Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51
 • በቦታው ላይ የተሠሩ ልዩ ልዩ ልማቶች መርቀዋል፡፡

በመምህር ሙሴ ኃይሉ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ሰኔ 21 ቀን 2008 ዓ.ም. በጥንታዊቷ የአምባ ሰነይቲ ውቅሮ ማርያም በዓለ ንግሥ አከበሩ ፡፡ ቅዱስ ፓትርያርኩ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትና ቅዱስ አባታችንን አጅበው የሔዱት የየመምሪያው ኃላፊዎች እምባሰነይቲ ሲደርሱ በአከባቢው ምእመናን ታላቅ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን ገዳሙ ሲደርሱም እንዲሁ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችና ምእመናን በከፍተኛ መንፈሳዊ አቀባበል ተቀብሏቸዋል፡፡

ቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በወቅቱ ለተገኙ ምእመናን ዙሪያውን ከባረኩ በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ በመግባት ጸሎተ ኪዳን ካደረሱ በኋላ የዓውደ ምሕረት መርሐ ግብር ተከናውኗል፡፡

ቅዱስ ፓትርያርኩ፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትና ከአዲስ አበባ የመጡ እንግዶች ቦታ ቦታቸውን እንደያዙ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና የአካባቢው የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች ለዕለቱ የሚስማማ ያሬዳዊ መዝሙርና ቅኔ በማቅረብ መርሐ ግብሩን ጀምረዋል፡፡

ከሊቃውንቱ በመቀጠል በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀደማዊ ፓትርያርክ መልካም ፈቃድ ቆሞስ አባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የትምህርት ማሠልጠኛ መምሪያ ኃላፊ ትምህርተ ወንጌል ከሰጡ በኋላ የጥንታዊቷ ማርያም ውቅሮ ታሪክ በመልአከ ሰላም ዓምደ ብርሃን አማካኝነት ሰፊ ገለጻ ተደርጓል፡፡

መልአከ ሰላም በመግለጫቸው ይህ ታሪካዊ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን በሁለቱም ነገሥታት አብርሃ ወአጽብሃ አማካኝነት ለመጀመሪያ ጊዜ የታነጸ ከወጥ ዓለት የተፈለፈለ እጅግ የመጠቀ ጥበብ ገንዘብ ያደረገ ቤተ ክርስቲያን መሆኑን ገልጸዋል ፡፡ ቅዱሳን ነገሥታት ይህንን አስደናቂ ቤተ ክርስቲያን ለማነጽ የተጠቀሙበት ‹‹እብነ አድማስ›› የተባለ መሣሪያቸው ለታሪክ እንዲሆን በቤተ ክርስቲያኑ ላይ ተንጠልጥሎ እንደሚገኝ ገልጸው አንዱ በአጼ ዮሐንስ ዘመን ንጉሡ አምጡልኝ ልየውና ይመለሳል ባሉት ትእዛዝ መሠረት ለመውሰድ ታስቦ ሰንሰለቱ ሲቆረጥ ወደ መሬት ገብቶ ቀዶ በመግባት እዚህ ደረሰ እንደማይባል ታሪካዊ ዳራውንና አሁን ያለበትን ነባራዊ ሁኔታ አነጻጽረው ሰፊ ገለጻ በማድረግ የቦታውን ታሪክ ለጉባኤው አስረድተዋል፡፡

ከዚህ በመቀጠል በዚህ ታሪካዊ ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ የሆነ ልማት በግል ሀብታቸው ከአካባቢው ሕዝብ ጋር በመሆን ያለሙ አቶ ብርሃነ ግደይ በዕለቱ እንደገለጹት ቤተ ክርስቲያን እጅግ ጥንታዊና በአስደናቂ ጥበብ የተፈለፈለ ቅርስ ቢሆንም አካባቢው ገደላማ በመሆኑ ለተሳላሚ ሕዝብ በጣም ያስቸግር እንደነበር ገልጸው ከ1999 ዓ.ም. ጀምሮ ከሕዝቡ ጋር በመመካከር እልህ አስጨራሽ የሆነ ሥራ በመሥራት አሁን ይህን ጥንታዊ ቤተ ክርስቲያን ለመሳለም የሚመጡ ምእመናን ጸሎት የሚያደርጉበት ሰፊ ሜዳማ አካባቢ አንዲሁም ቱሪስቶች በሚመጡበት ጊዜ የተሟላ ማረፊያ ማስገንባታቸውንና አጠቃላይ የልማቱ የሥራ ሂደትና ውጤቱን አስመልክተው ገለጻ አድርገዋል ፡፡
ከዚህ በመቀጠል አቶ ዮሐንስ አረፋይኔ የወርዒለኸ ወረዳ ኃላፊ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸውም በዋናነት በሀገር ወዳዱ ባለሀብት የተሠሩ ልማቶች ቤተ ክርስቲያኑ የቱሪስት መዳረሻ እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ገልጸው ተሰማቸው ደስታና በወረዳው ኃላፊዎችና በወረዳው ነዋሪ ሕዝብ ስም ምስጋናቸውን ገልጸዋል፡፡

የትግራይ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ዳዊት ኃይሉም በበኩላቸውም ታሪካዊ የኢትዮጵያ ቅርስ የሆነ ውቅር ቤተ ክርስቲያን የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ መንግሥት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መቆየቱን አስታውሰው አሁንም የቅዱስ ፓትርያርኩ በቦታው መገኘትና ልማታዊ ሥራዎች መሠራት እንደ መልካም አጋጣሚ በመውሰድ የተሻለ ሥራ እንደሚሠራ በመግለጫቸው አስረድተዋል፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ በዕለቱ በዚህ ታሪካዊ ቤተ ክርስቲያን ለተገኙት እንግዶችና ምእመናን ቃለ ምእዳንና ቡራኬ ከማስተላለፋቸው በፊት ለጋዜጠኞች ሰፊ መግለጫ ሰጥተዋል ፡፡ ቅዱስነታቸው በመግለጫቸው ወቅት በተለይ ወጣቱ ትውልድ አባቶቹ የሠሩትን እንደእነዚህ የመሳሰሉ አስደናቂ ታሪኮች በማወቅ ጠቀሜታቸውን በመገንዘብ ታሪኩና ቅርሱን ለመላ ዓለም እያስተዋወቀ ታሪኩን እንዲጠብቅ፤ በሀገራችን እየታዩ ያሉ የልማት ሥራዎች በንቃት በመሳተፍ ራሱንና ሀገሩን እንዲያለማ እንጂ ዋስትና ወደሌለው ሀገር እንዳይሰደድ አጽንኦት በመስጠት መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

በመጨረሻም ቅዱስ አባታችን በዕለቱ ለተሰበሰበው ሕዝብ ቃለ ምእዳንና ቡራኬ አስተላልፈዋል፡፡ በቃለ ምእዳናቸውም በሀገራችን ብዙ አስደናቂ አድባራትና ገዳማት መኖራቸውን ጠቁመው መንገድ አለመኖር ግን ዓለም ሳያውቃቸው ከእነዚህ ገዳማት መግኘት የነበረበትን በረከትና የታሪክ ጥበብ የዓለም ተመራማሪዎች ሳያገኙ መቆየታቸውን በስፋት አስረድተዋል ፡፡ መንገድ የሁሉም ነገር በር ስለሆነ የዚህ ታሪካዊ ቤተ ክርስቲያንም ሆነ የሌሎች ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት ታሪክ፣ ጥበብ፣ ቅርስ ወዘተ... በዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ እንዲታወቅና እንዲጎበኝ መንገድ ትኩረት ተሰጥቶ አሁን ካለው በይበልጥ መሠራት እንደሚገባው አሳስበዋል ፡፡ ገደላማ መልክዐ ምድር የነበረው ይኸው ጥንታዊ ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ገንዘብ በማውጣት እንዲህ አድርገው እግዚአብሔር በኅብረት እንድናመልክበት የደለደሉልን ባለሀብት ትልቅ ምስጋና ይገባቸዋል በማለት ካመሰገኑ በኋላ ሌሎች ባለሀብቶችም መንፈሳዊ ቅንዓት አድሮባቸው ሁሉም በየአካባቢያቸው ተመሳሳይ ሥራ እንዲሠሩ አደራ ጭምር መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የቅዱስነታቸውን ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ተከትሎ የተዘጋጀውን የምርቃት መጋረጃ ገልጠው ልማቶቹን መርቀው ተዘዋውረው ከጎበኙ በኋላ ቅዳሴ በቅዱስነታቸው መሪነት ተቀድሶ የበዐሉ ፍጻሜ ሆኗል ፡፡

የፎንት ልክ መቀየሪያ