Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

የቅዱስ ፓትርያርኩ ሐዋርያዊ ጉዞ በጋምቤላ

በመምህር ይቅርባይ እንዳለ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንት ሐዋርያዊ ጉዞ አደረጉ፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አሉኝ ከምትላቸው ታላላቅና የወቅቱ የሥራ ፍሬ ከሚታይባቸው ሀገረ ስብከቶች አንዱ የጋምቤላ ሀገረ ስብከት ነው፡፡ የጋምቤላ ሀገረ ስብከት ከቀድሞ ጀምሮ በከፍተኛ ደረጃ በብሔር ብሔረሰቦች መካከል አንድነትን፣ መተሳሰብንና አብሮ መኖርን በማስተማር የሚታወቅ ነው፡፡ በዚህ በያዝነው ወር ደግሞ ቅዱስነታቸው የሚገኙበትን ታላቅ መርሐ ግብር እንዳዘጋጀ በጥቂቱ ጠቁመናችሁ ነበር፡፡ በዚህኛው ድሑፋችን አጠቃላዩን መረጃ እናስነብባችኋለን፡፡

በጋምቤላ ክልል የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች ያሉ ሲሆን ባህላቸው እና የአኗኗር ዘይቤያቸው ከመማረኩም በላይ በአጋጣሚ ለጉብኝት የሚሄድ ሰው ሁሉ እዚሁ በቀረሁ የማይል እንደሌለ ይነገርለታል፡፡ ለእነዚህ ብሔር ብሔረሰቦች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዘመናዊ የአብነት ትምህርት ቤቶችን እየከፈተች በመስጠት ላይ ትገኛለች፡፡ የአሁኑ ሐዋርያዊ ጉዞ አንዱም ዓላማ ይሄንን የአብነት ትምህርት ቤት ለማስመረቅ ነው፡፡

ይህ የአብነት ትምህርት ቤት በጋምቤላ አንቀጸ ብፁዓን አቡነ ተ/ሃይማኖት ወአቡነ ሐራ ድንግል ዳግማዊ ገዳመ አስቄጥስ ውስጥ ሲሠራ ለመጀመሪያ ጊዜ 30ተማሪዎችን ተቀብሎ የሚያስተምር ሲሆን ተማሪዎቹ ወደ አብነት ትምህርት ቤቱ ሲገቡ ተመልሰው ህብረተሰቡን በቋንቋው እንዲያገለግሉ በማሰብ ስለሆነ ከአኙዋክ፣ ከኑዌር፣ ከመዥንግር፣ ከኦኮ እና ከኮሞ ብሔረሰብ ዕድሉ እንደተሰጣቸው ከሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መጋቤ አእላፍ ቆሞስ አባ ተ/ሐይማኖት ተገልጾልናል፡፡

መጋቤ አእላፍ ቆሞስ አባ ተ/ሐይማኖት እንደገለጹልን ይህ ትምህርት ቤት ከከተማው ጀምሮ እስከ ገጠሪቷ ቤተ ክርስቲያን ድረስ ያለብንን የዲያቆንና የቄስ ችግርን ይፈታል ብለዋል፡፡ ከዚህም በላይ በሥነ ምግባር የታነፀ ትውልድ ለመፍጠር ያስችላል ብለዋል፡፡ ማህበራዊ ጉዳይን በሚመለከት ረገድም አንድነትን ይፈጥራል፤ ልዩነትን ያጠፋል፤ ከአምስቱም ብሔር ተውጣጥተው በአንድ ትምህርት ቤት መማራቸው መልካም አርአያ ከመሆኑም በላይ ጠንካራ የሆነ የፍቅር ትሥሥርን ይፈጥራል ብለዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በዚህ ሐዋርያዊ ጉዞ ቅዱስነታቸው በጀጀቤ ተራራ ላይ የተሰራውን፤
-የአቡነ አረጋዊ እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን፤
-የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን በጋምቤላ ክልል ያሠራችውን ዘመናዊ ሙዚየም፤
-በኢታንግ ወረዳ የሚገኘውን የመድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን የመረቁ ሲሆን በመጨረሻም አዲስ ክርስትና የተቀበሉትን ሰዎች ከ300 በላይ አጥምቀዋል፡፡

የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ እንደገለጹልን ከመጀመሪያው ሐዋርያዊ ጉዞ እስከ አሁን ድረስ በአጠቃላይ ከ4767ብሔር ብሔረሰቦች በላይ ክርስትናን በመቀበል ተጠምቀዋል ብለዋል፡፡

በዚህ ሐዋርያዊ ጉዞ ላይ 15ሊቃነ ጳጳሳት እና የየመምሪያው ዋና ሥራ አስኪያጆች የክልሉ የመንግሥት ታላላቅ ባለሥልጣናት ተገኝተዋል፡፡ በመጨረሻም ይህ ሐዋርያዊ ጉዞ በሚቀጥሉት ጊዜያትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ገልጾዋል፡፡

 

የፎንት ልክ መቀየሪያ