Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51
 • ቅዱስነታቸው ለቤተ ክርስቲያኑ ማሠሪያ የ50 ሺህ ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡

በመምህር ሙሴ ኃይሉ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በመቀሌ ከተማ በአክሱም ጽዮን ዲዛይን በልዩ ቴክኖሎጂ በመገንባት ላይ የሚገኘው የዓዲሐውሲ ጌቴ ሴማኒ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትና ከአዲስ አበባ ከሔዱ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያ ኃላፈዎች፣ ከአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች፣ ከአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች በመሆን ሰኔ 20 ቀን 2008 ዓ.ም. ተዘዋውረው ጎበኙ፡፡

በጉብኝቱ ሥነ ሥርዓት የሕንፃ አሠሪ ኮሚቴው አጠቃላይ ከመጀመሪያ ጀምሮ አሁን እስከደረሰበት ያለውን አጠቃላይ የቤተ ክርስቲያኑ የሥራ ሒደት ሰፊ ሪፖርት አቅርበዋል ፡፡ ሪፖርቱም በዋናነት ይህ አዲስ የዓዲሐውሲ ጌቴሴማኒ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በመጨረሻ ግንቦት ወር 2002 ዓ.ም የመሠረት ድንጋይ በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ተቀምጦ ሥራ መጀመሩንና በዚህ ስድስት ዓመታት አሁን ከደረሰበት ደረጃ ሊደርስ መቻሉን ገልጸዋል ፡፡

ቤተ ክርስቲያኑ የልዩ ጥበባዊ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ መሆኑንና አጠቃላይ የቤተ ክርስቲያኑ ሕንፃ የሚያስፈልገው የገንዘብ መጠን 30 ሚሊዮን ብር መሆኑን በባለሙያ መተመኑን እንዲሁም እስከ አሁን ድረስ 12 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጎ በመሠራት ላይ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡

በመቀጠልም የቤተ ክርስቲያኑ ስፋት 1660 ሜትር ካሬ ሆኖ ባለ አንድ ፎቅና ዐራት ሺህ ሕዝብ መያዝ የሚችል ከአካባቢው በጣም ትልቅ ቤተ ክርስቲያን መሆኑን ገልጸው ደወል ቤቱ መቀሌ ከተማ በአግባቡ ሊያሳይና ለቱሪዝምም አመቺ በሆነ ሁኔታ 36 ሜትር ስፋትና 64 ሜትር ቁመት ያለው መሆኑን ዲዛይኑ ለቅዱስ አባታችንና በቦታው ለተገኙ እንግዶች ሁሉ በማሳየት ጭምር ገለጻ አድርገዋል፡፡

በመጨረሻም የቤተ ክርስቲያኑ ስፋትና ጥራት ብዙ ገንዘብ የሚያስፈልገው ስለሆነና የቤተ ክርስቲያንዋ ሕንፃ አሠሪ ኮሚቴም ከአካባቢው ውጭ ርዳታ የማይጠይቅ በመሆኑ ቤተ ክርስቲያኑ ተሠርቶ እስኪጠናቀቅ ድረስ ከፐርሰንት ክፍያ ነፃ እንዲሆኑ በመጠየቅና ቤተ ክርስቲያኑ ተጀምሮ እስኪያልቅ ድረስ ከዲዛይን ጀምሮ ቁጥጥርና ክትትል በሚደረግ በነፃ እያገለገለ ያለውን ኢንጅነር ቅዱስነታቸው እንዲያመሰግኑላቸው በመጠየቅ ሪፖርታቸውን አጠናቀዋል፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ በበኩላቸው በዚህ አዲስ እየተገነባ ባለው አካባቢ እየተገነባ ያለው ዘመናዊና ሁሉንም ሊያገለግል የሚችል በዓይነቱና በይዘቱ ለየት ያለ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በመጎብኘታቸው እጅግ መደሰታቸውን ገልጸው ይህ ቤተ ክርስቲያን ለሌሎችም ምሳሌ ሊሆን የሚችል የአካባቢው ኅብረተሰብ እየተሳተፈበት የሚገኝ ሰፊና ግሩም ዲዛይን ያለው መሆኑን ከቀረበላቸው ሪፖርት አኳያ ማብራሪያ ሰጥተዋል ፡፡ ቅዱስነታቸው የቤተ ክርስቲያኑ ዲዛይን ከመሥራት አንሥቶ በሀገራችን አዲስ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ሰፊ የሙያና የጉልበት አገልግሎት በነፃ በመስጠት እያገለገሉ የሚገኙትን ኢንጂነር በቤተ ክርስቲያን ስም ከፍተኛ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ቅዱስ ፓትርያርኩ በመቀጠልም በዚህ ግሩም የሆነ ሰፊ ቤተ ክርስቲያን ሕንፃ ግንባታ ሁሉም ምእመናንና በጎ አድራጊ ባለሀብቶች በንቃት እንዲሳተፉ በስፋት ከመከሩ በኋላ ለማበረታቻ እንዲሆን ቅዱስነታቸውም 50 ሺ ብር ለሕንፃ ግንባታ ድጋፍ አድርገዋል ፡፡

በመጨረሻም ቅዱስ ፓትርያርኩ፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትና የክብር እንግዶች ሁሉ አዲሱ ሕንፃ በመዘዋወር ከጎበኙና ሙያዊ ገለጻ ከኢንጅነሮቹ ካዳመጡ በኋላ መርሐ ግብሩ በቅዱስ አባታችን ጸሎት ተጠናቋል ፡፡

የፎንት ልክ መቀየሪያ