Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51
 • ለሕንፃው ግንባታ 40 ሺ ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡

በመምህር ሙሴ ኃይሉ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን አስከትለው በመቀሌ ከሳቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርትን ለመመረቅ በተገኙበት ወቅት የመንግሥት አደረጃጀትን ተከትሎ አዲስ የተቋቋመው የደቡብ ምሥራቅ ትግራይ ሀገረ ስብከት መንበረ ጵጵስና ጽ/ቤት ለመገንባት መንግሥት በመቀሌ ከተማ በሰጠው 2072 ሜትር ካሬ ቦታ ትልቅ ሕንፃ ለመሥራት ሰኔ 20 ቀን 2008 ዓ.ም. ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የደቡብ ምሥራቅ ትግራይ ሀገረ ስብከት የየወረዳው ቤተ ክህነት ኃላፊዎችና የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና ብዛት ያላቸው ምእመናን በተገኙበት የመሠረት ድንጋይ አስቀምጠዋል ፡፡

በዕለቱ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ በትግራይ ክልል የደቡባዊ ዞን ማይጨው፣ የደቡብ ምሥራቅና (መሠረት የሚቀመጥለት ሀገረ ስብከት) የምሥራቅ ዞን ዓዲግራት አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሀገረ ስብከቱ አመሠራረትና አሁን የደረሰበት ደረጃ አስመልክተው ሰፊ ገለጻ አድርገዋል ፡፡ ብፁዕነታቸው በመግለጫቸው ትኩረት ከሰጡባቸው ነጥቦች መካከል ቀደም ሲል ሀገረ ስብከቱ የመንግሥትን አደረጃጀት ተከትሎ በሀገረ ስብከት ደረጃ እንዲቋቋም ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኖ ከሰጠን ደብዳቤ ውጭ ምንም ዓይነት የጽ/ቤት አደረጃጀት እንዳልነበረው በመግለጽ ከዜሮ በመነሳት ሕዝቡንና ካህናቱን ለልማት በማነሣሣት ሀገረ ስብከቱ የግለሰብ ቤት ተከራይቶ ሥራውን መጀመሩን በስፋት አስረድተዋል ፡፡

አያይዘውም ሀገረ ስብከቱ እየተደራጀ ሲመጣ ራሱን ችሎ ኩሐ ከተማ በ250 ሜትር ካሬ ያረፈ ባለ 6 ክፍል ቤት የያዘ መሬት በ300 ሺህ ብር በመግዛት አገልግሎቱን እያካሔደ ቆይቶ አሁንም የሥራውን ብዛትና ቦታውን በመቀሌ ዙሪያ ለሚገኙ ሁሉም ወረዳዎቻችን ማዕከል ባለመሆኑ በመቀሌ ከተማ መስፍን እንጂነሪንግ አጠገብ 9 ክፍል ቤት የያዘና በ400 ሜትር ካሬ ያረፈ ቤትና ቦታ በ1.2 ሚሊዮን ብር በመግዛት ከፍተኛ የሆነ ልማታዊና መንፈሳዊ አገልግሎት በማበርከት ላይ መሆኑን ገልፀዋል ፡፡

ከዚህ ጎን ለጎንም መንግሥት የራሳችን ጽ/ቤት አቋቁመን የተሟላ አገልግሎት የምንሰጥበትን ቦታ እንዲሰጠን ከ1999 ዓ.ም. ጀምሮ ሰፊ ጥረት ሲያደርጉ መቆየታቸውን አስታውቀው መንግሥትም በጉዳዩ ላይ አምኖበት በመሐል ከተማ ላይ 2072 ሜትር ካሬ ቦታ መስጠቱን የክልሉ መንግሥት እጅግ ሊመሰገን እንደሚገባ በአጽንኦት ገልፀዋል ፡፡

ብፁዕነታቸው በመጨረሻም በዛሬው ዕለት በቅዱስ አባታችን የመሠረት ድንጋይ የተቀመጠለትን ሁለገብ ሕንፃ ከታች ለሀገረ ስብከት የገቢ ምንጭ ሆኖ የሚከራይ ሲሆን ከላይ የሚገነቡትን ክፍሎች ደግሞ ለሀገረ ስብከቱ አገልግሎት የሚውሉ መሆናቸውን ገልፀው ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን ቃለ ምእዳንና ቡራኬ እንዲሰጡ በመጋበዝ ንግግራቸውን አጠናቅቀዋል ፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን በበኩላቸው የሀገረ ስብከቱ የልማት ሥራዎችና ከዜሮ ተነሥቶ የደረሰበትን የዕድገት ደረጃ አድንቀውና እዚህ ደረጃ ላይ እንዲደርስ ከፍተኛ ሥራ ለሠሩት ለሊቀ ጳጳሱና ለሀገረ ስብከቱ ሠራተኞች ከፍተኛ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ አያይዘውም መንግሥት ቤተ ክርስቲያናችን የሀገሪቱ የልማት አጋር መሆንዋን በማመን ሀገረ ስብከቱ ለሚሰጠው መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት የሚሰጥ በዚህ መሀል ከተማ ቦታ መስጠቱ ተገቢና እጅግ የሚያስመሰግነው ስለሆነ በቤተ ክርስቲያናችን ስም ምስጋና አቅርበዋል ፡፡ አያይዘውም ይህንን ሁለገብ ሕንፃ ተጠቃልሎ ሲያልቅ ብዙ ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን የሚታና ለስብከተ ወንጌል ተልእኮ መፋጠን የራሱ የሆነ ትልቅ ድርሻ ስለሚኖረው ሁሉም የሀገረ ስብከቱ አብያተ ክርስቲያናት፣ ወረዳዎች እንዲሁም ገበርተ ሠናይ ምእመናን እንዲሳተፉበትና በአጭር ጊዜ ተጠናቆ እንዲመረቅ አደራ ብለዋል ፡፡

አያይዘውም ይህ አዲስ ሀገረ ስብከት ለሚያሠራው ሁለገብ ሕንፃ ለማበረታቻ በማለት 40,000 (ዐርባ ሺህ ብር) የለገሱ ሲሆን በተለይ የቤተ ክርስቲያን ከዋክብት የሆኑ ምእመናን ይህ ሕንፃ እውን እንዲሆን በሚችሉት ሁሉ በገንዘባቸው፣ በዕውቀታቸውና በጉልበታቸው እገዛና ድጋፍ እንዲያደርጉ በማሳሰብ የዕለቱ መርሐ ግብር በቅዱስ አባታችን ጸሎት ተዘግቷል ፡፡

የፎንት ልክ መቀየሪያ