዲቋቋሙ የተመቻቸ ሁኔታ የለውም፡፡

በአንፃሩ ግን በሀገራችን ካሉ የእምነት ተቋማት ውስጥ ከኢትዮጰያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በቀር አብዘኛዎቹ የእምነት ተቋማት በውጭ ከሚኖሩ አጋሮቻቸውና በሀገር ውስጥ ያሉ ተከታዮቻቸውን በማስተባበር ቅርብና አመች ከሆኑ ጎረቤት ሀገሮች የሥርጭት መሥመሮችን በመጠቀም በብዙ የሀገራችን ቋንቋዎች ሃይማኖዊ ትምህርቶቻቸውን በልዩ ልዩ የ24፡00 የሃያ አራት ሰዓት የሳተላይ ቴሌቪዥን ሥርጭቶች ሲያስተላልፉ ይታያሉ፡፡ ይኽንንም ትልቅ መብትና ዕድል መንግሥት ያለመገደቡ እጅግ መልካም አጋጣሚ ስለሆነ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰላምን፣ መከባበርን፣ መንፈሳዊና ማኅበራዊ እድገትን፣ የሕዝብን በፍቅር ተባብሮ መኖርን፣ የሰው ልጅ ደኅንነትንና የሀገርን በጎ ገጽታ ማሳየትን መሠረት ያደረጉ ልዩ ልዩ የመገናኛ ብዙኅንን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባት ታምኖበት ማእከላዊና ተጠያቂነት ያለው የብዙኀን መገናኛ አገልግሎት ሥርጭት እንዲቋቋም ቅዱስ ሲኖዶስ በግንቦት ወር 2006 ዓ/ም ወስኗል፡፡

በውሳኔው መሠረትም የታሰበውን አገልግሎት ወደ ተግባር እንዲለውጥ በቋሚ ሲኖዶስ በተሰየመ አንድ ቦርድ እና ቦርዱ በሾመው ሥራ አስኪያጅ አማካኝነት ልዩ ልዩ ጥናቶች ሲካሄዱ ቆይተው በቅርቡ ሥርጭቱን ለማስጀመር የሚያስችለን የውል ስምምነት ለመፈረም ተችሏል፡፡

በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት በድርጅታዊ መዋቅር የተቋቋመው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመገናኛ ብዙኀን ሥርጭት አገልግሎት ዋና መሥሪያ ቤቱ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ሲሆን ድርጅቱ ለሥርጭት የሚሆኑትን ማናቸውንም ዝግጅቶች በሀገር ውስጥ የሚያዘጋጅ ሲሆን አሁን በተገባው ውል መሠረት ሥርጭቱ በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ጋር በተደረገ ስምምነት እና ገዳሙ ካለበት ከኢየሩሳሌም በሚገኘው የሳተላይት ድርጅት አማካኝነት ሥርጭቱ ይከናወናል፡፡ ለዚህም የገዳማቱ ማኅበረ መነኰሳትና የኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳስ በቅርቡ ቅዱስ ፓትርያርኩ በቦታው ተገኝተው በመሩት ስብሰባና ውይይት ለዚህ አገልግሎት ያላቸውን ሙሉ ስምምነትና ፍላጎት በሙሉ ድምጽ አረጋግጠዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የሳተላይት ውልን በተመለከተ የውሉን ይዘት በሕግ ባለሙያዎች እንዲታይ ቦርዱ በሰጠው ውሳኔ በቅዱስ ፓትርያርኩ መመሪያ በሳተላይት ድርጅቱ የተላከው የውሉ ረቂቅ የተሰጣቸው ዓለም አቀፍ የሕግ ባለሙያ ፕሮፌሰር ጥላሁን ተሾመ እንደመረመሩትና እንዳስተካከሉት አፈ መምህር ገብረ ሥላሴ የመንበረ ፓትርያርክ ሕግ አገልግሎት ኃላፊ በቦርድ ስብሰባ ተገኝተው አስተያየት እንደሰጡበትና የቴክኒክ ባለሙያዎችን ውሉን በመመርመር እንደተሳተፉ ተረጋግጧል፡፡ በሕግ ባለሙያዎች የታረመው ውል አስፈላጊው ቅድመ ሁኔታ ከተደረገለት በኋላ ቅዱስ ፓትያርኩና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የመገናኛ ብዙኀን ድርጅት ቦርድ አባላት በተገኙበት ውሉ በድርጅቱ ሥራ አስኪጅ በመምህር ዳንኤል ሰይፈሚካኤልና በሳተላይት ድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ ሚ/ር ኤራን አማካኝነት ተፈርሟል፡፡ ከፊርማው በኋላ እንደተገለጸው በቅርቡ የሙከራ ሥርጭቱ የቴሌቪዥኑን ሎጎና አጫጫር ክሊፖችን በማሠራጨት እንደሚጀምር፣ አጠቃላይ ይዘቱን በተመለከተ አንድ ይዘት ዝግጅትና ኮሚቴና፣ የኤዲቶሪያል ኮሚቴ እንደሚቋቋም፣ የሌሎች ሠራተኞች ቅጥርም እንደሚፈጸም በቅርብ ይጠበቃል፡፡

ከ52000000 በላይ አማኞች ያሏት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከ1966 ዓ.ም ወዲህ ምዕመናንን ለማስተማር የቴሌቪዥን ጣቢያ መክፈት መቻል በዘመናችን ታላቅ ስኬት ነው፡፡

 

የፎንት ልክ መቀየሪያ