Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

መምህር ሙሴ ኃይሉ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያ ኃላፊዎች፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሥራ ኃላፊዎችና የአጥቢያው ምእመናንና የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች በተገኙበት ሐምሌ 10 ቀን 2008 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የፈለገ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ሰበካ ጉባኤ ለሚያሠራው አዲስ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን የመሠረት ድንጋይ ባርከው አስቀመጡ፡፡

በመርሐ ግብሩ መጀመሪያ የአጥቢያው ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ምእመናንና የሰንበት ትምህርት ቤቶች ወጣቶች ከፍተኛ የሆነ የመንፈሳዊ አቀባበል ያደረጉ ሲሆን የመሠረት ድንጋይ በቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት ተባርኮ ከተቀመተ በኋላም ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በያሬዳዊ ዝማሬ በዓሉን አድምቀውታል፡፡ በመቀጠልም የደብሩ አስተዳዳሪ ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ፣ ለብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትና በበዓሉ ላይ ለተገኙ እንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ በመልእክታቸውም ይህ ቤተ ክርስቲያን ቀደም ብሎ ለጥቂት ምእመናን ብቻ የተሠራ በመሆኑና በቤተ ክርስቲያኑ ዙሪያ ብዙ ምእመናን በመኖራቸው ሁሉንም ምእመናን አጠቃሎ ሊይዝ የሚችል ዘመናዊ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን በማስፈለጉ በዛሬው ዕለት በቅዱስነትዎ ተባርኮ የመሠረት ድንጋይ መቀመጡንና የደብሩ ሰበካ ጉባኤም ለልማት በእጅጉ መነሳታቸውን በስፋት ገልጸዋል፡፡

የሰበካ ጉባኤው ምክትል ሊቀ መንበር አቶ ኃይሉ ረታ አጠቃላይ የቤተ ክርስቲያኑ አመሠራረትና አሁን የደረሰበት ደረጃ አስመልክተው ሰፊ መግለጫ አቅርበዋል፡፡ በሪፖርታቸውም አሁን በአገልግሎት ላይ የሚገኘው መቃኞ ቤተ ክርስቲያን በ1994 ዓ.ም. ተሠርቶ በመጠናቀቁ ተባርኮ አገልግሎት መጀመሩንና እስከአሁን ድረስ እያገለገለ እንደሚገኝ ገልጸው አሁን ግን የመቃኞው ይዘት ከምእመኑ ብዛት ጋር አብሮ የማይሄድ ስለሆነ ዋናው ቤተ ክርስቲያን ለመሥራት ሰፊ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ዛሬ በቅዱስ ፓትርያርክ የመሠረት ድንጋይ ለማስቀመጥ መብቃታቸውን ገልጸዋል፡፡ ከዚህ በመቀጠል የደብሩ የቅኔ መምህራን ቅኔ በማቅረብ በዓሉን አስመልክተው መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ከዚህ መርሐ ግብር በኋላ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ትምህርተ ወንጌል አስተምረዋል፤ ብፁዕነታቸውም ‹‹አንተ ዓለት ነህ በዚህችም መሠረት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ በሚል መነሻ ጥቅስ ተነሥተው የቤተ ክርስሰቲያንን አመሠራረትና ክብር አስመልክተው ሰፊ ትምህርትና ምክር ሰጥተዋል፡፡

በመጨረሻም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ትምህርተ ወንጌል ቃለ ምእዳንና ቡራኬ አስተላልፈዋል፡፡

ቅዱስነታቸውም በቃለ ምዕዳናቸው እግዚአብሔር በረድኤት ቀርቦአችሁ በጸጋ ደግሞ ስለተዋሐዳችሁ ይህንን መቃኞ ሠርታችሁ ቀደም ሲል ይፈጸምበት ከነበረበት የኃጢአት ሥራ አውጥታችሁ ወደ ተቀደሰ ቤተ መቅደስ ቀይራችሁ መገልገላችሁ መንፈስ ቅዱስ እንዳነሣሳችሁ መገንዘብ ይቻላል፡፡ አሁን ደግሞ ሁሉንም ምእመናን ሊያገለግል የሚችል ሰፊና ዘመናዊ ሕንፃ ለመሥራት አቅዳችኋል፤ እግዚአብሔር ያስፈጽማችሁ፤ ካህናት በአግባቡ ካስተባበራችሁ ደግሞ ምእመናን ለጋሶች ናቸው፤ ይሠጣሉ እናም ይህ ግሩም ዲዛይን ገንዘብ ያደረገ ካቴድራል በጊዜው ተሠርቶ እንደሚጠናቀቅ እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡

ቅዱስነታቸው አያይዘው ከምእመናንና ከበጎ አድራጊ ባለሀብቶች የሚሰበሰበው ገንዘብ በአግባቡ ሥራ ላይ እንዲውል አደራ በማለት ተሠርቶ ቤተ ክርስቲያኑን ለመመረቅ ተመልሰን እንድንገናኝ ሁሌም እንጸልያለን በማለት ሰፊ ትምሀርትና ምክር ከሰጡ በኋላ ጉባኤውን በጸሎት ዘግተዋል፡፡

የፎንት ልክ መቀየሪያ