Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51
 • በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡

በመምህር ሙሴ ኃይሉ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የደብረ ሊባኖስ ገዳም ባደረገላቸው ገዳማዊ ጥሪ ምክንያት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያ ኃላፊዎች ሊቃውንትን አስከትለው በመሄድ ነሐሴ 28 ቀን 2008 ዓ.ም. የፍቼ ዞን አስተዳደር፣ የወረዳው አስተዳደር እና የዞኑ የፀጥታ ዘርፍ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የገዳሙ አበው መነኮሳት፣ የአካባቢው ምዕመናን እና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በተገኙበት በገዳሙ ሐዋርያዊ ጉብኝት በማድረግ የተሠሩ ልማቶችንም መርቀዋል፡፡

ቅዱስነታቸው ከገዳሙ ሲደርሱ የገዳሙ ማኅበረ መነኮሳት እና ያሬዳውያን ሊቃውንት በከፍተኛ መንፈሳዊ አክብሮት በዝማሬ የተቀበሏቸው ሲሆን፣ ቅዱስነታቸውም በአቀባበል መርሐ-ግብሩ ለተገኙት ልጆቻቸው በመስቀላቸው ባርከው የመግቢያ በር ላይ ተዘጋጅቶ የነበረውንም ሪቫን ከዞንና ከወረዳ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች ጋር በመሆን ቆርጠው ወደ ቤተ መቅደስ ገብተው ጸሎተ ኪዳን አድርሰዋል፡፡

የመድረክ መርሐ-ግብሩ በገዳሙ ሊቃውንት ያሬዳዊ መዝሙር እና ቅኔ የተጀመረ ሲሆን፣ የገዳሙ ጸባቴ አባ ወ/ማረያም አድማሱም በገዳሙ ተሠርተው ለምርቃት የተዘጋጁት እና በመሠራት ላይ ያሉ ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችን በተመለከተ መግለጫ አቅርበዋል፡፡ በመሆኑም በገዳሙ መዋዕለ ንዋይ የተገነቡና ለምርቃት የተዘጋጁት የገዳሙን ዙሪያ የሚከበውን መጠለያና የእንግዶች ሱባኤ ማስያዣ፣ የግብር ቤት መሰየሚያ (G+1)፣ የፉካ ግንባታ፣ የመስቀል ቤት አጥር፣ የሻወር እና የመጸዳጃ ቤቶች እንዲሁም የእንግዶች ማረፊያ ሲሆኑ በዕለቱ የመሠረት ድንጋይ የሚቀመጥላቸውም አዲሱ ዘመናዊ የስብከተ ወንጌል አዳራሽ (G+1)፣ የቅኔ ማኅሌት እና የገድል ቤት መሆናቸውን በስፋት አብራርተዋል፡፡

ከዚህ በመቀጠል የዞኑ አስተዳደር ኃላፊ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፣ የልማታዊ መንግሥታችንን የልማት ስትራቴጂ ከመተግበር አኳያ ገዳሙ እያከናወነው የሚገኘው የልማት እንቅስቃሴ እጅግ የሚያስመሰግነው መሆኑን በስፋት ገልጸው እንደ ከዚህ ቀደሙ አሁንም በገዳሙ የልማት ሥራዎች ጐን በመሰለፍ ዞኑ አስፈላጊ ድጋፍ እንደሚያደርግ በዕለቱ ቃል ገብተዋል፡፡ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስም ለቅዱስ ፓትርያርኩ የእንኳን ደህና መጡ ንግግር እና የታሪካዊውን ገዳም ልማት አስመልክተው አባታዊ መልእክት እና በልማቱ ለተሳተፉ ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ ገዳሙም በዚህ የልማት ሥራ በከፍተኛ ሁኔታ ለተሳተፉት ሁሉ ከዞኑ መስተዳድር ጀምሮ የምስጋና ሽልማት ሰጥተዋል፡፡

በመጨረሻም ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን በጉብኝት እና ምርቃት መርሐ-ግብሩ ለተገኙት ሁሉ ትምህርተ ወንጌል፣ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ አስተላልፈዋል፡፡ ቅዱስነታቸው በቃለ ምዕዳናቸው ገዳማውያኑ በጉባኤ ተወያይተው ይህ ታሪካዊ ገዳም እንደ ገዳማዊ ሕይወቱ በልማትም ለሁሉም አርአያ መሆን አለበት በማለት በሕብረት ተስማምተው ገዳሙን በልማት እዚህ ደረጃ በማድረሳቸው ከፍተኛ ምስጋና ለገዳሙ አስተዳዳሪ እና ለማኅበረ መነኮሳቱ አቅርበዋል፡፡ በመቀጠልም የቤተ ክርስቲያናችን የጀርባ አጥንት የሆኑ ምዕመናን ለገዳሙ ልማት በጉልበት፣ በዕውቀት፣ በገንዘብ እና በንብረት እገዛ ላደረጉት ሁሉ አባታዊ ምስጋናቸውን አቅርበው አሁንም ገዳሙ የጀመረውን የልማት እንቅስቃሴ በማጠናከር ተምሳሌታዊ ሥራ እንዲሠራ አባታዊ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በዕለቱ ለተሰበሰቡት ምዕመናን ስለ ሰላም፡ ስለ ጤና፣ ስለ ሕገወጥ ስደት አስከፊነት እና በመሳሰሉት ማኅበራዊ እሴቶች ሰፊ ትምህርትና ምክር ሰጠተው መርሐ-ግብሩን በጸሎት ከዘጉ በኋላ የጉብኝት መርሐ-ግብሩ ተከናውኗል፡፡ በጉብኝት መርሐ-ግብሩም ለምረቃ የተዘጋጁት በመመረቅ፣ የመሠረት ድንጋይ የሚቀመጥላቸው ከተቀመጠላቸው በኋላ ዙሪያውን በመዘዋወር አጠቃላይ የልማቱን አንቅስቃሴ ጐብኝተዋል፡፡

 

የፎንት ልክ መቀየሪያ