Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

በመምህር ሙሴ ኃይሉ

ቅድስት ልደታ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በ2008 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን በኮምፕሬሄንሲቭ ነርሲንግ በሚድዋይፍ፣ በሕክምና ላብራቶሪ ቴክኖሎጂና በፋርማሲ ቴክኖሎጂ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያ ኃላፊዎች፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሥራ ኃላፊዎች፣ የአድባራትና የገዳማት አስተዳዳሪዎች እንዲሁም የተመራቂ ቤተሰቦች በተገኙበት በቤተ ክህነት ስብከተ ወንጌል አዳራሽ ነሐሴ 21 ቀን 2008 ዓ.ም. በከፍተኛ መንፈሳዊ ድምቀት አስመረቀ ፡፡

የዕለቱ መርሐ ግብር የደብሩ የሰ/ት/ቤት መዘምራን ያሬዳዊ መዝሙር በማቅረብ የተጀመረ ሲሆን ከዚህ በመቀጠልም የኮሌጁ ዲን የሆኑት ወ/ሮ ሕሊና ሞገሴ የእንኳን ደህና መጣችሁና አጠቃላይ የኮሌጁ የትምህርት መርሐ ግብርን አስመልክተው ሰፋ ያለ ገለጻ አድርገዋል ፡፡

በንግግራቸው አጽንኦት ከሰጡት ዋና ዋና ሐሳቦች መካከልም ኮሌጁ በመደበኛና በማታው መርሐ ግብር በኅብረተሰብ ጤና መኮንናት 56 ዕጩ ምሩቃንን፣ በነርሲንግ 45፣ በኮምፕርሔንሲንግ 114፣ በሚድ ዋይፍ 37፣ በላቦራቶሪ ቴክኖሎጂ 17 እንዲሁም በፋርማሲ ቴክኖሎጂ 30 ሠልጣኖችን በአጠቃላይ 299 ዕጩ ምሩቃንን ለምርቃት ማቅረባቸውን ገልጸዋል ፡፡ በመቀጠልም ቅድስት ልደታ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከተመሠረተ ጊዜ አንሥቶ እስካሁን ድረስ 2312 ባለሙያዎችን በማስመረቅ ለአገልግሎት ማብቃቱን አስታውሰዋል ፡፡

ከዚህ በመቀጠል ዕጩ ምሩቃን በየትምህርት ዘርፋቸው በመነሣት የሙያ ግዴታቸው በአግባቡ ለማገልገል ቃል ከገቡ በኋላ ሁሉም ተመራቂዎች ዲግሪና ዲፕሎማቸውን ከቅዱስ ፓትርያርክ እጅ የተቀበሉ ሲሆን በትምህርታቸው የላቀ ውጤት ያስመዘገቡም ሽልማት ከቅዱስነታቸው እጅ ተቀብለዋል ፡፡ በመጨረሻም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ለዕለቱ ተመራቂዎና በሥነ ሥርዓቱ ለተገኙ ሁሉ ትምህርተ ወንጌል፣ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ አስተላልፈዋል ፡፡

ቅዱስነታቸው በቃለ ምዕዳናቸው ‹‹ተፈስሑ ለእግዚአብሔር ዘረድአነ፤ በረዳን በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ›› በሚል ቃል መነሻ በማድረግ ይህንን የሕክምና ዕውቀት እግዚአብሔር ረዳት ሆኖ ተምራችሁ ለምርቃ ላበቃችሁ እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ማቅረብ የሁል ጊዜ ሥራችሁ መሆን አለበት ብለው ከመከሩ በኋላ የኮሌጁ ማኅበረሰብ በየደረጃውና የዕለቱ ተመራቂዎች እንኳን ደስ አላችሁ በማለት የተመሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል ፡፡

በመቀጠልም ሙያዊ ትምህርት ቀስማችሁ በዛሬው ዕለት ቃለ መሐላ የፈጸማችሁ ልጆቻችን በዕድገትና በብልጽግና ጎዳና ለምትገኝ ሀገራችሁና በሕመም ለተቸገረ ወገናችሁ ለሙያችሁ ታማኝ ሆናችሁ እንድታገለግሉ ቤተ ክርሰቲያን አደራ ትላችኋለች በማለት ቅዱስነታች ለዕለቱ ምሩቃን ሰፊ ቃለ ምእዳን ሰጥተዋል ፡፡

በመጨረሻም ከዚህ ሙያዊ ግዴታችሁ በተጨማሪ በሀገራችሁ ሰላም፣ በግብረ ገብነት እንዲሁም በመሳሰሉ የመልካም እሴቶቻችን መገለጫዎቻችን ሁሉ ለሌሎች ልጆቻችን ምሳሌ መሆንን እንዳትዘነጉ ብለው በስፋት ያለውን ችግር አብራርተው ከመከሩ በኋላ መርሐ ግብሩን በጸሎት ዘግተዋል ፡፡

የፎንት ልክ መቀየሪያ