Get Adobe Flash player

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በስመ አብ ወወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ፣...

35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

በመምህር ዕንቈባሕርይ ተከስተ ዘመናትን በዘመናት የሚተካ እግዚአብሔር አምላክ 2008 ዓ.ም ዘመነ ዮሐንስን አሳልፎ ለ2009 ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ አደርሶናል፡...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

በመምህር ሙሴ ኃይሉ በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ተጠብቆ የቆየውን እና በየዓመቱ የሚከናወነውን የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር የዘንድሮ ዘመን መለወጫ በዓለ ...

ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ ...

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

በገዳሙ የተሠሩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መርቀዋል፡፡ በመምህር ሙሴ ኃይሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጰጳሳ...

 • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

  Thursday, 27 October 2016 06:16
 • 35ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ከጥቅምት 7-10 ቀን 2009 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ተጠቃቀ፡፡

  Tuesday, 25 October 2016 06:40
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ዓውደ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በመላ ሃገሪቱ ጸሎት እንዲደረግ ለሁለተኛ ጊዜ መመሪያ አስተላለፉ፤

  Thursday, 15 September 2016 11:54
 • ቃለ በረከት ዘእምኀበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፡፡

  Thursday, 15 September 2016 11:50
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ጐበኙ፡፡

  Wednesday, 07 September 2016 09:51

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ ከመጽሐፍ ቅዱስ ማህበር ጋር በመተባበር “ሚዲያና ሥነ ምግባር” በሚል ርዕስ ዐውደ ጥናት አካሄደ

በመምህር ይቅርባይ እንዳለ


ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝዳን ት የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንት ጉባኤውን ባርከው የከፈቱ ሲሆን በሚዲያ በኩል ሕዝብን የሚጻረር ወይም የሚነቅፍ ነገር ከክርስትና የሚመነጭ አለመሆኑን ገልጸው አንድ ጊዜ ሕዝቡ ውስጥ ተጽፎ የተሰራጨውን ነገር ተሳስቼ ነው ማለት አይቻልም ሲሉ ከሚዲያ በስተጀርባ የሚደረገውን የስም ማጥፋት ተግባር ኮንነዋል፡፡ በመቀጠልም ነጻነት የሰውን መብት ሳይነኩ መንቀሳቀስ እንደሆነ ገልጸው በሚዲያም የሚሠሩ ሰዎች ነፃነታቸውን ተጠቅመው የሰውንም መብት እና ስም ሳያጠቁ እንዲንቀሳቀሱ በመምከር ይልቁንም በሐይማኖት ሚዲያ ላይ የሚሠሩ ምሁራን ለሌሎች አርአያ መሆን እንዳለባቸው በመምከር ጉባኤው እንዲቀጥል አመራር ሰጥተው በብዙ ሺህ ሕዝብ ወደሚጠበቁበት ወደ እንጦጦ ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን ሄደዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ አቶ ይልማ የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማህበር ዋና ሥራ አስኪያጅ ስለ ኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማህበር በማብራራት ከ87 ዓመት በፊት በኢትዮጵያ ውስጥ ሲመሠረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጉልህ ሚና የተጫወተች እንደሆነች በመግለጽ እንዲሁም በርካታ መጻሕፍትን ማሳተሟንና የትርጉም ሥራን በመሥራት በበላይነት ስትንቀሳቀስ እንደነበረችና አሁንም ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ ላይ እንደምትገኘ ገልጸዋል፡፡

በአሁን ጊዜም መጽሐፍ ቅዱስ በሊቃውንት ጉባኤ በኩል በግእዝ ቋንቋ በመዘጋጀት ላይ መሆኑን ገልጸው ለዚህም ሥራ የሚገባው በጀት እንደተበጀተለትም ተናግረዋል፡፡ ምንም እንዃ ከዚህ በቀደሙት ጊዜያት የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማህበር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመናን እይታ ዘንድ እንደ ሌላ አካል ይታይ የነበረ ሲሆን ይህንንም ለመለወጥ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ፣ ከቅዱስ ሲኖዶስ ጋር በመሆን አመላካከቱ እንዲቀየር ከማድረጋቸውም በላይ በሚያስፈልገው ሁሉ እየረዱ መሆናቸውን ገልፀው ወደፊትም እንደማይለዩን እምነቴን እገልጻለሁ ብለዋል፡፡

አቶ ይልማ አክለው እንደገለጹት በአሁን ሰዓት ያለው የመጽሐፍ ቅዱስ ስርጭት በጣም ደካማና ውድ እንደሆነ ገልጸው የአንድ ሰማንያ አሐዱ መጽሐፍ ቅዱስ ዋጋ 85 ብር ሲሆን ነገር ግን አንድ መጽሐፍ ቅዱስ በውጪ ታትሞ ሀገራችን ውስጥ ገብቶ በካዚናችን የሚደርሰው 130 የኢትዮጵያ ብር በመጨረስ ነው በማለት ያለውን ችግር በግልጽ አስቀምጠዋል፡፡

ጉዳዩን በዋናነት የያዘው የስብከተ ወንጌል መምሪያ ሲሆን የተለያዩ ጥናታዊ ጽሑፍ የሚያቀርቡትን ምሑራን በመጋበዝ የጉባኤ ታዳሚ ንቃተ ሕሊና እንዲዳብር አድርጓል፡፡
ከቀረቡት ጥናታዊ ጽሑፎች መካከል፤
1.የመረጃ /የመገናኛ/ አውታርና ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር በሚል ዙሪያ በመ/ር ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል አጠቃላይ ስለመረጃ ያለው መረጃ ቀርቧል፡፡ጥናቱ የሚያጠናክረው ስለመረጃ የተሰጠ መረጃ ሲሆን በሙያዊ ክህሎት የተተነተነ ነው፡፡ የጽሑፉም አላማ በአጠቃላይ የመረጃን ምንነትና ታሪካዊ መገኛ ለመናገር ሳይሆን መረጃዎች በአሁኑ ወቅት በተለይም የቤተክርስቲያን መረጃዎች የቤተክርስቲያንን በሰው ልጆች ታሪክና ሕይወት በዚህ ዓለም እንደ ተቋምም ሆነ እንደ ሰማያዊ እንደራሴነቷ ልታከናውን የሚገባትን ዓላማ ከማስተላለፍ አንጻር ምን አይነት ስነ-ምግባራዊ መመሪያዎች እየተከተሉ እንደሆነና እንደሚገባቸው መጠነኛ ገለጻ ለመስጠት ነው፡፡
2.በመቀጠልም አቶ ጥበቡ ጋሹ ሚዲያና ሕግን በሚመለከት ረገድ ጥልቀት ያለውን ጥናታዊ ጽሑፍ አቅርበው ጉባኤው ተወያይቶበት ጥሩ የሕግ ግንዛቤ እንዲኖረው ተደርጓል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ለዚህ ጉባኤ በጣም አስፈላጊ ናቸው የተባሉት ጥናቶች በተለያዩ ምሁራን ቀርበው ለዛሬ የነበረው ጉባኤ የተጠናቀቀ ሲሆን በነገው ዕለት ማለትም በ17/6/2003ዓ.ም ጉባኤው እንደሚቀጥል በስብከተ ወንጌል መምሪያው ዋና ኃላፊ ዶ/ር ቆሞስ አባ ኃ/ማርያም መለሰ ተገልጾ የጉባኤው ማጠቃለያ ሆኗል፡፡

 

የፎንት ልክ መቀየሪያ