Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

በመምህር ሙሴ ኃይሉ

በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ቅዱስ ዮሐንስም መስከረም 2 ቀን 2009 ዓ.ም በጠቅላይ ቤተ ክህነት ስብከተ ወንጌል አዳራሽ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያ ኃላፊዎች እና አጠቃላይ ሠራተኞች፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ኃላፊዎችና ሠራተኞች፣ የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ የሰ/ት/ቤት ወጣቶች መዘምራንና ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች በተገኙበት በደማቅ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ተከብሮአል፡፡

የዕለቱ ተረኛ የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢ ታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ሊቃውንት ያሬዳዊ መዝሙር በማቅረብ የተጀመረ ሲሆን የሊቃውንት ቅኔ እና በመካነ ሕያዋን ሰ/ት/ቤት መዘምራን የአጫብር ቆሜ ወረብ በዓሉ እጅግ ደማቅ እንዲሆን አስችለውታል፡፡
በመቀጠልም ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና በክልል ትግራይ የደበባዊ ዞን፣ ደቡብ ምሥራቅ እና ምሥራቃዊ ዞን አኅጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አጠቃላይ የጠቅላ ቤተ ክህነት ሠራተኞችን በመወከል የእንኳን አደረስዎ መልካም ምኞት አስተላልፈዋል፡፡ ከብፁዕነታቸው ተከትሎም የአዲስ አበባ ገዳማት እና አድባራት አስተዳዳሪዎች እንደተለመደው የእንኳን አደረስዎ መልካም ምኞታቸውን በማኅበረ ካህናት እና ምዕመናን ስም አስተላልፈዋል፡፡

በዕለቱ መርሐ ግብር መሃል ላይ ቤተ ክርስቲን ለዘመናት በልዩ ክብር እና ጥንቃቄ ጠብቃ ያቆየችውን እና ቤተ ክርስቲያንዋን ከሚያስከብሩት ጥንታውያን የቅዱስ ያሬድ ድርሰቶች መካከል የሆነውን እና በከፍተኛ ጥናት እና ጥንቃቄ በቤተ ክርስቲያንዋ ታትሞ ለስርጭት የተዘጋጀውን መጽሐፈ ድጓ በቅዱስ ፓትርያርኩ ተመርቆ መታተሙን ይፋ የተደረገ ሲሆን በሁሉም አኅጉረ ስብከት እንዲሰራጭ ተደርጎ በተለይም ለዜማ መምህራንና ለአድራሽ የአብነት ተማሪዎች የዋጋ ጭማሪ እንዳይደረግበት ሆኖ ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን በዕለቱ ማሳሰቢያ ተሰጥቶአል፡፡

በመጨረሻም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ በመርሐ ግብሩ ለተገኙት ልጆቻቸው ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ አስተላልፈዋል፡፡ ቅዱስነታቸው በቃለ ምዕዳናቸው በዋናነት የሰላምን አስፈላጊነት በስፋት አትተው ሁሉም የሰላም ሐዋርያ ሆኖ በክርስቶስ መሾሙን አስረድተዋል፡፡ "ሰላም የምናመጣውም ሆነ የምናሳጣው እኛ ነን፤ ሰላም በእጃችን ሳለ እንደ ቀላል እንቆጥረዋለን ስናጣው ግን ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ እንረዳለን፤ የሰላም ባለቤት ኢየሱስ ክርስቶስ ሰላሙ ሰጥቶና፤ ይህ የክርስቶስ ሰላም በመላ ሀገራችን እንዲሁም በመላ ዓለማችን ጸንቶ እንዲኖር ሁላችንም የሰላም ሐዋርያት፣ የሰላም መምህራን፣ የሰላም መልእክተኞች በመሆን የሚጠበቅብንን መንፈሳዊ ኃላፊነት መወጣት አለብን" በማለት የሰላምን አስፈላጊነት በስፋት አትተው በየደረጃው የሚገኙ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች የሰላም ሐዋርያት ሆነው ሕዝቡን እንዲያገለግሉ አባታዊ መመሪያ አስተላልፈዋል፡፡ በመቀጠልም ያለፈውን ዓመት የነበረውን የሀገራችን የድርቅ ችግር አስታውሰው እግዚአብሔር የልጆቹ ጸሎት የሚሰማና ለልጆቹ የሚራራ ርህሩህ አምላክ ስለሆነ ያንን ድርቅ አሳልፎ ሀገራችን በሐመልማል በረከት ጎብኝቷል በማለት ያለውን ወቅታዊ የሀገራችን የአየር ጸባይ ካስረዱ በኋላ ይህ አሁን የምናየው ልምላሜ ከፍሬ እንዲያደርስልን እና እኛ ከማናውቀው መቅሰፍት ሁሉ ሰውሮ የተባረከ ዘመን እንዲያደርግል አሁንም ጸሎት ያስፈልጋል በማለት ሰፊ ትምህርተ ወንጌል ሰጥተዋል፡፡

በመጨረሻም ስለ ሰላም፣ ስለ አትክልቱ እና አዝርእቱ፣ ስለ ሕዝባች ፍቅር እና አንድነት፣ ስለ ዓለም ሰላም ሁሉ በማሰብ ዓውደ ዓመቱን በጸሎተ ምኅላ እንዲጀመር በማለት ለሁለተኛ ጊዜ የጸሎተ ምኅላ ሱባኤ እንዲያዝ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡ ቀደም ብሎ ለመጀመሪያ ጊዜ በጾመ ፍልሰታ ጊዜ ጸሎተ ምኅላ መታዘዙን ያስታወሱት ቅዱስ ፓትርያርኩ አሁንም ለሁለተኛ ጊዜ በሁሉም አድባራትና ገዳማት እንዲካሄድ መመሪያ ካስተላለፉ በኋላ ዘመኑ ዘመነ ሰላም፣ ዘመነ በረከት፣ ዘመነ ዕድገት እንዲሆንልን በመመኘት መርሐ ግብሩ በጸሎት ዘግተውታል፡፡

የፎንት ልክ መቀየሪያ